ወሰንሰገድ አሰፋ
The Rising South
የዓለም አቀፍ የኃይል ሚዛን እየተቀየረ ባለበት በዚህ ወቅት - ኢትዮጵያን፣ አፍሪካን እና ሌሎችን የሚቀርጹ የፖለቲካ፣ የኢኮኖሚ እና የማህበራዊ ሃይሎች ወደምንመለከትበት ወደ “ራይዚንግ ሳዉዝ” እንኳን በደህና መጡ፡፡ ደቡባዊ አመለካከቶችን ወደ ዓለም አቀፋዊ ውይይት መድረክ ስናቀርብ የአሰላሳዮችን ፣ የመሪዎችን እና የለዉጥ ፈጣሪዎችን ሃሳብ ያድምጡ።
Author
ወሰንሰገድ አሰፋ
Category
Podcast website
Latest episode
Jul 11, 2026
Where to listen?
Podcasts in the app Replaio Radio Coming soonPodcasts are coming to the app soon. Install now and be the first to see a whole new take on podcasts
Episodes
ሁለት የልማት ግንባሮች፣ የሳንባ ነቀርሳ በሽታን መዋጋትና ጠንካራ ኢኮኖሚን መገንባት 24.03.2026 1:00:00
"አብዛኞቹ ለቲቢ የምንጠቀማቸው መድኃኒቶች ከውጭ የሚገቡ ናቸው። ከፍተኛ የውጭ ምንዛሬ ያስወጣናል። ለውጭ ተፅዕኖ ተጋላጭ የሆንነውም ለዚህ ነው። ስለዚህ፣ በሀገር ውስጥ የማምረት አቅምን የምናጎለብትበት ዕድል ካገኘን፣ የገንዘብ ድጋፍ ቅነሳ የሚያስከትለውን ችግር መቋቋም እንችላለን። ለአገር ውስጥ መድኃኒት አምራቾች የራሳቸውን የምርመራ መሣሪያዎችና መድኃኒቶች ማምረት እንዲችሉ አቅማቸውን ማጠናከር ይገባል።" ሲሉ የ 'ቮለንተሪ ሄልዝ ሰርቪስ' ኢትዮጵያ ዋና ዳይሬክተር አቶ እንዳልካቸው ፍቃዱ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል፡፡ በዚህኛው የራይዚንግ ሳውዝ ዝግጅት፣ በቀዳሚነት መጋቢት 15 ቀን የሚከበረውን የዓለም የሳንባ ነቀርሳ ቀንን...
''ያልተበደረችውን ዕዳ የምትከፍለው አፍሪካ'':-የአየር ንብረት ለውጥ እና 'ዘመናዊ' ተብለው የቀረቡ የግብርና ወጥመዶች 17.03.2026 1:00:00
"ዓለም ቀደም ሲል ከነበረው የአስተሳሰብ ዘይቤ በተለየ መንገድ ማሰብ ይኖርበታል። መሰረታዊ ነገሮች መለወጥ አለባቸው፤ ምክንያቱም አሁን ያለው ሁኔታ ፍትሃዊ ያልሆነና ዘላቂነት የሌለው ነው። ስለዚህ፣ የምዕራባውያን ዓለም ለአየር ንብረት ለውጥ ካደረጉት አስተዋጽኦ ጋር የሚመጣጠን በቂ ድጋፍ የማቅረብ ኃላፊነትን ሊወስዱ ይገባል፡፡" ሲሉ የግብርና ሳይንቲስት እና ተመራማሪ ፀደቀ አባተ (ዶ/ር) ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል፡፡ በዚህ የራይዚንግ ሳውዝ ዝግጅት፣ በክፍል አንድ የአየር ንብረት ለውጥ የአፍሪካን ግብርና እንዴት እየቀየረው እንደሆነና አፍሪካ ለዓለም አቀፉ የጋዝ ልቀት የምታበረክተው አስተዋጽዎ በጣም አነስተኛ ቢሆንም፣ ለም...
