ወሰንሰገድ አሰፋ

The Rising South

Society EN ↓ 125 episodes

የዓለም አቀፍ የኃይል ሚዛን እየተቀየረ ባለበት በዚህ ወቅት - ኢትዮጵያን፣ አፍሪካን እና ሌሎችን የሚቀርጹ የፖለቲካ፣ የኢኮኖሚ እና የማህበራዊ ሃይሎች ወደምንመለከትበት ወደ “ራይዚንግ ሳዉዝ” እንኳን በደህና መጡ፡፡ ደቡባዊ አመለካከቶችን ወደ ዓለም አቀፋዊ ውይይት መድረክ ስናቀርብ የአሰላሳዮችን ፣ የመሪዎችን እና የለዉጥ ፈጣሪዎችን ሃሳብ ያድምጡ።

Author

ወሰንሰገድ አሰፋ

Category

Society

Latest episode

Jul 11, 2026

Where to listen?

Podcasts in the app Replaio Radio Coming soon

Podcasts are coming to the app soon. Install now and be the first to see a whole new take on podcasts

Get it on Google Play Install for free Android 5M+ downloads · 4.8 rating iOS soon

Episodes

ሰው ሰራሽ አስተውሎትን ለበጎ መጠቀም፦ ኢትዮጵያዊያን ተማሪዎች የደመቁበት ዓለም አቀፍ ዉድድር 06.08.2025

“እኛ ምን ያቅተናል?፣ ሀገራችንን ለማሳደግ ምን ያቅተናል?፣ ማይንድሴት /አመለካከት/ ላይ መስራት አለብን ፤ የሁሉም ማይንድሴት ላይ መሰራት አለበት ምክንያቱም [ከሌሎች ሃገራት ተወዳዳሪዎች ጋር] አቅማችን አንድ እንደሆነ አይቻለው፡፡” ተማሪ አቤል ደረጀ  በዚህ የራይዚንግ ሳውዝ  ዝግጅት፣ በጄኔቫ በተካሄደው ዓለም አቀፍ የሰው ሰራሽ አስተውሎት ውድድር ኢትዮጵያን በኩራት ወክለው 5ኛ ደረጃን ከያዙ ከተማሪ አቤል ደረጄ እና ፍሬወይኒ በላይነህ እንዲሁም ከውድድሩ የኢትዮጵያ ተወካይና አስተባባሪ መንግስቱ ወዳጄ ጋር ቆይታ እናደርጋለን፡፡ በወጣቶች ዘንድ ሰው ሰራሽ አስተዉሎትን ለበጎ የመጠቀም ውድድር አጠቃላይ ሂደቱን፣ የጄኔቫ ቆይ...

ኢትዮጵያ፡ በአገር በቀል የግጭት አፈታት ዘዴ ሰላምን የመገንባት ሂደት 04.08.2025

“መንግስት ቅጣትና ሪዋርድ [ማበረታቻ] ያመጣብኛል ብሎ ከሚያስበው ነገር ይልቅ ኃጢያትና ጥሩ ነው ተብለው በማህበረሰቡ የተፈረጁን ነገሮች የመቀበል አዝማሚያ አለ አንዳንድ ቦታ ላይ፤ ስለዚህ ማህበረሰባችን ለእነዛ ነገሮች ዋጋ ስለሚሰጥ ሁለቱን የግጭት አፈታት መንገድ (ዘመናዊውንም ባህላዊውንም) አቀናጅተን ችግሮች በሰላማዊ መንገድ እንዲፈቱ እያደረግን ነው፡፡” አቶ ቸሩጌታ ገነነ፣ በሰላም ሚኒስቴር የፌደራሊም እና ግጭት አስተዳደር ሚኒስትር ዳኤታ በዚህ የራይዚንግ ሳውዝ ዝግጅት፣ ከአቶ ቸሩጌታ ገነነ ጋር ኢትዮጵያ ዘላቂ ሰላምን ለመገንባት ያላትን የበለጸገ የባህል ቅርስ እንዴት እየተጠቀመች እንደሆነ እንቃኛለን። በዘመናዊ ተግዳሮቶ...

