ዐቢይ ሀብታሙ

Sovereignty Sources

Society EN ↓ 119 episodes

ዓለም በሉላዊነት ምክንያት ስትተሳሰር ፤ ፕሮግራሙም አፍሪካ ባላት እምቅ የተፈጥሮ ኃብት፣ በማደግ ላይ ባለው የሕዝብ ቁጥሯ ፣ በወጣት ኃይሏ እና በአህጉሪቱ ባሉ አዳዲስ ግኝቶችና የመፍትሄ ሃሳቦች  ያላትን የመወዳደር አቅምና ጥቅም በሰፊው ይዳስሳል፡፡ እንኳን ወደ 'ሶቨርኒቲ ሶርስ' ፕሮግራም በደህና መጡ፣

Author

ዐቢይ ሀብታሙ

Category

Society

Latest episode

Jul 11, 2026

Where to listen?

Podcasts in the app Replaio Radio Coming soon

Podcasts are coming to the app soon. Install now and be the first to see a whole new take on podcasts

Get it on Google Play Install for free Android 5M+ downloads · 4.8 rating iOS soon

Episodes

ሂፕ -ሆፕ (Hip hop) በሀገርኛ፡- የራስ ማንነትን በመገንባት ከውጭ ተፅዕኖ መላቀቅ 26.02.2026

''የራሳችን ማንነትና መገለጫ ያለው ሙዚቃ ነው የሚያስፈልገን። ለዚህ ደግሞ አስገራሚ ሀገር በቀል እውቀት፣ ባህልና ጥበብ ያላቸው ሰዎች አሉ። በውጩ ዓለም እየተሳደቡ የራፕ ሙዚቃ የሚዘፍኑ አሉ፣ ስለዚህ እኛ እርሱን በፍፁም አናበረታታም — ጋሽ ሙላቱ አስታጥቄ ኢትዮ ጃዝን እንደፈጠረ ሁሉ፣ እኛም ኢትዮጵያዊ ቀለም ያለው የጥቁር ምት (Black Note) መፍጠር ነው ዓላማችን። አሁን ላይ ሙዚቃዎችን ስንሰራ ጥንታዊ መሠረቶች የሆኑት ቀርቶ፣ ፉከራና ሽለላን ለማካተት እንሞክራለን'' ሲሉ የሙዚቃ አቀናባሪዉ እና ፕሮዲውሰሩ ሁንአንተ ሙሉ (ሁኔ) ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል። ሁለት ጉዳዮችን በምንወያይበት ፕሮግራማችን በክፍል አንድ የ...

ከሩሲያ ለአፍሪካ ወጣቶች የተመቻቸ የትምህርት ዕድል 20.02.2026

''ከሩሲያ የነፃ የትምህረት ዕድል ማግኘቴ እንደ አፍሪካዊ ብሎም ኢትዮጵያዊ ሴት እጅግ የሚያኮራኝ ነው። ሁላችንም ለማግኘት የምንመኘው ዕድል ነው። ሩሲያ በማደግ ላይ ካሉ ሀገራት ተማሪዎችን እየመረጠች ዕድል መሥጠቷ፣ የትምህርት ሥርዓት ላይና አዕምሮ ላይ መሥራቷ በጣም ትልቅና ወሳኝ ነገር ነው።'' ስትል በሩሲያ የከፍተኛ ትምህረት ነፃ ዕድል ተጠቃሚዋ ምህረት በፍቃዱ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግራለች። ሁለት አንኳር ጉዳዮችን በምንዳሥሥበት ፕሮግራማችን በክፍል አንድ ትምህርት በህብረተሰብ ዘንድ የሚያሳድረውን ማኅበራዊ ተፅዕኖ መሠረት አድርገን የቤተሰብ ደረጃን ለማሻሻል የማኅብረሰብ ልማትንም ለማጎልበት ሴቶችን ማስተማር ስለሚያበረክተ...

