ወሰንሰገድ አሰፋ

The Rising South

Society EN ↓ 125 episodes

የዓለም አቀፍ የኃይል ሚዛን እየተቀየረ ባለበት በዚህ ወቅት - ኢትዮጵያን፣ አፍሪካን እና ሌሎችን የሚቀርጹ የፖለቲካ፣ የኢኮኖሚ እና የማህበራዊ ሃይሎች ወደምንመለከትበት ወደ “ራይዚንግ ሳዉዝ” እንኳን በደህና መጡ፡፡ ደቡባዊ አመለካከቶችን ወደ ዓለም አቀፋዊ ውይይት መድረክ ስናቀርብ የአሰላሳዮችን ፣ የመሪዎችን እና የለዉጥ ፈጣሪዎችን ሃሳብ ያድምጡ።

Author

ወሰንሰገድ አሰፋ

Category

Society

Latest episode

Jul 11, 2026

Where to listen?

Podcasts in the app Replaio Radio Coming soon

Podcasts are coming to the app soon. Install now and be the first to see a whole new take on podcasts

Get it on Google Play Install for free Android 5M+ downloads · 4.8 rating iOS soon

Episodes

የኢትዮጵያ ፖስታ አገልግሎት የዲጂታል ሽግግር፦"ዲጂታል ኢትዮጵያ 2030" በተግባር 13.01.2026

"በኢትዮጵያ ፖስት ረገድ ላደንቀው የምፈልገው ነገር ቢኖር የአገልግሎት ምዝገባ ሂደቱን ነው። [...] የቨርቹዋል ሳጥን ተጠቃሚ ለመሆን የፋይዳ መታወቂያን መጠቀም ይቻላል፤ ከዚያም ሁሉም መረጃዎች ከፋይዳ ሥርዓት በቀጥታ ይሞላሉ። በመቀጠልም በተሳሰሩ የክፍያ መድረኮች አማካኝነት ክፍያ ይፈጸማል። በአንድ ወይም በሁለት ደቂቃ ባልሞላ ጊዜ ውስጥ የራሳችን የሆነ ቨርቹዋል ሳጥን እንዲኖረን ያስችለናል።" ሲሉ የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ አስተዳደር እና የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ባለሙያ አቶ እስክንድር መስፍን ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል፡፡ በዛሬው የራይዚንግ ሳውዝ የሁለት ክፍል ዝግጅታችን፣ የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ አስተዳደር እና የዲጂታ...

የኦንላይን እና ርቀት ትምህርት በኢትዮጵያ፣ ዕድል እና ተግዳሮት 02.01.2026

“አንድ ሀገር ማደግ፣ መለወጥ፣ መበልጸግ ካለባት በተማሩ ዜጎቿ ነው የሚወሰነው። አንድ ሀገር ዲሞክራቲክ ለመሆን ካስፈለጋት በተማሩ ዜጎቿን ነው የሚወሰነው። ያልተማረ ህብረተሰብ በፈለከው መስመር ልትነዳው፣ በፈለከው ጊዜ የፈለከውን ነገር ልጭንበት ትችላለህ።” በኦንላይን እና ርቀት ትምህርት ዘርፍ ተመራማሪ ረ/ፕ አደራጀው ተሰማ (ዶ/ር) ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል፡፡ በዚህ የራይዚንግ ሳውዝ ዝግጅት፣ በኢትዮጵያ ያለውን በኦንላይን እና ርቀት ትምህርት ዘርፍ ተመራማሪ ከሆኑት ከረ/ፕ አደራጀው ተሰማ (ዶ/ር) በመሆን የዲጂታሉ ዓለም እየተፋጠነ ባለበት በዚህ ወቅት፣ ኢትዮጵያ ወጥ ካልሆነ የኢንተርኔት ተደራሽነት፣ የመሠረተ ልማት...

