ዐቢይ ሀብታሙ
Sovereignty Sources
ዓለም በሉላዊነት ምክንያት ስትተሳሰር ፤ ፕሮግራሙም አፍሪካ ባላት እምቅ የተፈጥሮ ኃብት፣ በማደግ ላይ ባለው የሕዝብ ቁጥሯ ፣ በወጣት ኃይሏ እና በአህጉሪቱ ባሉ አዳዲስ ግኝቶችና የመፍትሄ ሃሳቦች ያላትን የመወዳደር አቅምና ጥቅም በሰፊው ይዳስሳል፡፡ እንኳን ወደ 'ሶቨርኒቲ ሶርስ' ፕሮግራም በደህና መጡ፣
Author
ዐቢይ ሀብታሙ
Category
Podcast website
Latest episode
Jul 11, 2026
Where to listen?
Podcasts in the app Replaio Radio Coming soonPodcasts are coming to the app soon. Install now and be the first to see a whole new take on podcasts
Episodes
የናኖ ቴክኖሎጂ ትሩፋት፡ ለንጹህ የኃይል ምንጭና ቀጠናዊ ትስስር 23.12.2025 1:00:00
''የፀሃይ ብርሃንን ተጠቅም የኃይል ምንጭን ለመፍጠር ናኖ ቴክኖሎጂ ጉልህ አስተዋፅዖ አለው። በተጨማሪም የካርበን ልቀትን ለመቆጣጠር የናኖ ቁሶች ጠቃሚ እንደመሆናቸው በሀገራችን ከዩኒቨርሲቲዎች ጋር በሚደረግ ትብብር በፕሮጀክት ጀረጃ እየተሰራበት ነው '' ሲሉ በባዮ እና ኢመርጂንግ ቴክኖሎጂ ተቋም የናኖ ቴክኖሎጂ ዘርፍ መሪ የሥራ ኃላፊ ወንድማገኝ ማሞ (ዶ/ር) ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል። ሶቨርኒቲ ሶርስስ በዛሬው መርሃ ግብሩ በክፍል አንድ የነገን ዋስትና ለማረጋገጥ፣ ቀጠናዊ ትብብርና ለማሳደግ የጋራ ችግሮችን ለመቅረፍ ንፁህ ኢነርጂ እና አካባቢን ከብክለት ለማንጻት ናኖ ቴክኖሎጂ ስላለው ፋይዳ የናኖ ቴክኖሎጂ ዘርፍ መሪ የሥ...
አፍሪካ፡ በባለ ብዙ ወገን ዓለም ውስጥ እያደገ ያለ አህጉር 23.12.2025 1:00:00
የአፍሪካ ሩሲያ ግንኙነት የእኩልነት መርህን መሰረት ያደርገ ነው '' ሉዓላዊ ትብብር የአፍሪካን ሉዓላዊነት እንደሚያመጣ ማየት ትችላላችሁ። ይህ የጌታና አሽከር ወይም የፈረስና ጋላቢ ግንኙነት አይደለም። የጋራ እሴቶች ባላቸው ህዝቦች መካከል ያለ ግንኙነት ነው። እነዚህ የጋራ እሴቶች ሉዓላዊ አፍሪካን ለመፍጠር እንዲሁም ሉዓላዊ የሩሲያ ፌዴሬሽንን ለማበረታታት የምንጠቀምባቸው ናቸው'' ሲሉ የዙምባቡዌ የውጭ ግንኙነትና ዓለምአቀፍ ንግድ ሚኒስትር ፕሮፌሰር አሞን ሙሩዊራ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል። ሶስት አንኳር ጉዳዮችን በምንዳስስበት የዛሬው ፕሮግራማችን በክፍል አንድ አፍሪካ በባለ ብዙ ወገን ዓለም ያላት ሚናን የሩሲያው ፕሬዝዳ...
የአፍሪካን ግብር ዘርፍ ፦ በቴክኖሎጂ የመደገፍ አንድምታዎቹ 18.12.2025 1:00:00
''በግብርናው ዘርፍ የበለጠ መሠራት ይኖርበታል። በዚህ ረገድ የገበሬውን ችግሮች ለመቅረፍ በጥናትና ምርምር እንዲሁም ቴክኖሎጂዎች የተደገፉ ተግባራት መሠራት አለባቸው። ለዚህ በጋራ መሥራት ይቻላል፣ ልምዶችንም ማደበር ያስፈልጋል — የአፍሪካ ሀገራት የእርስ በርስ አጋርነትና ሁለንተናዊ ትብብር መፍጠር ይኖርባቸዋል '' ሲሉ በጥናትና ምርምር ያሳለፉት፣ በሀገር ውስጥና ዓለም አቀፍ ተቋማት በሙያቸው ያለገለገሉት አቶ ወርቅነህ አበበ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል። ሁለት ጉዳዮችን በምንዳስስበት ፕሮግራማችን በመጀመሪያው ክፍል የአፍሪካ አህጉር የግብርና ዘርፍን በቴክኖሎጂ ሽግግር በመደገፍ ወደፊት ወደተሻለ ደረጃ ለማሸጋገር ሊደረጉ ስለ...