ማን ዋጋውን ይከፍላል? የአካባቢ ኢፍትሃዊነት እና በደቡባዊ አለም ላይ የሚሰነዘር ወቀሳ 31.07.2025

“ምዕራቡ ዓለም በኢንዱስትሪ ልማት ወቅት ማንኛውንም ዋጋ ቢያስከፍል፣ የአካባቢ ተጽእኖዎችን ችላ በማለት የኢኮኖሚ ዕድገትን ተከትሏል። የዛሬው የአካባቢ ቀውስ በአብዛኛው የዚያ አካሄድ ውጤት ነው፣ የተፈጥሮ ሀብቶች ላይ ከፍተኛ ጉዳትን በማድረስ—ምዕራቡ ዓለም ለአለም አቀፍ የአካባቢ ጉዳት ረገድ ታሪካዊ ተጠያቂ ያደርገዋል።” አቶ መልካሙ ኦጎ፣ የአካባቢ ጥበቃ ጠበቃ በዚህኛው የራይዚንግ ሳውዝ ዝግጅታችን የአካባቢ ጥበቃ ጠበቃ ከሆኑት ከአቶ መልካሙ ኦጎ ጋር ደቡባዊ አለም ላይ እየደረሰ ስላለው የአካባቢ ኢፍትሃዊነት እና ወቀሳ እንዲሁም ይህን መከላከል ስለሚቻልባቸው መንገዶች ሰፊ ውይይት አድርገናል፡፡

የምግብ ቅኝ ግዛት እና የአፍሪካ የምግብ ሉዓላዊነት ፍልሚያ 29.07.2025

"የውጭ ኩባንያዎች እና የውጭ መንግስታት በዘረመል የተሻሻሉ ሰብሎችን በዋናነት ይቆጣጠራሉ። በእነሱ ቁጥጥር ስር ናቸው። ምናልባት በነጻ ይሰጡናል ማለት ትችል ይሆናል። አንዴ መጠቀም ከጀመርክ በኋላ ግን፣ በብዙ ሌሎች ሀገራት ዘንድ እንዳየነው፣ የእነዚህ ሰብሎች ምርታማነት ይቀንሳል፣ በአካባቢያዊ ስነ-ምህዳር፣ በነፍሳት፣  እንስሳት እና በሌሎችም ይጠቃሉ። [...] የእጅ አዙር ቅኝ ገዢዎች በአፍሪካ ድህነትን አልቀነሱም፣ የተመጣጠነ ምግብ እጥረትን አላጠፉም፣ የገበሬዎችንም ገቢ አልጨመሩም። ያደረጉት ነገር በአፍሪካ ውስጥ ያሉ ወሳኝ፣ ወሳኝ ምግቦችን መተካት ወይም መቀነስ ነው።” በዚህ የራይዚንግ ሳውዝ መሰናዶ በአፍሪካ የምግብ ሉ...

ኢትዮጵያ በአፍሪካ አህጉራዊ ነጻ የንግድ ቀጣና ስምምነት ትግበራ 25.07.2025

“አህጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጣና ስምምነቱ ትልቅ ዕድል አለው። በ2045 የአፍሪካን ንግድ በ45 በመቶ ገደማ ማለትም በ275.7 ቢሊዮን ዶላር ይጨምራል […] እንዲሁም የአፍሪካ አገሮች የግብርና ምርቶችን ወደ ውጭ የኢንዱስትሪ ምርቶች እንዲልኩ ይረዳቸዋል።” በዚህ የራይዚንግ ሳውዝ ዝግጅት በኢትዮጵያ ፖሊሲ ጥናት ኢንስቲትዩት ተመራማሪ ከሆኑት አበበ አምባቸዉ (ዶ/ር) ጋር በመሆን የታሪፍ ቅነሳን በማስወገድ እና የኢንዱስትሪ እድገትን በማበረታታት የአህጉሪቱን የንግድና ኢኮኖሚያዊ ውህደትን ስለሚያሳድገው የዓለም ትልቁ የነፃ ንግድ ቀጠና ስምምነት ላይ ተወያይተናል ፤ የኢትዮጵያን የመጨረሻ ምዕራፍ ዝግጅቶችንም ዳስሰል።