አእምሮአዊ ሉዓላዊነት፦ በአፍሪካ እውቀትን የሚቆጣጠረው ማን ነው? 01.01.2026

"ራሴን እንደ ምሁር ሳይሆን በህብረተሰቡ ውስጥ እንደ ተማሪ አድርጌ ባስቀመጥኩባቸው ጊዜያት ሁሉ፣ በቋንቋዎቻችን ውስጥ ያለውን ጥልቅ የፍልስፍና ይዘት ይበልጥ ለመረዳት ችያለሁ።[…]ሰዎች ባሉበት ሁሉ አስተሳሰብ አለ፤ አስተሳሰብ ባለበት ሁሉ እውቀት አለ፤ እውቀት ባለበት ሁሉ ደግሞ ፍልስፍና አለ፡፡” ሲሉ በደቡብ አፍሪካ ዩኒቭርስቲ /ዩኒሳ/ መምህርት ፕ/ር ሻባላኒ ኖኩቱላ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል፡፡ በአእምሮአዊ ሉዓላዊነት እና የአፍሪካን ትምህርት ከቅኝ ግዛት ተጽዕኖ ነፃ ስለማውጣት በሚመለከት ከፕ/ር ሻባናኒ ኖኩቱላ ጋር አፍሪካ የፖለቲካ ነፃነት ብታገኝም፣ ብዙ የአፍሪካ ዩኒቨርሲቲዎች አሁንም የአፍሪካን ታሪክ፣ ቋንቋዎች...

''ቅድሚያ ለአሜሪካ የጤና ስምምነት'':- ለአፍሪካ አጋርነት፣ ጉልበት ወይስ ጥገኝነት? 30.12.2025

"[የአፍሪካ] መንግስታት ከሲቪል ማህበረሰብ፣ ከሰብዓዊ መብት ተሟጋች ቡድኖች እና ከሌሎች አካላት ጋር ቢመክሩ ኖሮ፣ ከእነዚህ ቡድኖች ሊመጣ በሚችለው ጫና ምክንያት መንግስታቱ ወደ ስምምነቱ ላይገፉ ይችሉ ነበር። በአሁኑ ወቅት ከኬንያ እያየን ያለነው በጣም የሚደነቅ ነገር ቢኖር ጠንካራ የሲቪል ማህበረሰብ ንቅናቄ መኖሩን ነው፤ ወደ 50 የሚጠጉ ድርጅቶች አሁን ያለውን ስምምነት በመቃወም መቆማቸው የስምምነቱን የተወሰነ ክፍል ለማስቆም አስችሏል።" ሲሉ በደቡብ አፍሪካ የሚግኙት የማህበረሰብ ጤና ባለሙያ የሆኑት ዶ/ር ሻኪራ ቹናራ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል፡፡ በዛሬው ልዩ የራይዚንግ ሳውዝ የሁለት ክፍል ዝግጅታችን፣ የአፍሪካን የ...

ዲጂታል ኢትዮጵያ 2030፦ የኢትዮጵያ የዲጂታል ሽግግር ጉዞ 25.12.2025

“እኛ [ኢትዮጵያውዊያን] በከፍተኛ ሁኔታ ከውጭ በሚገቡ የዲጂታል ሀብቶች ላይ ጥገኛ ነን። ስለዚህ ውይይታችን ስልታዊ እስከሆነ ድረስ እኔ የምመክረው የራሳችን የሆነ የመረጃ ሉዓላዊነት እንዲኖረን ነው። የመረጃ ሉዓላዊነትን የሚያበረታታ እና የሚሟገት የመረጃ አስተዳደር ፖሊሲ ሊኖረን ይገባል። [ለዚህም] በኢትዮጵያ ውስጥ የመረጃ ኤምባሲዎችን ማቋቋም ያስፈልገናል።” ሲሉ የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ አስተዳደርና ስትራቴጂ ባለሙያ እስክንድር መስፍን ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል። በዚህ የራይዚንግ ሳውዝ ዝግጅት የመጀመሪያው ክፍል የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ አስተዳደርና ስትራቴጂ ባለሙያው እስክንድር መስፍን፣ ታህሳስ 11 ይፋ የሆነውን “ዲጂታ...

የሆሊውድ የባህል ወረራ ፦ አፍሪካዊ ማንነቶች ላይ ያነጣጠረው አዲስ የቅኝ ግዛት መልክ 24.12.2025

“የሆሊውድ ተጽእኖ ምንም ጥርጥር የለውም፤ ከፍተኛ ተጽእኖ አለው፤ ጉዳቱ ያመዝናል ግን ቢሆንም ጠቃሚነቱም ደግሞ የሚካድ አይደለም። [...] ምዕራባውያን በአብዛኛው ፊልሞቻቸው ላይ የበላይነታቸውን ሊያሳዩን ይሞክራሉ፡፡ [...] በተቃራኒው ደግሞ የአፍሪካን ኋላቀርነት እና አስከፊ ገጽታ ለመገንባት ይሞክራሉ፤ ይህም ትውልዱ ራሱን እና ሀገሩን የሚያይበትን መንገድ የተበላሸ እንዲሆን ያደርጋሉ፡፡” ሲል ደራሲ ፣ ዳይሬክተርና ተዋናይ ቢኒያም ወርቁ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግሯል፡፡ በዚህኛው ባለሁለት ክፍል የራይዚንግ ሳውዝ ዝግጅት፣ በመጀመሪያው ክፍል፣ የፊልም እና ቲያትር ባለሙያ ከሆነው ከደራሲ ፣ ዳይሬክተርና ተዋናይ ቢኒያም ወርቁ ጋ...

