ዐቢይ ሀብታሙ

Sovereignty Sources

Society EN ↓ 119 episodes

ዓለም በሉላዊነት ምክንያት ስትተሳሰር ፤ ፕሮግራሙም አፍሪካ ባላት እምቅ የተፈጥሮ ኃብት፣ በማደግ ላይ ባለው የሕዝብ ቁጥሯ ፣ በወጣት ኃይሏ እና በአህጉሪቱ ባሉ አዳዲስ ግኝቶችና የመፍትሄ ሃሳቦች  ያላትን የመወዳደር አቅምና ጥቅም በሰፊው ይዳስሳል፡፡ እንኳን ወደ 'ሶቨርኒቲ ሶርስ' ፕሮግራም በደህና መጡ፣

Author

ዐቢይ ሀብታሙ

Category

Society

Latest episode

Jul 11, 2026

Where to listen?

Podcasts in the app Replaio Radio Coming soon

Podcasts are coming to the app soon. Install now and be the first to see a whole new take on podcasts

Get it on Google Play Install for free Android 5M+ downloads · 4.8 rating iOS soon

Episodes

የትራምፕ አስተያየት ስለ ሕዳሴ ግድብ፦ ዲፕሎማሲ ወይስ ረብሻ? የኢትዮጵያ የሉዓላዊነት መንገድ 21.07.2025

“ለምን እንደሆነ? አሜሪካ ለምን [በድርድር ሂደቱ] እንድትሳተፍ እንደሚፈልጉ አይገባኝም። ውሃው የሚፈሰው በኢትዮጵያ፣ ሱዳን እና ግብፅ ነው። ዉሃው የሚፈሰው በእነዚህ በሶስቱ ሀገራት ዘንድ ነው። ወንዙ [አባይ] ከአሜሪካ ተነስቶ ወደ ግብፅ የሚሄድ ነው ያስመሰሉት። ስለዚህ በአብዛኛው የድንበር ተሻጋሪ ወንዞች ላይ የሶስተኛ ወገኖች ተሳትፎ አይበረታታም ምክንያቱም ሶስተኛ ወገኖች ስጋቶችን፣ የሀገራትን ጭንቀትና ጥቅምም አይረዱም።'' በዚህ #SovereigntySourcess የሶቨርኒቲ ሶርስስ ፖድካስት አቅራቢው የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ስለ ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ በቅርቡ የሰጡትን አስተያየት መነሻ በማድረግ የውኃ...

ታላቁ ኔልሰን ማንዴላ ሲታወሱ ፦ የኢትዮጵያ ሚና በአፍሪካ የነፃነት ጮራ 18.07.2025

"ኢትዮጵያ በነጻነት ፋና ወጊነት አፍሪካን ነፃ የማውጣት ትልቅ ሚናን ተጫውታለች። በ1960ዎቹ ለነፃነት የሚደረግ ትግልን ደግፋለች — ማንዴላ በድፍረት የአፓርታይድ አገዛዝን በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት ባይታገል፣ የነፃነት ጮራ ለመፈንጠቅ ያለእርሱ ነገሮች ትንሽ ይከብዱ ነበር - ሲሉ የታሪክ ምሁሩ ፕ/ር አህመድ ዘካሪያ ተናግረዋል።" በዚህ የሶቨርኒቲ ሶርስስ ፖድካስት አቅራቢው የማንዴላ ዓለምአቀፍ ቀንን መሠረት አድርጎ በበርካታ ጉዳዮች ከታሪክ ምሁሩ ፕሮፈሰር አህመድ ዘካሪያ እና የፓን አፍሪካኒዝም አቀንቃኙ ጆሴፍ ኒዲኩሙኪዛ ጋር ተወያይቷል።