የጤፍ ባለቤትነት፦ የኢትዮጵያ ትግል ከብዝሃ-ህይወት ሃብት ዘረፋ ጋር 23.07.2025

የአፍሪካ ሼፎች ጉባኤ እና የሥርዓተ ምግብ የፖሊሲ ምክክር  ዛሬ በአዲስ አበባ ተጀምሯል፤ ጉባዔው ማጠንጠኛ ካደረገባቸው ጉዳዮች አንዱ የምግብ ሉዓላዊነት ይገኝበታል፡፡ ይህን ከሚፈታተኑ ተግባራት ውስጥም  በምዕራቡ ዓለም ኩባንያዎች የሚፈጸሙ የ'ባዮፓይሬሲ' ወይም የብዝሃ- ህይወት ሃብት ዘረፋ አንዱ ነው፡፡     “የብዝሀ ሕይወት ዘረፋ 'ባዮፓይሬሲ' ለደቡባዊ  ዓለም ሀገራት አሳሳቢ ጉዳይ ነው፤ ምክንያቱም እነዚህ ሀገራት  በተፈጥሮ የአዝርዕት ዘረመል ሀብት የበለፀጉ ናቸው። የሰሜኑ ዓለም ሀገራት ኩባንያ ባለቤቶች ግን እነዚህን የአዝርዕት ዘረመል ሀብቶችን ለመጠቀም [በራሳቸው ስም ለማስመዝገብ] ፍቃድ እየጠየቁ ነው። […] የአዝ...

የኤሌክትሪክ ኃይል፣ ቴክኖሎጂ እና የአፈር ማዳበሪያ ምርት፦ የኢትዮጵያ ልዕልና ሰንሰለቶች 22.07.2025

የሉዓላዊነት ትርጉም ከድንበር ያለፈ ነው። “የአፍሪካ ሉዓላዊነት መከበር አለበት — ድሃ ሀገር መሆን ሉዓላዊነትን አይቀንስም።” ሙሉጌታ ደበበ (ዶ/ር) በሲቪል ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካ ሳይንስና ዓለምዓቀፍ ግንኙነት መምህር፡፡ በዚህ The Rising South የራይዚንግ ሳውዝ ዝግጅትም የኢትዮጵያን የልዕልና እና የሉዓላዊነት ሰንሰለቶች  የምንችላቸውን  ከህዳሴ ግድብ እስከ ቴክኖሎጂያዊ የፈጠራ መንገዶች ደግሞም በምግብ ራስን ለመቻል መሰረት እስከሆነው የአፈር ማዳበሪያ ምርት ውጥን በጥልቀት እናያለን። የሳይበር ደህንነት ባለሙያዉ ፋሪስ ሙባረክ እና የግብርና ተመራማሪዉን ሲሳይ ሃይሉም ዕይታቸውን አጋርተውናል፡፡

የኢትዮጵያ ፋሽን ፈተና፦ ያገለገሉ ልብሶች /ቦንዳ/ ገበያ 18.07.2025

የኢትዮጵያ የፋሽን ኢንደስትሪ ፈተና መልኩ እንዲህ ነው “ድሮ የቦንዳ ልብሶችን ሰው ተሸማቆ ነበር የሚገዛው [...] አሁን ግን ትልልቅ ሞሎች ላይ የቦንዳ ልብሶች ይሸጣሉ።” ስትል ዲዛይነር ኢክራም መሐመድ ነግራናለች።   ከዚህ መውጫው መንገድ ደግሞ የህንድ ምሳሌ ነው። "የኢትዮያ ታምርት ፅንሰ ሃሳብን ማስረፅና በኢትዮጵያ ምርት የምንኮራበት ሁኔታ መመቻቸት አለበት፣” ሲል በባህርዳር ዩኒቨርስቲ የኢትዮጵያ ፋሽንና ጨርቃ ጨርቅ ኢንስቲትዩ አፓረል ዲን ቢኒያም

