ወሰንሰገድ አሰፋ
The Rising South
የዓለም አቀፍ የኃይል ሚዛን እየተቀየረ ባለበት በዚህ ወቅት - ኢትዮጵያን፣ አፍሪካን እና ሌሎችን የሚቀርጹ የፖለቲካ፣ የኢኮኖሚ እና የማህበራዊ ሃይሎች ወደምንመለከትበት ወደ “ራይዚንግ ሳዉዝ” እንኳን በደህና መጡ፡፡ ደቡባዊ አመለካከቶችን ወደ ዓለም አቀፋዊ ውይይት መድረክ ስናቀርብ የአሰላሳዮችን ፣ የመሪዎችን እና የለዉጥ ፈጣሪዎችን ሃሳብ ያድምጡ።
Author
ወሰንሰገድ አሰፋ
Category
Podcast website
Latest episode
Jul 11, 2026
Where to listen?
Podcasts in the app Replaio Radio Coming soonPodcasts are coming to the app soon. Install now and be the first to see a whole new take on podcasts
Episodes
ከተውሶ መዋቅር ወደ ሉዓላዊ ማዕቀፍ፡ የአፍሪካ ትምህርት ሥርዓት ዳግም ቅርጻ 11.07.2026 1:00:04
"አፍሪካ የራሷን የአእምሮ ነጻነት ማረጋገጥ ካለባት፣ የትምህርት ሥርዓቱ በሌላ ሀገር በተቀረጸ የተውሶ መዋቅር ላይ ሳይሆን፣ በራሷ ነባራዊ እውነታዎችና ምኞቶች ላይ የተመሠረተ ሉዓላዊ ማዕቀፍ ሆኖ እንደገና መነደፍ አለበት። የአፍሪካን አእምሮ ነጻ ማውጣት ማለት ፊታችንን ከዓለም ማዞር ማለት አይደለም፤ ይልቁንም በዚያ ዓለም አቀፍ መድረክ ላይ በገዛ የራሳችን ድምፅና ማንነት መቅረብ መቻል ማለት ነው::" ሲሉ የርቀት ትምህርት ረዳት ፕሮፌሰር አደራጀው ምሕረት ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል። በዚህ የራይዚንግ ሳውዝ ዝግጅታችን በክፍል አንድ ለዲጂታሉ ዘመን የሚመጥን እና ከአውሮፓውያን የተውሶ አስተሳሰብ የወጣ የአገር በቀል ትምህርት...
ከረግረጋማ መሬት ኢኮኖሚ እስከ ቡና ወጪ ንግድ ስኬት 11.07.2026 1:00:04
"የመንግስት ፖሊሲ በግብርናው ዘርፍ በጎን ከመስፋፋት ይልቅ የተጠናከረ (ምርታማ) ግብርናን መጠቀም አለብን የሚል ነው። የዚህ ግብርና በጎን መስፋፋት ተፅዕኖ ረግረጋማ መሬቶቻችንን በከፍተኛ ሁኔታ እና ከመጠን በላይ እንዲራቆቱ ያደርጋል። ስለዚህ ይህንን በመረዳት ግብርናን ከዘመናዊ ቴክኖሎጂዎች እና ከአግሮፎሬስትሪ ስርዓቶች ጋር በማቀናጀት ችግሩን መቆጣጠር ይኖርብናል።" ሲሉ በወራቤ ዩኒቨርሲቲ የኢኮኖሚክስ መምህርና የዌትላንድስ ኢንተርናሽናል ቀጣናዊ አስተባባሪ መሐመድ ኢሳ (ዶ/ር) ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል። በዚህ የራይዚንግ ሳውዝ ዝግጅት ሶስት ቁልፍ ጉዳዮችን እንመለከታለን፡፡ክፍል አንድ፦ የኢትዮጵያ ረግረጋማ መሬቶች (W...
ከአእምሮ ነፃነት እስከ አህጉራዊ የውኃ ሀብት ሉዓላዊነት 11.07.2026 1:00:04
"የአፍሪካ ትራንስፎርሜሽን ጉዞ የእውቀት ምርትን፣ ታሪካዊ ትውስታን እና ምሁራዊ ነፃነትን መልሶ ከመያዝ ትግል ጋር በቀጥታ የተገናኘ ነው። የትምህርት ሥርዓቶቻችን እና የታሪክ ትረካዎቻችን ከአሮጌው የቅኝ ግዛት አስተሳሰብ ነፃ ካልወጡ አህጉሪቱ እውነተኛ ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ሉዓላዊነትን ማረጋገጥ አትችልም።" ሲሉ የፓን-አፍሪካን አስተሳሰብ ትምህርት ቤት መስራች እና ዳይሬክተር ናይጄል ስቴዋርት ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል፡፡ በዚህኛው ባለሁለት ክፍል የራይዚንግ ሳውዝ ዝግጅታችን፣ «አእምሮን ከቅኝ ግዛት አስተሳሰብ ማውጣት፦ ትምህርት፣ ታሪክ እና የአፍሪካ ፖለቲካዊ መጻኢ ዕድል» በሚለው ዋና አጀንዳ ላይ ከፓን-አፍሪካን...