አህጉራዊ ፅናትን መገንባት፦ የሩሲያ–አፍሪካ ትብብር ሚና በግብርናው ዘርፍ 23.12.2025

"እያንዳንዱ ማህበረሰብ የራሱ የሆነ ጥበብ እና የራሱ የሆኑ ሀብቶች አሉት። በሚያሳዝን ሁኔታ ግን፣ ማህበረሰቦች እነዚህን ጥበቦች፣ ሀብቶች እና መሣሪያዎች በመደበኛው የትምህርት ሥርዓት ውስጥ ምን ያህል አካተውታል የሚለው ጉዳይ፣ በእኛ ላይ ተጽዕኖ ከማሳደሩም በላይ አሁን ላለንበት የልማት ደረጃ የራሱን አስተዋጽኦ ያበረክታል።" ሲሉ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የማህበረሰብ ጤና ትምህርት ቤት ባለሙያ እና ተመራማሪ የሆኑት ፕሮፌሰር ሚርጊሳ ካባ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል፡፡ በዚህኛው የራይዚንግ ሳውዝ ባለ ሁለት ክፍል ዝግጅት፣ በመጀመሪያው ክፍል በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የግብርና ኮሌጅ ዲን ከሆኑት ዘሪሁን ደምረው (ዶ/ር) ጋር በመሆን...

የሩሲያ - አፍሪካ ግንኙነት ፦ አዳዲስ አድማሶች፣ ነባር ወዳጆች 23.12.2025

"በበርካታ የአፍሪካ ሀገራት ውስጥ ሰላም በመጥፋቱ እንጨነቃለን፤ ምክንያቱም በአፍሪካ አህጉር ስለ ብልጽግና ማውራት የምንችለው ሰላም ሲኖር ብቻ ነው ብለን እናምናለን። ሰላም ካለ 'የምንመኛት አፍሪካ' ወደተሰኘው የአፍሪካ ህብረት አጀንዳ-2063 ግቦች ለመድረስ መስራት እንችላለን። እንደ ሩሲያ ያሉ ሀገራት ለዓመታት ያካበቱትን ልምድና አቅም በመጠቀም የተሻለች ዓለምን መገንባት እንደምንችል እናምናለን።" ሲሉ የቦትስዋና የዓለም አቀፍ ግኑኝነት ሚኒስትር ፌንዮ ቡታሌ (ዶ/ር) ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል፡፡ በዚህኛው የራይዚንግ ሳውዝ ዝግጅት፣ በመጀመሪያው ክፍል የቦትስዋና የዓለም አቀፍ ግኑኝነት ሚኒስትር የሆኑት ፌንዮ ቡታሌ (ዶ...

ደቡባዊው ዓለም በእንቅስቃሴ ላይ፦ ኢትዮጵያ ፣ ብሪክስ እና የኢኮኖሚ ሉዓላዊነት ትግል 20.12.2025

"የብሪክስ አገራት አንዱ ስምምነት በቴክኖሎጂ ሽግግር፣ በምርምር እና በፈጠራ፣ እንዲሁም በተለያዩ የፋርማሲዩቲካል እና የሕክምና መሣሪያዎች ጉዳዮች ላይ በጋራ መሥራት ነው። ይህም ከስኳር እና ከሌሎች መሰል ልማዳዊ አሠራሮች ወደ ከፍተኛ የቴክኖሎጂ ፈጠራ እና ተሳትፎ ለመሸጋገር ያስችላል። ምክንያቱም የብሪክስ መመሪያዎች፣ ስምምነቶች እና ፍላጎቶች ከነዚህ መሰል ልማዳዊ አሠራሮች ወደ ከፍተኛ ቴክኖሎጂዎች በመሸጋገር በእስያ እንዲሁም በአፍሪካ አገራት፣ በተለይም በኢትዮጵያ፣ ምርትን እና ምርታማነትን ማሳደግ ነው" ሲሉ በወራቤ ዩኒቨርሲቲ የኢኮኖሚክስ መምህር የሆኑት መሐመድ ሙሳ (ዶ/ር) ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል።  በዚህኛው የራ...