የአፍሪካን ዕጣፈንታ መገንባት፦ የህዝብ አገልግሎት — በሀገር በቀል ፈጠራ እና ትብብር 16.07.2025

ዛሬ በናይሮቢ በተካሄደው 'የስማርት ገቨርንመንት' ጉባኤ  የአፍሪካ ዲጂታል ሉዓላዊነት በዋናነት ተነስቷል — የህዝብ አግልግሎትን በእምነት፣ ግልጽነት እና ለዜጋ ቅድሚ በሰጠ ፈጠራ መምራት የሚለው ሀሳብም በሰፊው ተዳስሷል። ዘንድሮ በጎርጎሮሳዊያኑ ሰኔ 21 — ሰኔ 23 የተከበረው በ10ኛው የአፍሪካ የህዝብ አገልግሎት ቀን ከአዲስ አበባ እስከ ጆሃንስበርግ ድረስ የአፍሪካ ሀገራት በአገር ውስጥ ፈጠራ፣ ፍትሃዊነት እና በደቡብ-ደቡብ ትብብር የህዝብ አገልግሎትን መቀየር ላይ ትኩረት የሰጡበት ሆኗል።

የአፍሪካ ልማት ባንክ አዲሱ ፕሬዝዳንት እና የአፍሪካ ማንነትን ለመጠበቅ የሚደረገው ትግል 15.07.2025

ዛሬ በጎርጎሮሳዊያኑ ሐምሌ 15፣  በዓለም የወጣቶች ክህሎት ቀን ፣ የአፍሪካ ልማት ባንክ እያንዳንዱ ኢንቨስትመንት የወጣቶችን የስራ እድል ፈጠራን ለማስቀደም ያስችላል የሚለውን ስርዓት አስተዋውቋል።   ባንኩ የ10 ዓመት ስትራቴጂ አካል የሆነ የወጣቶች የስራና  ክህሎት 'ማርከር' ስርዓትን ከዓለም የስራ ድርጅት ጋር በመሆን ይፋ አድርጓል። ይህ ውሳኔ የመጣው ባንኩ  ሲዲ ኡልድ ታህን (ዶ/ር) ዘጠነኛ ፕሬዝዳንት አድርጎ ከመረጠ በኋላ የሆነ ነው።  እንዲህ ያሉ የአፍረካ ለውጦችን ዕውን ለማድረግ  የአፍሪካ ማንነትን መጠበቅና የወደፊት ትውልድን ማብቃት አስቸኳይ እንደሆነ ባለሙያዎች አጽንኦት ሰጥተዉ ይናገራሉ።

"የሌማት ትሩፋት"፦ የኢትዮጵያ የውስጥ አቅምና ዕውቀት ለምግብ ሉዓላዊነት 11.07.2025

እ.ኤ.አ በ2022 የተጀመረው የሌማት ትሩፋት፣ የኢትዮጵያን የምግብ ስርዓት ለመቀየር መንግስት ከፍተኛ ትኩረት የሰጠው ኢኒቬቲቭ ነው። ኢኒሼቲቩ የወተት፣ የዶሮ እርባታ፣ የማርና የአሳ ምርትን እያሳደገ፣ አምራቾችን እያበረታታ እንዲሁም እያንዳንዱ ቤተሰብ የራሱን ምግብ እንዲያመርት፣ በአካባቢ ገበያዎች እንዲሳተፍ እያደረገ ስለመሆኑም ከግብርና ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያሳያል፤ የኢትዮጵያን የምግብ ሉዓላዊነት ዉጥን  ከግብ ለማድረስም አጋዥ ነው ተብሎ ተስፋ ተጥሎበታል።