የአእምሯዊ ንብረት መብት ተጽዕኖ በአፍሪካ ፋርማሲዩቲካልስ ኢንዱስትሪ ላይ 17.03.2026 1:00:00
“አብዛኞቹ የተከናወኑት በምዕራባውያን እና በአውሮፓውያን ነው። ስኮቶች፣ እስያውያን እና አፍሪካውያን ደግሞ በማህበረሰብ ፋይናንስ እና መሰረተ ልማቶች ባላቸው ሰፊ ተደራሽነት ምክንያት ኢንቨስት እያደረጉ ነው። ስለዚህ፣ በርካታ ኢንቨስትመንቶች እንዳሉ እስማማለሁ:: እናም ኢንቨስትመንቱ ሊመለስላቸው ይገባል። ነገር ግን፣ ይህ መሆን ያለበት የፈጠራ ስራዎችን እና ምርምርን በማገድ መሆን የለበትም።” ሲሉ የኪሊች ኤስትሮ ባዮቴክ ኃ.የተ.የግ.ማ መስራችና ምክትል ዋና ስራ አስፈጻሚ እንዲሁም የኢትዮጵያ ፋርማሲስቶች ማህበር ፕሬዝዳንት የሆኑት ዶ/ር ዳንኤል ዋቅቶሌ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል። በዛሬው የራይዚንግ ሳው ዝ ዝግጅት በቀዳሚ...
መረጃ፣ ቋንቋ እና ሉዓላዊነት፦ የአፍሪካ የትርክት ትግል 16.03.2026 1:00:00
“ከዚህ ቀደም ምዕራባውያን በአካል መጥተው የወረሩን ጊዜያት ነበሩ። የአፍሪካን ሕዝብ በቅኝ ገዝተዋል። ዛሬ ግን ሥርዓቱ ሙሉ በሙሉ ተቀይሯል። አሁን ደግሞ በመረጃ ቋቶቻቸው አማካኝነት ሊገዙን እየሞከሩ ነው። የማይወክሉንን ነገሮች ሁሉ እየሰበሰቡ ‘የእናንተ ተሞክሮ ይህ ነው’ ይሉናል። ነገር ግን ያ እኛን አይገልጸንም። ለዚህ ነው አፍሪካውያን የራሳችን የሆነ ‘የመረጃ ስብስብ’ እና የራሳችን የሆነ የቋንቋ ማቀነባበሪያ ዘዴ (Language processing) ሊኖረን የሚገባው።” ሲሉ በርቀት እና ኢ-ለርኒንግ ትምህርት ረዳት ፕሮፌሰር የሆኑት ዶ/ር አደራጀው ምህረት ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል፡፡ ሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) ስለ...
ከአፍ መፍቻ ቋንቋ እስከ ፋይናንስ አቅም፦ የአፍሪካ መዋቅራዊ ሽግግር 16.03.2026 1:00:00
“የአፍሪካ የዕውቀት ሥርዓቶች አብዛኛውን ጊዜ የሥነ-ምግባር ወጎችን እና የማኅበረሰብ ትውስታዎችን ያካተቱ ነበሩ። እነዚህ ደግሞ በአፍሪካ ወይም በቅኝ ተገዢ አገሮች ላይ በተጫነው በጽሑፍ በሰፈረ ቀጥተኛ ቀኖናዊ (dogmatic) እና ቢሮክራሲያዊ አመክንዮ ሙሉ በሙሉ ተተኩ። […]ስለዚህ፣ ቋንቋ የአስተዳደራዊ ምክንያታዊነት መሣሪያ በመሆን፣ ተለዋዋጭ የነበሩ ማኅበራዊ ሥርዓቶችን ወደ ደረቅ፣ ሕጋዊ እና ቀኖናዊ የፖለቲካ መዋቅሮች ለውጦታል።” ሲሉ በ ጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ የማህበራዊ ሳይንስ እና ሂውማኒቲስ ኮሌጅ ዲን የሆኑት ዶ/ር አስቻለው ታደሰ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል። በዚህኛው የራይዚንግ ሳውዝ ዝግጅታችን፣ በመጀመሪያው ክፍል...
የመካከለኛው ምሥራቅ ውጥረት እና የአፍሪካ አህጉራዊ የልማት አማራጮች 11.03.2026 1:00:00
"በቅርቡ በኢራን የታዩትን ክስተቶች፣ አሜሪካ እና እስራኤል በኢራን ላይ በከፈቱት ጥቃት፣ እንዲሁም ትንሽ ቀደም ብሎ በቬንዙዌላ የሆነውን ስንመለከት፤ እነዚህ ክስተቶች ዓለም አቀፋዊውን መዋቅር እየቀየረ ያለ አዲስ ሥርዓት መኖሩን ይነግሩናል። አሁን ባለንበት ሁኔታም የኃይል ፖለቲካ ከሕግ የበላይነት በላይ እየገነነ መጥቷል። በዚህ ሂደት ውስጥ ደግሞ ይበልጥ ተጋላጭ የሆኑት የደቡባዊ ዓለም ሀገራት ያላደጉና በማደግ ላይ ያሉ አገራት ናቸው።" ሲሉ የልማት ኢኮኖሚስቱ እንዳልካቸው ስሜ (ዶ/ር) ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል። በዚህኛው የራይዚንግ ሳውዝ ዝግጅታችን፣ በመጀመሪያው ክፍል ከልማት ኢኮኖሚስቱ እንዳልካቸው ስሜ (ዶ/ር) ጋር...
