ዐቢይ ሀብታሙ
Sovereignty Sources
ዓለም በሉላዊነት ምክንያት ስትተሳሰር ፤ ፕሮግራሙም አፍሪካ ባላት እምቅ የተፈጥሮ ኃብት፣ በማደግ ላይ ባለው የሕዝብ ቁጥሯ ፣ በወጣት ኃይሏ እና በአህጉሪቱ ባሉ አዳዲስ ግኝቶችና የመፍትሄ ሃሳቦች ያላትን የመወዳደር አቅምና ጥቅም በሰፊው ይዳስሳል፡፡ እንኳን ወደ 'ሶቨርኒቲ ሶርስ' ፕሮግራም በደህና መጡ፣
Author
ዐቢይ ሀብታሙ
Category
Podcast website
Latest episode
Jul 11, 2026
Where to listen?
Podcasts in the app Replaio Radio Coming soonPodcasts are coming to the app soon. Install now and be the first to see a whole new take on podcasts
Episodes
እንሰት፡ ነገን በምግብ ዋስትና ለማረጋገጥ ተስፋ ሰጪ ምርምር የተደረገበት ተክል 25.09.2025 1:00:00
''እንሰት አንዱ የምግብ ግብዓት ሲሆን የአየር ንብረትን የሚቋቋም ተክል ነው። - አዲሱ ፍቃዱ (ዶ/ር)፣ የሉሲ እንሰት መሥራች ''የአካባቢው ነዋሪዎች በጣም ስለተደነቁ ፈጠራውን ለመጠቀም ጓጉተዋል።'' የምግብ ኬሚስቱ በላይ ጣፋ (ዶ/ር) በዚህ የሶቨርኒቲ ሶርስስ ዝግጅት አቅራቢ በጥናትና ምርምር አስደናቂ ፈጣራ የተደረገበትን ተክል እንሰትን በተመለከተ የሉሲ እንሰት መሥራች አዲሱ ፍቃዱ (ዶ/ር) እና የምግብና ቃና ኬሚስት እና የአካባቢ ተመራማሪ በላይ ጣፋ (ዶ/ር) አወያይቷቸዋል። በእንግሊዘኛ የቀረበውን ሙሉ ፕሮግራም ያዳምጡ:
ከሃይድሮ ኤሌክትሪክ ኃይል ወደ ኒውክሌር ፡ የኢትዮጵያ ሰላማዊ የኒውክሌር ኢነርጂ የመገንባት ውጥን 23.09.2025 1:00:00
“ለሀገር ልማትና ምጣኔ ሐብት ዕድገት፣ አስተማማኝ ኢነርጂ በጣም አስፈላጊ ነገር ነው። ስለዚህ፣ ሌሎች ምንጮች ላይ ጥገኛ ያልሆነ፣ የተረጋጋና አስተማማኝ የኢነርጂ የኃይል ምንጭ የሚሆን ፓወር ፕላንት መገንባቱ ጠቃሚ ነው '' ሲሉ የኒውክሌር ሶሳይት ኦፍ ኢትዮጵያ ፕሬዝዳንት ዶ/ር እምሻው ዳምጠው ተናግረዋል። የኮይሻ ሀይድሮፓወር ፕሮጀክት ምክትል ኃላፊ ኢንጂነር አባይነህ ጌትነት በበኩላቸው፡ - “ኢትዮጵያ አሁን ላይ ቀጠናው ለማስተሳሰር በብርቱ እየሰራች ናት። እስካሁን ሱዳን፣ ጅቡቲ እና ኬንያ የኤሌክትሪክ ኃይል እያስገቡ ነው። ወደ ታንዛንያም ለመላክ የስምምነት እና ሌሎች ተግባራት በመከናወን ላይ ይገኛሉ'' ብለዋል። ኢትዮጵያ...
