Hana Haile

እናትHood | EnatHood

Kids AF ↓ 31 episodes

EnatHood is a podcast dedicated to motherhood and what a mother cares for. It covers a range of topics, including pregnancy, childbirth, baby care, parenting, and healthy lifestyle choices. It is brought to you by Hana Haile from http://enathood.comእናትHood ፖድካስት ስለ እናትነትና እና እናት ስለሚመለከታት ሁሉ ነገር ላይ ትኩረት የሰጠ ፖድካስት ነው። እርግዝና ፣ ወሊድ ፣ የልጅ እንክብካቤ ፣ ወላጅነት እና ጤናማ የአኗኗር ዘይቤ ምርጫዎችን ጨምሮ የተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮችን ይሸፍናል። ተዘጋጅቶ የሚቀርበው በሐና ኃይሌ ከ http://enathood.com ጦማር ነው።

Author

Hana Haile

Category

Kids

Podcast website

enathood.com

Latest episode

Apr 22, 2026

Where to listen?

Podcasts in the app Replaio Radio Coming soon

Podcasts are coming to the app soon. Install now and be the first to see a whole new take on podcasts

Get it on Google Play Install for free Android 5M+ downloads · 4.8 rating iOS soon

Episodes

Motherhood, working in health care, marriage and spiritual life with Dr. Betelehem Asnake 22.04.2026

Dr. Betelehem M. Asnake, MD is a board certified Anesthesiologiest. She is also global health director at the University of California Los Angeles. She is a founder and manager of Mulu Mentor, which help underrepresented and disadvantaged pre-medical students navigate the medical school application process through targeted mentorship. Dr. Betelehem M. Asnake is a wife and a mom of three children....

ምግብ መራጭ ልጆችን ለማገዝ | How to help picky eaters ከብሩክታይት ወልደማርያም MPH, CLE, ICCE,CWC #enathood #habesha 31.03.2026

In this episode, we discuss what picky eating is and what we can do to help kids eat variety of foods. Beruktawet Woldemariam(MPH), a mom of two and a professional with extensive experience in maternal and children health. https://mydoctor.kaiserpermanente.org/ncal/providers/beruktawetwoldemariam https://www.instagram.com/itsbrook_?igsh=MWptdTR2Yzg1Mjdleg==

Parenting with Purpose with Helina Girma - ወላጅነትን በአላማ ከህሊና ግርማ ጋር 17.03.2026

Helina Girma is an International Leadership Trainer, Public Speaker, and a Life Coach. She began her career as a Medical Technologist after she earned her Bachelors in Biomedical Sciences. Helina is author of a weekly reflection journal called Parenting with Purpose. It intends to guide parents through intentional reflection on their parenting journey. Parenting with Purpose journal: https://amzn....

የልጆች ቁጥር ላይ በእርግዝና ጊዜ የሚሰጡ አስተያየቶች - Opinions about number of children 28.02.2025

In this episode of the EnatHood podcast, I shared and discussed the opinions and comments I received regarding my fourth pregnancy, family size, and related topics. Read the EnatHood blog here: https://enathood.com/ Download a free hospital bag checklist here: https://artisanal-thinker-4913.ck.page/6ab4fb3db3 Use the promo code ENATHOOD to get a 10% discount on the Fidel Sound Amharic book here: h...

የእናቶች እና የልጆች ጤና ከብሩክታይት ወልደማርያም የህዝብ ጤና ባለሙያ ፣ የወሊድ እና የጡት ማጥባት አስተማሪ Maternal and Children Health 21.02.2025

በዚህ የእናትHood ፓድካስት ክፍል ከብሩክታይት ወልደማርያም ጋር ስለ እናቶች እና ጨቅላ ህፃናት ጤና ፣ ስለወሊድ፣ ስለ ግል ኑሮ እና ትምህርት ፣ ህክምና በአሜሪካ እና እናትነት ተጨዋውተናል። እንደምትደሰቱበት እርግጠኛ ነኝ። መልካም ቆይታ። ብሩክታይት ለማግኘት ፦ https://mydoctor.kaiserpermanente.org/ncal/providers/beruktawetwoldemariam የብሩክታይት IG :- https://www.instagram.com/itsbrook_?igsh=MWptdTR2Yzg1Mjdleg== Maternal and Children Health with Beruktawet Woldemariam, MPH, CLE, ICCE, CWC In...