የምዕራባውያን በበላይነት የተቆጣጠሯቸው የፋይናንስ ተቋማት እና የአዲሱ ዓለም ሥርዓት ፈተናዎች 11.07.2026 1:00:04
“በዓለም አቀፍ የፋይናንስ ሥርዓቶች ላይ የተዘረጋው የምዕራባውያን የበላይነት የሚቀጥለው በተቋማዊ የበላይነት ቅንጅት አማካኝነት ነው። ይህም እንደ የአሜሪካ ዶላር ያሉ የመጠባበቂያ ገንዘቦች ካላቸው መዋቅራዊ ኃይል እና ከዓለም አቀፍ የክፍያ ስልቶች ላይ ካለው ቁጥጥር ጋር የተያያዘ ነው። እነዚህ ስልቶች በአንድ ላይ በመሆን፥ ምዕራባውያን አገራት በመላው ዓለም ላይ ከፍተኛ የሆነ የጂኦ-ፖለቲካዊ ኢኮኖሚ ተጽዕኖ እንዲያሳድሩ ያስችሏቸዋል።” ሲሉ በደቡብ አፍሪካ ዩኒቨርሲቲ የልማት ኢኮኖሚስት ለሄሳ ሞሎይ (ዶ/ር) ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል፡፡ ፡ በዚህ የራይዚንግ ሳውዝ ዝግጅታችን በክፍል አንድ የሩሲያዉ ፕሬዝደንት ሰርጌ ላቭሮቭ...
የአፍሪካ የቢዝነስ ትምህርት ለአህጉራዊ ሽግግር 11.07.2026 1:00:04
"አብዛኞቹ የቢዝነስ ትምህርት ተቋማት ኢንዱስትሪዎችን ሳያሳትፉ የትምህርት ሥርዓቱን (ካሪኩለሙን) በራሳቸው ብቻ ያዘጋጃሉ። ዩኒቨርሲቲዎች ወይም የአካዳሚክ ተቋማት ተማሪዎቻቸውን በምድር ላይ ካለው ተጨባጭ ሁኔታ ጋር ሳያስተዋውቁ እንዲሁ ንድፈ-ሃሳብን ብቻ ያስተምራሉ_ ይህ ሁኔታ እንዲቀየር በትጋት ልንሰራ ይገባናል፡፡" ሲሉ የኢትዮጵያ የዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት ዋና ፀሀፊ የሆኑት ዶ/ር ቀነኒሳ ለሚ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል፡፡ በዚህኛው የራይዚንግ ሳውዝ ዝግጅታቸን የአፍሪካ የቢዝነስ ትምህርት ቤቶች የአህጉሪቱን የኢኮኖሚ ትራንስፎርሜሽን በትክክል መምራት ይችላሉ? ወይንስ አሁንም ከአካባቢያዊ እውነታዎቻችን የራቁ የውጭ ሀገ...
ከአሰላለፍ ነፃነት ወደ ስትራቴጂካዊ ሉዓላዊነት፦ የአፍሪካ አዲሱ የውጭ ፖሊሲ አካሄድ 09.07.2026 1:00:04
"አፍሪካውያን በዓለም አቀፍ ግንኙነት ውስጥ ሁለቱንም ወገን ተጠቃሚ የሚያደርግ አካሄድን ሲያስቡ፤ የትኛውንም ሀገር ውይም ቀጠና በፍፁም በዕውር ድንብር ማመን የለባቸውም። በመጀመሪያ ደረጃ አፍሪካውያን ማድረግ ያለባቸው ትልቁ ነገር በመካከላቸው እምነትን መገንባት ነው።" ሲሉ በዲላ ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካ ሳይንስ መምህር ዳዊት መዝገበ (ዶ/ር) ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል። የሩሲያው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌይ ላቭሮቭ የአፍሪካ አገራት ጉብኝታቸውን ሐምሌ 30 2018 ዓ.ም በኢትዮጵያ ጀምረው ነሐሴ 1 እና 2 2018 በኒጀርና ሞዛምቢክ ይፋዊ የስራ ጉብኝት እያደረጉ ነው፡፡ ይህ በአህጉሪቱ ላይ ምን አዲስ የፖለቲካ አንድምታ ይዟል...