አፍሪካ የቱሪዝም አቅምን መክፈት፡- ዕድሎችን ማሰስ እና እንቅፋቶችን ማለፍ 10.07.2025

አፍሪካ አስደናቂ መልክዓ ምድር፣ የበለጸገ ባህል እና በፍጥነት እያደገ ያለው የዲጂታል ገጽታ በዓለም ቱሪዝም ውስጥ ያንቀላፋው ዘርፍ አድርጎት ቆይቷል። በዚህ የራይዚንግ ሳውዝ ክፍል፣ ስለዚሁ የአፍሪካ ያልተነካው ዘርፍ በስፋት እንዳስሳለን፡፡ ይህንን ያልተነካ እምቅ ሀብትም ከታላቅ ኢትዮጵያ አስጎብኚዎች ማኅበር መስራች ናሆም አድማሱ ጋር በመሆን እንመረምራለን። ከሥነ-ምህዳር ቱሪዝም እስከ ጂኦፓርኮች፣ አፍሪካ ለውጥ የመፈጠር መንገድ ላይ ነች — ነገር ግን እንቅፋቶችም አሉ፤ በቅጡ ያልለሙ መሠረተ ልማቶች፣ የደህንነት ስጋቶች እና በቂ ያለሆነው ኢንቨስትመንት ዘርፎን ወደኋላ ጎትተው ይዘዉታል።

የብሪክስ ሪዮ መግለጫ፦ ተጨባጭ የኃይል ሽግግር 08.07.2025

በብራዚሏ መዲና ሪዮ ዴ ጄኔሮ የተካሄደው የ2025 የብሪክስ ጉባኤ ለደቡባዊው ዓለም ትልቅ ለውጥ ያመጣል።  የብሪክስ ሀገራት የፋይናንስ ነፃነትን፣ የተባበሩት መንግስታት ማሻሻያን እና የቴክኖሎጂ ማካተትን የሚጠይቅ 126 ነጥቦችን የያዘ ሰፊ መግለጫ በማውጣት የዓለምን ሥርዓት በመቀየር ላይ መንገዳቸው ቀጥለዋል።

ዲግሪ ወይስ ጥበብ? “የተማረ”፦ ሊጤን የሚገባው ሃሳብ 07.07.2025

ዛሬ ሰኔ 30 ነው! ሰኔ 30 በተለምዶ የየዓመቱ የትምህርት ጊዜ መዝጊያ ተደርጎ ይወሰዳል ። ይህንኑ ዕለት መነሻ ያደረገዉ የዛሬው የራይዚንግ ሳውዝ ዝግጅታችን በኢትዮጵያ የትምህርት ሥርዓት ላይ በጊዜ ሂደት የታዩ ለውጦችን - ንድፈ-ሃሳብ ላይ ብቻ ወይም 'ሽምደዳ' ላይ ከማተኮር ይልቅ ተማሪዎች በነጻነት ምክንያታዊ አስተሳሰብን እንዲያጎለብቱ ወደሚያስችል የመማር ማስተማር ሂደት መቀየርን እንዳስሳለን። ከፍተኛ የትምህርት ባለሙያ ከሆኑት ከአቶ ማሞ መንገሻ ጋር በትምህርት ሥርዓቱ ውስጥ ስለታዩ ለውጦች እና አሳሳቢ እየሆነ ስለመጣው የብቁ መምህራን እጥረት ዙሪያ ውይይት እናደርጋለን፡፡