"ሩሲያ የዲሞክራሲያችን ጋሻ ናት" — ፕሬዝዳንት ፋውስቲን አርካንጅ ቱዋዴራ 10.03.2026 1:00:01
የማዕከላዊ አፍሪካ ሪፐብሊክ ፕሬዝደንት ፋውስቲን አርካንጅ ቱዋዴራ ከየካቲት 26 እስከ የካቲት 27 ፣ 2018 ዓ.ም በሩሲያ ሞስኮ ይፋዊ የስራ ጉብኝት አድርገዋል። ከሩሲያ አቻቸው ቭላድሚር ፑቲን ጋር በተለያዩ ጉዳዮች ዙሪያ ተወያይተዋል። "የሉዓላዊነት መርሆዎችን እና የሰላም ጥረቶችን እንደግፋለን። የመካከለኛው አፍሪካ ሪፐብሊክ ሕዝቧ አስቸጋሪ ጊዜያትን ያሳለፉ በመሆኑ፣ በዓለም ላይ ሰላም እንዲሰፍን ትፈልጋለች። ለዚያ ግብ ደግሞ መሥራት ይኖርብናል። ወደ ውይይት እና ድርድር ጠረጴዛ መቅረብ እና ከፍተኛ የሰው ሕይወት መጥፋትና የመሠረተ ልማት ውድመት እያስከተሉ ያሉ ጥቃቶችን በቀጥታ መፍታት አስፈላጊ መሆኑን እናምናለን።" ሲሉ...
ሉዓላዊነት ላይ ያነጣጠረ ጥቃት፦ በታለመ ግድያ የታወከው የመካከለኛው ምስራቅ ሰላም 05.03.2026 1:00:00
“ ከ1945 ጀምሮ ለዓለም መረጋጋት መሠረት የነበሩት ዘርፈ-ብዙ ሥርዓቶችና ስምምነቶች እየፈራረሱ ባሉበት ዓለም ውስጥ እንገኛለን። እስራኤልና አሜሪካ በኢራን ላይ የፈጸሙት ድርጊት በምንም መመዘኛ በሕግ የተደገፈ አይደለም፤ ይልቁንም የተባበሩት መንግሥታትን ቻርተር የጣሰ፣[...] ዲፕሎማሲን ለወታደራዊ ጥቃት እንደ መሸፈኛ መጠቀም፣ ለወደፊት ዓለም አቀፍ መረጋጋት አስፈላጊ የሆነውን እምነት ለዘለቄታው ያጠፋዋል።” ሲሉ በአፍሪካ ቀንድ እና በመካከለኛው ምስራቅ ጉዳዮች ተመራማሪ እና ተንታኝ የሆኑት ራሺድ አብዲ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል። በመካከለኛው ምስራቅ እየተባባሰ ስለመጣው ውጥረት በአፍሪካ ቀንድ እና በመካከለኛው ምስራቅ...
ከባዕድ ትርክት ወደ አፍሪካዊ እውነት፦ የስፑትኒክ አፍሪካ የኢትዮጵያ ቢሮ የአንድ ዓመት ጉዞ 03.03.2026 1:00:00
“አፍሪካውያን የራሳቸውን ታሪክ በራሳቸው መንገድ እና አተራረክ ዘዬ ማቅረብ አለባቸው የሚል ትልቅ የፓን-አፍሪካኒዝም እንቅስቃሴ አለ። […] ያ ትግል ረጅም ዓመት ሄዷል፣ ግን ያን ያህል ውጤታማ መሆን አልቻለም። ውጤታማ እንዳይሆን ያደረገው ትልቁ ምክንያት የመረጃ ክፍተት ነው። መረጃ ደግሞ ኃይል መሆኑን የምታውቀው ቢያንስ የራስህ ባይሆን እንኳን አንተ የምትቆጣጠረው ሚዲያ ወይም በአንተ መጫወቻ ሜዳ ላይ መሰረት ያደረገ ሲሆን ነው።” ሲል በስፑትኒክ አፍሪካ የኢትዮጵያ ቢሮ አዘጋጅ እና አቅራቢ የሆነው ዐብይ ሀብታሙ ተናግሯል። በዚህኛው ልዩ የራይዚንግ ሳውዝ ዝግጅት፣ ስፑትኒክ አፍሪካ በኢትዮጵያ ቅርንጫፍ ከፍቶ ስርጭት የጀመረበት...
