ዐቢይ ሀብታሙ

Sovereignty Sources

Society EN ↓ 119 episodes

ዓለም በሉላዊነት ምክንያት ስትተሳሰር ፤ ፕሮግራሙም አፍሪካ ባላት እምቅ የተፈጥሮ ኃብት፣ በማደግ ላይ ባለው የሕዝብ ቁጥሯ ፣ በወጣት ኃይሏ እና በአህጉሪቱ ባሉ አዳዲስ ግኝቶችና የመፍትሄ ሃሳቦች  ያላትን የመወዳደር አቅምና ጥቅም በሰፊው ይዳስሳል፡፡ እንኳን ወደ 'ሶቨርኒቲ ሶርስ' ፕሮግራም በደህና መጡ፣

Author

ዐቢይ ሀብታሙ

Category

Society

Latest episode

Jul 11, 2026

Where to listen?

Podcasts in the app Replaio Radio Coming soon

Podcasts are coming to the app soon. Install now and be the first to see a whole new take on podcasts

Get it on Google Play Install for free Android 5M+ downloads · 4.8 rating iOS soon

Episodes

ደቡባዊ ዓለም ሀገራት፡ ብሪክስን እንደ ጠንካራ አጋር የመጠቀም ምርጫቸው 11.07.2026

''ብሪክስ መፈጠሩ ጥሩ ነው፣ ለዓለምም ሰላም አምጥቷል። ተመጣጣኝ ሀይል ያላቸው በብሪክስ ውስጥ መኖራቸው ሚዛን ያስጠብቃሉ። የገበያ አማራጮችም ይኖራሉ — ብዙ ሀብት ያላቸው ያላደጉ ሀገራት ወደፈለጉበት መሸጥ ይችላሉ። ሲሸጡ ደግሞ አንድ ካልተመቻቸው ነፃ ገበያ ስላለ ተደረድረው መሸጥ ይችላሉ - ሲሉ በራያ ዩኒቨርሲቲ የሰላም፣ ግጭትና ልማት መምህርና ተመራማሪው አሌክሳንደር ኃይማኖት(ዶ/ር ) ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል።'' በዛሬው ፕሮግራማችን በክፍል አንድ የደቡባዊ ዓለም ሀገራት ከተፈጥሮ ኃብት ላኪነት እንደ ብሪክስ ያሉ አማራጭ ኃይሎችን በመጠቀም ወደ ኢኮኖሚያዊ ኃይል እንዴት መሸጋገር እንደሚችሉ በራያ ዩኒቨርሲቲ የሰላም፣...

የሩሲያ- አፍሪካ ትብብር:- የሰርጌይ ላቭሮቭ ቁልፍ የትብብር መልዕክቶች በአዲስ አበባ 08.07.2026

''የሰርጌይ ላቭሮቭ መግለጫ ሩሲያ በአፍሪካ አጠቃላይ ልማት ላይ አብዛኛውን ጊዜ አፅንዖት የምትሰጠውን ሰፊ ​​የዲፕሎማሲ ራዕይ ያንፀባርቃል — የሩሲያ- አፍሪካ ትብብር በንግድ፣ ኢንዱስትሪ ልማት፣ ሳይንስና ቴክኖሎጂ፣ የጤና አጠባበቅ፣ ትምህርትና ኢንቨስትመንት ዘርፎች ተጨባጭ ውጤቶችን ለማምጣት ከፖለቲካዊ ውይይት ባሻገር መጓዝ ይኖርበታል'' ሲሉ የኢሮናቲካል ምህንድስ ባለሙያው ሚኪያስ ዮሃንስ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል።  በዛሬው የሶቨርኒቲ ሶርስስ ፕሮግራማችን የአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር መሐሙድ አሊ ዩሱፍ የሩሲያ ፌዴሬሽን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌ ላቭሮቭ በጋራ ጥቅሞች ላይ የተመሰረተውንና እያደገ የመጣውን የአ...