የኢትዮጵያ እና ህንድ ግንኙት ፦ ከጥንታዊ የንግድ ትስስር እስከ ብሪክስ ጥምረት 17.07.2025

"በዶላር ወይም የራስህ ባልሆነ ምንዛሬ ስትገበያይ [...] ኪሳራ ስለሚኖር አንዳንድ ጊዜ እነዚህ አስቸጋሪ ቅድመ-ሁኔታዎች ናቸው። ስለዚህ ተግዳሮቶቹን ለመቅረፍ አዲሱ የልማት ባንክ ወይም ብሪክስ በብሔራዊ ገንዘቦች ለመገበያየት ሁነኛ መላ ዘይዷል" ሶቨርኒቲ ሶርስስ ፕሮግራም በዛሬው መርሃ ግብሩ የአፍሪካ ሀገራት ከብሪክስ አባላት ጋር ያላቸውን ግንኙነት፣ የኢትዮጵያና ህንድ ግንኙነትን አብነት አድርጎ በኢትዮጵያ የህንድ አምባሳደር አኒል ኩማር ሬይን ጋብዟቸዋል።

ኢትዮጵያ፦ የአፍሪካ የታዳሽ ኃይል ዐቢዮተኛ ሀገር 17.07.2025

ኢትዮጵያ 96% የኤሌክትሪክ ኃይል ምንጯ ታዳሽ ኃይል ነው።  ሶቨርኒቲ ሶርስ ፕሮግራም በዛሬው መርሃ ግብሩ ታዳሽ ያልሆኑ ሐብቶችን የመቀነስ አስፈላጊነት እና ተያያዥ ጉዳዮች ለመወያየት በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የፊዚካል ኬሚስትሪ ተባባሪ ፕሮፌሰር ጌታቸው አዳምወርቅ (ዶ/ር) ጋብዘናቸዋል።

ዕምነት በተግባር የተገለጠበት የህክምና ጥበብ - በኢትዮጵያ 14.07.2025

የተለመደ ታሪክ አይደለም። ግን ሁሌም ከፍ ብሎ የሚደመጥ የኢትዮጵያ ልጆች ድንቅ የህክምና ገድል ነው። የጥቁር አንበሳ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ተጣብቀው የተወለዱ ልጆችን በስኬታማ የቀዶ ህክምና እንዲለያዩ አድርጓል። የሶቨርኒቲ ሶርስስ ፕሮግራም በዛሬው መርሃግብሩ ተጣብቀው ስለተፈጠሩ ህፃናት፣ በጥቁር አንበሳ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የህክምና ቡድን ስለተደረገ ስኬታማ የቀዶ ህክምና በጥልቀት ለመወያየት የህፃኑ እናት ሙሉ ግርማን እና በሆስፒታሉ የጨቅላ ህፃናት ቀዶ ህክምና ክፍል ረዳት ፕሮፌሰር የሆኑት ዶ/ር አባይ ጎሳዬን አነጋግሯቸዋል።

የአፍሪካ የመጪው ዘመን ድል፦ የሥራ ፈጠራ ለወጣቶች እና የግብርና አቢዮት 10.07.2025

በአፍሪካ ሰፊ የህዝብ ቁጥር የሚይዘው ወጣቱን የህብረተሰብ ክፍል ከሥራ አጥነት ለማላቀቅ መንግስታት አዳዲስ የሥራ ፈጠራዎችን ሊያበረታቱ እንደሚገባ ይታመናል። ሶቨርኒቲ ሶርስስ ፕሮግራም በዛሬው መርሃ ግብሩ ስለአፍሪካ አህጉር የሥራ ፈጠራ እና የሀገራት የጋራ ቅንጅት በጥልቀት ለመወያየት የኢትዮጵያ የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ሙፈሪያት ካሚል አህመድን ጨምሮ ሌሎች የአህጉሪቱ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎችን ከሰኔ 30 እስከ ሐምሌ 2 በተካሄደው በ3ኛው የአፍሪካ የሥራ ፈጠራ ጉባኤ ላይ አነጋግሯቸዋል።