የታሪክ ባለቤትነት እና የይዞታ ባለቤትነትና ፍትሕ በአፍሪካ 20.12.2025

“ዓላማችን መሆን ያለበት የአፍሪካ ወጣቶችን አእምሮ ከቅኝ ግዛት አስተሳሰብ ነፃ ማውጣት ነው፤ ምክንያቱም ባለፉት ጥቂት መቶ ዓመታት የአፍሪካ ታሪክ ሲታጠብና ሲበረዝ ቆይቷል። [...]ስለሆነም፣ አሁን ባለው የግዙፍ የሃሳብ ለውጥ ወቅት፣ ታሪካችን ከአፍሪካ ነፃነት ጋር እንዳልተጀመረ በአፍሪካም ሆነ በመላው ዓለም ለሚገኙ ወጣቶች የማሳወቅ፣ የማስተማር እና ግንዛቤ የመፍጠር ኃላፊነት የኛ ነው።” ሲሉ የቱሪዝም ባለሙያ እና የባህል ጉዳዮች አንቂ ራስ አብይ ጥላሁን ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል፡፡ በዚህኛው ባለሁለት ክፍል የራይዚንግ ሳውዝ ዝግጅት፣ በመጀመሪያው ክፍል፣ የቱሪዝም ባለሙያ እና የባህል ጉዳዮች አንቂ ራስ አብይ ጥላሁን...

በርሊን ኮንፈረንስ፡-የምዕራባውያን ኢ-ፍትሐዊነት እና በደል በአፍካውያን ላይ 17.12.2025

“አፍሪካውያን ሸማቾች እንዲሆኑ፣ ከዛ በፊት አይተው የማያውቁትን የአውሮፓ እቃ መሸመት፣ መጠቀም እንዲችሉ ብዙ ተዘዋዋሪ መንገዶችን ይጠቀማሉ። አፍሪካውያን ያለነዛ ሽቀጦች ህይወታቸውን መምራት እንዳይችሉ አድርገው አጣብቂኝ ውስጥ ይከቷቸዋል።” ሲሉ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የታሪክ መምህርና ተመራማሪ ደቻሳ አበበ (ዶ/ር) ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል፡፡ በዚህኛው የራይዚንግ ሳውዝ ባለ ሁለት ክፍል ዝግጅት፣ በመጀመሪያው ክፍል፣ የአውሮፓ ወራሪ ኃይሎች በበርሊን ኮንፈረንስ ላይ ያደረጉት አፍሪካን የመቀራመት ስምምነት በአፍሪካ እና አፍሪካውያን ላይ ስላንጸባረቁት ኢ-ፍትሐዊነት እና ስላደረሱት በደል በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የታሪክ...

አፍሪካን ከውስጥ ወደ ውጭ መገንባት፡ ባህል፣ ገንዘብ (ምንዛሪ) እና የኃይል ትስስር 16.12.2025

“በእኛ የሥነ ምግባር እሴቶች ላይ በመመሥረት፣ ለህብረተሰቦቻችንና ለኅብረተሰባችን ጥሩ የሆነውንና አስፈላጊ የሆነውን ነገር መከላከል አለብን። በትክክለኛ መረጃ እና በተገቢው ግንኙነት በትክክል መከላከል አለብን። […]የመንግሥት መዋቅር በሽማግሌዎች ላይ እምነት ሊኖረውና ሥልጣንን በአግባቡ መወከል አለበት፤ ዝም ብሎ በስም ብቻ ሳይሆን።” ሲሉ የኢትዮጵያ የሽማግሌዎች ምክር ቤት ሊቀመንበር የሆኑትተስፋጽዮን ደለለው(ዶ/ር)  ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል፡፡ በዚህኛው የራይዚንግ ሳውዝ ባለ ሦስት ክፍል ዝግጅት፣ በመጀመሪያው ክፍል የኢትዮጵያ የሽማግሌዎች ምክር ቤት ሊቀመንበር የሆኑትተስፋጽዮን ደለለው(ዶ/ር) ጋር ባህላዊ የግጭት አፈ...