የታላቁ ህዳሴ ግድብ ከዲፕሎማሲዊ ውይይቶችና ድርድሮች አኳያ ሲቃኝ 19.09.2025 30:00
''ለአካባቢ ጉዳይ የየሀገራትን ድርሻ በህግ መወሰን ይጠይቃል። ይህ ከሌለ ሦስቱም ሀገራት ሆኑ ሌሎቹ በዘላቂነት መንገዶቻቸውን ሊያቀኑ አይችሉም። የውኃ ክፍፍል ወይም መጋራት የሚባለው በህግ መመሥረት አለበት — ኃብት ባጠረ ቁጥር እኔ እለቅልሃለሁ፤ አልጎዳህም ብቻ በማለት ሀሳባቸው ሊረጋ አይችልም "- ሲሉ ሀይድርሎጁስቱ፣ የውኃ ሐብቶች መሃንዲስና የታላቁ የህዳሴ ግድብ ተደራዳሪው ፕሮፌሰር ይልማ ስለሺ ተናግረዋል። የታላቁ የህዳሴ ግድብ ጋር በተገናኘ የሚነሱ አንኳር ዲፕሎማሲዎችና የባይንዲንግ አግሪመንት ጉዳዮች የሶቨርኒቲ ሶርስስ ፕሮግራም አቅራቢ ከሀይድሮሎጂስት ፣ የውኃ ሀብቶች መሃንዲስና የታላቁ ህዳሴ ግድብ ተደራዳሪው ፕሮፌሰ...
''አዲስ የዓለም መልክ'': - የአፍሪካ የመደመጥ አቅም በተባበሩት መንግስታት የፀጥታው ም/ቤት 17.09.2025 1:00:00
የተባበሩት መንግሥታት ዋና ፀሐፊ አንቶኒዮ ጉቴረዝ የፀጥታው ምክርቤትን ማሻሻል ሙሉ ስሜት የሚሰጥ (አሳማኝ) ነገር ነው ሲሉ ተናግረዋል ፡፡ ይህ ለአፍሪካ ምን ማለት ነው ? '' አፍሪካን የሚመለከቱ ጉዳዮች ላይ በቀጥታ ድምጿን ማሰማት ትችላለች። የሚጎዳቸው ከሆነ ማገድ ይችላሉ፣ የሚጠቅማቸው ከሆነ ደግሞ ማስተላለፍ ይችላሉ '' - ጃራ ሳሙኤል ቱራ በአርሲ ዩኒቨርስቲ የህግ ትምህርት ክፍል መምህር የትምህርት ክፍሉ ዲንና መምህር አበራ ለሚ በበኩላቸው፡- ''[አፍሪካ] ቋሚ መቀመጫ ማግኘቷ ከምጣኔ ሀብት አኳያ ካየነው የተለያዩ ኢንቨስትመንቶችን በመሣብ ከሌሎች ዓለማት ጋር ያላትን ዲፕሎማሲ ለማጠናከር ይረዳታል '' ሲሉ ተናግረዋል።...
የታላቁ የህዳሴ ግድብ፡ የኢትዮጵያ የኃይል ሚዛን ገፀ በረከት 12.09.2025 1:00:00
'የናይል ተፋሰስ ውስጥ ያለው አመለካከት ሁለት ነው። ውኃ አመንጫ ሀገራት የውኃ መብት አለን፣ ውኃው የሁላችንም የጋራ ሐብት ነው። በትብብር ብናለማው ለሁላችንም ይጠቅማል የሚል ሀሳብ ነው ያላቸው - ሁለት የታችኛው ተፋሰስ ሀገራት ውኃው ሙሉ ለሙሉ የኛ ነው የሚገባው የሚሉ ናቸው - ሲሉ ከህዳሴ ግድብ ተደራዳሪዎች አንዱ ዶ/ር ያዕቆብ አርሳኖ አቲቶ ተናግረዋል።'' የአፍሪካ ጉዳዮች ተመራማሪው ዶ/ር ጋሻው አይፈራም በበኩላቸው፡- 'የናይል ወንዝ ለኢትዮጵያ ጂኦ ፖለቲካዊ ጠቀሜታ አለው። ኢትዮጵያ ቀጠናው ላይ የምትጫወተውን ሚና ከፍ ሊያደርግ ይችላል። የምጣኔ ሐብታዊ ጠቀሜታም አለው - ብለዋል።'' 🎙የታላቁ የህዳሴ ግድብ በሰፊው የ...