የፊፋ 2026 የዓለም ዋንጫ ውዝግቦች 22.06.2026

''እንደኔ አሜሪካ በኢራንና በሶማሊያዊው ዳኛ ላይ የያዘችው አቋም የፖለቲካ አቋም ነው። ለነዚህ ሀገራት ያላት አመለካከት ምን ይመስላል የሚለውን ነገር ቁልጭ አድርጎ ያሳየናል —ፊፋ እንደዚህ ዓይነት ነገሮች ድጋሚ እንዲፈጠሩ መፍቀድ የለበትም '' ሲል አንጋፋው የስፖርት ጋዜጠኛ ዘርዓይ እያሱ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግሯል። ሶቨርኒቲ ሶርስስ በዛሬው መርሃ ግብሩ ከሰሞኑ በካናዳ፣ ሜክሲኮና አሜሪካ አማካኝነት እየተሠናዳ የሚገኘው የ2026 የፊፋ የዓለም ዋንጫ ውዝግቦችን ከሜዳና ውስጥና ሜዳ ውጪ ክስተቶች ጋር በማጣመር እንወያያለን።  አንጋፋው የስፖርት ጋዜጠኛ ዘርዓይ እያሱና ሌላኛው የስፖርት ጋዜጠኛ ሳምሶን አበበ ሙያዊ ዕይታቸውን...

የሳተላይት ቴክኖሎጂን የማጎልበት ሀገራዊ ህልም 22.06.2026

''የሳተላይት መረጃ በመሠረታዊነት ነገሮች ከመባባሳቸው በፊት ቅድመ እና ወቅታዊ መረጃ ይሰጣል። ለምሳሌ የሳተላይት መረጃን በመጠቀም የሰብል ውድቀትን አስቀድሞ ለመተንበይ ወይም ለመገመት እንችላለን ምክንያቱም ከሳተላይቶች፣ በጣም ትንሽ የሆነ የእርሻ ቦታን መመልከት እና የእያንዳንዱን ሰብል የጤና ሁኔታ በጥልቀት መመርመር ስለሚችሉ ብለዋል -- ኪሩቤል መንበሩ አለሙ፣ የኢትዮጵያ ስፔስ ሳይንስ ሶሳይቲ ማኔጂንግ ዳይሬክተር ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግሯል።'' ሶቨርኒቲ ሶርስስ በዛሬው መርሃ ግብሩ በክፍል አንድ የሳተላይት ቴክኖሎጂ እና የአየር ንብረት ቁጥጥርን በተመለከተ በኢትዮጵያ ውስጥ ድርቅን፣ ዝናብ እና5 የመሬት መራቆትን ስለመከ...

ዓለም ወደ ባለብዝሃ ወገን የፖለቲካ ስርዓት የምታደርገው ፈጣን ጉዞ 12.06.2026

''ቻይናን፣ ሩሲያና ህንድ የመሳሰሉ ሀገራት የራሳቸውን አሻራ እያስቀመጡ ነው እየመጡ ያሉት፤ ጠንካራ የሚባል ኢኮኖሚ፣ ሰራዊት፣ ዲፕሎማሲ ገንብተዋል። በተለይ ከግሎባል ሳውዝ ሀገራት ጋር ጠንካራ ግንኙነት እየፈጠሩ ነው — የዓለም አቀፍ ፖለቲካዊ ስርዓት ወደ ባለብዙ ወገን ስርዓት እየተለወጠ እንደሆነ ማየት እንችላለን '' ሲሉ በደብረ ማርቆሰ ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካ ሳይንስና ዓለም አቀፍ ግንኙነቶች መምህር ደረጄ መለስ ለስፑትኒክ አፍሪካ  ተናግረዋል። በዛሬው ፕሮግራማችን የሶቨርኒቲ ሶርስስ ፕሮግራማችን በክፍል አንድ የዓለም ባለብዙ ዋልታ የዓለም ስርዓትና የወደፊት ዕጣን በተመለከተ በደብረ ማርቆሰ ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካ ሳይንስና ዓለ...

ሩሲያ በአፍሪካዊያን ዓይን እንዴት ትታያለች? በሚዲያ የሚነገረው መሬት ላይ ካለው እውነታ ጋር ሲነፃፀር 10.06.2026

'' በምዕራቡ በኩል የሚነገረው ፕሮፓጋንዳ እንደሆነ እረዳለሁ። አብዛኛው የሚነገረው እውነት የሆነ፣ መሬት ያለው ነገር አይደለም። ዛሬም ያ ነገር ቀጥሏል። ይሻሻላል ተብሎ ቢጠበቅም ያው ነው አሁንም — ያንን ሀገር ፈርጆ ላይ ላዩን ሊጭኑብህ የሚፈልጉት ነገር አለ '' ሲሉ የቀድሞ የሶቪየት ኅብረት ተማሪ ክብሩ ቸርነት (ዶ/ር) ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል።  ሁለት አንኳር ጉዳዮች በሚዳሱበበት የዛሬው የሶቨርኒቲ ሶርስስ ፕሮግራም በክፍል አንድ ሩሲያ በአፍሪካዊያን ዓይን እንዴት እንደምትታይ መሰረት በማድረግ የቀደመ የሚዲያ ትርክቶችን መሬት ላይ ካለው እውነታ ጋር በማነፃፀር የቀድሞ የሶቪየት ኅብረት ተማሪ ክብሩ ቸርነት (ዶ/ር)...