ከስትራተጂ እስከ ሉዓላዊነት የዘለቀው የአፍሪካ የሠው ሰራሽ አስተውህሎት ጉዞ 17.12.2025 1:00:00
''መሠረታዊው መልዕክት፣ የሠው ሠራሽ አስተውህሎት በአፍሪካ አህጉር ውስጥ በአፍሪካዊያን ለአፍሪካዊያን መገንባት ይኖርበታል የሚል መሆን አለበት — ለአካባቢያው ችግሮችም በሀገር በቀል እውቀቶች ነው መፍትሔ መሠጠት ያለበት። ስለዚህ ሉዓላዊነት የውይይቱ ማዕከላዊ ነጥብ ይሆናል ማለት ነው'' ሲሉ በኢመርጂንግ ኢንስቲትዩት የሠው ሠራሽ አስተውህሎት ባለሙያው ዮናስ ገብረሚካኤል ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል። በሁለት ዐበይት ሀሳቦች ዙሪያ በምንወያይበት የ ሶቨርኒቲ ሶርስስ ፕሮግራም፣ በመጀመሪያው ክፍል በአፍሪካ አህጉር ተስፋ ሰጪ ምልክቶችን እያሳየ የመጣው የሠው ሠራሽ አስተውሎት ዘርፍ የበለጠ እንዲጎለብት ደግሞ ከስትራቴጂ ወደ ሉዓላ...
የፀረ ቅኝ ግዛት ቀን፡ የከሰመው ግን መልኩን ለውጦ የመጣው ቅኝ ግዛት ሲገመገም 15.12.2025 1:00:00
''አፍሪካ ትናንት በቅኝ ግዛት የደረሰባት ነገር አይዘነጋም፣ ራስ ገዝ እና ሉዓላዊነት በሌለበት ነፃነት አይኖርም። በዚህም ሀገራት የራሳቸውን ነፃነት የማወጅ ሙሉ መብት አላቸው — የአፍሪካ ሆኑ ሌሎች ሀገራት ባለፉ ዘመናት በምዕራባውያን ከደረሰባቸው ተፅዕኖ አንፃር ወደፊት ሌሎች አማራጮችን በጂዮ ፖለቲካው ላይ መቃኘት ይኖርባቸዋል '' ሲሉ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካ ሳይንስና ዓለም አቀፍ ግንኙነቶች መምህሩ የእዮብዘር ዘውዴ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል። ሁለት አንኳር ጉዳዮችን በምንቃኝበት ፕሮግራማችን፣ በመጀመሪያው ክፍል ዓለም አቀፉ የፀረ ቅኝ ግዛት ቀንን መነሻ በማድረግ ዕለቱን ለውጥ ለማምጣትና መልኩን የቀየረውን...
ኢትዮጵያ በምሥራቅ አፍሪካ ቀጣና ቁልፍ የኃይል ቋት የመሆን ብርቱ ጥረቷ ሲቃኝ 12.12.2025 1:00:00
''የኃይል ዘርፍ ለአንድ ሀገር ዕድገት ምሰሶ የሚባል ነው — ከዚህ አኳያ እንደ ሀገር የራስን ፍላጎት ሸፍኖ ወደ ቀጠናው በመላክ የበለጠ የምጣኔ ሐብት ተፅዕኖን መፍጠር የሚያስችል እጅግ በጣም ወሳኝና ለዕድገት ዘለቄታዊነት ቁልፍ ስትራተጂ የሚባል ነው - ሲሉ በኮይሻ ሀይድሮ ፓወር የፕሮጀክቱ ምክትል ዳይሬክተር ኢንጂነር አባይነህ ጌትነት ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል።'' ሁለት አንኳር ጉዳዮችን በምንቃኝበት ፕሮግራማችን፣ በክፍል አንድ ኢትዮጵያ ከፍተኛ የኤሌክትሪክ ኃይልን በማምረት ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገ ከመጣው የኃይል ፍላጎት ባለፈ በምትገኝበት ቀጠና ቁልፍ የኃይል ቋት የመሆን ብርቱ ጥረቷን በተመለከተ በኮይሻ ሀይድሮ ፓወር...