ለምንም የውጭ እርዳታ እና ገደብ ፦ ኢትዮጵያን በውስጣዊ አቅሟ መተማመንን ያረጋገጠችበት ግድብ 10.09.2025 1:00:00
''የህዳሴ ግድብ መሠራት አንዱ ሞዕራፍ ነው። ወንዙ ግን የኢትዮጵያ ልብ ውስጥ ከፍተኛ፣ ሚና ያለው የሶሺዮ - ፖለቲካ መገለጫ፣ የኢትዮጵያ ማንነትና ባህል ጋር ከፍተኛ ቁርኝት ያለው ነው - ብለዋል የውጭ ጉዳዮች ኢንስትቲዩት ምክትል ዳይሬክተር የተከበሩ ዶ/ር አብዲ ዘነበ።'' ዶ/ር አረጋዊ በርሄ የታላቁ ህዳሴ ግድብ ማስተባበሪያ ፕሮጀክት ጽ/ቤት ኃላፊ በበኩላቸው፡- ''አባይ፣ በአፍሪካ ትልቁ ግድብን መገደብ ከተቻለ፣ ሌሎች ግድቦችን ለመገንባት የሚያግደን ምንም ነገር የለም።'' የታላቁ የህዳሴ ግድብ ተጠናቆ በይፋ መመረቁን መሠረት አድርገን ከውጭ ዕርዳታ ውጪ በሰፋ የህዝብ ተሳትፎ መሠራቱ ያለው አንድምታና ሌሎች ተያያዥ ጉዳዮ...
አረንጓዴ አሻራ፡ አካባቢን ከጥፋት ለመታደግ የሚደረግ ችግኝ የመትከል ዘመቻ 08.09.2025 30:00
“በአረንጓዴ አሻራው ደስተኛ ነኝ፣ እናም የኢትዮጵያን አርአያነት በመከተል ተግባራዊ ልናደርገው ይገባል። በዓመት አንድ ጊዜ ብቻ ሳይሆን በሁሉም የአፍሪካ ሀገራት ቢያንስ በወር አንዴ ተግባራዊ ልናደርገው የተገባ ነው'' ሲሉ ሚስ ጆይስ ሜንዴዝ ኮል ተናግረዋል። በዚህ የሶቨርኒቲ ሶርስስ ፕሮግራም አቅራቢው በኢትዮጵያ ለተከታታይ ዓመታት እየተተገበረ ያለውን የአረንጓዴ አሻራን፣ የአፍሪካ የሴቶች ቀን እና ስለ ቅርስ ጥበቃ ጉዳዮች በሶስት ክፍሎች ለመወያየት የአፍሪካ የሴቶች አመራር ኔትወርክ ዋና ዳይሬክተር ሚስ ጆይስ ሜንዴስ ኮልን ጨምሮ በርካታ እንግዶችን ጋብዟቸዋል።
የኢትዮጵያ እግርኳስ እና የአፍሪካ ጨዋታዎች መልክ 05.09.2025 1:00:00
የአፍሪካ አህጉር እግር ኳስ ዕድገትና እንቅስቃሴን መሠረት አድርጎ የአህጉሪቱ የእግር ኳስ ዕድገት፣ የ2029 የአፍሪካ ዋንጫ፣ ስለኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን፣ የውጭ ተጫዋቾችና አሰልጣኞች በኢትዮጵያ እና ሌሎች ተያያዥ ጉዳዮች በተመለከተ የሶቨርኒቲ ሶርስስ ፕሮግራም አቅራቢው የእግር ኳስ ጋዜጠኛው አያናው ወልደ ሚካኤል፣ የእግር ኳስ ተንታኙ ልዑል ታደሰ እና የፓን አፍሪካ ፉትቦል ጸሐፊው ኦምና ታደለን በጥልቀት አወያይቷቸዋል።
የኢትዮጵያ የጤና ስርዓት ወደ ቱሪዝም መዳረሻነት የመለወጥ ተስፋዎች 03.09.2025 1:00:00
“የጤና ስርዓት ቱሪዝምን መገንባት አስፈላጊ ነው ምክንያቱም የሰው ኃይልን መገንባት ስለሚኖርብን። ብዙ ሙያተኞቹን እያበቃን ነው። ብቃት ያላቸው በርካታ ሀኪሞች እየተፈጠሩ በመሆናቸው በየቦታው ሙያቸውን ተግባራዊ እያደረጉ ይገኛሉ። ስለዚህ መሠረተ ልማቶችና ማዕከላት ለጠቅላላ ሀኪሞችና ስፔሻሊስቶች ምቹ ከሆኑ የጎረቤት ሀገራትን ጨምሮ በርካታ የውጭ ዜጎችን ለህክምና እንዲመጡ ማድረግ ይቻላል" ብለዋል የኢትዮጵያ ጋስትሮኢንትሮሎጂ ማኅበር ኤክስኪዩቲቭ ኮሚቴ ዋና ፀሃፊው ዶ/ር ካሳ ታምሩ። በርካታ የምስራቅ አፍሪካ ሀገራት ዜጎች በተለይም እንደ ጅቡቲ፣ ሱዳንና ሶማሌ ላንድ ያሉት የተሻለ ህክምና ለማግኘት ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ ኢትዮጵያን...