የአፍሪካ ድምፅ በአፍሪካዊያን፦ ስፑትኒክ አፍሪካ በኢትዮጵያ ! 03.03.2026 1:00:02
“ስፑትኒክን በተመለከተ ፣ እኛ አማራጭን ብቻ ነው የምናቀርበው። የተለየ የዕይታ ነጥብ እያቀረብን ነው፤ እንዲሁም ለደቡባዊው ዓለም አገራት ድምፅ ለመስጠት እየሞከርን ነው። ስለዚህ፣ እኛ ምንም ዓይነት ነገር በማንም ላይ እየጫንን አይደለም። እኛ ያልተነገሩትን ነገሮች እየተናገርን ነው፤ አድማጮቻችን እና አንባቢዎቻችን ደግሞ የራሳቸውን መደምደሚያ እንዲያሳርፉ እንጋብዛለን። ስለዚህ፣ ለደቡባዊው ዓለም አገራት በመገናኛ ብዙኃን ዓለም ውስጥ እንዲህ ዓይነት አማራጭ ማግኘታቸው ትልቅ ዕድል ነው።" ሲሉ የስፑትኒክ አፍሪካ የኢትዮጵያ ቅርንጫፍ ቢሮ ኃላፊ አሌክሳንደር ሺፒን ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል። በዚህኛው ልዩ የራይዚንግ ሳውዝ ዝ...
የዓድዋ ድል፦ የኢትዮጵያዊያንን የትብብር አቅም የገለጠ የአፍሪካዊያን ኩራት 02.03.2026 1:00:00
ዓድዋ የጥቁር ህዝቦች ክብርና ችሎታ ምልክት ሆኗል።[...]ፓን አፍሪካኒስቶች ማንሰራራት የቻሉት የ1896 እ.ኤ.አ የአድዋ ድልን ተከትሎ ነው። ስለዚህ እነዚህ ሰዎች ኢትዮጵያን እንደ ማረጋገጫ ወስደው፣ አፍሪካውያን የአውሮፓን የበላይነትና ቅኝ ግዛት መቋቋም እንደሚችሉ ተመልክተዋል። ሲሉ በወሎ ዩኒቨርስቲ የታሪክ ትምህርት ረዳት ፕሮፌሰር አሰፋ ባልቻ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል። በዛሬው የራይዚንግ ሳውዝ ዝግጅታችን በኢትዮጵያ ለ130ኛ ጊዜ እየተከበረ ያለውን የዓድዋ ድል በዓል መነሻ አድርገን ሉዓላዊነትን በሶስት መልኩ ቃኝተነዋል። በቀዳሚነት ኢትዮጵያ በዓድዋ የተቀዳጀችውን ድል መነሻ አድርገን ለአፍሪካ ስላለው ትርጓሜ በወሎ...
የቤተሰብ ዕቅድ እና የስነ-ተዋልዶ ጤና አገልግሎትን ከእርዳታ ጥገኝነት ነጻ የማድረግ ጅምር በኢትዮጵያ 20.02.2026 1:00:00
“የጤናውን ሴክተር ስንመለከት ጤና ብቻውን በአንድ የሚቆም።[…] የዓለም ጤና ድርጅት ደግሞ 'Health in All Policies' ነው የሚለው። የጤና ፖሊሲዎች በሁሉም ፖሊሲዎች ውስጥ መኖር አለባቸው። ምክንያቱም ግብርና ብንለው፣ ትምህርት ብንል፣ ሁሉም ብንላቸው የጤና ፖሊሲ ከሌላቸው ሙሉ አይሆኑም፤ ምክንያቱም ዋናው ጤና ስለሆነ ማለት ነው።” ሲሉ በጤና ሚኒስቴር የስነ-ተዋልዶ ጤና፣ የቤተሰብ እቅድ፣ የአፍላ ወጣቶች እና ወጣቶች ፕሮግራም ኃላፊ ዶ/ር አለማየሁ ሁንዱማ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል። በዚህ የራይዚንግ ሳውዝ ዝግጅት በመጀመሪያው ክፍል በጤና ሚኒስቴር የስነ-ተዋልዶ ጤና፣ የቤተሰብ እቅድ፣ የአፍላ ወጣቶች እና ወ...