እናትHood ፓድካስት ተመልሷል - EnatHoood podcast is back! 18.02.2025

EnatHood Podcast is Back! I’m Back! A New Chapter Begins. After a long break, I’m excited to reconnect with all of you! In this episode, I share my journey during my time away, what I’ve learned, and the inspiration fueling my return. Get ready for fresh content, exciting stories, and a glimpse into what the future holds. I can't wait to dive back in and share more with you all. Let’s embark on th...

የአራት ልጆች እናት ፣ የተሸላሚ የልጆች መፅሀፍ ፀሐፊ ፣ የሳይበር ደህንነት ኢንጂነር ከዘኒት ከማል | Zinet Kemal children book author 27.06.2024

በዚህ የእናትHood ፓድካስት ከዘኒት ከማል ጋር ስለ እናትነት ጉዞዋ ፣ ስለ ፃፈቻቸው አራት መፅሀፎች ፣ ስለ ስራዋ ፣ ኑሮ በሚኒሶታ አሜሪካ ከአራት ልጆች ጋር ፣ ስለ ዘጠኝ አመት እስከ ማስተርስ የትምህርት ጉዞዋ ፣ ስለ ስኬት ሚስጥሯ ጨምሮ በስራዋ ስለተሸለመቻቸው ለመዘርዘር ከሚያዳግቱ ብዙ ሽልማቶቿ እና ሌሎችም በጣም ጠቃሚ ነገሮች ተነጋግረናል። እንደምትደሰቱበት እርግጠኛ ነኝ። መልካም ቆይታ። Zinet Kemal is a mother of four, a multi-award winning cybersecurity advocate and a four times best-selling author. She is currently working as Clo...

የወላጅነት ጉዞ ከኦቲዝም ጋር ፤ የመልካም አባት ተምሳሌት ቢኒያም ንጉሴ #ethiopian #fatherlove #autism #enathood 17.06.2024

በዚህ የእናትHood ፓድካስት ክፍል ከወትሮ በተለየ የአባቶችን ታሪክ ይዘን መጥተናል። የመልካም አባት ተምሳሌት የሆነው ቢንያም ንጉሴ የወላጅነት የአባትነት ጉዞውን ፥ እና የሶስተኛ ልጁን ታሪክ ፥ ከኦቲዝም ጋር ተያይዞ የገጠመውን ውጣ ውረድ ፥ የተጠቀመበትን እና የረዳውን ሁሉ ነገር በሰፊው አጫውቶናል። ቢኒያም የሶስት ልጆች አባት ሲሆን ለልጆቹ በጣም ቅርብ እና በለት ተለት ኑሮአቸው ከፍተኛ ተሳትፎ የሚያደርግ አባት ነው። በተለይም ለሶስተኛ ልጁ በሚያደርገው በትጋት የተሞላ ክትተል የኦቲዝም ልዮ ፍላጎት ቢኖረው በጥሩ መሻሻሎችን እንዲያመጣ ሊረዳው ችሏል። 👉🏾 ቢኒያም ቲክቶክ - https://www.tiktok.com/@beny...

የሳይበር ደህንነት (cybersecurity) ለራሳችን እና ለልጆቻችን ከሳይበር ደህንነት ባለሙያ ከሁስኒ አወል ጋር 31.05.2024

በዚህ የእናትHood ፓድካስት ክፍል የሳይበር ደህንነት (cybersecurity) ኢንጅነር እና አማካሪ ከሆነው ሁስኒ አወል ጋር የራሳችን እና የልጆቻችንን የሳይበር ደህንነት እንዴት እንደምንጠብቅ ተነጋግረናል። ጠቃሚ መረጃዎች እንደምታገኙበት እርግጠኛ ነኝ። መልካም ቆይታ። ሁስኒ አወል የሳይበር ደህንነት (cybersecurity) ኢንጅነር እና አማካሪ ነው። በአሁን ጊዜ ለToyota Financial Services በአማካሪነት እየሰራ ይገኛል። በኢትዮጵያ በግል እና የመንግስት የሳይበር ደህንነት ስራዎች ላይ በመሳተፍ ለማህበረሰባችን በሙያው አገልግሎት ይሰጣል። #amharic #ethiopia #ethiopian #cybersecurity...