ከጎጂ ተክልነት ወደ ግንባታ መሣሪያ ግብዓትነት የተለወጠው የወያኔ ዛፍ ወይም 'ፕሮሶፒስ ጁሊፍሎራ' 01.09.2025 30:00
“ሀሳቤ ለሞቃታማ ሥፍራዎች ተስማሚ ጥሩ የግንባታ መሣሪያ ማምራት ነበር። ስለዚህ ዋናው ሀሳቤ ከሄምፕክሪት ግንባታ ነበር የመነጨው። ከዛ ነበር ቴክኖሎጂውን የቀዳሁት። ፕሮስክሪት ወደተባለው የራሳችን ምርት ነበር የቴጂክኖሎጂ ሽግግር የተደረገው” ሲል ሲቪል መሃንዲሱ ሱራፌል በላይ ተናግሯል። 'ጁሊፍሎራ' በኢትዮጵያ በረባዳማ ሥፍራዎች ወይም በቆላማ አካባቢዎች የብዝሃ ህይወትን የሚያዛንፍ የአርሶ አደርና አርብቶ አደሩን ህይወት እየጎዳ ያለ መጥፍ ዕፅ ነው። ይህን ተክል ለማስወገድ ብዙ ጥረቶች ተደርገዋል። በዚህ ረገድ የሶቨርኒቲ ሶርስስ አቅራቢ በተለምዶ 'የወያኔ ዛፍ' ተብሎ የሚጠራዉን 'ፕሮሶፒስ ጁሊፍሎራ' ን ከጎጂ ተክልነ...
የጤናው ዘርፍ የቴክኖሎጂ ዐቢዮት በአፍሪካ 28.08.2025 30:00
“የዲጂታል መሩ ጤና የወደፊቱ የዓለም ስርዓተ ለውጥ ነው። ፕላኔታችን የዓለም ምጣኔ ሐብት ነው። የዲጂታል መር ጤና ቅንጦት ሳይሆን መሠረታዊ ጉዳይ ነው። የእናቶች ሞት፣ ዕድሜያቸው የገፉ ሰዎች፣ በፅኑ ህመም ያሉ ህመምተኞች ባሉበት ሁኔታ የዲጂታል መር ጤና ተግዳሮቶቹን የመቋቋሚያ ሁነኛ መላ እየሆነ መጥቷል” ሲሉ የፓን - አፍሪካ ዲፕሎማቲክ ማኅበር ዋና ኃላፊ ዶ/ር ሶስተንስ ባጉሜምሄ ተናግረዋል። ዶ/ር ሶስተንስ አክለውም፡- “የእርዳታ ድጋፍ መቋረጥ የዓለማችን ዋነኛ እክሎች ቢሆኑም የተለያዩ ዲጂታል መር የጤና ባለድርሻዎች እንዳተባበሩ በማድረግ በዋሻው ጫፍ ላይ ጮራ እንዲፈነጥቅ የሚያደርግ ነው'' ብለዋል።
በአፍሪካ የጋዜጠኝነት ትምህርት ተግዳሮትና ተስፋዎቹ 26.08.2025 1:00:00
“የቅኝ ግዛት ሚዲያዎች በአህጉሪቱ ላይ ችግሮችን ይፈጥራሉ። ምክንያቱም ምዕራባዊያን ሚዲያዎች የአፍሪካ መልካም ጎኖችን ሊዘግቡ ስለማይችሉ። አፍሪካን ሁልጊዜ እንደ ጦርነት፣ ርሃብ እና በሽታ መናኸሪያ ብቻ አድርገው ነው የሚስሉት" ሲሉ በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የጋዜጠኝነትና ተግባቦት ት/ቤት መምህር ረዳት ፕሮፌሰር መኩሪያ መካሻ ተናግረዋል። የአፍሪካ የጋዜጠኛነት ትምህርትን ዳግም ማጤን በርካታ ችግሮችን እንደሚፈታ ይታመናል። በዚህም የዘርፉን ጠቀሜታ እና ተፅዕኖ ለማሳደግ እምቅ መፍትሔዎችን የሚያመጣ እንደመሆኑ በዚህ የሶቨርኒቲ ሶርስስ ፕሮግራም አቅራቢው በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የጋዜጠኝነትና ተግባቦት ት/ቤት መምህራን የሆኑት...