ሀገር በቀል ጥበብ ከዲጂታል ኢኖቬሽን ጋር፦  ነገን በሠው ሰራሽ አስተዉሎት እና ባህል ማገናኘት 09.07.2025

የሶቨርኒቲ ሶርስስ ፕሮግራም በዛሬው መርሃ ግብሩ የድምፅ አስተውህሎት በተለይም በሠው ሠራሽ አስተውህሎት የሚታገዘው መተግበሪያ እንዴት የአፍሪካን ቋንቋዎች በዲጂታል መንገዱ ተደራሽና እጅግ ጠቃሚ እንደሚያደርግ፣ በዘርፉ የሀገራት ተሞክሮና እንደ ሩሲያ ካሉ በዘርፉ የመጠቁ ሀገራት ጋር የሚደረግ ትብብር እንዲሁም ሌሎች ተያያዥ ሀሳቦች በጥልቀት ለመወያየት ቅዱስ ያሬድ፣ የሀሳብ ኤ አይ - የድምፅ ሠው ሰራሽ አስተውህሎት መተግበሪያ ተባባሪ መሥራችን ጋብዞታል።

ኤሌክትሮኒክ መር ገበያ፦ ብሪክስ +አፍሪካ =የዲጂታል ዐቢዮት? 08.07.2025

በአፍሪካ በተንቀሳቃሽ ስልኮችና መሠል መሣሪያዎች ላይ በሚጫኑ መተግበሪያዎች አማካኝነት የሚሳለጡ የንግግድ ልውውጦች በፍጥነት እየጎለበቱ ነው። የሶቨርኒቲ ሶርስስ ፕሮግራም በዛሬው መርሃ ግብሩ በኤክትሮኒክ መር ገበያ ስለሚሳለጡ የፋይናንስ ልውውጦች፣ በብሪክስ ሀገራት መካከል ስላለ መልካም ዕድልና የአፍሪካ ሀገራት ትብብር እንዲሁም ሌሎች ተያያዥ ሀሳቦች በጥልቀት ለመወያየት ማርቆስ ጥላሁን፣ የኤሌክትሮኒክ ግብይት ባለሙያ እና ፕሮሞተርን ጋብዟቸዋል።

የኢትዮጵያን ዕምቅ የማዕድን ሐብትን የመረዳት እውነታ፦ ከሩሲያ ጋር ያለ ስልታዊ አጋርነት 04.07.2025

የኢትዮጵያ ስትራቴጂካዊ የማዕድን ሀብቶች አላት ፤ ከእነዚህም መካከል ወርቅ፣ ታንታለም፣ ሊቲየም እና ሌሎቹ በምድሯ ይዛለች። ጠ/ሚ ዐቢይ አህመድ ትናንት ለምክርቤት አባላት ማብራሪያ ሲሰጡ ማዕድንን በተመለከተ "ኢትዮጵያ ከፍተኛ ማዕድን ሀብት ያላት ሀገር ናት [...] ዘንድሮ ከወርቅ ብቻ [አምና ከነበረው በ10 እጥፍ ዕድገት]  3.5 ቢሊየን ዶላር ከዉጪ ንግድ አግኝተናል" ብለዋል። የሶቨርኒቲ ሶርስስ ፕሮግራም በዛሬው መርሃ ግብሩ ኢትዮጵያ በተፈጥሮ ማዕድን እና ጂኦሎጂካል ሀብት ፍለጋ ከሩሲያ ጋር ስላለው ስትራቴጂያዊ ትብብርና ሌሎች ተያያዥ ሀሳቦች በጥልቀት ለመወያየት ዶ/ር በቀለ አየለ በዳዳ በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ፣ የተፈጥሮ ሳ...