የ39ኛው የአፍሪካ ኅብረት ጉባዔ አንድምታዎች 16.02.2026

''አፍሪካ ቀጣይዋ የልማት፣ ሽግግር እና የኢንዱስትሪ ዘርፍ መሻሻል የፍልሚያ ሥፍራ ናት። አህጉሪቱ ይህን ህልም ለማሳካት በምን ዓይነት መልኩ ቢሆን የተፈጥሮ ኃብቶች ያስፈልጓታል'' ሲሉ የኡጋንዳ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሄነሪ ኦሪየም ኦኬሎ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል። ሦስት አንኳር ጉዳዮችን በምንዳስስበት የዛሬው ፕሮግራማችን በክፍል አንድ የ39ኛው የአፍሪካ ኅብረት ጉባዔን መሠረት አድርገን ቁልፍ የትኩረት አቅጣጫዎችን በተመለከተ ከውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች፣ ከኡጋንዳው ሄነሪ ኦሪየም ኦኬሎ፣ ከሪፐብሊክ ኦፍ ጊኒው ሞሪሳንዳ ኩያቴ እና ከቱኒዚያው ሞሃመድ አሊ ናፍ ቲ ጋር ተወያይተናል። በክፍል ሁለት የኢንዱስትሪ ዘርፍ ማቀላጠፍ እን...

አማራጭ የክፍያ ስርዓት ፣ የፋይናንስ ሉዓላዊነት የእዳ ጫና እፎይታ ለአፍሪካ፡- አፍሪካ ህብረት ጉባኤ 2026 13.02.2026

''አፍሪካ በፋይናንስ ስርዓቶችና ምህንድስና ረገድ በታሪክ ኢፍትሃዊነትን እየተጋፈጠች ነው። ከምዕራባዊያን ሀገራት ጋር ሲነፃፀሩ የአፍሪካ ሀገራት ከዓለም አቀፍ የፋይናንስ ተቋማቶች እየተበደሩ ያሉት በከፍተኛ መጠን ነው'' ሲሉ የሌሴቶ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሌጆኒ ምፖትጁዋና ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል። 48ኛው የአፍሪካ ኅብረት የሥራ አስፈጻሚ ምክር ቤት መደበኛ ስብሰባ እ.ኤ.አ ከየካቲት 11 እስከ 12 በአፍሪካ ኅብረት ዋና መሥሪያ ቤት ተደርጓል።  የአፍሪካ አገራት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች በ39ኛው የአፍሪካ ኅብረት የመሪዎች ጉባዔ የሚቀርቡ አጀንዳዎች ላይ አእና ሌሎች ጉዳዪች ላይ እንደመወያየቱ ፣ በክፍል አንድ የሌሴቶ የው...

የብሪክስ መሥፋፋት ሚዛናዊ ዓለምን እንዴት ይፈጥራል ? 12.02.2026

''ስትራተጂካዊ ጠቀሜታ ያለው ብሪክስ አሁን ላይ ያቀፋቸው አባል ሀገራት ውስን ቢሆኑም ቁጥራቸው የበለጠ እየጨመረ ሲመጣ የዓለም ፖለቲካ ሚዛንን ለማስጠበቅ አቅሙን ያሳድጋል —ቡድኑ አማራጭ የፋይናንስ ልማትን ይፈጥራል። በዚህ ረገድ አዲሱ የልማት ባንክን ማንሳት ይቻላል'' ሲሉ ታምራት ተስፋዬ፣ የዓለም ወጣቶች ኮንፍረንስ አምባሳደር እንዲሁም በኢትዮጵያ የብሪክስ ተማሪዎች ምክር ቤት ፕሬዝዳንትና በሩሲያ የሩድን ዩኒቨርሲቲ የሁለተኛ ድግሪ የኢኮሎጂ ተማሪ ለስፑትኒክ አፍራካ ተናግረዋል። በክፍል አንድ የብሪክስ መሥፋፋት መሠረት አድርገን አዳዲስ አባላት ለዓለም ኃይል ሚዛን መጠበቅ ያላቸውን ሚና ከታምራት ተስፋዬ፣ የዓለም ወጣቶች ኮን...

የአፈር ብዝሃ ህይወት፡ ከእግራችን ሥር የሚገኘው ውዱ የተፈጥሮ ኃብት ከምግብ ዋስትና አኳያ ሲቃኝ 10.02.2026

''አፈር ውዱ የተፈጥሮ ኃብት ነው። ህይወትም በምድራችን ላይ እንዲቀጥል የሚያደርግ ነው። በዚህም አፈር ሲታመም ሊታከም ይገባል። እንደ ሀገር ለኢትዮጵያ የሚያስፈልገን በየጊዜው ምርምርና ክትትል በማድረግ የአፈር ብዝሃ ህይወት ለምግብ ዋስትና ጥረት የሚያበረክተውን አስተዋፅዖ ከፍ ማድረግ ያስፈልጋል'' ሲሉ በወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ የአፈር ሳይንስ እና ኦርጋኒክ ኬሚስትሪ ተባባሪ ፕሮፌሰሩ አለሙ ሌላጎ (ዶ/ር) ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል። ሁለት ጉዳዮችን በምንዳስስበት የዛሬው ፕሮግራማችን በክፍል አንድ ስለአፈር ብዝሃ ህይወት (Soil Biodiversity) እንዲሁም የምግብ ዋስትና ማረጋገጥ ጋር በማዛመድ  በወላይታ ሶዶ ዩኒቨ...