ዓለም አቀፉ ወንጀለኞች ፍርድ ቤት፡ ለምዕራባዊያን የወገነው ማንነቱ ሲገለጥ 09.12.2025 1:00:00
''የዓለም አቀፉ ወንጀለኞች ፍርድ ቤት ገለልተኛ አይደለም። የፍርድ ቤቱ ፍልስፍናም ያለምንም ማቅማማት የአውሮፓውያን ነው — በተግባር ሲፈተሽ የምዕራቡን የህግ ፍልስፍልና ነው በሥራ ላይ የሚያውለው። የቅኝ ግዛት አሻራ፣ የምጣኔ ሐብት ብዝበዛ ያሉ ስር መሠረቶችን የሚዘነጋ ነው፣ በዚህ የተነሳ ፍትህን ማስፈን ተስኖታል'' - ሲሉ በወራቤ ዩኒቨርሲቲ የሶሺዮ አንትሮፖሎጂ መምህሩ መሃመድ አወል ሀጎስ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል። ሁለት ጉዳዮችን በምንቃኝበት ፕሮግራማችን የዓለም አቀፉ ወንጀለኞች ፍርድ ቤት ከአውሮፓዊ መሠረቱ ባሻገር በዓለም ላይ ለሚፈፀሙ ኢ - ፍትህና እና መድሎዎች መፍትሄ ለመስጠት እንዴት ዓለም አቀፍ ዕይታ የለው...
የውኃ ነገር፡ በቀጠናዊ አጋርነት እና ሁለንተናዊ አህጉር አቀፍ ትብብር ፍትሃዊ ክፍፍል የሚሻው ውዱ የተፈጥሮ ኃብት 04.12.2025 1:00:00
''ውኃ ጥቅም ብዙና ድንበር ተሻጋሪ የተፈጥሮ ኃብት እንደመሆኑ በዋነኝነት አንዳንድ ሀገራት ለግብርና ሲያውሎት፣ አንዳንዶቹ ለሥራ ፈጠራ ዕድል፣ ሌሎቹ ደግሞ ኃይል ለማመንጨት ይጠቀሙበታል — ሀገራት እርስ በርስ በትብብር መሥራት የሚችሉባቸው መሠረቶቹ ሲኖሩ ደግሞ ከውኃ የሚገኘውን ከፍተኛ ኃብት መቋደስ ይችላል፡፡'' ሲሉ በውኃና መሬት ኃብቶች ማዕከል ምክትል ዳይሬከተሩ ጠና አላምረው (ዶ/ር) ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል። ሁለት ጉዳዮችን በምንዳስስበት ፕሮግራማችን የመጀመሪያ ክፍል ፍትሃዊ የውኃ ኃብት ክፍፍል በሀገራት መካከል እንዲፈጠር ቀጠናዊ አጋርነቶች እንዲሁም ሁለንተናዊ አህጉር አቀፍ ትብብር መጠናከር በሚመለከት በውኃና...
ልፍ ኦፍ ጊኒ፡ የጂዮ - የፖለቲካ እና ደኅንነት ቁልፍ የትኩረት ቀጠና 02.12.2025 1:00:00
''በገልፍ ኦፍ ጊኒ የሚታቀፉ ሀገራት ብዛትና ያላቸው የጂዮ - ፖለቲካ ሁኔታና የውስጥ የፖለቲካ ስርዓተ መንግስቶቻቸውና ድንበራቸውን ያለፉ ጉዳዮችን ጭምር ሊዳኙና ሊተባበሩ በሚችሉባቸው ጉዳዮች ነው ወሳኝ ሆነው የሚታዩት [...] ሩሲያ እና ቻይና ተሰሚነታቸው እየጨመረ በመምጣቱ በአፍሪካ ብሎም በቀጠናው ከባህላዊው የምዕራባዊያን አካሄድ በተለየ አማራጭ የአጋርነት መንገድን ይከፍታል '' ሲሉ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካ ሳይንስና ዓለም አቀፍ ግንኙነቶች መምህሩ የእዮብዘር ዘውዴ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል።' ሁለት ጉዳዮችን በምንዳስስበት ፕሮግራማችን በመጀመሪያው ክፍል የገልፍ አፍ ጊኒ ጂዮ-ፖለቲካ እና በቀጠናው ያንዣበበ...