የአፍሪካ ኢኮኖሚ ለውጥ፦የአለም ፖለቲካዊ መዋዠቅ ለአፍሪካ ኢንዱስትሪ አዲስ መንገድ እንዴት እየፈጠረ ነው? 02.07.2026 1:00:00
"ከቅኝ ግዛት ዘመን ጀምሮ የአፍሪካ ኢኮኖሚ መዋቅር ለምዕራባውያን ተገዢ እንዲሆን ተደርጎ ነው የተቀረጸው። የአሁኑ የዓለም አቀፍ አቅርቦት ሰንሰለት መቋረጥ ግን ወደ ውስጥ እንድንመለከት፣ አምራች እንድንሆን እና በአህጉራዊ የነፃ ንግድ ቀጠና በኩል እርስ በርስ እንድንተሳሰር ትልቅ ዕድል የፈጠረልን 'የመቀስቀሻ ደወል' ነው።" ሲሉ በኢትዮጵያ የፖሊሲ ጥናትና ምርምር ኢንስቲትዩት ከፍተኛ ተመራማሪ ጀማል መሐመድ (ዶ/ር) ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል። በዚህ የራይዚንግ ሳውዝ ዝግጅት በክፍል አንድ፦ የአፍሪካ የንግድ ሪፖርት 2026ን መነሻ በማድረግ የዓለም ፖለቲካዊ መዋዠቅ ለአፍሪካ የኢንዱስትሪ ሽግግርና ለአህጉራዊ ነፃ ንግድ ቀ...
ከዲጂታል ጥገኝነት ወደ ዲጂታል ሉዓላዊነት፦ የአፍሪካ የቴክኖሎጂ አስተዳደር ፈተና 29.06.2026 1:00:00
"ለእኔ ዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ማለት ቴክኖሎጂን መግዛት ብቻ አይደለም፤ ቴክኖሎጂውን እንዴት እንደምንጠቀምበት፣ የዜጎችን ዲጂታል ሀብት እንዴት እንደምንጠብቅበት እና ማኅበረሰቡን እንዴት እንደሚያገለግል መቅረጽም ነው። […] አፍሪካ የራሷን የቴክኖሎጂ አስተዳደር ማዕቀፍ ካልገነባች በቴክኖሎጂ ዘርፍ የቅኝ ግዛት ሰለባ የመሆን አደጋ አለ።" ሲሉ የዲጂታል ትራንስፎርሜሽንና የቴክኖሎጂ አስተዳደር አማካሪ እስክንድር መስፍን ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል። በተጨማሪም "ገንዘብ ካለህ ቴክኖሎጂን በአንድ ሌሊት መግዛት ትችላለህ፤ ነገር ግን ዲጂታል ብቃት፣ የሰው ኃይል አቅምና ተገቢ የአስተዳደር ሥርዓት ያለ ቴክኖሎጂ በማይበቅል መሬት ላይ...
የጥንታውያን የአፍሪካ መንግስታት ዳግም ውህደት፦ ባህል፣ ስልጣን እና ልማት ከቅኝ ግዛት ድንበሮች ባሻገር 29.06.2026 1:00:00
"ወጣቶቻችን እውነተኛ ማንነታቸውን አውቀው እንዲታጠቁ ካደረግን ከ10 እና 20 ዓመታት በኋላ የሚጠፉ አይሆኑም፤ ይልቁንም በባህላቸው እየኮሩ ለዓለም የሚያስተዋውቁ እነሱ ይሆናሉ።" ሲሉ በጋና የባህላዊ መሪ፣ የ'ቴስት ኦፍ አፍሪካ' ተባባሪ መስራች እና የ'ሲስተር ኪንግደም ኔትወርክ' መስራች የሆኑት ቴንጎል ክፕሌማኒ ለስፕትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል፡፡ በዚህ የራይዚንግ ሳውዝ ዝግጅታችን፤ አፍሪካ ከመደበኛው የመንግስት መዋቅር ባለፈ በጥንታውያን መንግስታቷ እና በባህላዊ እሴቶቿ አማካኝነት ያላትን የአንድነት አቅም እንቃኛለን። በጋና የባህላዊ መሪ፣ የ'ቴስት ኦፍ አፍሪካ' ተባባሪ መስራች እና የ'ሲስተር ኪንግደም ኔትወርክ' መስራች ከ...