ከAyla’s የልጆች መጫወቻ እና መማሪያ አዘጋጅ ሳራ ሱከር Ayla’s Kids Learning Tools with Sara Suker #የልጆች #ኢትዮጵያ #እናት 14.05.2024

በዚህ የእናትHood ፓድካስት ከሳራ ሱከር ጋር ስለ እናትነት ጉዞዋና ለልጆች መጫወቻ እና መማሪያ ስለምታዘጋጃቸው ነገሮች ፣ ስለ ቢዝነስ እና ሌሎችም ነገሮች ተነጋግረናል። ጠቃሚ ሆኖ እንደምታገኙት እርግጠኛ ነኝ። ሳራ የሁለት ልጆች እናት ናት። በቅርቡ የሙሉ ጊዜ ስራዋን በቤት ከልጆችዋ ጋር ለመሆን ወስና በቤት ቤተሰቧን እየተንከባከበች ትገኛለች። እንዲሁም ለልጆች መጫወቻ እና መማሪያ የሚሆኑ የተለያዮ በእጇ የምታዘጋጃቸውን ነገሮች ለገበያ ታቀርባለች። ስለገጠሟት ተግዳሮቶች ፣ ከእናትነት ልምዷ ፣ እና ሌሎችም ነገሮችን አካፍላናለች። መልካም ቆይታ!! Instagram : aylas_playthingz TikTok : Ayla's play...

ከሆስፒታል ዉጪ ለመውለድ ከሩዋንዳ ወደ አሜሪካ ፤ ለምን? ከህይወቴ ታደሰ ጋር (MPH) 08.05.2024

በዚህ የእናትHood ፓድካስት ክፍል የማህበረሰብ ጤና ባለሙያ (MPH) ከሆነችው ከህይወቴ ታደሰ ጋር ስለ ሶስተኛ ልጇ የወሊድ ዝግጅት ፣ ለምን ከሩዋንዳ ወደ አሜሪካ ተጉዛ ከሚድዋይፍ ጋር ለመውለድ እንዳቀደች ፣ የእናትነት ጉዞዋን እና ለሎችም ተያያዥ ነገሮችን ተጨዋውተናል። በጣም ብዙ ጠቃሚ መረጃዎችን አካፍላናለች። ሀሳብ አስተያየታችሁን አካፍሉን። ጥያቄ ካላችሁም ብትልኩልን እንመልሳለን። ተመልክታችሁ ወይም አድምጣችሁ ከወደዳችሁት ለጓደኛ ወይም ለወዳጅ ለቤተሰብ አካፍሉት። ህይወቴ የሶስት ልጆች እናት ናት። እንደ እቅድዋና ምኞትዋ ሶስተኛ ልጇን በ ማዋለጃ ማዕከል (Birthing Center) ፍፁም ተፈጥሮአዊ በሆነ መንገድ ወል...