አፍሪካን ከውጪ ከሚሸመቱ ምግቦች የማላቀቅ ፋይዳዎች 02.06.2026

''ያሉንን የተፈጥሮ ኃብቶች በአግባቡ እየተጠቀምን አይደለም። የግብርና መሠረተ ልማት ከፍተኛ ምርት ለማውጣት እንደ ጀርባ አጥንት የሚወሰድ ነው — መንግስታት ከፍተኛ ጥረት እያደረጉ መሆናቸው ቢታወቅም ከውጪ የሚሸመቱ ምግቦችን ለመቀነስ አሁንም ብዙ ነገሮች ይጠበቅባቸዋል '' ሲሉ በአርባምንጭ ዩኒቨርሲቲ የምግብ ቴክኖሎጂ ተባባሪ ፕሮፌሰሩ አዲሱ ፍቃዱ (ዶ/ር) ለስፑትኒክ አፍሪካ አብራርተዋል። ሁለት ጉዳዮች በሚቃኙበት የዛሬው ፕሮግራማችን በክፍል አንድ ከፍተኛ የተፈጥሮ ኃብት ያላት አፍሪካ ስለምን በከፍተኛ ሁኔታ ከውጪ ተሸምተው ወደ ሀገር ውስጥ የሚገቡ ምግቦች ጥገኛ ሆነች ደግምስ ቀጣዩ ዘመናት ምን መምሰል አለባቸው ስንል በአር...

የዓለም አሃዳዊ ዋልታ የኃይል ስርዓት እያከተመ ነው ? 28.05.2026

''ዋሽንግተን መሪዎችን በመግደል እና ኃይሏን በመጠቀም ኢራንን በአጭር ግዜ ውስጥ አንበረክካለሁ ብላ አስባ ነበር። በተቃራኒው ኢራን ድብደባዎቹን ተቋቁማ፤ መከላከሏን ቀጠለች እንዲሁም የጦር ሜዳውን ወደ ባሕረ ሰላጤው፣ ወደ አረቦች እና ወደ ሌሎች የዓለም ክፍሎች አስፋፍታለች። በዚህም አሜሪካ የበላይነቷን አሳያለሁ ብላ ድክመቷን አጋልጣለች ” - የወራቤ ዩኒቨርስቲ መምህር መሃመድ አዎል ሀጎስ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል፡፡ በዛሬው ሶቨርኒቲ ሶርስስ ፕሮግራም በክፍል አንድ የዓለም አሃዳዊ ዋልታ የኃይል ስርዓት እያከተመ ስለመሆኑ ከጂዮፖለቲካዊ አኳያ ከወራቤ ዩኒቨርስቲ መምህር መሃመድ አዎል ሀጎስ ጋር ተወያይተናል። በሁለተኛው ክ...

የሀገር በቀል እውቀት ለብዝሃ ህይወት ጥበቃ 20.05.2026

ዓለም የባዮሎጂካል ብዝሃነት ዓለም አቀፍ ቀንን በፈረንጆቹ ግንቦት 22 ቀን ያከብራል። '' አፍሪካ ለአየር ንብረት ለውጥ የተጋለጠች አህጉር ነች፣ በእርግጥ አንድ ዓይንት  ስነ ምህዳር አይደለም ያላት። ስለዚህ ይህ የሀገር በቀል እውቀት ለብዝሃ ህይወት ይጠቅማል። ብዝሃ ህይወት ስንል ብዙ ዝርያ ያላቸው እንስሳት፣ ዕፅዋትና ደቂቀ ነፍሳትን አንድ ላይ የያዘ ነው ''  - ሲሉ የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የአካባቢ ብዝሃ ህይወት ጥበቃ ዋና ዳይሬክተሩ ሺቲ ጋተው(ዶ/ር)  ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል። በዛሬው ፕሮግራማችን በክፍል አንድ የአፍሪካን ስነ ኑረቶችና ብዝሃ ህይወትን ለመጠበቅ ሀገር በቀል እውቀቶች ያላቸውን ሚናዎች የአርባ...