ዓለምአቀፍ የሬዲዮ ቀን፦ ከሬዲዮ ሞስኮ እስከ ስፑትኒክ የሩሲያ የመረጃ ተደራሽነት በአፍሪካ 14.02.2026 1:00:00
ዛሬ አለምዓቀፉ የሬዲዮ ቀን በመላው ዓለም እየተከበረ ነው። ስፑትኒክ አፍሪካም በአዲስ አበባ ማህበረሰብ ሬዲዮ 99.4 ኢትዮጵያን ፣ አፍሪካን እና መላው ዓለምን የሚዳስሱ ዝግጅቶችን በአማርኛና በእንግሊዝኛ እያቀረበ ይገኛል። ‘’ [...]ስፑትኒክ አፍሪካ በኢትዮጵያ በከፈተው ቢሮ ኢትዮጵያን እና አፍሪካን የሚመጥኑ ጠንካራ ይዘቶችን እየሰራ ነው።[...] የስፑትኒክ ጋዜጠኞችን በደቡብ አሜሪካ ሀገራት ጥናት ምርምርን ሲያቀርቡ አግኝቻቸው ነበር። ይህ የሩስያን ቀናነትና አብሮ የመስራት ፍላጎት የሚያሳይ ነው።” ሲሉ አንጋፋው ጋዜጠኛ ጥበቡ በለጠ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል። በዛሬ የራይዚንግ ሳዉዝ ዝግጅታችን ዓለም አቀፍ የሬዲዮ ቀ...
የኢትዮጵያ የሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) ዩኒቨርሲቲ የመገንባት እቅድ 04.02.2026 1:00:00
“ለዓመታት በአፍሪካ ውስጥ ስንጠቀምባቸው የቆዩትን መረጃዎች (Data) የሀገር በቀል ማድረግ ይገባናል። ምክንያቱም የ-AI ሞዴሎች የሚቀረጹት በሰለጠኑበት መረጃ ልክ ነው። ያ መረጃ በብዛት የመነጨው ከሰሜናዊው የዓለም ክፍል ስለሆነ፣ የሚያንጸባርቀው የእነሱን ማንነት እንጂ የእኛን አይደለም። ስለዚህ በራሳችን መረጃዎች የተደራጀ የሰው ሰራሽ አስተውሎት ሊኖረን ይገባል።” ሲሉ ከፍተኛ የትምህርት ባለሙያ የሆኑት ረዳት ፕ/ር አደራጀው ምህረት ለስፑትኒክ አፍሪ ካ ተናግረዋል። በዚህ የራይዚንግ ሳውዝ ዝግጅት፣ በመጀመሪያው ክፍል፣ ከፍተኛ የትምህርት ባለሙያ ከሆኑት ከረዳት ፕ/ር አደራጀው ምህረት ጋር በመሆን ኢትዮጵያ ልዩ የሆነ የሰው...
የባህል ኃይል፦ ባሕላዊ አመራር፣ ፋሽን እና የአፍሪካ የወደፊት ጉዞ 04.02.2026 1:00:00
“የዓለም አቀፍ ሕግ፣ በምዕራባውያን ወገን ሕጎች የሚጥሱትን እንዲታሰሩ የሚያደርግ ነው። አንድ አፍሪካዊ መሪ በፖለቲካዊ መልኩ የአፍሪካን መንገድ ለመከተል ከወሰነ፣ ኢላማ ይደረጋል። በአንተ ላይ መጥፎ የሆኑ ስሞችን በመለጠፍ መገናኛ ብዙኃንን ተጠቅመው ሕዝቡ አንተን በመጥፎ ዓይን እንዲመለከትህ ማድረግ ይጀምራሉ። ይህንንም በአንተ ላይ የሚወስዱትን እርምጃ ትክክለኛ እንደሆነ ለማስመስል ይጠቀሙበታል። እስካሁንም ያለው አካሄድ ያው ነው።” ሲሉ በጋና ባሕላዊ መሪ እና የ‘ዘ ቴስት ኦፍ አፍሪካ’ ተባባሪ መስራች የሆኑት ቴንጎል ኬፕሌማኒ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል። በዚህ የራይዚንግ ሳውዝ ዝግጅት፣ በመጀመሪያው ክፍል፣ በጋና ባሕላዊ...