የአሜሪካ የጋዛ ዕቅድ፡ በረከት ወይስ ስውር ዓለማ? 26.11.2025 1:00:00
''ከጊዜ ወደ ጊዜ አሜሪካ ኃይሏ እየተሸረሸረ መምጣቱን በማሰብ 'አሜሪካ ድጋሚ ትልቅ እናደርጋለን' የሚል መርህ በመያዝ ነው ይሄንን አቋም እያሳዩ ያሉት - የዓለም አቀፍ አሰላለፍም ይሁን ይዘን የመጣናቸው ፖሊቲካዊም ይሁን ኢኮኖሚያዊ እሳቤዎች የአንድ ወገን ናቸው፣ ወደ አንድ ወገን ያጋደሉ ናቸው[....] '' ሲሉ በዋቻሞ ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካ ሳይንስና ዓለም አቀፍ ግንኙነቶች መምህሩ አበራ ሄቢሶ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል። ሁለት ጉዳዮችን በሚዳስሰው ፕሮግራማችን በመጀመሪያው ክፍል አሜሪካ በጋዛ ለመተግበር የነደፈችውን ዕቅድ፣ የፍልስጤማዊውያን ሉዓላዊነት፣ የራሷን ጥቅም የማስጠበቅ አካሄዷን እና ተያያዥ ጉዳዮችን በዋቻሞ ዩ...
የባዮ ኢኮኖሚ ለውጥ በአፍሪካ፡- ከአህጉሪቷ እስከ ብሪክስ ማዕቀፍ የተዘረጋው ትብብር 21.11.2025 1:00:00
'ኢትዮጵያ እንደ ሀገር ያሏት የኢንዱስትሪያል ፓርኮች ለሌሎቹ ሀገራት ምሳሌ መሆን የሚችሉ ናቸው — የብሪክስ ማዕቀፍ በአህጉሪቱ ያሉ ሀገራት በዘርፉ የላቀ ደረጃ እንዲደርሱ ትልቅ ዕድልን አመቻችቷል ። '' ሲሉ በባዮ ኢመርጂንግ ቴክኖሎጂ ተቋም የኢንዱስትሪያል ባዮ ቴክኖሎጂ ዳይሮክቶሬት ስር ተመራማሪና የቡድን መሪ ፍሬው ታፈሰ (ዶ/ር) ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል። ሁለት ጉዳዮችን በምንዳስስበት የሶቨርኒቲ ሶርስስ ፕሮግራም በክፍል አንድ የአፍሪካ ሀገራት በባዮ ኢኮኖሚ ዘርፍ እንዴት በብሪክስ ማዕቀፍ ስር ራሳቸውን ያሥተሳስሩ ስንል በባዮ ኢመርጂንግ ቴክኖሎጂ ተቋም የኢንዱስትሪያል ባዮ ቴክኖሎጂ ዳይሮክቶሬት ስር ተመራማሪና የቡድ...
ኢትዮጵያ '' የምስራቅ አፍሪካ ዓይን '' ፡ ቀጠናውን የማስተሳሰር እና የማስተባበር ሚናዋ ሲገለጥ 18.11.2025 1:00:00
''በምስራቅ አፍሪካ ቀጠና ያሉ ሀገራት የሚጋሯቸው በርካታ ጉዳዮቾ ያሏቸው ሲሆኑ እንደ ማኅበረሰባዊነት፣ ቀጠናዊነት፣ ቋንቋና ባህል ያሉት ተጠቃሾች ናቸው —ኢትዮጵያ በታሪክ በቀጠናው እንዲሁም ከዛም ባለፈ አዎንታዊ ሚናን በመጫወት የምትታወቅ ሀገር ናት ሲሉ '' የውጭ ጉዳዮች ኢንስቲትዩት ምክትል ዳይሬክተር አብዲ ዘነበ (ዶ/ር) ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል። አክለውም፡ ''በቀጠናው እየጎለበቱ ያሉ በርካታ ልማቶች ይገኛሉ። ቁልፍ የሚባል የለውጥ ሽግግርም እያደረገ ነው። እናም የውደፊቱ ብሩህ እንደሚሆን በእርግጠኝነት እናምናለን - ብለዋል'' ሁለት ርዕሰ ጉዳዮችን በምንዳስስበት የዛሬው ፕሮግራማችን በመጀመሪያው ክፍል በምስራቅ...