ያልታየና ያልተነገረ፡ የካንሰር በሽታ በኢትዮጵያ 15.12.2025

“በኢትዮጵያ በየዓመቱ ከ80,000 ሰዎች በላይ አዳዲስ የካንሰር በሽታ ይያዛሉ። ከእነዚያ ከ80,000 ኬዞች መካከል ደግሞ 54,000 ያህሉ በዚያው ዓመት ህይወታቸው ያልፋል […] ከኤች አይ ቪ፣ ቲቢ እና ወባ ጋር ሲነጻጸር የካንሰር ሞት መጠን ከሦስቱ በሽታዎች ጥምር ይበልጣል።” ሲሉ የካንሰር ኤፒዲሚዮሎጂስት፣ የስታቲስቲክስ ባለሙያ እና የአዲስ አበባ ከተማ ካንሰር ምዝገባ ሥራ አስኪያጅ ሰለሞን አስማረ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል፡፡ በዚህ የራይዚንግ ሳውዝ ዝግጅት፣ የኢትዮጵያን እየጨመረ የመጣውን የካንሰር ጫና ከባለሙያ እንመረምራለን። ብዙ የካንሰር ኬዞች በጣም ዘግይተው የሚታወቁት ለምንድን ነው? ማዕበሉን ለመቀየር ምን መ...

የውጭ እርዳታ መቀነስ፡ በኢትዮጵያ የጤና ዘርፍ ላይ ተስፋና ስጋት 15.12.2025

“የውጭ እርዳታ ማጣት በጣም አሳሳቢ ጉዳይ ነው […] ለቲቢ፣ ኤች አይ ቪ እና ወባ አስፈላጊ የሆኑ መድኃኒቶችን ግዥ ያለ እርዳታው በተግባር የማይቻል ነው። ነገር ግን አርቀን ስንመለከት ይህ የማንቂያ ደወል ሊሆን ይችላል። ለአፍሪካ ለቲቢ፣ ኤች አይ ቪ ወይም ጤና ብቻ ሳይሆን ለእርሻ፣ ትምህርት እና ሌሎችም ሀብትን በማሰባሰብ በራሷ ላይ ለመደገፍ ጥሩ አጋጣሚ ሊሆን ይችላል።” ሲሉ የ'ቮለንተሪ ሄልዝ ሰርቪስ' ኢትዮጵያ መስራችና ዋና ዳይሬክተር እንዳልካቸው ፍቃዱ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል፡፡  በቲቢ በሽታ ከፍተኛ ጫና ካለባቸው አገሮች መካከል የሆነችው ኢትዮጵያ የጤና አጠባበቅ ሥርዓቷ ዋነኛ የጀርባ አጥንት የነበረው የውጭ እ...

ኢትዮጵያዊው ጠበቃ የህግ የበላይነት ተጋድሎ፡ የምሥራቅና ደቡብ አፍሪካ የጋራ ገበያ (ኮሜሳ) ክስ ጉዳይ 12.12.2025

“ይህ ክስ ለመላው አህጉር ታላቅ ምሳሌ የሚሆን የሕግ መሠረት መጣል የቻለ ነው። […] በአኅጉራዊና ክልላዊ አካላት ውስጥ ያሉ አንዳንድ ባለሥልጣናት ውሳኔያቸው የማይነኩ እና የማይጠየቁ እንደሆኑ ሊያስቡ ይችላሉ። ነገር ግን መጠየቅ አለበት። እናም፣ በዚህ ዓይነት ክስ የሚጠቀሙት የመጀመሪያው አካል ክሱን ያቀረበው ግለሰብ ሳይሆን፣ ተቋሙ ራሱ ነው።” ሲሉ የፓን አፍሪካ ህግ ባለሙያዎች ህብረት እና የኢትዮጵያ የጠበቆች ማኅበር ፕሬዚዳንት ቴዎድሮስ ጌታቸው ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል፡፡ በዚህኛው የራይዚንግ ሳውዝ ባለ ሁለት ክፍል ዝግጅት፣ በመጀመሪያው ክፍል የፓ ን አፍሪካ ህግ ባለሙያዎች ህብረት እና የኢትዮጵያ የጠበቆች ማኅበር...