ቢትኮይን ፣ ባህል እና ደቡባዊው ዓለም፦ የኢትዮጵያ ዲጂታል እድገትና የባህል አንድነት 04.07.2025

በክፍል አንድ፡ የቢትኮይን ባለሙያው ቃል ካሳ የኢትዮጵያ እያደገ የመጣዉ የኤሌክትሪክ ኃይል የክሪፕቶ ኢንደስትሪውን እንዴት እየመገበው እንደሆነይናገራል፤ በያዝነው ዓመት ብቻ ዘርፉ ከ200 ሚሊየን ዶላር በላይ ገቢ አስገብቷል፡፡ በክፍል ሁለት፡ ራይዚንግ ሳዉዝ የደቡባ ትብብር ካውንስል ፌስቲቫልን መነሻ አድርጎ፣ የባህል ነጻነትን ስለመቀዳጀት የተለያዩ ሀሳቦችን ራይዚንግ ሳዉዝ በሰፊው ዳስሷል፡፡

የትናንቱን ዕውቀት መመለስ፡ ትምህርትን ከቅኝ ግዛት ተፅዕኖ ማላቀቅ በአፍሪካ 30.06.2025

የአፍሪካ ትምህርት በቅኝ ግዛት ከመታወኩ በፊት በአገር በቀል እውቀት የተቀረፀ ጥልቅ፣ የተለያየ ታሪክ ያለው ነበር። ዛሬም  አህጉሪቱ የራሷን እሴቶች እና እውነታዎች ለማንፀባረቅ ከቅኝ ግዛት ዘመን የተወረሱ ስርዓቶችን የመቀየር ፈተና ተጋርጦባታል። በዚህ የራይዚንግ ሳዉዝ መሰናዶም የሚዲያ እና ትምህርት ለልማት አፍሪካ ፎረም ጥምረት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ላዋሊ ኮል ጋር  ያልተነገረውን የአፍሪካን ትምህርት ታሪክ  ፤  የቅድመ ቅኝ ግዛት የእውቀት መገለጫዎችና፣  የቅኝ ግዛት ዘመን ጥፋቶችን በሰፊው እንመረምራለን።

ሉዓላዊነትን እና ትብብርን ማዳበር፡ የአፍሪካ የግብርና ለውጥ ሥር እየሰደደ ነው 25.06.2025

“የትሮፒካል ክልል  [የደቡባዊ ዓለም] ሀገራት ድህነትን እና ረሃብን በጋራ ለመጋፈጥ አንድ ላይ መሆን በሚያስፈልግበት ወቅት ላይ ነን” ሲሉ የብራዚል የግብርናና የእንስሳት እርባታ ም/ ሚኒስትር ክሌበር ሶአሬስ ከ7ኛው የአግሮ ፉድ ኢትዮጵያ ሁነት በጎንዮሽ ተናግረዋል።  

ከተረጅነት ወደ አጋርነት ፦ የምዕራባውያን ዕርዳታ መቀነስ እና ብሪክስ ይዞት የመጣው ዕድል በኢትዮጵያ 23.06.2025

የዓለም የምግብ ፕሮግራም የኢትዮጵያ ዳይሬክተር የሆኑት ዝላታን ሚሊሲች አሜሪካ እና ሌሎች ምዕራባዊያን ሀገራት ለዓለም የምግብ ፕሮግራም የሚያደርጉትን ዕርዳታ በመቀነሳቸው ምክንያት በኢትዮጵያ ውስጥ ሊደረግ ከታሰበው ዕርዳታ በግማሽ ያህል እንደሚያንስ ተናግረዋል። የሚቀነሰው የዕርዳታ መጠን በአሀዝ ሲገለጽ 222 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር ወይም 28 ቢሊየን ብር ገደማ እንደሚሆን ጠቁመዋል።

የወደፊቱ የዲጂታል ዓለም ፦ አፍሪካ በቴክኖሎጂ ዘመን ያላት ድምፅ 19.06.2025

አፍሪካ በዲጂታሉ ዓለም መስቀለኛ መንገድ ላይ ቆማለች። የምዕራባውያን ቴክኖሎጂ እና የሰው ሰራሽ አስተውሎት  የበላይነት በያዙበት በዚህ ወቅት ጥያቄው ግልጽ ነው፡- አፍሪካ ማንነቷን ጠብቃ ዲጂታል ዓለሙን በመምራት ቀዳሚ መሆን ትችላለችን ?