የታሪክ ማህተም፦ የሩሲያ 81ኛው የድል በዓል 11.05.2026

''ራሺያኖች ሉዓላዊነታቸውን በመጠበቅ፣ ራሳቸውን በማስታጠቅ እና በአርበኝነት ረገድ በጣም ጥሩ ናቸው። ባህላቸውም በሚገባ የጎለበተ እና የተብላላ ነው። ስለዚህ አፍሪካዊያን ከእነርሱ ጋር ምንም ዓይነት የቅኝ ግዛት ግንኙነት ከሌላት ራሺያ ብዙ መማር ይችላሉ '' ሲሉ የእዮብዘር ዘውዴ በአዲስ  አበባ ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካ ሳይንስና ዓለም አቀፍ ግንኙነቶች መምህር ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል። ሁለት ጉዳዮችን በምንቃኝቀት ፕሮግራማችን በክፍል አንድ የራሺያ 81ኛው የድል ቀንን መሠረት በማድረግ ከፓን አፍሪካኒዝም አንድነት ጋር በማስተሳሰር የዮብዘር ዘውዴ በአዲስ  አበባ ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካ ሳይንስና ዓለም አቀፍ ግንኙነቶች መምህር...

ህጻናትና ወጣቶችን ከሳይበር ጥቃት፣ ብዝበዛ እና ጫናዎች የመጠበቅ ኃላፊነት 04.05.2026

''አሁን ላይ ልጆች ላይ እየደረሰ ያለው ነገር አስፈሪ በሚባል ደረጃ እየሄደ ያለ ነው። የተለያዩ ጥቃቶች እየተፈፀሙ ነው። እነዚህ ልጆችም ለማይሆኑ ነገሮች እየተጋለጡ ይገኛሉ — የዲጂታሉ ዓለም ገደብ የለውም። ከስነልቦና፣ ከእውቀታቸውና ራሳቸውን መቆጣጠር ከሚችሉበት በላይ የሆኑ ነገሮችን እየተመለከቱ ለብዙ ነገሮች እየተጋለጡ ይገኛሉ። ጥፋቱ ከፍተኛ ነው ማለት እንችላለን - '' ሲል በአሶሳ ዩኒቨርሲቲ የሜካኒካል ምህንድስና መምህሩና የማኅበራዊ ሚዲያው ተጽዕኖ ፈጣሪና የመረጃ ሰጪ ይዘት ያላቸው ዜናዎችን በቲክቶክ የሚያጋራው ብሩክ ጫላ ለስፑትኒክ አፍሪካ አፍሪካ ተናግሯል ። ሶቨርኒቲ ሶርስስ በዛሬው ዝግጅቱ በክፍል አንድ ታዳጊ...

ኢራንን እንደ ሀገር ያቆማት ጠንካራ ብሔራዊ ማንነት 27.04.2026

''መሪዎችን መግደል፣ ዜጎችን መግደል፣ ሁሉም ነገር እንዳይንቀሳቀሱ ማድረግ ግፍ ነው። እኛ የምንላችሁን ስሙ፣ እኛ ኃያላን ነን፣ ሁሉንም ነገር ማድረግ እንችላለን ነው የሚሉት። ኢራን በቀጥታ የተፈፀመባት ወረራ ነው -'' ሲሉ በራያ ዩኒቨርሲቲ የሰላም፣ ግጭትና ልማት መምህርና ተመራማሪው ዶ/ር አሌክሳንደር ኃይማኖት ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል።  በክፍል አንድ ሰሞነኛው የኢራን - አሜሪካ - እስራኤል ግጭትን መሠረት አድርገን በህገወጥ መንገድ በተለይም በውጭ ጣልቃ ገብነቶች ስለሚደረጉ የመንግስት ለውጥ ከሀገራት ሉዓላዊነት እና ህጋዊ አንድምታዎች አኳያ በራያ ዩኒቨርሲቲ የሰላም፣ ግጭትና ልማት መምህርና ተመራማሪው ዶ/ር አሌክሳ...