ሰው ሰራሽ አስተውህሎት:- የኢትዮጵያ የኪነ ህንፃ ታሪክና ባህል ከቴክኖሎጂ አኳያ 22.08.2025 1:00:00
''አዲሱን ቴክኖሎጂ ከቀደምቱ የኢትዮጵያ ኪነ ህንፃ ጋር ለማዋሃድ በቅድሚያ መደረግ ያለበት ጥናት ነው፡፡ ከዚህ በፊት የነበሩት ኪነ ህንፃዎች ምን ምን የተለየ የራሳቸው ነገሮች አላቸው፣ ጠባያቸው ምንድነው፣ በምን አይነት ቴክኖሎጂ ነው እየተሰሩ የነበሩት፣ ማቴሪያል ምናምን የሚሉ ነገሮችን በደንብ ማጥናት ያስፈልጋል፡፡ ከዚያም አዲሱን ቴክኖሎጂ መላመድ ያስፈልጋል'' ሲል የዘርፉ ባለሙያ ዳንኤል ተመስገን ይናገራል ። 🎙 በዚህ የሶቨርኒቲ ሶርስስ ፕሮግራም አቅራቢው በኢትዮጵያ የኪነ ህንፃ ዘርፍ ታሪክና ባህልን ከቴክኖሎጂ ጋር ለማዋሃድ ሰው ራሽ አስተውህሎት የሚጫታወቸው ወሳኝ ሚና እንዲሁም ተያያዥ ጉዳዮች ለመወያየት የምህንድስና ባ...
እናትን ከሞት መታደግ ቤተሰብን ማዳን ነው፦ የእናቶች ጤና አገልግሎት በኢትዮጵያ 20.08.2025 30:00
"የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር በእናቶች ሞት ጉዳይ በትኩረት ሲሰራ የተሻለ በጀት፣ ትኩረት፣ የስልጠና ዕድሎች፣ የመሠረተ ልማት ግንባታዎች፣ የጤና ባለሙያዎችን በጎለበተ እውቀትና መሠረተ ልማት ማስታጠቁ፣ እነዚህ ሁሉ ነገሮች ከፍተኛ አስተዋፅዖ አድርገዋል። የእናቶች ሞት ብዬ መናገር እችላለሁ። ለዚህም ሁልጊዜም አመስጋኞች ነን። አንዲት እናትን ማዳን አንድ ቤተሰብ እንደመታደግ ነው'' ሲሉ የጽንስና የማህፀን ስፔሻሊስት ዶ/ር ምስክር አንበርብር ተናግረዋል። በዚህ የሶቨርኒቲ ሶርስስ ፕሮግራም አቅራቢው በወሊድ ሆነ በድህረ ወሊድ ወቅት ስሚፈጠር የእናቶች ሞት፣ ኢትዮጵያ በዘርፉ እያደረገች ያለችውን አበረታች ሥራዎች እና ተያያዥ ጉዳዮችን ለ...
የፑቲን እና ትራምፕ ስብሰባ መልዕክት ፦ ዓለም በባለብዙ ዋልታ ማዕቀፍ 18.08.2025 1:00:00
“ከፕሬዝዳንት ትራምፕ ይልቅ ፕሬዝዳንት ፑቲን ያሸነፉ ይመስለኛል። ትራምፕ በድጋሚ ከተመረጡ በኋላ ዩክሬንን በተመለከተ የታዘብነው አንድ ነገር፣ በምዕራባውያን ኃይላትና አጋራት መካከል ትልቅ ክፍፍል ተፈጥሯል። ቀደም ባሉት ጊዜያት በባይደን አስተዳደር ዘመን አውሮፓውያን ከዋሽንግተን የሚወጣውን ማንኛውንም ነገር በጥብቅ ይከታተሉ ነበር። አሁን ግን ግልጽ ተቃውሞ አይተናል። ዜለንስኪ ቢሆን ፕሬዚዳንት ትራምፕን ይቃረናቸዋል። ስለዚህ አንድ ግልጽ የሆነው ነገር በምዕራባውያን አጋራት መካከል መለያየት ያለ ይመስለኛል " ሲሉ ምሁሩና የፖለቲካ ሳይንቲስቱ ዶ/ር አስናቀ ከፋለ ተናግረዋል። በዚህ የሶቨርኒቲ ሶርስስ ፕሮግራም አቅራቢው ኃያላኑ...