የደረቅ ቆሻሻ አያያዝ እና አወጋገድ አዋጅ:- የአዋጁ ይዘት እና ቅጣቶቹ 16.06.2025

በኢትዮጵያ የከተሞች መስፋፋት እና እድገት፣ ከሕዝብ ቁጥር እድገትና ለዉጥ ጋር ተዳምሮ በደረቅ ቆሻሻ አወጋገድ ላይ የራሱን የሆነ አሉታዊ ጫና እየፈጠረ ነው፡፡ ይህንንም ተከትሎ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤትም  ግንቦት 26 ቀን፣ 2017 ዓ.ም፤ በዋለው የ33ኛ መደበኛ ስብሰባው ላይ የደረቅ ቆሻሻ አያያዝና አወጋገድ ረቂቅ አዋጅ ቁጥር 1383/2017 ን በሙሉ ደምጽ አፅድቋል። በዚህኛው የራይዚንግ ሳውዝ ቆይታችን በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የውሃ፣ መስኖ፣ ቆላማ አካባቢና አካባቢ ልማት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ምክትል ሰብሳቢ የሆኑት ዶ/ር አወቀ አምዛዬ በጉዳዩ ላይ ሰፊ ማብራሪያ ሰጥተውናል፡፡ 🔇ዶ/ር አወቀ ስለዚህኛው አዋጅ ሲያብራሩ...

የአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጣና ስምምነት የአፍሪካን የዕዳ ጫና ወደ ኢኮኖሚያዊ ጥንካሬ ይቀይረዋልን? 10.06.2025

የአፍሪካ የዕዳ ጫና ከጠቅላላ የአህጉራዊ ምርት ውስጥ ከ 66 በመቶ በላይ ሆኗል ። ለዚህም ደካማ የብድር ስርዓት እና ሙስና ምክያቶቹ ናቸው፡፡ ይህ የጤና ስርዓት ላይ እና ትምህርትን በማደናቀፍ ረገድም አሉታዊ ሚናን እየተጫወተ ነው። በዛሬው የራይዚንግ ሳዉዝ ዝግጅታችን ከኢትዮጵያ የፖሊሲ ጥናት ኢንስቲትዩት የጋበዝናቸዉ ዶ/ር ጀማል መሐመድ እንዲህ ሲሉ ያብራራሉ። “ብድር በግድ ውሰዱ ብለው አያስወስዱንም፡፡ [...] ከጀርባ ግን ብድር እንድንጠይቅ የሚገፋፉ ነግሮች አሉ ፡፡ ወርልድ ባንክም አይ ኤም ኤፍም፡፡ [...] በተለይ አፍሪካ አካባቢ ደግሞ ይህንን ለመቆጣጠር የሚያስችሉ ተቋማት ስለሌሉ አብዛኛው [ብድር] በካፒታል ፍላይት...

ያረጁ ትርክቶችን ልሳን መዝጋት: ደቡባዊ ዓለም መጪውን ጊዜ የሚቀረጽበት ሂደት 04.06.2025

በዚህ የራይዚንግ ሳውዝ ዝግጅት በደቡባዊው ትብብር ድርጅት /Organization of Southern Cooperation/ የቴክኖሎጂ ፈጠራ እና ዲጂታላይዜሽን ማበልጸግ ምክትል ዋና ጸኃፊ የሆኑት ሹመቴ ግዛው /ፒ.ኤች.ዲ/ የዓለም አቀፉ የኃይል ሚዛን ስለሚቀየርበት መንገድ ወሳኝ ነጥቦችን አጋርተዋል። “የደቡባዊው ትብብር ድርጅት በታላቁ ደቡባዊ ዓለም ውስጥ የሚገኙ ሀገራትን እና ማኅበረሰቦችን አቅም ማጎልበት ላይ ያምናል። ለአብነት ያህል ባህላዊ እና ሀገር-በቀል ዕውቀቶቻቸውን በመውሰድ ዓለም-አቀፍ በሆኑ መድረኮች ላይ እንዲሰሙ ያደርጋል።" በማለት ተናግረዋል። ምክትል ዋና ሥራ ፈጻሚዉ የዓለም-አቀፉ የፋይናንስ ሥርዓት ሀገራትን ዕ...