በሰብዓዊነት ሽፋን የሉዓላዊ ጣልቃ ገብነት የገጠማት ናይጄሪያ 13.11.2025 1:00:00
''ናይጄሪያ ከፍተኛ የነዳጅ ሀብት ያላት በምዕራብ አፍሪካ ትልቋ ሀገር ነች። የተባበሩት መንግስታት ድርጅት አንቀፅ 2 በተለይም ንዑስ አንቀፅ 4 የትኛውም ሀገር ሉዓላዊ እንደሆነ ነው የሚያስቀምጠው — ጣልቃ የሚገባባቸውን ሁኔታዎቸችንም በግልፅ ያስቀምጣል ሲሉ የፖለቲካ ሳይንስ እና ዓለም አቀፍ ግንኙነቶች ሌክቸረሩ አበራ ለሚ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል።'' አክለውም፡ ''አሁን በዓለም ፖለቲካ አማራጮች እየበዙ ነውና አፍሪካም ቆም ብላ እነዚያን የትብብር አማራጮች መመልከት ይኖርባታል '' ብለዋል። በዛሬው የሶቨርኒቲ ሶርስስ ፕሮግራም ሁለት ርዕሰ ጉዳዮችን እንዳስሳለን፡፡ በመጀመሪያው ክፍል አሜሪካ የምዕራብ አፍሪካዊቷ ሀገር ና...
ነገን አሻግሮ መመልከት፡ ኢመርጂንግ ሳይንስን ከፈጠራ ጋር የማዋሃድ ጥረት 10.11.2025 1:00:00
''ዓለም ውስጥ እንደመሆናችን ቴክኖሎጂ ተቀባይ ብቻ መሆን የለብንም፣ ቢያንስ ግንዛቤው ሊኖረን ይገባል። የምንቀበለው ምንድነው የሚለውንም ማወቅ ይገባል — ኢመርጂንግ ሳይንስ ለእያንዳንዱ ችግሮቻችን መፍትሔ የሚስጥ ስለሆነ ከዓለም ወደኋላ መቅረት የለብንም [...] ኢመርጂንግ ቴክኖሎጂ ሳይንስ ለምሳሌ ምርትና ምርታማነትን በመጨመር የግብርና ዘርፍን ሊያጎለብት ይችላል '' ሲሉ በባዮ እና ኢመርጂንግ ኢንስቲትዩት የኢመርጂንግ ማዕከል ውስጥ አስተባባሪና ተመራማሪው ዶ/ር ከበደ ጋሞ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል:: በፕሮግራሙ ክፍል አንድ በባዮ እና ኢመርጂንግ ኢንስቲትዩት በኢመርጂንግ ማዕከል ውስጥ አስተባባሪና ተመራማሪው ዶ/ር ከበደ...
በምዕራባዊያን የጦር መሣሪያ ሽያጭ የምትነደው ሱዳን 05.11.2025 1:00:00
አፍሪካ የጦር መሣሪያ አምራቾች ማራገፊያ፣ ክንደ ፈርጣማዎቹ ጡንቻቸውን የሚለካኩባት ቦታ እንዲሁም በዓለም አቀፍ የዲፕሎማሲያዊ መድረክ ንቁ ሚና ከመፍጠር ይልቅ ተቀባይ ሆናለች — ይህ ደግሞ ለሱዳንና መላ አፍሪካዊያን ወንድሞች አሰቃቂ ገጠመኝ ነው '' ሲሉ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካ ሳይንስና ዓለም አቀፍ ግንኙነቶች ሌክቸረሩ የእዮብዘር ዘውዴ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል። ሁለት ኃይላት የሚያደርጉት ደም አፋሳሽ ጦርነት ሱዳንን ከድጡ ወደማጡ ከቷታል። ጦርነቱ ሺዎችን ሲቀጥፍ ሚሊዮኖች ከቀያቸው አፈናቅሏል። የቀሩት ደግሞ ሱዳን የምድር ሲዖል ሆናባቸዋለች። በፕሮግራማችን የመጀመሪያ ክፍል ይህን ጉዳይ በሰፊው ለመዳሰስ በአ...