ኢነርጂ፣ ኢንቨስትመንትና የሩሲያ ቴክኖሎጂ፦ የኢትዮጵያ የኑክሌር ጉዞ 23.06.2026 1:00:00
"የኑክሌር ኃይል ማመንጫ መገንባት ሀገሪቱ አስተማማኝ እና ቋሚ የኤሌክትሪክ ኃይል ምንጭ እንድታገኝ ያስችላታል። […] ይህ አሠራር ደግሞ ድርጅቶችና ፋብሪካዎች ያለምንም መቆራረጥ ሥራቸውን እንዲያከናውኑ፣ ኢንቨስትመንትን ለመሳብ እና አዳዲስ የሥራ ዕድሎችን ለመፍጠር በር ከፋች ነው። እንዲህ ያሉ ፕሮጀክቶችን መተግበር በሩሲያ እና በኢትዮጵያ መካከል ያለውን የቴክኖሎጂ ትብብር ወደ ላቀ ደረጃ የሚያሸጋግር ዋነኛ ማሳያ ሊሆን ይችላል::" ሲሉ በኢትዮጵያ የሩሲያ ፌዴሬሽን የንግድ ተወካይ ያሮስላቭ ታራሲዩክ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል። በዚህኛው የራይዚንግ ሳውዝ ዝግጅታችን፣ ከብሪክስ አባልነት በኋላ እያደገ የመጣውን የኢትዮጵያና...
ሉዓላዊነት በተግባር፡ ከዓለም አቀፍ አጋርነት እስከ አፍሪካ የጤና ነፃነት 23.06.2026 1:00:00
“ከብሪክስ አንጻር ሲታይ፣ ኢትዮጵያንና ጥቂት ሌሎች የአፍሪካ ሀገራትን ያካተተ ዘርፈ-ብዙ ገጽታ አለው። ይህ ዘርፈ-ብዙ ግንኙነት ራሱ የአፍሪካ-ሩሲያን ግንኙነት ለማጠናከር የበኩሉን አስተዋጽኦ ያበረከተ ሲሆን፣ ይህም የደቡብ-ደቡብ ትብብር ዋነኛ ምሰሶ ነው። እንዲሁም ይህ ግንኙነት ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገ የመጣ ነው። ይህ ግንኙነት እየሰፋ የመጣ መስክ ያለው ሲሆን፣ ለሁለቱም ወገኖች ማለትም ለሩሲያ ፌዴሬሽን እና ለአፍሪካ ሀገራት የጋራ ተጠቃሚነትን የሚያረጋግጥ ነው።” ሲሉ በህዝብ ተወካዮች ምክርቤት የውጭ ግንኙነትና ሰላም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አባል አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል፡፡ በዚህ የራይዚንግ ሳ...
የብር ምንዛሬ ለውጥ፦ በኢትዮጵያ የፋይናንስ ዘርፍ ላይ ምን ለውጥ አመጣ ? 23.06.2026 1:00:00
“ገንዘቡ እንደ አስፈላጊነቱ ከተለቀቀ ችግሩ የዋጋ ንረትን ያባብሳል። ህዝቡ የዋጋ ንረት መሸከም አይችልም። በተለይ ቋሚ ገቢ ያላቸው።” ሲሉ የዘመን ባንክ ዋና የፋይናንስ ኦፊሰር አቶ መሰረት ወንድም ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል፡፡ በዚህ የራይዚንግ ሳውዝ ዝግጅት፣ የዘመን ባንክ ዋና የፋይናንስ ኦፊሰር ከሆኑት ከአቶ መሰረት ወንድም ጋር በመሆን የ[ኢትዮጵያ]ብር ምንዛሬ ለውጥ፣ ለገንዘብ ፍሰት፣ ለብድር እና ህዝቡ በፋይናንስ ሴክተሩ ስርዓቱ ላይ ያለው እምነት ላይ ምን ሊፈጥር እንደሚችል የዳሰስን ሲሆን፤ በክፍል ሁለት ደግሞ የዲጂታል አስተዳደር እና ትራንስፎርሜሽን አማካሪ ከሆኑት ከአቶ እስክንድር ቸርነት ጋር፣ በአርቴፊሻል...