በባለብዙ ወገን ዓለም የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የወደፊት እጣፈንታ 15.04.2026

'' የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በተለይ ከጎርጎሮሲያኑ 2000 ወዲህ ከፍተኛ ችግሮች እየገጠሙት ይገኛል — የተቋቋመበትን የዓለም አቀፍ ሰላምና ድኅንነትን የማስፈን ተግባር በተቋቋመበት ዓለማ አስጠብቆ እየሄደ ነው ለማለት አዳጋች ነው። ስለዚህ ባለብዘ ወገን ስርዓት እየተፈጠረ ባለበት ዓለም ተገዳዳሪ አየሆኑ የመጡ ሀገራትን ያካተተ፣ ድምፃቸውንም የሚያስተጋባ መሆን አለበት'' - ሲሉ በአርሲ ዩኒቨርሲቲ የህግ ትምህርት ክፍል መምህሩ ጃራ ሳሙኤል ከስፑትኒክ አፍሪካ ጋር ባደረጉት ቆይታ ተናግረዋል።  ሶቨርኒቲ ሶርስስ በዛሬው መርሃ ግብሩ በክፍል አንድ ዓለም ከነጠላ የፖለቲካ ስርዓትና አስተዳደር ወደ ባለብዙ ወገን ስርዓት እየተሸጋ...

የዩሪ ጋጋሪን ውለታ፡ የመጀመሪያው ጉዞ ወደ ህዋ 13.04.2026

''ስፔስ ሳይንስን ልዩ የሚያደርገው የማናውቀውን ነገር ለማወቅ ጥረት የምናደርግበት ነው። በዚህ ረገድ የስፔስ ሳይንስ ምርምር መስመር እንዲይዝ ዩሪ ጋጋሪን መሰረት የጣለ ታላቅ ሰው ነው - ሲሉ የዘርፉ ተመራማሪው አለምዬ ማሞ(ዶ/ር) ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል።" በዛሬው ፕሮግራም በክፍል አንድ በየዓመቱ በጎርጎሮሲያኑ መጋቢት 12 የሚከበረውን የሰው ልጅ ለመጀመሪያ ጊዜ ወደ ህዋ የተጓዘበትን ቀንና የህዋ ሳይንስ ጉዳይ ከኢትዮጵያ ኑውክላር አነርጂ ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነሩ አብድረዛቅ ኡመር እና የስነ ህዋ ተመራማሪው ዶ/ር አለምዬ ማሞ ጋር ጥልቅ ምልከታ ተከናውኗል። በመካከለኛው ግጭት ሳቢያ በንግድና ፋይናንስ ላይ ተፅዕኖ ቢፈ...

የትንሳዔ በዓል መጽሐፍ ቅዱሳዊ መሠረቶች 11.04.2026

''እኛ ፋሲካ የምንለው የክርስቶስ ትንሣኤ በዓል፣ በአጠቃላይ በክርስትና ትውፊት ውስጥ በተለይ ለኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ከዋና ዋናዎቹ እና እጅግ በጣም አስፈላጊ ከሆኑት በዓላት አንዱ ነው — የመጽሐፈ ሄኖክ እና ኩፋሌ፣ በተለይም ደግሞ የሄኖክ መጽሐፍ፣ ሙሉ ይዘቱ በግዕዝ ቋንቋ፣ በኢትዮጵያ ብቻ ይገኛል። ከጥቂት መቶ ዓመታት በፊት ጄምስ ብሩስ የተባለ አንድ እንግሊዛዊ ተጓዥ የሄኖክን መጽሐፍ ከጣና ሐይቅ አካባቢ በስጦታነት ተቀብሎ ወደ አገሩ ወስዶታል። ለጉብኝቱ እና ለኢትዮጵያ ቆይታው እንደ ስጦታ በወቅቱ ከነበሩት የኢትዮጵያ ንግሥቶች በአንዷ፣ በንግሥት ምንትዋብ ተሰጥቶታል።'' - ሲሉ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ...

የፀጥታና ደህንነት ጥገኝነት ያስከተለው መዘዝ:- የምዕራባውያን ሚና በመካከለኛው ምሥራቅ ቀውስ 10.04.2026

''የመካከለኛው ምሥራቅ በተለይም የአረብ ሀገራት የውጭ ግንኙነታቸው፣ ከፀጥታ ጋር የተገናኘው በአሜሪካ ላይ ጥገኛ እንደሆነ እናውቃለን — የአረብ ሀገራት በአንድም በሌላ መንገድ የሚኖራቸው የመልስ ምት ወሳኝ ነገር ነው'' - በወልዲያ ዩኒቨርስቲ የፖለቲካ ሳይንስና ዓለምአቀፍ ግንኙነት መምህሩ መሃመድ ሰዒድ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል። ሶቨርኒቲ ሶርስስ በዛሬው መርሃ ግብሩ በክፍል አንድ በግጭት ወጥመድ ውስጥ የሚገኙት የአረብ ሀገራትን መነሻ በማድረግ የምዕራባዊያን ተፅዕኖዎችና የድሮን ጦርነቶችን በወልዲያ ዩኒቨርስቲ የፖለቲካ ሳይንስና ዓለምአቀፍ ግንኙነት መምህሩ መሃመድ ሰዒድ ጋር እንዳስሳለን። በከፍል ሁለት ስለኢነርጂ እና...

