ECFC in Finland
Ethiopian Christian Fellowship Church in Finland
This is a podcast from the Ethiopian Christian Fellowship in Finland, where you can listen to biblical teachings, messages, and sermons. May God bless all our listeners.
Author
ECFC in Finland
Category
Podcast website
Latest episode
Jul 5, 2026
Where to listen?
Podcasts in the app Replaio Radio Coming soonPodcasts are coming to the app soon. Install now and be the first to see a whole new take on podcasts
Episodes
047_የእግዚአብሔር ምህረት ክፍል 2 14.04.2019 47:42
ይህ "የእግዚአብሔር ምህረት" በሚል ርዕስ በወንጌላዊ ዘገዬ መኮንን የቀረበ የእግዚአብሔር ቃል ቀጣይ ክፍል ነው::
046_የእግዚአብሔር ምህረት ክፍል 1 07.04.2019 54:29
የእግዚአብሔር ምህረት በሚል ርዕስ በወንጌላዊ ዘገዬ መኮንን የቀረበ የእግዚአብሔር ቃል መልዕክት::
045_የጌታን ራት የሚካፈል ማን ነው? 31.03.2019 31:56
"የጌታን ራት የሚካፈል ማን ነው?" በሚል ርዕስ በ1ቆሮ. 11:26-32 ባለው ክፍል ላይ ተመሥርቶ በወንጌላዊ ዘገዬ መኮንን የቀረበ የእግዚአብሔር ቃል መልዕክት::
044_እግዚአብሔርን የመምሰል ምስጢር 24.03.2019 57:29
"እግዚአብሔርን የማወቅ ምስጢር ታላቅነት" በሚል ርዕስ በወንድም ተከለ ማርቆስ (ዶ/ር) የቀረበ የእግዚአብሔር ቃል መልዕክት::
043_የጌታ ራት 17.03.2019 59:24
"የጌታ ራት" በሚል ርዕስ በወንጌላዊ ዘገዬ መኮንን የቀረበ የእግዚአብሔር ቃል መልዕክት ነው::
042_የልብ ንጽህና ክፍል 3 10.03.2019 1:08:25
ይህ "የልብ ንጽህና" በሚል ርዕስ በወንድም ያቬሎ ናታዬ እየቀረበ ያለው ተከታታይ የእግዚአብሔር ቃል ትምህርት የመጨረሻው ክፍል ነው:: የዚህ ክፍል ዋና ትኩረት የልብ ንጽህና ፋይዳዎች የሚል ሲሆን ሁለት መሠረታዊ አሳቦች ትኩረት ተሰጥቶባቸዋል:: 1) የልብ ንጽህና እግዚአብሔርን እንድናይ ይረዳናል:: 2) የልብ ንጽህና የእግዚአብሔርን ፈቃድ እንዳንስት ይረዳናል::
41_እግዚአብሔር በቤታችን እንዴት ነው? 03.03.2019 46:43
"እግዚአብሔር በቤታችን እንዴት ነው?" በሚል ርዕስ በእህት ለምለም ጌታቸው የቀረበ የእግዚአብሔር ቃል መልዕክት::
040_የልብ ንጽህና ክፍል 2 24.02.2019 1:00:50
ይህ ትምህርት "የልብ ንጽህና" በሚል ርዕስ በማቴ. 5:8 ላይ ተመሥርቶ በወንድም ያቬሎ ናታዬ የሚቀበው ተከታታይ መልዕክት ሁለተኛው ክፍል ሲሆን ልብን እንዴት ንጹህ ማድረግ ይቻላል? የሚለውን ጥያቄ የሚመልስ ክፍል ነው::
039_የልብ ንጽህና ክፍል 1 17.02.2019 56:06
የልብ ንጽህና በሚል ርዕስ በማቴ. 5:8 ላይ ተመሥርቶ በወንድም ያቬሎ ናታዬ ያታሣ የቀረበ ተከታታይ የእግዚአብሔር ቃል መልዕክት የመጀመሪያው ክፍል ነው:: ይህ ክፍለ ጊዜ "የልብ ንጽህና ምንድን ነው?" እና "ስለልብ ንጽህና ማሰብና መማር አስፈላጊ ነውን?" የሚሉ ጥያቄዎችን ይመልሳል::
038_ኢየሱስን መውደድ 10.02.2019 38:54
ኢየሱስን መውደድ በሚል ርዕስ በሉቃ. 7:36-50 ባለው ክፍል ላይ ተመሥርቶ በወንጌላዊ ዘገዬ መኮንን የቀረበ የእግዚአብሔር ቃል መልዕክት!