የሐይማኖታዊ እና ባህላዊ እሴቶች ሚና ጾታን ጥቃቶችን ለመከላከል 12.12.2025

“የመጀመሪያው ትልቁ ነገር የሰውን ልጅ ክብር ማሳወቅ ነው። የሰው ልጅ ክብር፣ አንዱ ጉልበት ስላለው ሌላውን ጉልበት የሌለውን የማጥቃት መብት እንዳለው ተደርጎ የሚቆጠርበት አለመሆኑን፣ ሰውን ማክበርን ፈጣሪን መፍራትን፣ ህግን መጠበቅን በተለይ ደግሞ አጥቂነትን፣ የአጥቂነት ባህሪን በተቻለ መጠን አውግዞ በማስተማር የሀይማኖት ተቋማት ትልቅ ድርሻ አላቸው።” ሲሉ በቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ የስነመለኮት መምህር የሆኑት መምህር ዳንኤል ሰይፈሚካኤል ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል፡፡ በዚህኛው የራይዚንግ ሳውዝ ባለ ሁለት ክፍል ዝግጅት፣ በመጀመሪያው ክፍል በኢትዮጵያ ውስጥ ስላለው ጾታን መሰረት ስላደረገ ጥቃት እንዲሁም በመንግስት...

ትምህርትና ሉዓላዊነት ፡- የአፍሪካ የመምህራን ሥልጠናን ከቅኝ ግዛት ጥላ ነጻ መውጣት 11.12.2025

“ቀጥታ የውጭውን ዓለም የሥርዓተ ትምህርት ከኢትዮጵያውያን ህይወት ጋር ብዙም ግንኙነት የሌለው፣ ልጆቹን ትራንስፎርም የማያደርግ፣ አካባቢውን የማይለውጥ፣ አካባቢውን ያልተገነዘበ ሥርዓተ ትምህርት ታመጣና [...] ኢትዮጵያ አምጥተህ ስታስቀምጠው አይገጣጠምም፡፡” በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የቋንቋ እና የትምህርት ኮሌጅ የሳይንስ ትምህርት ረዳት ፕሮፌሰር እና በትምህርት ሚኒስቴር የከፍተኛ ትምህርት አማካሪ ምክር ቤት አባል ሰለሞን በላይ (ዶ/ር) ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል፡፡ በዚህኛው የራይዚንግ ሳውዝ ዝግጅት ላይ፣ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የቋንቋ እና የትምህርት ኮሌጅ የሳይንስ ትምህርት ረዳት ፕሮፌሰር እንዲሁም በትምህርት ሚኒ...

አማራጭ ሀብት ለአፍሪካ ዕድገት፡ ከባህላዊ የኢንቨስትመንት መንገዶች ባሻገር 11.12.2025

“የአማራጭ ሀብቶች ፣ ለምሳሌ የሰው ካፒታል መረጃ ጠቋሚ ምርታማነት፣ የህዝቡ መጠን እና የኢኮኖሚዎ ስፋት—ተቋማዊ ሁኔታዎችንሊቀይሩ/ሊያስተካክሉ ይችላሉ። ስለዚህ፣ አማራጭ ሀብቶች ልክ እንደ ቀጥተኛ የውጭ ኢንቨስትመንት በተመሳሳይ መንገድ ተጽዕኖ አያድርባቸውም፡፡” ሲሉ የማኔጅመንትና ኢኮኖሚክስ አማካሪ ሳታ አብርሃም (ዶ/ር) ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል፡፡ በዚህኛው የ ራይዚንግ ሳውዝ ባለ ሁለት ክፍል ዝግጅት፣ በመጀመሪያው ክፍል ከሰሃራ በታች ያሉ የአፍሪካ ሀገራት በአማራጭ ሀብት ላይ ከሚሰሩ ቀደምት ተመራማሪዎች አንዱ ከሆኑት ሳታ አብርሃም (ዶ/ር) ጋር በመሆን ከሰሃራ በታች ባሉ የአፍሪካ ሀገራት ወስጥ የግል ሀብት ፣ ቬንቸ...

የማካካሻ ፍትህ ፦ ለአፍሪካ ለምን አስፈላጊና ወሳኝ ጥያቄ ሆነ ? 09.12.2025

“የቅኝ ግዛት ካሳ ጉዳይ ማንሳት ከታሪካዊ እይታ አንጻር ብቻ ሳይሆን ከፖለቲካዊና ከሥነ-ልቦናዊ እይታ አንጻርም ጭምር በጣም አስፈላጊ ነው። ይህም አሁን ያለው የምዕራቡ ዓለም ትውልድ እንዲሁም አሁን በአፍሪካ እና በሌሎች በዓለም ዙሪያ በሚገኙ የቅኝ ግዛት ሥር በነበሩ አገሮች የሚኖሩት ትውልዶች በእነዚህ አካባቢዎች ጭቆና፣ ብዝበዛ እና አሰቃቂ የቅኝ ግዛት አገዛዝ እንደነበረ ማወቅ አለባቸው።” ሲሉ የፖለቲካ ሳይንስና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ምሁሩ ዳዊት መዝገበ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል፡፡ በዚህኛው የራይዚንግ ሳውዝ ባለ ሁለት ክፍል ዝግጅት፣ በመጀመሪያው ክፍል የ ፖለቲካ ሳይንስና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ምሁሩ ዳዊት መዝገበ ፣...