የፑቲን - ትራምፕ ውይይት፡ የዓለም ዓይኖች ሁሉ አላስካ ላይ አማትረዋል 15.08.2025 1:00:00
"ከአውሮፓውያኑ እና ዩክሬን የበለጠ አስፈላጊው የሩሲያ እና የአሜሪካ ንግግር ስለሆነ ዩክሬን ብቻ ሳትሆን አውሮፓውያኑም ከዚህ ሂደት ውጭ ናቸው። ስለዚህ ትራምፕ ራሳቸውን አጋር ለማድረግ ከሌሎች ኃይሎች የበለጠ ጠንካራ ከሆነችው ሩሲያ ጋር ለመነጋገር ብልህ መሆንን የተረዱ ይመስለኛል" ሲሉ የታሪክ ምሁሩና የፖለቲካ ተንታኙ ዶ/ር ኢብራሂም ሙሉ ሸዋ ተናግረዋል። በዚህ የሶቨርኒቲ ሶርስስ ፕሮግራም አቅራቢው ኃያላኑ የዓለም መሪዎች ቭላድሚር ፑቲንና ዶናልድ ትራምፕ በአላሳካ በሚያደርጉት ተጠባቂ ስብሰባ በሰፊው ይዳስሳል። በስብሰባው የሚነሱ አንኳር ጉዳዮች፣ የግንኙነታቸው ፖለቲካዊ አንድምታና ሌሎች በርካታ ተያያዥ ሀሳቦች ለመወያየት...
ከሩሲያ ለዘመናት የተዘረጋው የትምህርት ዕድል ለወጣት አፍሪካዊያን 13.08.2025 1:00:00
“በውጤቱ እኛንና መሰል ሰዎች ተገኝተዋል፡፡ አሁን በአብዛኛው በተለያዩ የህክምና፣ የእርሻ እና ሌሎች ዘርፎች የሚሰሩ የቀድሞ ተማሪዎች አሉ፤ በፖለቲካው ረገድም ትልቅ ቦታ የደረሱ ሰዎች አሉ፤ በከፍተኛ የስልጣን ወይም የሥራ አመራር ደረጃ ላይ የተቀመጡ ናቸው፡፡ በዚህም በአገሪቷ የተማረው የሰው ኃይል ቁጥር እየጠነከረና እየሰፋ ይሄዳል ማለት ነው፡፡ በምርምሩም የተሰማሩ ሰዎች አሉ ዛሬም ድረስ - ሲሉ ዶ/ር ክብሩ ቸርነት ተናግረዋል” በዚህ የሶቨርኒቲ ሶርስስ ፕሮግራም አቅራቢው በየጊዜው እየጨመረ የመጣው ሩሲያ ለወጣት አፍሪካዊያን ተማሪዎች እያመቻች ያለችው የትምህርት ዕድልና ተያያዥ ጉዳዮች ለመወያየት የቀድሞ የሶቭየት ኅብረት ተ...