የኦቲዝም ቀን በኢትዮጵያ፦ ማኅበራዊ መገለልን ድል የነሳው የ24 ዓመታት የጽናት ጉዞ 02.04.2026

"ልጄ 10 ዓመት እስኪሞላት ድረስ እናቴ ከሶፋ ጋር እያሰረችልኝ እኔ መስተንግዶ እሰራ ነበር። 'ከእሷ ጋር አትሁኑ' ተብዬ ለማኅበረሰቡ መጥፎ ምሳሌ ተደርጌ ነበር፤ 'ትምህርት ያቆመችው እንዲህ ዓይነት ልጅ ወልዳ ነው' ይባላል። ጫናው እናቴን እስከመጨረሻው መቃብር ውስጥ እስኪከታት ደርሶ ነበር። [...] መጀመሪያ 'ከእሷ ጋር አትሁኑ' ተብዬ ለማኅበረሰቡ መጥፎ ምሳሌ ተደርጌ ነበር። ዛሬ ግን ልጄ ቦርሳዋን አዝላ ወደ ትምህርት ቤት ስትሄድ እናቴ 'በቃ ልጄ ዛሬ ከበሽታ ድናለች' ብላ ተደሰተች።አሁን ከአሁን በኋላ ምንም እስራት የለብኝም፤ እንደ ልጅነቴ መስራት፣ መማርና የምፈልገውን መሆን እንደምችል አውቄያለሁ።" — ስትል የኦቲዝ...

ከምዕራባዊያን ተፅዕኖ ለመላቀቅ የአፍሪካ ኅብረትን የማጠናከር አንድምታዎች 02.04.2026

''በአህጉር ደረጃ አፍሪካ በ2063 ልትደርስበትና ልታሳካ በምትችለው ነገር ሀገራቱ አንድ ዓይነትና የጋራ ራዕይ ኖሯቸው ግልፅ በሆነ መርሃ ግብር መተግበር አለባቸው — አፍሪካ አንደ አህጉር መጠንከር ካለባት ሀገራት ያላቸው ራዕይና ግብ አህጉሪቱን ካስቀመጠችው ጋር የተጣጣመ መሆን ይኖርበታል '' ሲሉ በወልድያ ዩኒርቨሲቲ የፖለቲካ ሳይንስና ዓለም አቀፍ ግንኙነት መምህሩ ሽሽጉ ዓለሙ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል። ሰፋ ያለ ውይይት በምናደርግበት የዛሬው ሶቨርኒቲ ሶርስስ ፕሮግራማችን በክፍል አንድ የልማት ፖሊሲዎችን በማቀናጀት ከምዕራባዊያን ተፅዕኖ ነፃ የሆነ አውድን ለመፍጠር የአፍሪካ ኅብረትን ስለማጠናከር በወልድያ ዩኒርቨሲቲ የ...

የሠው ሰራሽ አስተውህሎት ትውውቅ በኢትዮጵያ ሙዚቃ 23.03.2026

''ይህ የሙዚቃ ቴክኖሎጂ በእኛ ሀገር ኢንዱሰትሪ ሆነ በዓለም አቀፍ ደረጃ መምጣቱ ዕድል ነው። በእርግጥ በኢትዮጵያ የትውውቅ ደረጃ ላይ ነው ያለው ማለት እንችለላለን — ግን በመምጣቱ ብቻ፣ በኢትዮጵያ የሙዚቃ ኢንዱስትሪ በመቀላቀሉ ብቻ አዲስ ዓይነት ድምፅ፣ ቅንብር፣ የሙዚቃ መሣሪያ መሥራት ለናፈቃቸው፤ ከዛም ባለፈ የሚፈራ የነበረው አደጋችና አልፊ የነበረው የመሉ ባንድ ዓይነት ስሜት ያላቸውን ሙዚቃዎችን ለመሥማት ዕድልን የፈጠረ ነው '' ሲል በሰው ሠራሽ አስተውሎት (AI) የታገዙ 'ቀሽቲ' እና 'መኖር' አልበሞች የግጥምና ዜማ አዘጋጅ ጋዜጠኛ ቴዎድሮስ ብርሃኑ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግሯል። ሁለት አንኳር በምንዳስስበት ፕሮግራማ...