'' አታላዩ አርቲስት ቮሎድሚር ዜለንስኪ ''፡- ከህዝቡ ህልውና ይልቅ ስልጣኑን የሙጥኝ ያለው ''ተዋናይ'' 06.02.2026

የፕሬዝዳንታዊ ስየፕሬዝዳንታዊ ስልጣኑ በግንቦት 2024 የተጠናቀቀው ቮሎድሚር ዜለንስኪ፡ ከህዝቡ ይልቅ ስልጣኑን ማስጠበቅን ይመጣል የሚሉ አንቂ ድምፆች መደመጥ ጀምረዋል። ለመሆኑ ስለዜለንስኪ የዘርፉ ተንታኞች ምን ይላሉ? ''በዩክሬን በስልጣን ላይ ያሉት ሰው የዓለም አቀፍ ፖለቲካ ግንዛቤያቸው ዝቅተኛ ነው። ስልጣናቸውን አራዝመዋል፤ እናም የዩክሬን ብሄራዊ አንድነት፣ ሉዓላዊነት፣ ጠንካራ ቁርኝት እንዲሁም በቀጠናው ሰላምና ደኅንነትን የሚጠብቁ ናቸው ብዬ አላምንም። የፖለቲካ ሳይንስ ለግለሰቦች ከሚሰጠው ብያኔ አንጻር [...] ይህ ሰው አሁንም እያታለለ ገንዘብ እንደሚቀበል አርቲስት ሆኖ ነው የምናገኘው። '' ሲሉ በአዲስ አበባ ዩ...

የአፍሪካ ከተሞች አዳዲስ ገፅታዎች 05.02.2026

''የአፍሪካን የወደፊት ራዕይ አሻግረን ስንመለከት፣ ያልተበረዘና ሀገር በቀል እውቀትም የተካተተበት አስተሳሰብ ሊኖረን ይገባል - አንዳንድ የአፍሪካ ሀገራት አዲስ አበባን ጨምሮ በመሠረተ ልማት ግንባታዎችና ራሳቸውን ዲጂቲላይዝድ በማድረግ ሂደት በምርጥነት የሚጠቀሱ ናቸው'' ሲሉ የምህንድስና ባለሙያው ምንተስኖት ታምሩ ለስፑትኒክ አፍሪካ ገልፀዋል። ሦስት ጉዳዮችን በምንቃኝበት የዛሬው ፕሮግራማችን በክፍል አንድ የአፍሪካ ከተሞች በመሠረተ ልማቶች ዲጂታላይዝ በማድረግ አዳዲስ ገፅታዎች እንዲይዙ የሚደረገውን ጥረት ከምህንድስና ባለሙያው ምንተስኖት ታምሩ ጋር ቃኝተነዋል። በክፍል ሁለት በኮንስትራክሽን ዘርፍ ህንድ ከአፍሪካ ጋር ያላትን...

የአፍሪካ ፀሃይን እንደአማራጭ የኃይል ምንጭ የመጠቀም ጅምሮች 03.02.2026

''ሞሮኮ በፀሃይ ኃይል ዘርፍ በአፍሪካ የምትመራ ሀገር ናት። በዚህ ረገድ ኢትዮጵያ በንፅፅር ወደኃላ ካሉ ሀገራት መካከል ነው የምትመደበው። ይሁንና ከሶላር ፓነል ኃይል ለመጨመር አበረታች እቅዶች አሉ። ለምሳሌ የመተሃራ ፓነል ፕሮጀክት አለ፣ ወደ 500 ሜጋ ዋት እንዲያመነጩ የታቀዱ ከ8 በላይ ፕሮጀክቶች አሉ'' ሲሉ ንዋይመድህን አበራ (ዶ/ር)፣ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የፊዚክስ ተባባሪ ፕሮፌሰር ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል።  ሁለት ጉዳዮችን በምንዳስስበት ፕሮግራማችን በክፍል አንድ የኃይል አቅም መጠንን ለማስፋፋት የፀሃይ ኃይልን እንደ አማራጭ ምንጭ መጠቀምን ጉዳይ ከንዋይመድህን አበራ (ዶ/ር) በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የ...