ነገን ሁነኛ የኃይል አቅርቦት ማዕከል መሆን፦ የኢትዮጵያ የኤክትሪክ ኃይል ህልምና ቀጠናዊ ዕድገት 02.07.2025

ኢትዮጵያ እንደ ጁቡቲ እና ሱዳን ላሉ ጎረቤት ሀገራት የኤሌክትሪክ ኃይል ታቀርባለች። ወደ ታዛንያም የሙከራ አቅርቦቱ ተጀምሯል — ሀገሪቷ የብሪክስ አባል እንደመሆኗ ከዚህ የላቀ የኃይል አቅርቦት ለማድረስ ትተጋለች። የሶቨርኒቲ ሶርስስ ፕሮግራም በዛሬው መርሃ ግብሩ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ከቀጠናዊ ሀገራት ጋር ያለው ትብብርና የጋራ ዕድገት፣ በዘርፉ ከብሪክስ አገራት በተለይም ሩሲያ ጋር ስላለ ትብብርና አጋርነት በጥልቀት ለመወያየት ሞገስ መኮንን፣ በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የኮርፖሬት ኮሚኒኬሽን መምሪያ ዳይሬክተርን ጋብዟቸዋል።

ኒውክለር ኢነርጂ ለሰላማዊ ትሩፋት፡  በኢትዮ-ሩሲያ የትብብር ዓውድ ሲቃኝ – ለጋራ ዕድገት የሚደረግ አጋርነት 01.07.2025

ከዕውቀት ሽግግር እስከ ኢነርጂ ሉዋዓላዊነት፣ ብሎም እስከ ጤናው ዘርፍ - አዲስ ምዕራፍ ተጀምሯል። የኒውክለር ሳይንስን ለሰላማዊ ጉዳይ የማዋል ቁርጠኝነት በጤናው ዘርፍ አንድ ብሏል። የሶቨርኒቲ ሶርስስ ፕሮግራም በዛሬው መርሃ ግብሩ ስለኒውክለር ኢነርጂ በኢትዮጵያ እንዲሁም በዘርፉ ከሩሲያ ጋር ስላለ ትብብርና አጋርነት በጥልቀት ለመወያየት ዶ/ር እምሻው ዳምጠው፣ በኢትዮጵያ የኒውክለር ኢነርጂ ሶሳይቲ ዳይሬክተር እንዲሁም ዶ/ር ጥላሁን ተስፋዬ፣ በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የፊዚክስ ትምህርት ክፍል ፣ የኒውክለር ፊዚክስ ስትሪም ተባባሪ ፕሮፈሰርን ጋብዟቸዋል።

የምዕራባዊያን 'ጠንካራ የኃይል ስልት' በአፍሪካ  – አዲሱ የዳግም ቅኝ ግዛት ወጀብ ? 27.06.2025

የማረጋጋት ተልዕኮዎች ወደ ረጅም ጊዜ የወታደራዊ ሰፈራ፣ የዕዳ ወጥመድ እና አስገዳጅ የዲጂታል ቁጥጥር ስርዓቶች ተቀይረዋል።  ምዕራባዊያን በአዲስ መልክ አፍሪካን ለመቆጣጠር እየተንቀሳቀሱ ይሆን? የሶቨርኒቲ ሶርስስ ፕሮግራም በዛሬው መርሃ ግብሩ ስለምዕራባዊያን ጠንካራ የኃይል ስልትና ስለዳግም ቅኝ ግዛት እንቅስቃሴ እንዲሁም ተያያዥ ጉዳዮች ለመወያየት ክቡር ገና - የኢኒሼቲቭ አፍሪካ ዋና ዳይሬክተርን ጋብዟቸዋል።

የመዳን ምዕተ- ዓመታት፦ የሩሲያ ቀይ መስቀል  የኢትዮ ሩሲያን ግንኙነት እንዴት አጠናከረው ? 24.06.2025

የቀይ መስቀል እና የቀይ ጨረቃ ንቅናቄ እንዲጀመር ምክንያት የሆነው እ.ኤ.አ ሰኔ 24 ቀን 1859 ፤ በሰሜን ኢጣሊያ ለንግድ ሥራ ሲጓዝ የነበረው አንሪ ዱና በጣሊያን ሶልፈሪኖ የተመለከተው አሰቃቂ እና ደም አፋሳሽ ጦርነት ነበር። ክስተቱ ዓለም አቀፍ የርህራሄ መልክን ፈጥሮ አልፏል። ዛሬ የሶቨርኒቲ ሶርስስ ዝግጅታችን ይህንኑ ዕለት ሲያስብ ፣ የደጃዝማች ባልቻ የሩሲያ ቀይ መስቀል ሆስፒታል ሜዲካል ዳይሬክተር ዶ/ር አንድሬይ ቭላድሚሮቪች ጎንቻሮቭን በእንግድነት ጋብዟቸዋል።