የሆርሙዝ ሰርጥ በደቡባዊ ዓለም ሀገራት ዓይን ሲቃኝ 17.03.2026

''የኢነርጂ ዋጋ እየተመነጠቀ ነው፣ ተፅዕኖውንም እያስተዋልን ነው፤ የደቡባዊ ዓለም ሀገራት ከዓለም ፖለቲካ ትይዩ የሆነ ስርዓት መፍጠር ይኖርባቸዋል — የደቡባዊ ዓለም ሀገራት ድምፅ የሚሆናቸው ያስፈልጋቸዋል፣ በዚህም የስፑትኒክ አፍሪካ ጥረት የሚደነቅ ነው።'' ሲል ቀጠናዊና ዓለም አቀፋዊ ጉዳዮን የሚከታተለው ጋዜጠኛ ቢንያም ካሴ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግሯል። ሦስት ጉዳዮች በምንዳስስበት የሶቨርኒቲ ሶርስስ ፕሮግራማችን፣ በክፍል አንድ በኢራን ጦርነት የተዘጋው የሆርሙዝ ሰርጥ በደቡባዊ ዓለም ሀገራት ላይ የሚያሳድረው ተፅዕኖን ከጋዜጠኛ ቢንያም ካሴ ጋር ቃኝተነዋል። በክፍል ሁለት ስለአፍሪካ ከተሞች ዕድገት በፕላን እና ልማት ሚኒስ...

የቅኝ ግዛት ባህልን ለመንቀል ቶጎ ያቀረበችው የአፍሪካ አዲስ ዓመት ሀሳብ 16.03.2026

''መሠረታዊው ነገር እሪካዊያን ተግባራዊ አንድነት፣ ተምሳሌታዊ አንድነት፣ የፓን አፍሪካኒዝም ወንድማማችነት እንዲሁም ከቅኝ ግዛት ባህል መውጣት ነው በዚህ የቶጎ ጉዳይ ውስጥ እንደ አነሳሽ ሀሳቦች ሆነው የሚታዩት። ደግሞም በተቋም ደረጃ ለምሳሌ ለአፍሪካ ኅብረት ትልቅ መነቃቃትን ይፈጥራል - ሲሉ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካ ሳይንስና ዓለም አቀፍ ግንኙነቶች መምህሩ የዕዮብዘር ዘውዴ ለ ስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል።'' በክፍል አንድ የምዕራብ አፍሪካዊቷ ሀገር ቶጎ ባህላዊው ቅኝ ግዛትን በመቃወም አፍሪካ የራሷ የዘመን መቁጠሪያ፣ አዲስ ዓመትም ያስፈልጋታል በሚል በይፋ ያቀረበችውን ምክረ ሀሳብን ከተለያዩ አህጉራዊና ዓለም አቀ...

የምዕራቡ ዓለም ሚዲያዎች ዝምታ፦ በኢራን ጉዳይ ላይ ለምን ''መረጃን መደበቅ'' መረጡ? 12.03.2026

''የምዕራባዊያን ሚዲያዎቹ ህፃናት፣ ሴቶች እንዲሁም አረጋዊያንን ከግምት ሳያስገቡ ነው ከኢራን በኩል ያለን የደኅንነት ስጋት ለማስወገድ በሚመስል ጉዳዩን እየቃኙ ያሉት - ሲሉ በፐብሊክ ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ የፖሊሲ ጥናት መምህሩ ሙከረም ሚፍታህ (ዶ/ር) ሲሉ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል።'' በዛሬው የሶርቨርኒቲ ሶርስስ ፕሮግራማችን የኢራን ጦርነትነን መሠረት አድርገን የምዕራባዊያን ሚዲያዎች ሚዛን አልባ ዘገባዎች እንዲሁም በአንዳንድ ጉዳዮች የሚያሳዩትን ዝምታ እንቃኛለን። ለዚህም በፐብሊክ ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ የፖሊሲ ጥናት መምህሩ ሙከረም ሚፍታህ (ዶ/ር) እና በወሎ ዩኒቨርሲቲ የጋዜጠኝነትና ተግባቦት መምህሩ ኢብራሂም ሰይድ አህመ...