የኢትዮጵያ የባህር በር ፍላጎት እና የደቡባዊው ዓለም የቴክኖሎጂ ሽግግር 03.02.2026 1:00:00
"[ኢትዮጵያ] በአፍሪካ በሕዝብ ቁጥር ብዛት ሁለተኛዋ ሀገር እንደመሆኗ፣ በአንድ [በጅቡቲ] ወደብ ላይ ጥገኛ መሆን በጣም አስቸጋሪ ነው። ስለዚህ አሁን ፍላጎታችንና ጥቅማችን በጣም የተለያየ ነው። በዚህም ምክንያት ተጨማሪ ወደቦችን መጠቀም፣ መመልከት ወይም መፈለግ እጅግ አስፈላጊ ነው።" ሲሉ በጅማ ዩኒቨርሲቲ የምስራቅ አፍሪካ የዲፕሎማሲ እና የፖለቲካ ታሪክ መምህር የሆኑት አቶ በላይ በየነ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል፡፡ በዛሬው የራይዚንግ ሳውዝ የሁለት ክፍል ዝግጅታችን፣ በመጀመሪያው ክፍል፣ የኢትዮጵያ ከፍተኛ የልዑካን ቡድን በርበራን ከጎበኘ በኋላ፣ የኢትዮጵያን እየተለወጠ የመጣውን የባህር ላይ እና የጂኦ-ፖለቲካ ስትራቴጂ...
ከቅኝ ግዛት እስከ ስልታዊ አጋርነት፡- በዲፕሎማሲው መስክ የቀጠሉ ሁነቶች 02.02.2026 1:00:00
የደቡባዊው ዓለም ሀገራት ከምንጊዜውም በላይ የእርስ በእርስ ግንኙነታቸውን ማጠናከር የግድ የሚላቸው ጊዜ ላይ ደርሰዋል፡፡ የምዕራቡ ዓለም ሀገራት የማእድን ሀብታቸውን ሲሉ በታዳጊ ሀገራት ላይ ቀጥተኛና ህገወጥ ወታደራዊ ጣልቃ ገብነት መፈጸም ቀጥለዋል፡፡ “ይህ የተመድ ድክመት ነው። ምክንያቱም እነዚህ አገራት በሙሉ፣ ድሃም ይሁኑ ሀብታም፣ ነፃ አገራት ናቸው። አሜሪካ በእነዚህ አገራት ላይ ጥቃት መፈጸም የለባትም። ይህ የኢምፔሪያሊዝም መገለጫ ነው። በመሆኑም ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ በአንድነት ሊቆም እና በነፃና ሉዓላዊ አገራት ላይ የሚፈጸመውን የጥቃት ድርጊት መቃወም አለበት።” ሲሉ በአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ የ...
የሉዓላዊነት ጉዞ፦ ኢትዮጵያ በጤና፣ በምግብ እና በአየር ትራንስፖርት ዘርፎች እያመጣች ያለችው አዲስ ለውጥ 02.02.2026 1:00:00
"የኢትዮጵያ የምግብ እና የመድኃኒት ባለሥልጣን የደረጃ ሶስት (Maturity Level 3) እውቅናን ማግኘቱ ለሀገሪቱ ብቻ ሳይሆን ለቀጠናው፣ እንዲሁም ለእኛ እንደ ኢንዱስትሪ ባለቤቶች ጨዋታ ቀያሪ ትልቅ ክስተት ነው።[...]የምስክር ወረቀቱን በቀላሉ በመጠቀም በኢትዮጵያ የተመረተን ማንኛውንም ምርት በመላው አፍሪካ አልፎም ከዚያ በላይ ማሰራጨት እንችላለን።" ሲሉ 'ፋርማኮሎጂስት' እና የኢትዮጵያ የፋርማሲ ባለሙያዎች ማህበር ፕሬዝዳንት ዶ/ር ዳንኤል ዋክቶሌ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል፡፡ በዚህ የራይዚንግ ሳውዝ ዝግጅት በቀዳሚነት ፋርማኮሎጂስት እና የኢትዮጵያ የፋርማሲ ባለሙያዎች ማህበር ፕሬዝዳንት ከሆኑት ከዶ/ር ዳንኤል ዋ...
ኃይል ወይስ ሕግ፦ ተመድ አሁንም በሕግ የሚመራ ተቋም ነውን? 27.01.2026 1:00:00
“የቪቶ (ድምፅን በድምጽ የመሻር) ስልጣን ያለአግባብ ጥቅም ላይ ውሏል፤ ተበድሏልም። በ2003 በኢራቅ ላይ በአሜሪካ ጥቃት ሲሰነዘር ሩሲያ ለዚያ ወረራ እና ወታደራዊ ጣልቃገብነት ድምፅ አልሰጠችም። […] አፍሪካ በ2026 ያላትን ቋሚ ያልሆኑ መቀመጫዎች ብንመለከት እንኳ፣ የቪቶ ስልጣን ባላቸው አምስቱ ቋሚ አባላት እና የቪቶ ስልጣን በሌላቸው ቋሚ ባልሆኑ አባላት መካከል ያለው ልዩነት ምንም አይነት ትርጉም አይሰጥም። ይህ ሁኔታ በእውነቱ ዓለም አቀፍ ህግን መሳቂያ ያደርገዋል።” ሲሉ በደቡብ አፍሪካ ዩኒሳ የታቦ ምቤኪ የዓለም አቀፍ ጉዳዮች ኮሌጅ ውስጥ ተመራማሪ የሆኑት ራስ አድቮኬት ሲፎ ማንቱላ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል፡፡...