የለዉጥ ጎዳና - የኢትዮጵያ ሽግግር ወደ ኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች 03.06.2025

የኤሌትሪክ ኃይልን በመጠቀም ከብክለት የጸዳ የትራንስፖርት ማዕከል ለመሆን የሚደረግ ኢትዮጵያዊ ጉዞ! 🎙በዚህኛው የራይዚንግ ሳውዝ ዝግጅት የትራንስፖርት ባለሙያው አቶ ሞገስ ነጋሽ ኢትዮጵያ ከፖሊሲ እስከ ትግበራ ድረስ በትራንስፖርት ረገድ የያዘችውን ጉዞ ፣ እንዲሁም በኬንያ ስለሚካሄደው አውቶኤክስፖ ከቡርኪናፋሶ እና ናይጀሪያ የተሽከርካሪ ምርት ስኬት ጋር አያይዘው ስለ አፍሪካ አረንጓዴ ጉዞ ሀሳባቸውን አጋርተውናል። 🌍 "በኢትዮጵያ ውስጥ ርካሽ የሰው ኃይል አለ....የፀሐይ ብርሃን፣ መልክዓምድራዊ አቀማመጡን ስትመለከት ኢትዮጵያ የቃጣናውን የኤሌትሪክ ተሽከርካሪ ምርት በበላይነት ለመምራት የሚያስችላት ትልቅ ዕድል አለ።" "ኢትዮ...

ብዝኃ-ሕይወት እና ሉዓላዊነት:- ከተፈጥሮ ጋር ስምም ለመፍጠር ኢትዮጵያ የያዘችው መንገድ 30.05.2025

የኢትዮጵያ ብዝኃ-ሕይወት ተቋም የአመራር አካላት ከሆኑት ከዶ/ር አብዮት ብርሃኑ እና ከአቶ ውብሸት ተሾመ ጋር የዓለም-አቀፍ የብዝኃ-ሕይወት ቀንን አስመልክቶ ከራይዚንግ ሳውዝ ጋር የተደረገ ቆይታ

ብሪክስ:- የዓለም አቀፉን ንግድ እና ኢንቨስትመንት ጨዋታ ቀያሪ 26.05.2025

"የብሪክስ ስኬት በመላው ዓለም የሚገኙ በቢሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎችን ሕይወት ያሻሽላል።" ሲሉ በኢትዮጵያ የፋይናንስ ፎረም ላይ የተገኙት የ ሲቢኢ ካፒታል ኢንቨስትመንት ባንክ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ዘመዴነህ ንጋቱ ተናገሩ። ኢትዮጵያ አባል የሆነችበት ይህ ህብረት "በዓለም አቀፍ ንግድ እና ኢንቨስትመንት ላይ ሚዛን የሚፈጥር ነው" ብለው በአጽንኦት ተናግረዋል። "ለአብነት ያህል የብሪክስ ባንክን ብንወስድ በማደግ ላይ ላሉ ገበያዎች እጅግ አስፈላጊ ለሆነው መጠነ-ሰፊ የመሠረተ-ልማት ግንባታ ፋይናንስ የሚያቀርብ ነው።" በማለት አክለዋል። 🎤 በፎረሙ ላይ የተሳተፉት የፋይናንስ ባለሙያው አቶ ጌታቸው ባሻህውረድ, የባንክ አማካሪው አቶ...

Listen to the The Rising South podcast in Replaio

Radio and podcasts in one app - free, with no sign-up. Install today and do not miss the launch

Get it on Google Play

Replaio is not a podcast publisher; show names, artwork and audio belong to their authors and are distributed through public RSS feeds.