ከአድማስ ወዲህ፡ የሠው ሠራሽ አስተውህሎት ዐቢዮት በኢትዮጵያ 03.11.2025 1:00:00
''የሠው ሠራሽ አስተውሎት በመላው ዓለም ምጣኔ ሐብን እየለወጠ ይገኛል። በዚህ ረገድ ከሌላው ሀገር ወደኃላ መቅረት የለብንም — እንደሚታወቀው ሠው ሰራሽ አስተውሎት የዲጂታል ኢኮኖሚ ላይ ተፅዕኖ አለው። ስለዚህ እንደ አፍሪካ ኅብረት አባልነታችን በአህጉር ደረጃ በርካታ ሥራዎችን እየሰራን ነው ፡፡ '' ሲሉ በባዮ እና ኢመርጂንግ ቴክኖሎጂ ተቋም የኮምፒቲሽናል ሳይንስ እና የሠው ሠራሽ አስተውህሎት ዳይሬክተሩ ዮናስ ገ/ሚካኤል ድፈር ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል። ሶቨርኒቲ ሶርስስ በዛሬው መርሃ ግብሩ በክፍል አንድ የሠው ሰራሽ አስተውህሎት ቴክኖሎጂን ፈር ለማስያዝ እንዲሁም ፈጣራን ለማበረታታት ስለሚጫወተው ቁልፍ ሚና ለመወያየት በ...
አፈወርቅ ተክሌ ፡ የአፍሪካ ታሪክ ፣ ኃይል እና ኩራት ሰዓሊ 30.10.2025 1:00:00
''የሀገሩን ባህል፣ ታሪክና ልማድ ጠንቅቆ የሚያውቅ ታላቅ ሰዓሊ ነበር — ስብዕናውን ከኢትዮጵያ ጋር ከነበረው ቁርኝት ነጥሎ ማየት ከባድ ነው '' - ሲል በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ አለ ት/ቤት የፋይን አርትስና ዲዛይን መምህር በቀለ መኮንን ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግሯል። ሶቨርኒቲ ሶርስስ በዛሬው መርሃ ግብሩ በክፍል አንድ ፡ እጅግ የተከበሩ የዓለም ሎሬት ሜትር አርቲስት አፈወርቅ ተክሌ የተወለዱበትን ጥቅምት 12 , 1925 ዓ.ም መነሻ ያደርጋል ፤ ለዘመናት የተሻገረውን የኪነ ጥበብ አሻራቸውን ፣ ማንነትና አፍሪካዊ ትርክትን ለመወያየት በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ አለ ት/ቤት የፋይን አርትስና ዲዛይን መምህር በቀለ መኮንን በእ...
ኪን ኢትዮጵያ፡ ለዓለም የቀረበ የባህልና ጥበብ ትዕይንት 23.10.2025 59:59
ኪን-ኢትዮጵያ የጥበብና ባህል ጉዞ ኢትዮጵያን ለዓለም የማስተዋወቅ ዓላማ አድርጎ ብሪክስ አባል ሀገራት እያቀረበ ነው፣ በቻይና እና ሩሲያ ስራዉን ያቀረበው ቡድኑ፣ በቅርቡም ወደ ብራዚል ያቀናል ፡፡ ''ኪን - ኢትዮጵያ ትልቅ የባህል፣ የጥበብ እና የዲፕሎማሲ፣ የብዙ የኪነጥብ ባለሙያዎች ስብስብ ነው። ኅብረትን መሠረት ያደረገ ሥራ በመሥራታችን ውጤቱ እጅግ የሚደነቅ ነው[...] ብሪክስ የዓለምን ሚዛንን ለማስተካከል የተፈጠረ አቅም ስለሆነ አባል መሆናችን በብዙ ይጠቅመናል።'' ሲል የኪን ኢትዮጵያ ቡድን መሪ፣ አሰልጣኝና ድምፃዊ ወንድዬ አበበ (ወንድዬ ኮንታ) ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግሯል ። ሶቨርኒቲ ሶርስስ በዛሬው መርሃ ግብሩ...
የዕድል በሮችን መክፈት፡ የአፍሪካ የምጣኔ ሐብት ሉዓላዊነት 20.10.2025 59:59
''አፍሪካ የተለያዩ የተፈጥሮ ኃብት አላት። ይህ ደግሞ ለኢንዱስትሪያላይዜሽን ሂደት ትልቅ አስተዋፅዖ ቢኖረውም ቅኝ ግዛት የምጣኔ ሀብት እድገት ላይ ትልቅ ተፅዕኖ ፈጥሮ አልፏል። ይህ ደግሞ እንደ ትልቅ ጫና የሚቆጠር ነው።'' ሲሉ በአምቦ ዩኒቨርሲቲ የዴቨሎፕመንታል ስተዲስ መምህሩ ፍራፊስ ሀይሉ(ዶ/ር) ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል። ሶቨርኒቲ ሶርስስ በዛሬው ሁለት ጉዳዮችን በሚዳስስበት መርሃ ግብሩ በክፍል አንድ አፍሪካ በኢንዱስትሪ ራሷን ስለመቻል እና የምጣኔ ሀብት ሉዓላዊነትን ስለሚፈጠርበት ጉዳይ በአምቦ ዩኒቨርሲቲ የዴቨሎፕመንት ስተዲስ መምህሩ ፍራፊስ ሀይሉ (ዶ/ር) አነጋግሯቸዋል። በክፍል ሁለት ከምዕራባዊያን እርዳታ ተ...