የግብርና መድህን ሽፋን በኢትዮጵያ 01.12.2025

“የግብርና መድህን በአገራችን ውስጥ የሚፈለገውን ያህል አላደገም፡፡ ከአጠቃላይ ኢንዱስትሪው ከሚሰጠው የመድህን ሽፋን የግብርና ኢንሹራንስ ስናየው ከ 1 በመቶ አይዘልም፡፡ እስካሁን የተሰራው፡፡ እሱም ቢሆን ደግሞ በአብዛኛው ኮሜርሻል ፋርም ጋር የሚያያዝ ነው፡፡” ሲሉ የኢትዮጵያ የኢንሹራንስ ባለሙያዎች ማህበር ም/ፕሬዝደንት እንዲሁም የኢትዮጵያ ጠለፋ መድን አክሲዮን ማኅበር የስትራቴጂ እና ቢዝነስ ዴቨሎፕመንት ሥራ አስፈጻሚ አቶ ፍቅሩ ፀጋዬ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል፡፡ በዚህኛው የራይዚንግ ሳውዝ ባለ ሁለት ክፍል ዝግጅት፣ በመጀመሪያው ክፍል በኢትዮጵያ ውስጥ የግብርና መድህን ያለበትን ደረጃ እና አገልግሎቱን ተደራሽ በማድረግ...

የአፍሪካ አህጉራዊ የካሳ ጥያቄ ፡ የቅኝ ግዛት ዘመኑን በደል ምን ሊክሰው ይችላል ? 27.11.2025

“ገንዘብ እጅግ ጥሩ ያልሆነ የካሳ ዓይነት ይመስለኛል። የአውሮፓ አፍሪካን የመቆጣጠር ጥቅም፣ ከቅኝ ግዛት፣ ከአዲሱ ቅኝ ግዛት እና ከባርነት የተገኘው፣ ዘላቂ ችግር ነው። ስለዚህ፣ የካሳው ጥቅምም እንዲሁ ዘላቂ መሆን አለበት ብዬ አስባለሁ።[…]የቀድሞ ጨቋኞች በአህጉሪቱ ላይ የአንድነት መሠረተ ልማቶችን መገንባት አለባቸው። ይህ ማለት እንደ ካሳ ፣ መላውን አፍሪካ ከምዕራብ እስከ ምሥራቅ አፍሪካ የሚያገናኝ የባቡር ሐዲድ መገንባት አለበት።[...] ይህ አፍሪካ ዛሬ ከምናደርገው በበለጠ መልኩ በውስጥዋ ውጤታማ ንግድ እንድትፈጽም ያስችላታል።” ሲሉ የፓን-አፍሪካኒዝም አቀንቃኝ እና አማካሪ ካባላ ጆን ካባላ ጆን ለስፑትኒክ አፍሪካ ተ...

ከጥገኝነት ወደ ለውጥ፡ አፍሪካ ከውጭ ለምታስገባው ምግብ የምታወጣውን የ100 ቢሊዮን ዶላር እንዴት መቀነስ ትችላለች ? 26.11.2025

“አፍሪካ ቢያንስ 100 ቢሊዮን ዶላር የሚጠጋ ገንዘብ [በዓመት] ምግብ ለማስገባት ታወጣለች። ይህ የግብርና ዘርፍ ሊለውጠው ይችል ነበር። ስለዚህ [...] መንግስታት በዋና ዋና መሠረተ ልማቶች ላይ ኢንቨስት ማድረግ አለበት። ከእነዚህም መካከል መስኖ ቁጥር አንድ ሊሆን ይችላል፤ ሜካናይዜሽን ደግሞ ቁጥር ሁለት፤ የገበያ መሠረተ ልማት ደግሞ ቁጥር ሶስት ነው። ” ሲሉ የአሊያንስ ፎር ግሪን ሪቮሊዩሽን አፍሪካ ዳይሬክተር እና የ2025 የአፍሪካ የግብርና ባለራዕይ ሳይንቲስት ፕሮፌሰር ጥላሁን አመዴ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል ፡፡ በዚህ የራይዚንግ ሳውዝ ባለ ሁለት ክፍል ዝግጅት፣ በመጀመሪያው ክፍል የአሊያንስ ፎር ግሪን ሪቮሊዩሽን...