የሴቶች አስተዋፅዖ በኢትዮጽያ የከተማ ግብርና ዘርፍ 03.02.2026

''ከሌማት ትሩፋት ጋር በተያያዘ ባለሃብቶች እንዲደግፉ በማድረግ ሴቶችን ተጠቃሚ እንዲሆኑ ለማስቻል ምንም የሌላት እናት ቢያንስ 5 ዶሮዎች ከነቤታቸው ይሰጣታል፤ ከዛ በመነሳት በመቶዎችና ሺዎች ደረጃ የደረሱ አሉ '' ሲሉ በአዲስ አበባ የከተማ ግብርናና አርሶ አደር ኮሚሽን ባለሙያ በለጠች ተሠማ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል። ሁለት ጉዳዮችን በምንቃኝበት በዛሬው ፕሮግራማችን በክፍል አንድ በሰው ሰራሽ አስተውህሎት ማዕቀፍ ስር በአፍሪካ አህጉር የቴክኖሎጂካል ኮሚኒኬሽን ምን ይመሥላል በሚለው ጉዳይ የሰው ሰራሽ አስተውህሎት ባለሙያው ልንገረው ጌቴ ጋር ተወያይተናል።  በሁለተኛው ክፍል ደግሞ ሴቶች በከተማ ግብርና ዘርፍ ያላቸውን ጉ...

የውኃ ቴክኖሎጂ ትብብር ለጠንካራ ቀጠናዊ ልማት 02.02.2026

''ሀገራት ውኃን በተመለከተ የጋራ ፕሮጀክቶች ሊኖራቸው ይገባል፤ አንድ ሀገር ለሚያለማው ፕሮጀክት ሌሎቹ ትብብር መፍጠር ይኖርባቸዋል። ፕሮጀክቶች ወንድማማችነትና ጠንካራ የትብብር መንፈስ ሊፈጥሩ ይገባል። በዚህ ረገድ ተቋማትን ማሻሻልና የመረጃ አያያዛቸውን ማጠናከር ያስፈልጋል —ውኃን መሠረት ያደረጉ ኢንቨስትመንቶችን ከተመለከትን የመሠረተ ልማት ግንባታዎች ትልቁን ቦታ ይይዛሉ - ሲሉ በአርባምንጭ ዩኒቨርስቲ የውሃ ቴክኖሎጂ ሳይንቲፊክ ዳይሬክተር ዶ/ር ኢንጂነር ታምሩ ተሠማ ለስፑትኒክ አፍሪካ ገልፀዋል።'' ሁለት ጉዳዮችን በምንዳስስበት ፕሮግራማችን በክፍል አንድ በቀጠናዊ አጋርነቶቾ የውኃ ቴክኖሎጂ ፕሮጀክቶችን መደገፍ ስለሚቻልባ...

የአሜሪካ በመካከለኛው ምሥራቅ ወታደራዊ ተሳትፎ ትናንትና ዛሬ ሲቃኝ 30.01.2026

''የአሜሪካ ዓላማ ቀጠናው እንዳይረጋጋ በማድረግ ፍላጎታቸውን ማሳካት ነው። ኢራቅን ለአብነት ብንወስድ፣ አውዳሚ የጦር መሣሪያ አለ በሚል ሽፋን ጥንታዊ ስልጣኔ ባለቤት ሀገርን ያለምንም ማስረጃ በሴራ ንድፈ ሀሳብ አውድመዋል። በዚህም በራሷ የሚደገፉ የሽብር ኃይላትም ተፈልፍለዋል'' ሲሉ በአፍሪካ ቀንድና መካከለኛው ምሥራቅ ጂዮፖለቲካ ተንታኙ መሃመድ ንጉስ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል። በዛሬው የሶቨርኒቲ ሶርስስ ፕሮግራማችን በክፍል አንድ አሜሪካ በተለያዪ ጊዜያት በመካከለኛው ምሥራቅ ባደረጋቻቸው ወታደራዊ ጣልቃ ገብነቶች ምክንያት የተፈጠሩ ቀውሶች በተመለከተ  ከ  ጂዮግራፈር፣ ካርቶግራፈር እንዲሁም በአፍሪካ ቀንድና መካከለኛው...