የሰብአዊ እርዳታ ሉዓላዊነት፡- የሀገርን ነፃነትና ክብር የማስጠበቅ ተግባር 23.06.2026 1:00:00
"የሰብአዊ እርዳታ ሉዓላዊነትን ማረጋገጥ አሁን ላይ ለማንኛውም ሀገር ምርጫ አይደለም፤ በተለይም ስለ ሀገር ክብር፣ ነፃነት እና ሉዓላዊነት ለሚያስብ ሀገር ይህ ጉዳይ የግድ የሚል ተግባር ነው።" ሲሉ የብሄራዊ የአደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ኮሚሽነር አምባሳደር ሽፈራው ተክለማርያም ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል፡፡ በዚህኛው ባለ ሶስት ክፍል የራይዚንግ ሳውዝ ዝግጅት፤ በመጀመሪያው ክፍል በአርኪኦሎጂ እና በሰው ልጅ አመጣጥ ላይ ያተኮረ ሲሆን፤ በኢትዮጵያ ቅርስ ባለስልጣን የፓሊዮአንትሮፖሎጂ ተመራማሪዎች ከሆኑት ከዶ/ር በርሄ አስፋው እና ከዶ/ር ዮናስ በቀለ ጋር በመካከለኛው አዋሽ ስለተገኙ አዳዲስ የሳይንስ ግኝቶች እንወያያለ...
የኢኮኖሚ እና የቅኝ ግዛት ድንበሮች፡- የአፍሪካ ልማት ሁለት ግንባሮች 08.06.2026 1:00:00
“የቅኝ ግዛት ድንበሮች ተፈጥሯዊ ድንበሮች አይደሉም… የተፈጠሩት ለአፍሪካ ሕዝቦች ጥቅም አይደለም። [……]እነዚህ የዘፈቀደ ድንበሮች የጎሳ፣ የባህል እና የቋንቋ እውነታዎችን ችላ ብለው የተበጣጠሰ ማንነትን አስከትለዋል።” ሲሉ የታሪክ መምህርና ተመራማሪው አሰፋ ባልቻ (ዶ/ር) ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል፡፡ በዚህ የራይዚንግ ሳውዝ ዝግጅት፣ በክፍል አንድ፣ የምጣኔ ሀብት ተመራማሪ እና የአለም አቀፍ ልማት አማካሪ ሳታ አብራሃም (ዶ/ር ) ጋር በመሆን የአፍሪካን የሥራ ፈጠራ ዘርፍ ዕድሎች እና ተግዳሮቶች የቃኘን ሲሆን፤ በክፍል ሁለት ደግሞ የታሪክ መምህርና ተመራማሪው አሰፋ ባልቻ (ዶ/ር) ጋር በመሆን የሕዝቦቿን ሁኔታ ከግን...
የአፍሪካ የኢኮኖሚ ሉዓላዊነት፦ ከጥሬ ዕቃ ወደ ማኑፋክቸሪንግ እና የሴንትፒተርስበርግ ጉባዔ ሚና 04.06.2026 1:00:00
“ለአፍሪካውያን የመጀመሪያው እና ዋናው ተግባር የገዛ ቤታችንን ማስተካከል ነው። ወደ እነዚህ ዓለም አቀፍ መድረኮች የምንሄደው የምንሸጠውን ነገር ሳንለይና ሳናደራጅ መሆን የለበትም፤ የሌለንን ነገር ለመሸጥ መሞከር ዘበት ነው። በመጀመሪያ የተፈጥሮ ሀብታችንን እና የፋይናንስ መዋቅራችንን በራሳችን ማደራጀት አለብን። ይህንን ካደረግን ወደ መድረኩ የምንመጣው በበላይነት እና በጥንካሬ ነው፤ ያለበለዚያ ግን፣ ውይይቶቹን ስንከታተል እንደምናየው፣ የምንሄደው ሁልጊዜ የእርዳታ እና የችሮታ ልመና ሰነድ ይዘን ብቻ ይሆናል።” ሲሉ በማላዊ ብሔራዊ የፕላኒንግ ኮሚሽን የልማት ኢኮኖሚስት የሆኑት ኦስቲን ቺንግዌንግዌ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል...