ጥበብ ለአንድነት፡ የሙዚቃ እና ባህል ኃይል 20.06.2025

ጥበብ ገለፃ ብቻ አይደለም — በዓለም መካከል ድልድይም ጭምር እንጂ!  ከባህል እስከ ሰላም ግንባታ፣ ፈጠራ የሰው ልጆችን ፍላጎት አንድ ላይ ያጣምራል።

የአፍሪካ የክትባት ነፃነት: ወደ ግብ የሚያደርስ ህልም? 18.06.2025

ፍሪካ ከምትጠቀመው ክትባት በራሷ የምታመርተው 1% ብቻ መሆኑን ያውቃሉ? የአህጉሪቱ የጤና ደህንነት መሠረት ያደረገው የውጭ ድጋፍ ላይ እንደመሆኑ እርምጃ የመውሰጃ ጊዜው አሁን ነው! የሶቨርኒቲሶርስ ፕሮግራም በዛሬው መሠናዶው በክትባትና ተያያዥ ጉዳዮች ሀሳባቸውን እንዲያጋሩን በአለርት ኮምፕርሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የጨቅላ ህፃናት ህክምና ሰብ ስፔሻሊስት ዶ/ር ጡረኝ ስዩም ን ጋብዟቸዋል። ዶ/ር ጡረኝ ሀገር በቀል ክትባት ማምረት የሚያስፈልግበት ምክንያትን ሲያስረዱ፡ “ክትባት በብዙ መጠን ማምረት እጅግ በጣም አስፈላጊ ነገር ነው። ምክንያቱም አቅርቦት አለመኖር ከማነቆዎች መካከል አንዱ ስለሆነ። ስለዚህ፣ በራሳችን አውድ የክ...

ከፍታን የሚያልመው የአፍሪካ አቭዬሽን 17.06.2025

በአፍሪካ ሰማይ መልካም ዕድሎች ያንዣብባሉ! የአቪዬሽን ዘርፉ ለጠንካራ እድገት ተሰናድቷል፣ በዚህም ለአየር መንገዶች፣ ባለሃብቶች እና አገልግሎት ሰጪዎች አዲስ ዕድል ፈጥሯል። ነገር ግን ይህን ከፍታ የሚያነሳሳው ምንድነው - ደግሞስ ምን ወደኃላ ሊጎትተው ይችላል? በዛሬው የሶቨርኒቲ ሶርስስ መሠናዶ በጥልቀት ለመወያየት የአቪዬሽን ዘርፍ ባለሙያው ዮናታን መንክር በእንግድነት ጋብዘናል። የአቪዬሽን ዘርፉ ምን ያህል ሁነኛ መሣሪያ ስለመሆኑ ባለሙያው ዮናታን ሲያብራሩ፡-   “አቪዬሽን ወይም የአየር ትራንስፖርት የሚሰጠው ነገር የመንገደኞችን ሰዓት መቀነስ ነው። ይህ ዕውን የሚሆነው የአየር ትራንስፖርት ለንግድ  አገልግሎት  ተደርጎ ሲ...