ከስደት ወደ ተጽዕኖ ፈጣሪነት፡ የአፍሪካ ዲያስፖራዎች ለአፍሪካ ሉዓላዊነት 14.10.2025 1:00:00
በቅኝ ግዛት ዘመን አፍሪካ ነፃ እንድትወጣ የአፍሪካ ዲያስፖራዎች ትልቅ ሚና ተጫውተዋል — የአፍሪካ ሀገራት እርስ በርስ መተሳሰርና ውስጣቸውን ማጠናከር አለባቸው '' ሲሉ በወለጋ ዩኒቨርስቲ የፖለቲካ ሳይንስና ዓለም አቀፍ ግንኙነቶች ምሁሩ ጉተማ ዳንኤል (ዶ/ር) ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል። ሶቨርኒቲ ሶርስስ በዛሬው መርሃ ግብሩ በክፍል አንድ የአፍሪካ ዲያስፖራዎች በመላው ዓለም ቁልፍ ሚና በተመለከተ በወለጋ ዩኒቨርስቲ የፖለቲካ ሳይንስና ዓለም አቀፍ ግንኙነቶች ምሁሩ ጉተማ ዳንኤል (ዶ/ር) አነጋግሯቸዋል። ከምዕራባዊያን እርዳታ ተላቅቆ የውስጥ አቅምን ለማጎልበትና ከድህነት ለመውጣት የሚደረግ ትግልን በተመለከተ በክፍል ሁለ...
የኢትዮጵያ የህክምና ቁሳቁሶችን የማምረት ጅምር ፡ ለህክምና ሉዓላዊነት 10.10.2025 1:00:00
ከሩሲያ ኩባንያዎች ጋር በቅርበት እየሰራን እንገኛለን። በአሁኑ ሰዓት ከአራቱ ድርጅቶች ጋር ስምምነት ተፈራርመናል። — ገበያው የሚሆነው ኢትዮጵያ ላይ ብቻ ሳይሆን በመላ አፍሪካም ጭምር ይሆናል - ሲሉ የቅጥራን ማኒፋክቸሪኒንግ የሜዲካል ኢኪዩፕመንት ትሬዲንግ ባለቤትና ምክትል ስራ አስኪያጅ ተሾመ በየነ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል'' በዛሬው የሶቨርኒቲ ሶርስ ፕሮግራም አቅራቢው የሜዲካል ሉዓላዊነት፣ የጤና ዘርፍ ትራንስፎርሜሽን እና አህጉራዊ ተፅዕኖ ጉዳይ ላይ ለመወያየት የቅጥራን ማኒፋክቸሪኒንግ የሜዲካል ኢኪዩፕመንት ትሬዲንግ ባለቤትና ምክትል ስራ አስኪያጅ ተሾመ በየነ ጋብዟቸዋል። በአዲስ አበባ ከተማ የሚስተዋለውን የተሽከርካ...
ብሪክስ ፡ የደቡባዊ ዓለም ሉዓላዊነት መገለጫ 09.10.2025 1:00:00
'' ብሪክስ ከፈጠራቸው መልካም ነገሮች መካከል አዲሱን የልማት ባንክ መፍጠሩ ነው። በርግጥ ከፋይናንስ ተቋማትም በላይ ነው — ብሪክስ የደቡባዊ ዓለም አቅም በሚገባ ያሳያል። '' ሲል አንትሮፖሎጂስት የታሪክ ተመራማሪ መሀመድ አወል ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግሯል። በዛሬው የሶቨርኒቲ ሶርስስ ፕሮግራም አቅራቢው አድማሱን እያሰፋ ያለውን ብሪክስ በተመለከተ በሁለት የተለያዩ ዕይታዎች ከአንትሮፖሎጂስቱ መሃመድ አወልና የኢ - ኮሜርስ ኤሌክትሮኒክ ግብይት ባለሙያው ማርቆስ ጥላሁን ጋር በጥልቀት ተወያይቷል። በዚሁ መሰናዶ በአዲስ አበባ የተከናወነው የ11ኛው የአፍሪካ ቲንክ ታንክ ጉባኤም በፕሮግሳሙ የተካተተ ሌላኛው ጉዳይ ነው። ሙሉ መረጃው...