ወሊድ በአሜሪካ ከሆስፒታል ውጪ ፣ እናትነት ፣ ኑሮ በተለያየ አገር እና ጉዞ ከህይወቴ ታደሰ ጋር (ክፍል 1) 01.05.2024

በዚህ የእናትHood ፓድካስት ክፍል የማህበረሰብ ጤና ባለሙያ (MPH) ከሆነችው ከህይወቴ በቀለ ​⁠ ጋር ስለ ሶስተኛ እርግዝናዋ እንዴት ለወሊድ እየተዘጋጀች እንዳለች ፣ እናትነት ፣ በተለያዩ አገራትና ባህል ልጆችን ማሳደግ ፣ ወሊድ በሆስፒታል እና በማዋለጃ ማዕከል (birthing center) እና የመሳሰሉትን ነገሮች ተጨዋውተናል። መልካም ቆይታ። ህይወቴ የሶስት ልጆች እናት ናት። በማህበረሰብ ጤና ማስተርስ አላት (Masters of Public Health) ጤናማ ተፈጥሮአዊ አኗኗር ላይ ትኩረት ታደርጋለች። ህይወቴ ጤናን ከተለመደው የህክምና እና በመድሀኒት ማከም በተለየ መልኩ አማራጭና ሁሉን አቀፍ የሆነ ወይም alternati...

ኦቲዝምና ተመሳሳይ ኑሮሎጂክ መዛባትን የሚረዳ አመጋገብ / A diet that helps with Autism and related disorder 24.04.2024

Our latest podcast opens the world of autism motherhood, where challenges meet triumphs, especially when raising a child with autism. Let’s discover together Sel Seyoum’s book on how a healing diet program tailored for autism can be a game-changer, offering crucial support and day to day management. From modern cities to remote corners of countries, families with children in the spectrum and relat...

የጥቁር እናት ነኝ ፀሀፊ እና ገጣሚ መሰረት ክንፈ ጋር የተደረገ ቆይታ - ስለ ኦቲዝም #autismawareness #enathood 09.04.2024

በዚህ የእናትHood ፓድካስት ክፍል ከመሰረት ክንፈ ጋር ስለ እናትነት ጉዞዋ ፥ ልዮ ፍላጎት ያለውን ልጅዋን ስታሳድግ የሚገጥማትን የለት ተለት ኑሮ ፥ ስለመፅሀፏ “የጥቁር እናት ነኝ” ፥ ስለምትሰራው የበጎ አድራጎት ስራ እና ሌሎችም ተጨዋውተናል። መሰረት ክንፈ “የጥቁር እናት ነኝ” መፅሀፍ ፀሀፊ እና ገጣሚ ስትሆን የሁለት ወንድ ልጆች እናት ናት። የመጀመሪያ ልጇ ኦትስቲክ ወይም ልዮ ፍላጎት ያለሁ በመሆኑ የገጠማትን ውጣ ውረድ ፥ የህይወት እይታዋን እና ትዝታዎችዋን በግጥም አስውባ በማቅረብ ትታወቃለች። “የጥቁር እናት ነኝ” መፅሃፍ ሽያጭ ለበጎ አድራጎት በማዋል በኢትዮጵያ የሚገኙ የተቸረጉ እናቶችና ልጆችን እየረዳች ለብዙዎች...

ስለ ኦቲዝም ከሊያ ስዮም ከ Reaching Families ኘሬዝዳንት ጋር / Autism with Leah Seyum 02.04.2024

በዚህ የእናትHood ፓድካስት ክፍል ከሊያ ስዩም የ Reaching Families Advocacy and Support Group መስራችና ኘሬዝዳንት ጋር ስለ ኦቲዝም (ልዩ ፍላጎት ያላቸው ልጆች) ሰፋ ያለ ውይይት አድርገናል። ሊያ የግል የእናትነት ጉዞዋን እንዲሁም እየመራች ያለችው የበጎ አድራጎት ድርጅት ዉስጥ የሚሰሩ ስራዎች እና ማህበረሰባችን ስለ ኦቲዝም ማወቅ ያለበትን ሁሉ ከሙያ ልምዷ ጨምራ አካፍላናለች። መልካም ቆይታ። ✨ሊያ ስዩም የአራት ልጆች እናት ስትሆን ሁለቱ ልጆችዋ ኦትስቲክ ወይም ልዩ ፍላጎት ያላቸው ናቸው። በዚህም የተነሳ ልዩ ፍላጎት ያላቸው ልጆችን እና ወላጆችን የሚደግፍ የበጎ አድራጎት ድርጅት መስርታ ዳላስ...