የብሪክስ አዲስ ልማት ባንክ ከአፍሪካ ንግድና ምጣኔ ሐብት አኳያ ሲቃኝ 28.01.2026

''ብሪክስ እንደ አላማ አድርጎ ከተነሳው መካከል የፋይናንስ፣ ኢኮኖሚ፣ ንግድ፣ የመሠረተ ልማት ዝርጋታ፣ ንፁህ የአየር ከባቢ መፍጠርና የዲጂታል ሥራዎች ማስፋፋት ይገኙበታል። እኛ አፍሪካዊያን ነገሮችን በብስለት መምራትና መጠቀም ከቻልን ከብሪክስ የልማት ባንክ ብዙ መጠቀም እንችላለን። የልማት ባንኩ ከቀደመው የምዕራባዊያን የኢኮኖሚ ጫናም እንድወጣም የሚያስችል ነው '' ሲሉ አሉላ ተክለብርሃን አዲሱ፣ የምጣኔ ሀብትና ተያያዥ ጉዳዮች ባለሙያ እንዲሁም በሩሲያ፣ ቅዱስ ፒተርስበርግ ፖሊቴክኒክ ዩኒቨርሲቲ በኢኮኖሚክስ የትምህርት ክፍል እጩ ዶ/ር ለስፑትኒክ አፍሪካ አስረድተዋል። ሁለት አንኳር ጉዳዮችን በምንቃኝበት ፕሮግራማችን በክፍል...

የመንግሥት እና የግል ዘርፍ አጋርነት ለተቀላጠፈ የንፁህ ኃይል መሥፋፋት 23.01.2026

''የንፁህ ኢነርጂ ልማት ጉዳዮች ያለ ግል ዘርፉ ተሳትፎ እውን ሊሆኑ አይችሉም። ስለዚህ የመንግስትና የግል ዘርፍ አጋርነት እጅግ ጠቃሚ ነው ብዬ አስባለሁ — መንግስታት፣ የግል ዘርፎች እንደ ቴክኖሎጂና ልማት ሥራዎች ላይ መዋዕለ ንዋያቸውን እንዲያውሉ ማነቃቃት ይኖርባቸዋል።'' ሲሉ ቤካ መገርሳ፣ የዘርፉ አማካሪ እና በፕላንና ልማት ሚኒስቴር የቀድሞ ቴክኒካል አማካሪ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል። ሁለት ጉዳዮች ለውይይት በሚቀርቡበት የዛሬው የሶቨርኒቲ ሶርስሰ ፕሮግራማችን፣ በክፍል አንድ የመንግስትና የግል አጋርነት የተቀላጠፈ የንፁህ ኃይል መስፋፋት እንዲፈጠር የሚያበረክተውን አስተዋፅዖ በተመለከተ ከቤካ መገርሳ፣ የዘርፉ አማካ...

የወንዝ ዳርቻ ልማት አዲሱ የከተማ ገፅታ በኢትዮጵያ 21.01.2026

''የአዲስ አበባ የወንዝ ዳርቻ ልማት ፕሮጀክት ከተማን በማሳደግ ረገድ ከፍተኛ ሚና ይጫወታል። በሁሉም ከተሞች ውስጥ ቢበረታታ መልካም ነው እላለሁ -  ሲሉ ሺቲ ጋተው(ዶ/ር) ፣ የብዝሃ ህይወት ምርምርና ጥበቃ ማዕከል ዳይሬክተር ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል።'' ሁለት ጉዳዮችን በምንዳስስበት ፕሮግራማችን በክፍል አንድ የግብርና እሴት ሰንሰለት፣ ክምችት እና የድህረ ክምችት ብክነት ቅነሳን በተመለከተ ከእንግዳችን  አዲሱ ፍቃዱ (ዶ/ር)፣ በአርባምንጭ ዩኒቨርሲቲ የምግብ ቴክኖሎጂ ተባባሪ ፕሮፌሰር ጋር ሠፋ ባለ መልኩ እንዳስሳለን።   በሁለተኛው ክፍል የከተሞች ወንዝ ዳርቻ ልማት እና የከተሜነት መነቃቃትን መሠረት ያደረገ ውይይት...

የማዕድን ሀብቶችን በአፍሪካ:- የኢኮኖሚ ዕድገት መሠረት የማድረግ እንቅስቃሴ 20.01.2026

''ወርቅ በአሁኑ ሰዓት ለምጣኔ ሀብት ዕድገት ቀዳሚ ቦታ የሚሠጠው የማዕድን ዓይነት — አንድ ሀገር ብቻዋን ማደግ አትችልም። ቢያንስ የቴክኖሎጂ ሽግግር መውሰድ ይኖርባታል። በዚህም ከአደጉ ሀገራት ጋር ትብብር መፍጠር የሚጠበቅ ነው። በዚህ ረገድ ከራሺያ ጋር ያለን ግንኙነት ለዘመናት የዘለቀ በመሆኑ በጥሩ መልኩ ነው የሚታየኝ '' ሲሉ በሐዋሳ ዩኒቨርስቲ የጂኦሳይንስ ክፍል ረዳት ፕሮፌሰር በቀለ አየለ (ዶ/ር ) ከስፑትኒክ አፍሪካ ጋር በነበራቸው ቆይታ አስረድተዋል። ሁለት አንኳር ጉዳዮች በሚዳሰሱበት የሶቨርኒቲ ሶርስስ ፕሮግራማችን በክፍል አንድ የማዕድን ኃብት ዘርፍ በአፍሪካ የምጣኔ ሐብት ዕድገትን ለመፍጠርና ለማፋጠን ስለሚያበ...