81ኛ ዓመት የድል ቀን መታሰቢያ፦ የኢትዮጵያና የሶቪየት ህብረት የጋራ የፀረ-ፋሺዝም ትግል 03.06.2026 1:00:00
"የሶቪየት ህብረት በናዚ ጀርመን ላይ የተቀዳጀችው ድል የሩሲያውያን ብቻ ሳይሆን የኢትዮጵያውያንም ጭምር ነው፤ ምክንያቱም ሁለቱም ሀገራት ለነፃነትና ለሉዓላዊነት ሲሉ ለከፈሉት መስዋዕትነት ትልቅ ማሳያ በመሆኑ ነው።" ሲሉ የታሪክ ተመራማሪውና ደራሲ አቶ ጥላሁን ጣሰው ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል፡፡ "በናዚ ጀርመን ላይ የተገኘው ድል የሁላችንም ድል ነው፤ ለሩሲያውያን ብቻ ሳይሆን ለአፍሪካውያን በተለይም ደግሞ ላልተገዛችው ኢትዮጵያ ትልቅ ትርጉም አለው፡፡" በማለት ፕሮፌሰር ዳንኤል ቅጣው አክለዋል፡፡ በዚህኛው የራይዚንግ ሳውዝ መሰናዶአችን፤ የሶቪየት ህብረት በናዚ ጀርመን ላይ ድል የተቀዳጀችበትን 81ኛ ዓመት መታሰቢያ አስመልክ...
ከመገኛነት ወደ ጠንካራ የምርት መለያነት፦ የኢትዮጵያ ስፔሻሊቲ ቡና በአለም አቀፍ መድረክ 03.06.2026 1:00:00
"የኢትዮጵያ ቡና ከሰራነው በላይ ፈጣሪ የሰጠን ትልቅ ሀብት ነው። እንዲያውም የኢትዮጵያ ቡና ከአለም ቢጠፋ፣ ቡና ከአለም ላይ እንደሚጠፋ ያውቃሉ? ምክንያቱም የቡና ዝርያ ክምችቱና (Genetic Reserve) መሰረቱ ያለው እዚሁ ኢትዮጵያ ውስጥ ነው።" ሲሉ የኢትዮጵያ ቡና ላኪዎች ማህበር ዋና ስራ አስኪያጅ የሆኑት አቶ ግዛት ወርቁ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል፡፡ በዚህኛው ባለሁለት ክፍል የራይዚንግ ሳውዝ ዝግጅት፤ በዓለም አቀፍ ደረጃ የሚታየው የዋጋ አለመረጋጋት እና በመካከለኛው ምስራቅ ያለው ውጥረት የኢትዮጵያን የቡና ኤክስፖርት እንዴት እያስተጓጎለ ይገኛል? ይህስ ለውጭ ምንዛሬ፣ ለኑሮ ሁኔታ እና ለገበያ መረጋጋት ምን ትር...
ታሪካዊናባህላዊ ትስስር፦ ውኃ የአፍሮ-ዲያስፖራ የጋራ ቅርስ 03.06.2026 1:00:00
"ውኃ ለአፍሪካ እና ለአፍሮ-ዲያስፖራው ከቀላል የተፈጥሮ ሃብትነት ባለፈ፣ አህጉራትንና ትውልዶችን የሚያገናኝ ታሪካዊ፣ ባህላዊና ኢኮኖሚያዊ ድልድይ ነው። ሳይንስን ከባህል፣ ቴክኖሎጂን ከአካባቢያዊ እውቀት ጋር በማጣመር የአየር ንብረት መረጃ ሉዓላዊነታችንን ማረጋገጥ እና በግሎባል ሳውዝ አገራት መካከል ጠንካራ ትብብር መፍጠር ይኖርብናል፡፡" ሲሉ የኢትዮጵያ ኦሽን ኢንስቲትዩት ተባባሪ መስራች እና ዋና ስራ አስፈፃሚ ኪዳን ኒኪታ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል፡፡ በዚህኛውየራይዚንግ ሳውዝ ዝግጅታችን፣ "የሰማያዊ ኢኮኖሚዎችን ማስተሳሰር፦ አፍሪካን እና አፍሮ-ዲያስፖራን በውኃ ማገናኘት" በሚል ዋና ርዕስ ዙሪያ የውቅያኖስ ሳይንቲስት እ...
የአየር ንብረት ለውጥን የሚቋቋም የምግብ ዋስትና በኢትዮጵያ፦ ከፖሊሲ ወደ ተግባር 28.05.2026 1:00:00
"የምግብ ስርዓት የምንለው ከምርት ጀምሮ እያንዳንዱ ሂደት አልፎ ምግብ የሸማቹ አፍ ውስጥ እስከሚገባ ድረስ ያለውን አጠቃላይ ሰንሰለት ነው።... የአየር ንብረት ለውጥ በአሁኑ ወቅት በአጠቃላይ የዕሴት ሰንሰለቱ ላይ ምርታማነትንና ፍጆታን አደጋ ላይ የሚጥሉ መዛባቶችን እየፈጠረ ነው። የአየር ንብረት ለውጥን የሚቋቋም የምግብ ሥርዓት መገንባት ማለት ሥርዓቱ እነዚህን አስደንጋጭ ክስተቶች መቋቋም እንዲችል ማድረግ ነው፤ በዚህም የቤተሰብን ኑሮ እና የተመጣጠነ ምግብ አቅርቦትን በዘላቂነት ማስቀጠል ይቻላል።" ሲሉ በፖሊሲ ጥናት ኢንስቲትዩት ከፍተኛ ተመራማሪ የሆኑት ሰላማዊት ገብረእግዚአብሔር (ዶ/ር ) ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል፡፡...