ኢትዮጵያ - ለተመራማሪዎች የተፈጥሮ ቤተ- ሙከራነት ለምን ተመራጭ ሆነች? 11.08.2025 1:00:12
'የመሬት መንቀጥቀጥ ብዙ ቦታዎች ላይ ቢፈጠርም በአብዛኛው ከባህር ወይም ከውቅያኖስ በታች የሚፈጠር ነው፡፡ አትላንቲክ ውስጥ አለ፣ ህንድ ውቅያኖስ ውስጥ አለ፣ ልዩ ልዩ ቦታ አለ፡፡ በደንብ ግን የመፈጠሩ ሂደት የሚታየው ኢትዮጵያን ጨምሮ የምስራቅ አፍሪካ ሰምጥ ሸለቆ አካባቢ ነው ።'' የሶቨርኒቲ ሶርስስ ፕሮግራም በዛሬው መሠናዶው በርዕደ መሬት እና ተያያዥ ጉዳዮች ሙያዊ ሃሳባቸውን እንዲያጋሩን በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የጂኦ ፊዚክስ፣ ስፔስ ሳይንስና አስትሮኖሚ ተቋም ተመራማሪ ተባባሪ ፕሮፌሰር ኤልያስ ሌዊ (ዶ/ር) ጋብዟቸዋል።
ዓለም አቀፉ የጦር ወንጀለኞች ፍርድ ቤት ኢ-ፍትሃዊነትና ድብቅ ፖለቲካዊ አጀንዳ፦ በፓን አፍሪካኒዝም ዕይታ 07.08.2025 30:00
"የዓለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት ከተመለከታቸው 33 ጉዳዮች መካከል 90% በላይ የሚሆኑት የደቡባዊ ዓለም ላይ ያነጣጠሩ ናቸው። በአጋጣሚ ብቻ የሆነ አይደለም፤ ይልቁን የምዕራባውያንን ጥልቅ አድልዎ የሚያሳይ ነው። አንድም ክንደ ፈርጣማ የምዕራቡ ዓለም መሪ ወደ ፍርድ ቤቱ አልቀረበም፣ ይህም እምነትን ያዳክማል። ስለዚህ ለተለያዩ ሰዎች የተለያዩ ህጎች እንዳሉ ያረጋግጣል።" ሲሉ የማህበራዊ አንትሮፖሎጂስት ምሁሩ መሀመድ አወል ሀጎስ ተናግረዋል። በዚህ የሶቨርኒቲ ሶርስስ ፕሮግራም አቅራቢው ስለፓን አፍሪካኒዝም፣ የዓለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት አድሏዊ ፍትህና ሌሎች ተያያዥ ጉዳዮች በጥልቀት ለመወያየት በወራቤ ዩኒቨርሲቲ...
ኢትዮጵያን እንቃኛት፡ የእምቅ ብዝሃ ህይወት እና የአካባቢ ጥበቃ ተምሳሌት 05.08.2025 30:00
"ኢትዮጵያ በዓለም አቀፍ ደረጃ የብዝሃ ህይወት ምንጭ ከሆኑ ሀገራት መካከል አንዷ ነች። ለዚህም ከ125 ሜትር የባህር ወለል በታች፣ ዳሎል እስከ ከፍተኛው የተራራ ጫፍ ወይም 4620 ሜትር የሚረዝመው ራስ ዳሽን ተራራ በአብነት ይጠቀሳሉ። በደን ብዝሃ ህይወት ረገድ በርካታ የዱር እንስሳት፣ እፅዋት፣ አዕዋፋት እና ሌሎቹ ሀገሪቷን ልዩ እንድትሆን አድርገዋታል።” በዚህ የሶቨርኒቲ ሶርስስ ፕሮግራም አቅራቢው የዱር እንስሳትን እና ቱሪዝምን የሚደግፍ የኢትዮጵያ ከፍተኛ የብዝሃ ህይወት እና አረንጓዴ እድገት እንዲሁም ተያያዥ ጉዳዮች ለመወያየት የብዝሃ ህይወትና አካባቢ ጥበቃ አማካሪው ስሜነህ አድማሱን ጋብዟቸዋል።
የአፍሪካ የማዕድ ጥበብ ሲገለጥ 01.08.2025 1:00:00
“የአፍሪካ አህጉር የበርካታ ሀገር በቀል የምግብ ስርዓቶች ባለቤት ናት። እነዚህ የምግብ ስርዓቶች በእምቅ እውቀት፣ በዘላቂና ዘመን ተሻጋሪ አውዶች የተሞሉ ናቸው'' ሲሉ ሼፍ ፋትማታ ቢንታ ተናግረዋል። 🎙 በዚህ የሶቨርኒቲ ሶርስስ ፕሮግራም አቅራቢው ስለአፍሪካ የምግብ ስርዓትና ሌሎች ተያያዥ ጉዳዮች ለመወያየት እንደ ሼፍ ቢንታ ያሉ ሙያተኞችን ጨምሮ በርካታ የዘርፉ ባለሙያዎችና የባህል መሪዎችን ጋብዟቸዋል።
የኒውክለር ኢነርጂ ትግበራ በጤናው ዘርፍ - የሮሳቶም አሻራ በኢትዮጵያ 30.07.2025 1:00:00