ስለ GAPS አመጋገብ እና በቤት ውስጥ ልጆችን ትምህርት ማስተማር ከሜላት ማሞ ጋር (MPH) ክፍል 2 - Gut & Psychology Syndrome 17.03.2024

በዚህ የእናትHood ፓድካስት ክፍል ካለፈው የቀጠለ ዉይይት ከሜላት ማሞ ጋር ስለ GAPS አመጋገብና ልጆችን በቤት ውስጥ ስለማስተማር ተጨዋውተናል። ሜላት በተከታታይ ሁለት ክፍሎች የልጇን የቆዳ ህመም (Eczema) ለማዳን እና ለቤተሰቧ ጤና የረዳትን የ GAPS (Gut and Psychology Syndrome) የአመጋገብ ልምድ ላይ ያላትን እውቀትና ልምድ እንዲሁም የለት ተለት ተሞክሮ አካፍላናለች። ጠቃሚ ሆኖ እንደምታገኙት እርግጠኛ ነኝ። ሐሳብና አስተያየታችሁን ላኩልን። መልካም ቆይታ!! ሜላት የሁለት ልጆች እናት ናት። በሙያዋ የማህበረሰብ ጤና ስፔሻሊስት እና licensed ASCP ናት። በአሁን ጊዜ ሙሉ ጊዜዋን በቤት ውስጥ...

ስለ GAPS አመጋገብ ፣ እናትነት እና ኑሮ በአቡዳቢ ከሜላት ማሞ (MPH, licensed ASCP) 20.02.2024

በዚህ የእናትHood ፓድካስት ክፍል ከሜላት ማሞ ጋር ስለ እናትነት ፣ በቤት ውስጥ ሙሉ ጊዜ መሆንና ቤተሰብን መንከባከብ ፣ እና ስለ ኑሮ በአቡዳቢ ተጨዋውተናል። በሰፊው የልጇን የቆዳ ህመም (Eczema) ለማዳን እና ለቤተሰቧ ጤና የረዳትን የ GAPS (**Gut and Psychology Syndrome) የአመጋገብ ልምድ ላይ ያላትን እውቀትና ልምድ እንዲሁም የለት ተለት ተሞክሮ አካፍላናለች።** ጠቃሚ ሆኖ እንደምታገኙት እርግጠኛ ነኝ። መልካም ቆይታ!! ሜላት የሁለት ልጆች እናት ናት። በሙያዋ የማህበረሰብ ጤና ስፔሻሊስት እና licensed ASCP ናት። በአሁን ጊዜ ሙሉ ጊዜዋን በቤት ውስጥ በመሆን ልጆችዋን በማሳደግ እና ቤተሰ...

የቆዳ ውበት አጠባበቅ ፣ እራስን መንከባከብ እና እናትነት ከHanSim Skin ባለቤት ምልጃዬ ስሜ ጋር Skincare, Self-care, & Motherhood 07.12.2023

በዚህ የእናትHood ፓድካስት ክፍል ከምልጃዬ ስሜ የሃንሲም የቆዳ መንከባከቢያ ምርቶች - HanSim Skin መስራች እና ባለቤት ጋር የፊትና የሰውነታችን ቆዳ እንዴት መንከባከብ እንደምንችል ተወያይተናል። በተጨማሪም እራስን መጠበቅ እና እናትነት እንዴት አብሮ ማስኬድ ይቻላል የሚሉ ጉዳዮች ላይ ተነጋግረናል። የቢዝነስ ስራዎችዋን ከቤተሰብ ሃላፊነት ጋር እንዴት እንደምታስኬድ የግል ልምዷን ጨምራ ጠቃሚ መረጃዎችን አካፍላናለች። መልካም ቆይታ። የ HanSim ምርቶችን ለማግኘት:- HanSim Online Store 👉🏾 https://hansimskin.com/ በአዲስ አበባ የሚገኙ መሸጫና አገልግሎት የሚሰጥበት ቦታ:- 1. የቆዳ መን...