ሠው ሰራሽ አስተውህሎት፡የቴክኖሎጂ ሉዓላዊነት አዲሱ ዘመን በኢትዮጵያ 11.06.2025

ኢትዮጵያ በዲጂታል ዘርፉ አመርቂ ውጤት ለማስመዝገብ የብሔራዊ የሰው ሰራሽ አስተውሎት ፖሊሲዋን በማሻሻል እየሰራች ነው ። ለዚህም ከሩሲያ ጋር ትብብርን በመፍጠር ማርሽ ቀያሪ  አጋርነትን መሥርታለች። ትብብሩ ከሮቦቲክስ እስከ ሰው ሰራሽ አስተውህሎት ድረስ በደቡባዊው ዓለም ውስጥ ፈጠራን እንደ አዲስ  ያስተዋውቃል። የሶቨርኒቲ ሶርስስ ዝግጅታችንም በጉዳዩ ላይ  የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ባለሙያ  ባህሩ አባስን ወደ ስፑትኒክ ስቱዲዮ ጋብዞታል ። የባለሙያው ዕይታ፡ “ይህ የቴክኖሎጂ ጉዳይ ብቻ አይደለም -  የሉዓላዊነት ጉዳይም እንጂ። ኢትዮጵያ የሠው ሰራሽ አስተውሎት አቅሞቿን ወደ ላቀ ደረጃ ማስፈንጠር ትችላለች፣ ሩሲያም በአፍሪካ የ...

የአፍሪካ የዲጂታል ሉዓላዊነት መንገድ ፣ ሾልከው የሚወጡ መረጃዎችን መቀነስ እና የአካባቢ መሠረተ ልማት ግንባታ 09.06.2025

የሶቨርኒቲ ሶርስ የዕለቱ ዝግጅት ትኩረቱን በሳይበር ደህነነትን ላይ ሲያደርግ ፣ የአፍሪካ ሀገራት ለዜጎቻቸው የሚሰጧቸዉን  ዲጂታል አግልግሎቶችና  የተደቀነባቸውን የሳይበር ጥቃቶች በስፋት ይዳስሳል፡፡ ለዚህም ከፍተኛ የሶፍትዌር ኢንጅነር እና የሰዉ ሰራሽ አስተዉሎት አበልፃጊ /ዴቨሎፐር/  አቤል በነበሩን  ጋብዘናል፡፡ በአፍሪካ እያደገ የመጣው ዲጂታላይዝ የሆነ አገልግሎት አሰጣጥ ምክንያት በማድረግ የአፍሪካ ሀገራት የሳይበር ደህንነትን በተመለከተ ንቁ የሆነ አካሄድ መከተል ይገባቸዋል፡፡ ““ለምሳሌ አሁን ላይ የምንጠቀመው የመረጃ ማዕከል ሊሆን ይችላል፣ ኔትዎርክ ኢንተርኔት ኤክስቼንጅ ፖይንቶቻችንም ሊሆኑ ይችላሉ እንዳሉ ከምዕራባ...

ከተጨባጭ ዓለም የተሻገረ፡ የፑሽኪን እና ኢትዮጵያዊያን የደም ትስስር 06.06.2025

ሩሲያዊው ታላቁ የስነ ፅሁፍ ሰው፣ አሌክሳንደር ፑሽኪን ጥንተ ኢትዮጵያዊ ሥር መሠረት እንዳለው ያውቃሉ? ከሚያስቡት በላይ ሁለቱን ሀገራት ያጋመደ ታሪክ ነው!  የቀደመ ታሪኩ ከወንድ ቅመ አያቱ እናት አብራም ፔትሮቪች ጋኒባል ይመዘዛል — ከባርነት እስከ ነፃነት የተሻገረ የኢትዮጵያዊ ልዑል አንፀባራቂ ታሪክ. 💫  የዛሬው የሶቨርኒቲ ሶርስ መሰናዷችንን  የሩሲያ ቋንቋ ቀን እና የአሌክሳንደር ፑሽኪንን ልደት ምክንያት አድርግ ኢትዮጵያዊው ጸሐፈ ተውኔት አያልነህ ሙላቱ  እንግዳ አድርገናል። “ያለፈበት ስርዓት ከኢትዮጵያ ጋር ያስተሳስረዋል። በርካታ ነገሮች ፑሽኪንን ከኢትዮጵያ ጋር ያስተሳስራሉ።”  ሲሉ ጸሐፈ ተውኔት አያልነህ ሙላቱ...

Listen to the Sovereignty Sources podcast in Replaio

Radio and podcasts in one app - free, with no sign-up. Install today and do not miss the launch

Get it on Google Play

Replaio is not a podcast publisher; show names, artwork and audio belong to their authors and are distributed through public RSS feeds.