ታላላቅ ሩሲያዊያን ጸሃፊዎች ሲታወሱ፡- ከአሌክሳንደር ፑሽኪን እስከ አንቶን ቼክሆቭ 20.01.2026

''የሩሲያዊያን ስነፅሁፎች ጭፍን ጥላቻን አያንፀባርቁም፤ ይልቁን የማኅበረሰቡን ባህል፣ ወግና ታሪክ የሚያንፀባርቁ ናቸው - ከታላላቅ ፀሃፊዎች መካከል የአንቶን ቼክሆቭ ሥራዎች በዓለም ላይ ምርጥ 50 ተውኔቶች መካከል የሚመደቡ ናቸው። በዚህም በሥራዎቹ በትልቅ ደረጃ የሚገለፅ ነው - ሲል'' ከቼክሆቭ ሥራዎች ውስጥ አራቱን ወደ አማርኛ ቋንቋ የተረጎመው ተዋናይ ሳምሶን ብሬ ለግሃር ለስፑትኒክ አፍሪካ አስረድቷል።  በመጀመሪያው የፕሮግራሙ ክፍል የታላላቅ ራሺያውያን ፀሃፊዎችን ዘመን ተሻጋሪ አሻራን መሠረት በማድረግ ከአሌክሳንደር ፑሽኪን እስከ አንቶን ቼክሆቭ ያሉ ታላላቅ የስነ ፅሁፍ ሰብዕናዎችን ከተርጓሚ፣ ተዋናይና በጥብቅና ሙያ...

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ከየት ወዴት? 15.01.2026

የአፍሪካ ዋንጫ ጨዋታዎች አእየተደረጉ ነው35ኛው የአፍሪካ እግር ኳስ ዋንጫ ውድድር በሰሜን አፍሪካዊቷ አገር ሞሮኮ አስተናጋጅነት እየተካሄደ ነው። አጋጣሚውን ተጠቅመን ስለኢትዮጵያ እግርኳስ መጠየቅ ወደድናል፡፡ ''የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ጎል የማይገባበት ሊግ ነበር የሆነ ጊዜ፤ ስታዲየም አካባቢ በነፃነት ተከራይህ መኖር ትችል ነበር ጎል ስለማይገባ፣ ጩኸት ስለማይኖረው። የዚህን ያህል ነፃነት ነበረው '' ሲል ኢትዮጵያዊው የእግር ኳስ ጋዜጠኛ አያናው ወልደ ሚካኤል ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግሯል፡፡ በዚህኛው የሶቨርኒቲ ሶርስስ ፕሮግራም አቅራቢው የአፍሪካ አህጉር እግር ኳስ ዕድገትና እንቅስቃሴን መሠረት አድርጎ የአህጉሪቱ የእግር...

ትምህርት፣ ክህሎት እና ፈጠራ፡- ለኢኮኖሚ ዕድገት ምን ሚና አላቸው ? 14.01.2026

'' በአፍሪካ ጠንካራ ምጣኔ ሀብት መፍጠር ያስፈልጋል። ለዚህም ኢንዱስትሪውን ማጎልበት፣ ፈጠራዎችን ማስፋፋት በተጨማሪም በእውቀትና ክህሎት መደገፍ ተገቢ ነው - ለአንድ አካል የሚተው ባለመሆኑ የግል ዘርፉንም ያካተተ ትብብርና አጋርነት መፈጠር አለበት። ፖሊሲዎችን መከለስና በሁሉም ዘርፎች ውስጥ ማሻሻያዎችን ማፋጠን ያስፈልጋል'' ሲሉ በአምቦ ዩኒቨርሲቲ የዴቨሎፕመንት ስተዲስ መምህሩ ፍራፊስ ሀይሉ (ዶ/ር) ለስፑትኒክ አፍሪካ ገልፀዋል። ሁለት አንኳር ጉዳዮች በሚዳሰሱበት የዛሬው ፕሮግራማችን በክፍል አንድ በአፍሪካ ጠንካራ የምጣኔ ሐብት ዕድገትን ለመፍጠር የሠው ኃይልን እንደ መሠረት መጠቀምን በተመለከተ በአምቦ ዩኒቨርሲቲ የዴቨሎ...