አፍሪካ በቴክኖሎጂ ጎዳና፡ የሠው ሠራሽ አስተውህሎት ሚና 06.10.2025 1:00:00
''በአፍሪካ እንደ አህጉር ቴክኖሎጂን በማስፋፋት ረገድ የሚታዩ አንዳንድ ለውጦች አሉ። እነዚህም ጥሩ የሚባሉ ለውጦች ናቸው። - ሲል የሶፍትዌር ኢንጂነርና የአርቴፊሺያል ኢንተለጀንስ ባለሙያ ልንገረው ጌቴ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግሯል። በሁለት ክፍል በተሰናዳው በዚህ የሶቨርኒቲ ሶርስ ፕሮግራም አቅራቢው በሰው ሰራሽ አስተውህሎት ማዕቀፍ ስር በአፍሪካ የቴክኖሎጂ ኮሚኒኬሽን ምን ይመስላል የሚለውን ጉዳይ የሶፍትዌር ኢንጂነርና የአርቴፊሺያል ኢንተለጀንስ ባለሙያ ልንገረው ጌቴን እንዲሁም ሴቶች በከተማ ግብርና ያላቸው ጉልህ አስተዋፅዖ በሰፊው ተመልክተናል ። ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ፕሮግራሙን ያዳምጡ:
ኒውክሌርን ለህክምና እና ለአማራጭ ኃይል በኢትዮጵያ ፣ የሮሳቶም የትብብር ሚና 03.10.2025 1:00:00
'' የኒውክሌር ኃይል ወይም ህክምናን የመገንባት ህልም ላለን ለእኛ የመጀመሪያው ነገር መሆን ያለበት እንደ ሮዛቶም ካሉ ዓለም አቀፍ ተቋማት ጋር መተባበር ነው።'' ሲሉ የኒውክሌር ህክምና ስፔሻሊስት ዶ/ር ኪሩቤል ተስፋዬ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል፡፡ የኒውክሌር ህክምና ስፔሻሊስት ዶ/ር ታከለ ሎዳሞ በበኩላቸው ፡ ''ሮሳቶም ብዙ ሪአክተሮችን [ማብላያዎችን] የገነባ የዳበረ ልምድ ያለው ተቋም ነው።" የዛሬው የሶቨርኒቲ ሶርስስ ዝግጅት የኒውክሌር ህክምና በኢትዮጵያ እና ለሠላማዊ ዓላማ የሚውል ኒውክሌር ኃይል የመገንባት ህልም እንዲሁም ዓለም አቀፍ ትብብርን በተመለከተ የኒውክሌር ህክምና ስፔሻሊስቶቹ ዶ/ር ኪሩቤል ተስፋዬ እና...
ሰርጌ ላቭሮቭ በተመድ ጠቅላላ ጉባዔ፡ የአፍሪካ ፣ እስያ እና የካሪቢያን ሀገራት ድምጽ ሊደመጥ ይገባዋል 30.09.2025 1:00:00
''ሰርጌይ ላቭሮቭ አፍሪካና ካሪቢያን ሀገራትን በተመለከተ ያነሷቸው ነጥቦች ሁነኛ ማንቂያ ናቸው።" - ሲነሳ ደምሴ ''የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ብቻ ሳይሆን ሌሎች ዓለም አቀፍ የፋይናንስ ተቋማትም እንደ አዲስ መታደስ አለባቸው።" - ዶ/ር ሰዒድ አህመድ የዛሬው የሶቨርኒቲ ሶርስስ ዝግጅት በተባበሩት መንግስታት ጉባዔ ላይ የሩሲያው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌይ ላቭሮቭ ያነሷቸውን ቁልፍ ነጥቦች በተመለከተ የፖለቲካ ሳይንስና ዓለም አቀፍ ግንኙነቶች ባለሙያዎች ዶ/ር ሰዒድ አህመድ እና ሲነሳ ደምሴን ጋብዟቸዋል። በእንግሊዘኛ የቀረበውን ሙሉ ፕሮግራም ያዳምጡ:
Similar podcasts
Replaio is not a podcast publisher; show names, artwork and audio belong to their authors and are distributed through public RSS feeds.