የአርሶ አደሮች የፈጠራ ክህሎት እና የሀገር በቀል እውቀት ሚና 14.05.2026 1:00:00
“እውቀት ፓስፖርት የለውም፤ እውቀት ተግባር (ልምድ) ነው ያለው። አርሶ አደሮቻችን ምርጥ ዘር ሲመርጡ 'ዝርያ ማሻሻል'፣ ዝናብን ሲተነብዩ ደግሞ 'የጥናት ዘዴ' እንበለው፤ ለሥራቸው ሳይንሳዊ ስሙን በመስጠት የሚገባቸውን ክብር ልንሰጣቸው ይገባል፡፡ ግባችን ጥገኝነት ሳይሆን ክብር፣ ጽናትና ሀገራዊ እራስን መቻል ነው፡፡” ሲሉ የመዳ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ብርሃነመስቀል ጠና ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል፡፡ 🔉በዚህኛው የራይዚንግ ሳውዝ መሰናዶ፣ በመዳ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ አዘጋጅነት "ከአርሶ አደሮች፣ ለአርሶ አደሮች፣ በአርሶ አደሮች" በሚል መሪ ቃል የተካሄደውን ልዩ አገር አቀፍ ጉባኤ...
ዓለም አቀፍ የነዳጅ ቀውስ እና የኢትዮጵያ የስትራቴጂካዊ አማራጮች ፍለጋ 11.05.2026 1:00:00
“ከውጭ ነዳጅ ጥገኝነት ለመውጣት የተቀናጀ ስትራቴጂ ያስፈልጋል። ትኩረታችንን የኤሌክትሪክ መሠረተ-ልማትን በማዘመን፣ በፀሐይ ኃይል እና በአገር ውስጥ የተፈጥሮ ጋዝ ምርት ላይ በማድረግ የኢነርጂ ሉዓላዊነታችንን ማረጋገጥ ይኖርብናል።” ሲሉ በኢትዮጵያ ፖሊሲ ጥናት ኢንስቲትዩት (PSI) ወስጥ ከፍተኛ ተመራማሪ የሆኑት ዶ/ር ጀማል መሀመድ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል፡፡ ከነዳጅ ፖለቲካ እስከ ቀጠናዊ ደህንነት፦ ኢትዮጵያ በአዲሱ የዓለም የኃይል አሰላለፍ ውስጥ! በዛሬው የራይዚንግ ሳውዝ ዝግጅታችን ሁለት አንገብጋቢ ጉዳዮችን ከባለሙያዎች ጋር በጥልቀት እንመረምራለን፦ የነዳጅ ጂኦ-ፖለቲካ እና የኢትዮጵያ ፈተና፦ የዓለም የነዳጅ ገበ...
የሥነ-ምግባር ሉዓላዊነት፦ አፍሪካ የሞራል መሠረቷን ከምዕራባውያን ተፅዕኖ እንዴት ትጠብቅ? 07.05.2026 1:00:00
"ሥነ-ምግባር ለአንድ ማህበረሰብ ህልውናው ነው። አፍሪካ የራሷን የሞራል መሠረትና እሴቶች መጠበቅ ካልቻለች፣ በግሎባላይዜሽን ማዕበል ውስጥ ማንነቷን አጥታ የሌሎች እሴቶች ተገዢ ትሆናለች።"ሲሉ የኢትዮጵያ የሥነ-ምግባር ማዕከል ፕሬዝዳንት እና የቅድስት ሥላሴ ዩኒቨርሲቲ መምህር የሆኑት ዶ/ር አባ መዝገቡ ካሳ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል፡፡ የዛሬው የራይዚንግ ሳውዝ ዝግጅታችን፣ ሥነ-ምግባር ዓለም አቀፋዊ ነው ወይስ በባህልና በስልጣን የሚወሰን? የአፍሪካ ማህበረሰቦች የውጭ 'እሴቶችን' እየተቀበሉ ነው ወይስ ያለ ምርጫ እየተጫኑባቸው ነው ? ቤተሰብ፣ ትምህርት ቤቶች እና የሃይማኖት ተቋማት የሞራል መሸርሸርን ለመከላከል ምን እያ...