“ኢትዮጵያ ከሮሳቶም ጋር በመደራደር ለኢትዮጵያውያን ብቻ ሳይሆን፣ ለሌሎች ሀገራት ባለሙያዎች እና ተማሪዎች ክፍት የሚሆን፣ የኒውክሌር ማሠልጠኛ ማዕከል ወይም የነፃ ትምህርት ዕድል ፕሮግራም ማቋቋም ትችላለች'' ሲሉ በወልዲያ ዩኒቨርሲቲ የኒውክለር ፊዚክስ ተመራማሪው ቸሬ ሲሳይ ተናግረዋል። በዚህ የሶቨርኒቲ ሶርስስ ፕሮግራም አቅራቢው የኒውክለር ኢነርጂ ትግበራ በጤናው ዘርፍ እና ሌሎች ጉዳዮች ለመወያየት በወልድያ ዩኒቨርሲቲ የኒውክሌር ፊዚክስ ተመራማሪው ቸሬ ሲሳይ እና በመቀሌ ዩኒቨርስቲ የኒውክለር ህክምና ረዳት ፕሮፌሰር ዶ/ር ኩሩቤል ተስፋዬን ጋብዟቸዋል።
ገዳይ ግን ቀድመው የሚከላከሉት፦ የኢትዮጵያ ትግል ከጉበት በሽታ ጋር 28.07.2025 30:00
“ባለን መረጃ መሠረት የጉበት በሽታ ከባድ ችግር ነው። ምናልባት ተኝቶ ህክምና ከሚገቡት 12% የሚሆኑ ታካሚዎች ከጉበት በሽታ ቫይረስ ጋር የሚዛመዱ ሲሆን በሆስፒታል ውስጥ የሟቾችን መጠን በተመለከተ 30 ወይም 31% ሟቾች በቀጥታ ከጉበት በሽታ ቫይረስ ጋር የተገናኙ ናቸው።” በዚህ የሶቨርኒቲ ሶርስስ ፕሮግራም፣ አቅራቢው የዓለም የጉበት በሽታ ቀንን መሠረት በማድረግ በዓለም ላይ ገዳይ ከሆኑ ተላላፊ በሽታዎች አንዱ ስለሆነው የጉበት በሽታ እና ቫይረሱን ለማጥፋት ኢትዮጵያ እያደረገች ስላለችው ትግል ለመወያየት በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የጥቁር አንበሳ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የጨጓራ እና ሄፓቶሎጂስት ረዳት ፕሮፌሰር ዶ/ር ረዘነ በ...
የዲጂታል መር የጤና ሥርዓት ዐቢዮት በኢትዮጵያ! 24.07.2025 30:00
"ዲጂታል መፍትሄዎች የጤና አጠባበቅ ስርዓቱን ማሻሻል ብቻ ሳይሆን አገልግሎት የምንሰጥበትን መንገድ በአዲስ መልክ ፈጥረውታል። በዚህ ሂደት ውስጥ ዲጂታል አገልግሎቱ የጤና አሰጣጥ ስርዓትን የሚያሻሽልባቸው በርካታ ተግባራዊ መፍትሔዎቼ አሉት።" በዚህ የሶቨርኒቲ ሶርስስ ፖድካስት አቅራቢው ስለዲጂታል መር የጤና አልግሎት ስርዓትና የስታርታፖች ሚና በኢትዮጵያ ጉዳይ ለመነጋገር ጋይኒኮሎጂክ ኦንኮሎጂስት እና የዊኬር ኢንተገሬትድ የጤና ኔትወርክ መሥራችና ሥራ አስኪያጅ ዶ/ር ቤተል ደረጄን ጋብዟቸዋል።
የቴአትር ጥበብ፦ የኢትዮ-ሩሲያ የትስስር መልክ 22.07.2025 1:00:00
የባህል ገፆች፣ መንፈሳዊ፣ አካላዊ እና ቁሳዊ ባህሎችን መለዋወጥ መቻል ትልቅ ዕድል ነው። ይህም ጸሐፊያን በኢትዮጵያና ሩሲያ መካከል ያለ የቀደመ መስተጋብራዊ ልማትን በአንክሮ እንዲፈትሹ ያደርጋቸዋል።'' በዚህ Sovereignty Sources የሶቨርኒቲ ሶርስስ ፖድካስት፣ አቅራቢው ስለ ቴአትር ጥበብ፣ የኢትዮ - ሩሲያ ግንኙነትን ለማጠናከር ስላለው ፋይዳ ለመወያየት ጳውሎስ አዕምሮ (ዶ/ር)፣ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የቲያትሪካል ጥበባት እና የባህል ማዕከል አካዳሚክ ዲን ጋብዟቸዋል።
Similar podcasts
Replaio is not a podcast publisher; show names, artwork and audio belong to their authors and are distributed through public RSS feeds.