የዘረመል ንቅለ ተከላ እና ጂኦፖለቲክስ፡ የኢትዮጵያን የወደፊት ሁኔታ የሚቀርጹ ሁለቱ ኃይሎች 20.11.2025

“[ምዕራቡ ዓለም] ወጥመድ ውስጥ ለማስግባት ይሞክራሉ፣ ምክንያቱም በገንዘብ በሚረዱበት ጊዜ ሁሉ የራሳቸውን መስፈርት ያስቀምጣሉ። የአንተ ፍላጎት በእነሱ ቅድሚያ የሚሰጠው አይደለም።[...] አንተ ቅድሚያ የሚሰጣቸው ነገሮች የትኞቹ እንደሆኑ መወሰን አለብህ። ለእነዚያም ቅድሚያ ለሚሰጣቸው ዘርፎች ከሀገር ውስጥ ገንዘብ እንዲገኝ ማድረግ ይገባል።” ሲሉ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በአፕላይድ ጄኔቲክስ ተባባሪ ፕሮፌሰር ደረጀ በየነ (ዶ/ር)  ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል። በዚህኛው የራይዚንግ ሳውዝ ባለ ሁለት ክፍል ዝግጅት፣ በመጀመሪያው ክፍል የ የዘረመል ንቅለ ተከላ (Genome Editing) የአፍሪካን የምግብ ስርዓት፣ ሳይንሳዊ...

የባህል ኃይል፡ ከጋና አሳንቴ ቅርስ እስከ የአፍሪካ ሴቶች የፍትህ ትግል እና የምግብ ሉዓላዊነት 17.11.2025

“ብዙ ሰው እንደሚያስበው ባህል የአኗኗር ዘይቤ አደለም፤ ባህል ራሱ ሕይወት ነው። ሁሉም ህይወት ባህል ነው። ባህል ማንነትህን ይገልጻል። ባህል አንተ ማን እንደሆንክ ያደርግሃል። ባህል ህይወት ነው ስል፣ ባህልን እንወልዳለን። ባህልን እናወራለን። በባህል እንኖራለን። በባህል እንተኛለን። በባህል እንንቀሳቀሳለን። በባህል እንሄዳለን። እና ባህልን እንሰራለን። ስለ ህይወት ያለው ነገር ሁሉ ባህል ነው። ባህልህን የሚቆጣጠር ሁሉ ሀብትህን ይቆጣጠራል።” ሲሉ   የቴስት ኦፍ አፍሪካ ተባባሪ መስራች እና ዋና ሥራ አስፈጻሚ ቴንጎል ኬፕለማኒ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል። በዚህኛው ሦስት ጉዳዮችን በሚዳስሰው የራይዚንግ ሳውዝ ዝግጅት፣ በ...

በኢትዮጵያ አሳሳቢ እየሆነ የመጣው የስኳር በሽታ: መንስኤዎች፣ ተግዳሮቶች እና መፍትሄዎች 14.11.2025

"በሕክምና አገልግሎታችን የምናየው ነገር ቢኖር በስኳር ህመምተኞች ቁጥር ላይ ከፍተኛ ጭማሪ መኖሩን ነው — ዓይነት 1 እና ዓይነት 2 ላይ ጭማሪ ይታያል። እንዲያውም ጥናቶች እንደሚያሳዩት በ13 ዓመታት ጊዜ ውስጥ የስኳር በሽታ ያለባቸው ሰዎች ቁጥር በእጥፍ ሊጨምር ይችላል።" ሲሉ ጠቅላላ ሐኪም ዶ/ር ሩት ዳኛቸው ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል ፡፡ በዚህኛው የራይዚንግ ሳውዝ ባለ ሁለት ክፍል ዝግጅት፣ በመጀመሪያው ክፍል በዓለም-አቀፍ ደረጃ በዛሬው ህዳር 5 የሚከበረውን የስኳር በሽታ ቀንን በማስመልከት በኢትዮጵያ በፍጥነት እየጨመረ ያለውን የስኳር በሽታ ታማሚዎች ቁጥር መንስኤዎች፣ ተግዳሮቶች እና መፍትሄዎች ጠቅላላ ሐኪም ከሆኑ...

Listen to the The Rising South podcast in Replaio

Radio and podcasts in one app - free, with no sign-up. Install today and do not miss the launch

Get it on Google Play

Replaio is not a podcast publisher; show names, artwork and audio belong to their authors and are distributed through public RSS feeds.