ቬኔዙዌላ፡- የፖለቲካ ጣልቃገብነት እና የሉዓላዊነት ጥሰት ማሳያ 08.01.2026

''ቬኔዙዌላ አሁን ላይ የውጭ ጣልቃገብነት ተጠቂ ሀገር ናት። [...] በውስጥ አንድነት ለዓለም አቀፍ ማኅበረሰቡ ፍትህ መጠየቅ ይኖርባታል - የተፈጠረው ነገር ከቬንዙዌላ ባሻገር ለሌሎች ሉዓላዊ ሀገራት በሙሉ የማንቂያ ደውል ነው '' ሲሉ በ ዋቻሞ ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካ ሳይንስና ዓለም አቀፍ ግንኙነቶች መምህሩ አበራ ሄብሶ ለስፑትኒክ አፍሪካ አጋርተዋል። ሁለት ዐበይት ጉዳዮችን በምንቃኝበት ፕሮግራማችን በክፍል አንድ የፖለቲካ ጣልቃገብነትን እና ብሔራዊ ሉዓላዊነትን በተመለከተ ሰሞነኛው የቬኔዝዌላን ጉዳይ መነሻ በማድረግ በዋቻሞ ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካ ሳይንስና ዓለም አቀፍ ግንኙነቶች መምህሩ አበራ ሄብሶ ጋር ተወያይተናል። በሁለተኛ...

ብሔራዊ የልማት ዕቅድ ከዓለም አቀፍ የባንክ አሰራሮች አንጻር ዕድሎችና ተግዳሮቶች 02.01.2026

''ሀገር ሊያድግና ሊለወጥ የሚችለው በውስጥ አቅም ነው፤ በብድርና ድጋፍ ብቻ የተለወጠ ሀገር የለም። ስለዚህ የውስጥ አቅምን በሚገባ አውጥቶ መጠቀም ያስፈልጋል '' ሲሉ በባንክ ዘርፍ በተለይም በማርኬቲንግና ብራንዲንግ የረጅም ዓመታት ልምድ ያካበቱት አሰቻለሁ ታምሩ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል። ሁለት ጉዳዮችን በምንዳስስበት ፕሮግራማችን በክፍል አንድ በብሔራዊ ልማት ቅድሚያ የሚሰጣቸውን ጉዳዮች ከዓለም አቀፍ የባንኪንግ ልምዶች እንዴት ማዛመድ ይቻላል የሚለውን ጉዳይ በባንኪንግ ዘርፍ በተለይም በማርኬቲንግና ብራንዲንግ የረጅም ዓመታት ልምድ ያካበቱት አሰቻለሁ ታምሩ ጋር ቃኝተናቸዋል። በሁለተኛው ክፍል ደግሞ የአዝዕርቶችን አቅም...

ባለሁለት ስለቱ ማኅበራዊ ሚዲያ፡ መልካም ዕድሎቹና አሉታዊ ተፅዕኖዎቹ 01.01.2026

''ቴክኖሎጂ ወደፊት እያደገ ሲመጣ የራሱን መልካም ገፅታዎችን ይፈጥራል። ለምሳሌ ሰዎች በማኅበራዊ ሚዲያዎች ባሉበት ቦታ የመማር ፍጥነታቸውን ጨምሮላቸዋል። በአንፃሩ ወጣቶች የበሰለ የማኅበራዊ ሚዲያዎች አጠቃቀም ክህሎት ባለማዳበራቸው ከፍተኛ ቀውስ ሲፈጥሩ ይስተዋላሉ'' ሲሉ በማኅበራዊ ሚዲያዎች አጠቃቀምና አመራር የረጅም ዓመታት ልምድ ካላቸው አቶ አማኑኤል አክሊሉ ለስፑትኒክ አፍሪካ አስረድተዋል። ሁለት አንኳር ጉዳዮችን በምንቃኝበት ፕሮግራማችን በክፍል አንድ በሁለት መልክ የሚታየው የማኅበራዊ ሚዲያን በተመለከተ መልካም ዕድሎቹንና አሉታዊ ተፅዕኖዎቹን ከሌሎች ተያያዥ ዝርዝር ሀሳቦች ጋር በማጣመር በማኅበራዊ ሚዲያዎች አጠቃቀምና...