ኢትዮጵያ፣ የእንቦጭ አረምን በአረንጓዴ አብዮት ጥቅም ላይ ማዋል 27.01.2026 1:00:00
"በጣና ሐይቅ ያለው የእንቦጭ አረም ለታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ስጋት ነው። ምክንያቱም ጣና ሐይቅ በላይኛው ጫፍ ላይ ስለሚገኝ ለግድቡ ተጽእኖ ይኖረዋል።" ሲሉ በባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ የዓሳ ሀብትና የውሃ ሳይንስ ተመራማሪ የሆኑት ዶ/ር አያሌው ወንዴ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል፡፡ በዚህ የራይዚንግ ሳውዝ ዝግጅት፣ ከዶ/ር የህዝቤ ካሳ፣ በጎንደር ዩኒቨርሲቲ ረዳት ፕሮፌሰር፣ ከአቶ ደበበ ደፈርሶ፣ በውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር የሃይድሮሎጂ እና የተፋሰስ መረጃ መሪ ሥራ አስፈፃሚ እና ከዶ/ር አያሌው ወንዴ፣ በባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ የዓሳ ሀብትና የውሃ ሳይንስ ተመራማሪ ጋር በመሆን ኢትዮጵያ ወራሪውን የእንቦጭ አረምን በመዋጋት ረገ...
አፍሪካ በወደቦች እና በኃይል መካከል፦ በባለብዙ-ዋልታ ዓለም ውስጥ ያለ ልማት እና ዲፕሎማሲ 22.01.2026 1:00:00
“ሩሲያ እ.ኤ.አ. እስከ 2027 ድረስ በአፍሪካ ውስጥ የኤምባሲዎቿን ቁጥር ወደ 49 አካባቢ ለማድረስ እየሠራች ነው። የሩሲያ ተዓማኒነትን በተመለከተ ከቅኝ ግዛት ታሪክ ነፃ መሆኗ ትልቁ ዲፕሎማሲያዊ ሀብት ታሪኳ ነው። እንደ ብሪታንያ፣ ፈረንሳይ ወይም ቤልጂየም ሳይሆን፣ የአፍሪካን ግዛቶች በቅኝ ግዛት አልገዙም። [...]ይህ ታሪክ ወደ “የእኩልነት አጋርነት” ትረካ የተቀየረ መሆኑ ነው፤ ይህም በተፈጥሮ ሀብታቸው፣ በወደፊት እጣ ፈንታቸው፣ በታሪካቸውና በውርሳቸው ላይ ሙሉ ሉዓላዊነትን ለማረጋገጥ ለሚጥሩ አገራት ትልቅ ትርጉም የሚሰጥ ነው።” ሲሉ በአሶሳ ዩኒቨርሲቲ የኢኮኖሚክስ መምህር የሆኑት አቶ መሀመድ ኢብራሂም ለስፑትኒክ አፍ...
ዕዳን እንደ መሣሪያ፦ ዓለም አቀፍ የፋይናንስ ሥርዓት አፍሪካን ጠፍሮ የያዘበት መንገድ 21.01.2026 1:00:00
“የእነዚህ ተቋማት (አይ.ኤም.ኤፍ እና የዓለም ባንክ ) መሠረታዊ ዳራ፣ ምን እንዲሠሩ ታስበው እንደነበር ወይም ምን እንዲያሳኩ ይጠበቅባቸው እንደነበረ በመነሳት ነው። እኔ እንደ አፍሮ-ሴንትሪስት (አፍሪካን ማዕከል እንደሚያደርግ ሰው)፣ ዓለም አቀፍ የፋይናንስ ተቋማት የምዕራባውያንን የበላይነት ከሚያስፋፉ ወኪሎች ጋር ተመሳሳይ ናቸው የሚል ፍጹም የተለየ መከራከሪያ አለኝ። እነዚህ ተቋማት የተቋቋሙት ለአፍሪካ መልካም ጥቅም ነው የሚለውን መመሪያ በመቀበል፣ የምዕራባውያንን ብልሹነት ለማረጋገጥ በምናደርገው ጥረት በበላይነት ፖለቲካቸው ውስጥ ራሳችንን የምናስር ከሆነ፣ መዘንጋት የሌለብን ነገር ይሄ እርዳታ እንዳልነበረ ነው። ይህ በ...