ፍጹም ተፈጥሮአዊ ወሊድ በዉሃ ውስጥ ፤ የሶስተኛ ልጃችን የወሊድ ታሪክ - Super Natural Water Birth 15.11.2023

የዚህ ክፍል የእናትHood ፓድካስት ስለ ሶስተኛ ልጄ የወሊድ ታሪክ የተመለከተ ነው። የወለድኩት በወሊድ ማእከል/birthing center ውስጥ ያለ ምንም መድሀኒት ፣ ፍፁም ተፈጥሮአዊ በሆነ መልኩ ከሚድዋይፎች እገዛ ጋር ነበር። ለሁለተኛ ጊዜ ሰላም የሰፈነበት ወሊድ በዉሀ ዉስጥ ተሳክቶልኛል። ቪዲዮን መመልከት ከፈለጋችሁ በYouTube ታገኙታላችሁ።

የወሊድን ምጥ በኢፒዱራል አንስቴዚያ ወይስ ያለ ኢፒዱራል አንስቴዚያ Childbirth with Epidural Anesthesia vs without 30.09.2023

በዚህ የእናትHood ፓድካስት ክፍል የወሊድ ምጥ በኢፒዱራል አንስቴዚያ (Epidural Anesthesia) ወይስ ያለ ኢፒዱራል አንስቴዚያ በሚል በሁለቱም መንገድ ያለኝ ልምድ አካፍያለሁ። የመጀመሪያ ልጄን በኢፒዱራል አንስቴዚያ ስወልድ ያጋጠመኝን ፤ ሁለተኛ ልጄን ያለምንም መድሀኒት ስወልድ የነበረውን ሁኔታ በንፅፅር እና ሶስተኛ ለመውለድ እንዴት እየተዘጋጀሁ እንደሆነ ጨምሮ ተያያዝ ነገሮችን አንስቻለሁ። ጠቃሚ ሆኖ እንደምታገኙት ተስፋ አደርጋለሁ። መልካም ጊዜ!! 👉🏾  Everything You Need to Know about Epidural Anesthesia with Dr. Betelehem M. Asnake, MD – ስለ ኢፒዶራል አን...

ስለ ኢፒዶራል አንስቴዚያ ከዶ/ር ቤተልሔም አስናቀ ጋር - Everything You Need to Know about Epidural Anesthesia 15.09.2023

በዚህ የእናትHood ፓድካስት ክፍል አንስቲዚኦሎጂስት ከሆነችው ዶ/ር ቤተልሔም አስናቀ ጋር ስለ ኢፒዶራል አንስቴዚያ/Epidural Anesthesia ማለትም በአብዛኛው ጊዜ በወሊድ እና በቀዶ ጥገና ጊዜ ስለሚሰጠው የማደንዘዣ መድሀኒት ተወያይተናል። ሙያዊ ልምዷን ጨምራ በኢፒዶራል አንስቴዚያ ዙሪያ በተደጋጋሚ ለሚነሱ ጥያቄዎች ሁሉ መልስና ማብራሪያ ሰጥታናለች። መልካም ቆይታ። Dr. Betelehem M. Asnake, MD is a board certified Anesthesiologist and anesthesia global health director at the University of California Los Angeles. 👉🏾 Dr. Bete...

በእርግዝና ጊዜ ማጥባት እና ሁለት ልጆችን በጋራ ማጥባት - Breastfeeding during Pregnancy and Tandem Nursing 02.09.2023

በሶስት አመት የጡት ማጥባት ጉዞዬ ውስጥ ያደረግኩት በእርግዝና ጊዜ ማጥባት እና ሁለት ልጆችን በጋራ ማጥባት ብዙ ጥያቄና አስተያየት ያስተናገድኩበት ነው። ሳይንስ የሚለውን እና የራሴን ልምድ በዚህ ክፍል አካፍያለሁ። ጠቃሚ ሆኖ እንደምታገኙት ተስፋ አደርጋለሁ። 💫 ተመልክታችሁ ወይም አድምጣችሁ ከወደዳችሁት ለጓደኛ ወይም ለወዳጅ ለቤተሰብ አካፍሉት። 🌟 የቀደሙ የጡት ማጥባት ዉይይቶች 👉🏾 የጡት ማጥባት ጥቅም ለልጆች https://youtu.be/WodjPq3RHJE?si=Pw9CGJajEzNrfeCs 👉🏾 የጡት ማጥባት ጥቅም ለእናቶች https://youtu.be/TVHwglULAD4?si=oKG_ePx44sxwLHQb 👉🏾 የእናት...