የኢትዮጵያን የጤና ዘርፍ ክፍተት በቴክኖሎጂ፣ ጥናትና ምርምር የመቅረፍ ተስፋ 30.12.2025

''እያንዳንዱ የጤና ቴክኖሎጂ የራሱ ሳይንሳዊ የውጤታማነት መለኪያ አለው። ለአብነትም የመመርመሪያ መሣሪያዎችን መውሰድ እንችላለን —ሀገራችን ራሷን በክትባት አቅም ማብቃት ይኖርባታል፣ እኛም እንደተመራማሪ ክትባቶችን በሀገር ውስጥ ማምረት አለብን '' ሲሉ በዘርፉ የረጅም ዓመታት ተመራማሪው ዶ/ር ሞላልኝ ቢተው ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል። ሁለት አንኳር ጉዳዮችን በምንቃኝበት ፕሮግራማችን በክፍል አንድ በምርምር፣ አዲስ ሀሳብ በማፍለቅ እንዲሁም ተስማሚ ቴክኖሎጂዎችና ፈጠራዎችን በመተግበር በጤናው ዘርፍ የሚስተዋሉ ክፍተቶችንና ተያያዥ ሀገር አቀፍ ችግሮችን መቅረፍ ስለሚቻልባቸው ጉዳዮች በዘርፉ የረጅም ዓመታት ተመራማሪው ዶ/ር ሞ...

ፕሬዝዳንት ትራምፕ ደቡብ አፍሪካን በቀጣዩ የቡድን 20 ጉባዔ ለሞን አንጋብዝም አሉ? ፖለቲካ መር ወይስ የህግ መሠረት ያለው ጉዳይ? 25.12.2025

''ፕሬዝዳንት ትራምፕ በቀጣይ በሀገራቸው በሚካሄደው የቡድን 20 ሀገራት ጉባዔ ደቡብ አፍሪካን እንደማይጋብዙ መናገራቸው ወደፊት የቡድኑን አቃፊነትና ተቀባይነት ጥያቄ ውስጥ የሚያስገባ ነው - የፕሬዝዳንቱ ንግግርን ተከትሎ በርካታ ሀገራት አጋርነታቸውን ለደቡብ አፍሪካ አሳይተዋል '' ሲሉ በአርሲ ዩኒቨርሲቲ የህግ ትምህርት ክፍል መምህሩ ጃራ ሳሙኤል ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል። ሶቨርኒቲ ሶርስስ በዛሬው ፕሮግራሙ በክፍል አንድ፣ በቅርቡ በደቡብ አፍሪካ የተደረገውን የቡድን 20 ሀገራት ጉባዔን ተከትሎ የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በቀጣዩ ጉባዔ ደቡብ አፍሪካን እንደማይጋብዙ መናገራቸውን በተመለከተ ከዓለም አቀፍ ህግና የሞ...

የኢትዮጵያ 2029 የአፍሪካ ዋንጫ ማሰናዳት ጥያቄ፦ ከእግርኳስ የሚሻገር ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ትሩፋቶቹ 24.12.2025

''ሀገራችን እንደ አፍሪካ ዋንጫ ያሉ ትልልቅ ውድድሮችን ማዘጋጀት ከቻለች የሚያስገኙላት በረከቶች በርካታ ናቸው - ኢትዮጵያ አንድ ወቅት እንደ ክቡር ይድነቃቸው ተሰማ ዓይነት ህይወቱን ለእግር ኳስ የሠጠ ታላቅ የአግር ኳስ መሪ የነበራት ሀገር ናት'' ሲል የስፖርት ጋዜጠኛው ዮናስ አዘዘ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል። ሁለት ጉዳዮችን በምንዳስስበት ፕሮግራማችን በክፍል አንድ ኢትዮጵያ የ2029 የአፍሪካ ዋንጫን ለማዘጋጀት ያቀረበችው ይፋዊ ጥያቄ በእግር ኳስ አውድ ከሚገለፁ ጥቅሞች ባሻገር የሚያስገኝላትን ማኅበራዊ፣ ኢኮኖሚያውና ሌሎች ተያያዥ ጥቅሞችን ከስፖርት ጋዜጠኛው ዮናስ አዘዘ ጋር ቃኝተነዋል። በሉዋንዳ አንጎላ የተካሄደውን...

Listen to the Sovereignty Sources podcast in Replaio

Radio and podcasts in one app - free, with no sign-up. Install today and do not miss the launch

Get it on Google Play

Replaio is not a podcast publisher; show names, artwork and audio belong to their authors and are distributed through public RSS feeds.