ፓን-አፍሪካኒዝምን የማክሸፍ ዘመቻ፦ በሳህል ቀጣና ለአሸባሪዎች መረጃ የሚሰጠው ማን ነው? 05.05.2026 1:00:00
'' የተራቀቀ መረጃና ቴክኖሎጂ እየቀረበላቸው ነው፤ የፈረንሳይ ሚናም ይኸው ነው። ፈረንሳይ ለረጅም ጊዜ የጨበጠችውን ነገር በቀላሉ ለመልቀቅ ፍቃደኛ አይደለችም።[...] "እነዚህ ሶስት ሀገራት (ማሊ፣ ቡርኪና ፋሶ እና ኒጀር) ከሩሲያ ጋር ለመሰለፍ መወሰናቸው በዩክሬን አይን እንደ ጠላት እንዲታዩ አድርጓቸዋል። ፈረንሳይ እነዚህን ሀገራት ኢላማ ለማድረግ ከዩክሬን ጋር የደህንነት መረጃዎችን ስታስተባብር እንደነበር መረጃዎች አሉ። " ሲሉ ፓን አፍሪካኒስትና የቢዝነስና የማህበረሰብ ልማት አማካሪው ካባላ ጆን ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል፡፡ በዛሬው የራይዚንግ ሳውዝ ዝግጅታችን፣ በምዕራብ አፍሪካ እየተከሰተ ያለውን የጂኦ-ፖለቲካዊ ሽ...
የኢትዮጵያ ቡና፣ አበባ እና ወጣቶች፦ የአፍሪካን ልማት እንደገና መመልከት 31.03.2026 59:59
"በአየር ንብረት ለውጥ ተጽዕኖዎች ላይ ባደረግነው ጥናት መሰረት፣ በአሁኑ ወቅት ለቡና ልማት የምንጠቀምበት አካባቢ ወደ 60% የሚጠጋው በአየር ንብረት ለውጥ ምክንያት ሊጠፋ እንደሚችል ደርሰንበታል። አንዱ የመላመጃ መንገድ ደግሞ ቡናን በከፍተኛ ከፍታ ላይ ወደሚገኙ ቦታዎች ማዛወር ሲሆን፣ እነዚህ ከፍተኛ ቦታዎች ግን የደን ሽፋናቸውን ያጡ ናቸው። ስለዚህ የ'አረንጓዴ አሻራ' እና ሌሎች የደን ልማት ተነሳሽነቶች ደኖች እንዲያገግሙ በማድረግ ረገድ ትልቅ አስተዋጽኦ ይኖራቸዋል።" ሲሉ የ አካባቢ እና የቡና ደን ፎረም ዋና ዳይሬክተር የሆኑት ታደሰ ወ/ማርያም (ዶ/ር) ስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል። በዚህ የራይዚንግ ሳውዝ ዝግጅት፣...
ከሰንሰለት እስከ ስርአት፡- ያልተቋጨው የባርነት ታሪክ 26.03.2026 1:00:00
‘‘… እጅግ በጣም በርካታ የሆኑ የተፈጥሮ ማዕድናት ያሏት አህጉር ፤ አሁንም ድረስ የቅኝ ግዛትና የባዕዳን የንግድ ሥርዓቶችን እንድትከተል መገደዷ በጣም ያሳዝናል።[…]ምክንያቱም እስከ ዛሬዋ ቀን ድረስ አፍሪካ ገና ከቅኝ ግዛት የኢኮኖሚ ጥቃትና ጭቆና እንዳልነቃች ነው የምትቀሳቀሰው። ይህ ለኔ ከዚሁ አህጉር የሚወጡ ሰዎችን ሌሎች የዓለም ክፍሎችን ለማበልጸግ በጉልበት ሠራተኝነት ከሚጠቀምበት ሥርዓት ጋር ቀጥተኛ ትስስር አለው። ይህ ሥርዓት ዛሬም ድረስ በግልጽ እየተሠራ ነው። ለምሳሌ የተፈጥሮ ማዕድኖቻችን አሁንም ከአህጉሪቱ ተነቅለው ወደ ሌላ አገር ሄደው ይመረታሉ፤ ከዚያም ተመልሰው ለእኛው ይሸጡልናል።" ሲሉ የፖለቲካ ሳይንስ ም...
Similar podcasts
Replaio is not a podcast publisher; show names, artwork and audio belong to their authors and are distributed through public RSS feeds.