የእናት ጡት ወተት ማለብ ጠቃሚ ልምዶች ከብርቱካን አሊ (CRNA, DNP) - Breast Milk Pumping Best Practice 27.08.2023

የነሀሴን ወር የጡት ማጥባት ግንዛቤ ወር መሆኑን አስመልክተን በተከታታይ የጡት ማጥባት ዉይይቶችን እያደረግን በመሆኑ ከአድማጮች የተነሱ ስለ ጡት ወተት ማለብ እና አቆይቶ መጠቀም ጥያቄዎችን ከብርቱካን አሊ ጋር በመወያየት ከልምድና ከሙያዋ ብዙ ጠቃሚ መረጃዎችን አካፍላናለች። ብርቱካን የሶስት ልጆች እናት ናት። በሙያዋ Certified Registered Nurse Anesthetist, (CRNA DNP) ማለትም ነርስ እና የማደንዘዣ ወይም የሰመመን መድሀኒት ሰጪ ናት። 🌟 በውይይታችን የተጠቀሱ ጡት ወተት ማለቢያ እና ማስቀመጫ - Medela Breast Pump / የጡት ወተት ማለቢያ https://www.medela.us/breastfee...

የእናት ጡት ወተት ጥቅም ለልጆች ከህይወቴ በቀለ (MPH) - Benefits of Breast Milk for Children 13.08.2023

የነሀሴን ወር የጡት ማጥባት ግንዛቤ ወር መሆኑን አስመልክተን በዚህ የእናትHood ፓድካስት ክፍል የማህበረሰብ ጤና ባለሙያ (MPH) ከሆነችው ከህይወቴ በቀለ ጋር ስለ የእናት ጡት ወተት ለልጆች ያለውን ጥቅም ተወያይተናል። እናም ጠቃሚ መረጃዎችን አካፍላናለች። በተጨማሪም በህይወቴ የYouTube channel ላይ ጡት ማጥባት ለእናቶች ያለውን ጥቅም። ተወያይተናል። በጣም ጥሩ መረጃዎችን የያዘ ነው። እንደተመለከቱት እጋብዛችሁአለሁ። ሀሳብ አስተያየታችሁን አካፍሉን። እንዲሁም ጥያቄ ካላችሁም ብትልኩልን እንመልሳለን። 💫ተመልክታችሁ ወይም አድምጣችሁ ከወደዳችሁት ለጓደኛ ወይም ለወዳጅ ለቤተሰብ አካፍሉት።

የእናቶች ታሪክ በአለም ዙሪያ - ረቂቅ አዕምሮ ከዳላስ (Mother's Stories Around the World) 28.07.2023

በዚህ የእናትHood ፓድካስት ክፍል ረቂቅ አዕምሮ የእናትነት ጉዞዋ አካፍላናለች። እናትነት ለሷ ምን ማለት እንደሆነ ፣ የዕለት ተለት ስኬትና ተግዳሮቶችን ጨምሮ እና ኑሮ በዳላስ ቴክሳስ ምን እንደሚመስል አጫውታናለች። መልካም ቆይታ። ረቂቅ አዕምሮ የአንድ ቆንጆ ሴት ልጅ እናት ናት። ከባለቤቷ እና ከልጇ ጋር በቴክሳስ ዳላስ ትኖራለች። ሙሉ ጊዜዋን በቤት ውስጥ በመሆን ልጇን እና ቤተሰቧን ትንከባከባለች።

Listen to the እናትHood | EnatHood podcast in Replaio

Radio and podcasts in one app - free, with no sign-up. Install today and do not miss the launch

Get it on Google Play

Replaio is not a podcast publisher; show names, artwork and audio belong to their authors and are distributed through public RSS feeds.