የታላቁ አድዋ ድል በጥበባት አውድ ትርክቱ ምን መምሰል ይገባል? 10.03.2026

''አድዋ ተራ ጦርነት አይደለም፤ ሰብዓዊነትን ገልጿል።  የኢትዮጵያዊያን ብቻ ሳይሆን የመላ ጥቁር መገለጫም ነው — በጥበባት አውድ ከተመለከትነው በሚገባው ከፍታ ልክ መተረክና መተንተን ይኖርበታል።'' ሲሉ የቪዢዋል አርቲስት፣ ሰዓሊ እና ቀራፂ በቀለ መኮንን (ፕ/ር) ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል። ሁለት አንኳር ጉዳዮችን በምንዳስስበት ፕሮግራማችን በክፍል አንድ  የታላቁ አድዋ ድል በጥበባት አውድ ሊኖረው የሚገባን ትርክት መሠረት አድርገን ከቪዢዋል አርቲስት፣ ሰዓሊ እና ቀራፂ በቀለ መኮንን (ፕ/ር) ጋር ተወያይተናል። 🇮🇷 በክፍል ሁለት ደግሞ የኢራኑ መንፈሳዊ መሪ አያቶላህ ኾሚኒ ግድያን ከዓለም አቀፍ ህግ ጥሰት አኳያ ከመኪ...

የሩሲያ 10 ኢምባሲዎችን በአፍሪካ ዳግም የመክፈት እቅዷ ለተጠናከረ ወዳጅነት 04.03.2026

''የአፍሪካና የሩሲያ ግንኙነት ዘመን ተሻጋሪ ነው። ሩሲያ ካደጉ ደግሞ ተፅዕኖ ከሚፈጥሩ ሀገራት አንዷ ናት። ለምሳሌ ድምፅን በምድፅ የመሻር አቅሟን ማንሳት ይቻላል። ስለዚህ ከእንዲች ያለች ሀገር ጋር ወዳጅነት መፍጠር እጅግ በጣም ጠቃሚ ነው - ሩሲያ በቀጣይ ዓመታት ወደ አስር የሚጠጉ ኢምባሲዎችን በአፍሪካ ለመክፈት ማቀዷ በዓለም አቀፍ መድረክ ተደማጭነትን የሚጨምር ነው'' ሲሉ የአፍሪካ ፖሊሲ ጥናት ተመራማሪው አበራ ኤልያስ (ዶ/ር) ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል። ሁለት ጉዳዮችን በምንቃኝበት የዛሬው መርሃ ግብራችን በክፍል አንድ ሩሲያ በአፍሪካ አህጉር አስር ኢምባሲዎችን ዳግም ለመክፈት የገለፀችበትን ዕቅዷን መሠረት አድር...

የኔልሰን ማንዴላ ሙዚየም በአዲስ አበባ 02.03.2026

''የኔልሰን ማንዴላ ሙዚየም በአዲስ አበባ ሲከፈት ማሟላት ያለባቸውን ነገሮች፣ አንደኛው እሳቸው በነበሩባቸው ጊዜያት ያረፉባቸው ክፍሎች፣ የተጠቀሙባቸው ዕቃዎች፣ የሥልጠና ቦታና የወሰዷቸውን የስልጠና ዓይነቶች ያካተተ ነው — የአሁኑ ትውልድ እንደ አደዋ ካሉ የትናንት የአባቶቻችን ታሪክ ብዙ ተምሮ፣ ይህ መነሻ ሆኖ ለነገው ትውልድ ደግሞ ስንቅ ሆኖ መተላለፍ አለበት።'' ሲሉ ኮማንደር አሳቤ ባይሳ፣ ኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ሎጀስቲክ መምሪያ የንብረት አስተዳደር ጠቅላላ አገልግሎት ዋና ኃላፊ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል። ሁለት ጉዳዮችን በምንዳስስበት ፕሮግራማችን በክፍል አንድ በአዲስ አበባ ኮልፌ የቀድሞው የፈጥኖ ደራሽ ግቢ ውስጥ...

Listen to the Sovereignty Sources podcast in Replaio

Radio and podcasts in one app - free, with no sign-up. Install today and do not miss the launch

Get it on Google Play

Replaio is not a podcast publisher; show names, artwork and audio belong to their authors and are distributed through public RSS feeds.