ሀገር በቀል ሳይንስ፦ የኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ እና የወደፊቱ የእውቀት አመራር 21.01.2026 1:00:00
“የብሪክስ ሀገራት ተሰባስበው በብዙ ጉዳዮች ላይ እየተወያዩ ነው። የብሪክስ አካዳሚዎች ማህበር፣ የሳይንስ ማህበራት እና ሌሎችም አሉ። ይህ ደግሞ የበለጠ መቀጠል አለበት። አሁን ያለው ገና በጅማሮ ወይም በጨቅላነት ደረጃ ላይ ነው። ይህ ወደ ከፍተኛ ደረጃ ማደግ እና ወደ ተግባር መለወጥ ይኖርበታል።” ሲሉ ፕሮፌሰር ተከተል ዮሐንስ፣ የኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ ዋና ዳይሬክተር ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል፡፡ በዚህ የራይዚንግ ሳውዝ ዝግጅት፣ የኢትዮጵያን የሳይንስ እና የልማት ምኞቶች ቁልፍ ሚና የሚጫወተውን የኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚን በትኩረት እንቃኛለን። የአካዳሚው ዋና ዳይሬክተር ፕሮፌሰር ተከተል ዮሐንስ ፣ ተቋሙ ከኢትዮጵያ...
ግብርና እንደ የኃይል ምንጭ፦ የአፍሪካ የግብርና ልማት ጥያቄዎች 20.01.2026 1:00:00
"የኢትዮጵያ የግብርና ምርት 94 በመቶው በጥሬው ነው ወደ ውጭ የሚላከው። ምንም ዓይነት እሴት አይጨመርበትም። [...] እኔ ማየት የምፈልገው አፍሪካ ራሷን መመገብ ብቻ ሳይሆን ለቀሪው ዓለምም ምግብ ስታቀርብ ነው። አፍሪካ ምግብ ለመግዛት በየዓመቱ ከ120 ቢሊዮን ዶላር በላይ እያወጣች መቀጠል የለባትም ስለዚህ ራሷን መመገብ ብቻ ሳይሆን ከዚያም በላይ የምትተርፍ አፍሪካን፤ በቂ የምግብ ምርት ለውጭ ገበያ የምትልክ አፍሪካን ማየት እፈልጋለሁ።" ሲሉ የግብርና ሳይንቲስት እና ተመራማሪ ፀደቀ አባተ (ዶ/ር) ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል። በዚህ ባለ ሁለት ክፍል የራይዚንግ ሳውዝ ዝግጅት በክፍል አንድ ከታዋቂው የግብርና ሳይንቲስት...
ከአንድነት ወደ ኃይል፦ በዓለም አቀፍ መድረክ የአፍሪካውያንን ተፅዕኖ የመገንባት ጉዞ 14.01.2026 1:00:00
"ጠንካራ የሆነ አለም አቀፍ የጥቁሮች ድርጅት ሊኖር ይገባል። ያለ እሱ፣ ሁሉም ነገር የቁጣ፣ የተቃውሞ እና የተስፋ መቁረጥ መግለጫ ብቻ ሆኖ ይቀራል። እኛ ጥቁር ህዝቦች ትኩረት ማድረግ ያለብን ገለልተኛ፣ አለም አቀፍ ተጽዕኖ ፈጣሪ እና ጠንካራ የሆኑ የጥቁር ተቋማትን በመገንባት ላይ መሆን አለበት።” ሲሉ የግሎባል ብላክ ሴንተር መስራች እና ዋና ፀሐፊ ከአቶ ፀጋዬ ቻማ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል፡፡ በዛሬው የራይዚንግ ሳውዝ ዝግጅታችን፣ ከግሎባል ብላክ ሴንተር መስራች እና ዋና ፀሐፊ ፀጋዬ ቻማ ጋር ስለ ፓን-አፍሪካኒዝም፣ ዓለም አቀፍ የካሳ ክፍያ እንዲሁም ተያያዥ ጉዳዮች እንወያያለን። በኢትዮጵያ ትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ...
Similar podcasts
Replaio is not a podcast publisher; show names, artwork and audio belong to their authors and are distributed through public RSS feeds.