037_አንተም እንዲሁ አድርግ 03.02.2019 44:53
"አንተም እንዲሁ አድርግ" በሚል ርዕስ በሉቃስ ወንጌል ምዕራፍ አሥር ላይ ተመሥርቶ በወንጌላዊ ዘገዬ መኮንን የቀረበ የእግዚአብሔር ቃል መልዕክት::
036_የእምነት ተግዳሮቶች 27.01.2019 1:00:58
የእምነት ተግዳሮቶች በሚል ርዕስ በወንድም ተከለ ማርቆስ (ዶ/ር) የቀረበ የእግዚአብሔር ቃል መልዕክት::
035_እምነት 20.01.2019 1:04:32
"እምነት" በሚል ርዕስ በወንድም ተከለ ማርቆስ (ዶ/ር) የቀረበ የእግዚአብሔር ቃል መልዕክት::
034_እግዚአብሔርን ማመስገን! 13.01.2019 58:21
"እግዚአብሔርን ማመስገን" በሚል ርዕስ በወንጌላዊ ዘገዬ መኮንን የቀረበ የእግዚአብሔር ቃል መልዕክት!
33_የዕይታ ለውጥና የግል ህይወት ተሃድሶ 06.01.2019 54:19
ይህ የእግዚአብሔር ቃል መልዕክት በመዝሙር ምዕራፍ 73 ላይ ተመሥርቶ በወንድም ያቬሎ ናታዬ የቀረበ ሲሆን የመልዕክቱ ማዕከላዊ አሳብ ዕይታችን በዙሪያችን ባሉ ሰዎችና ሁኔታዎች ላይ ስናደርግ ሳናውቀው ከመንፈሳዊ ከፍታችን እንንሸራተታለን ነገር ግን በእግዚአብሔር ህልውና ውስጥ ስንሆንና እንደ እግዚአብሔር ዕይታ ነገሮችን ማየት ስንጀምር የነገሮች ሁሉ ፍጻሜ ግልጽ ይሆንልናል የሚል ነው::
032_እግዚአብሔር ዓላማዬ ነው! 31.12.2018 45:53
"እግዚአብሔር ዓላማዬ ነው!" በሚል ርዕስ በዘጸ.17:8-16 ላይ ተመሥርቶ የቀረበ የእግዚአብሔር ቃል መልዕክት ነው::
031_ጀግና አይታዘንለትም! 30.12.2018 1:07:23
"ጀግና አይታዘንለትም!" በሚል ርዕስ በሉቃ. 23:26-29 ባለው ክፍል ላይ ተመሥርቶ በፓስተር ዮሴፍ ፈንታው የቀረበ የእግዚአብሔር ቃል መልዕክት ሲሆን የመልዕክቱ ዋና ጭብጥ ኢየሱስ ስለሰው ልጆች መከራን የተቀበለው እንዲናዝንለት ሳይሆን እንድናምንበት ነው:: ሊታዘንላቸው የተገባቸው የተደረገላቸውን ያልተረዱና ክርስቶስን ያልተቀበሉት ናቸው::
30_ንጉሥ ለሚወደው ሰው እንዲህ ይደረግለታል! 29.12.2018 52:59
"ንጉሥ ለሚወደው እንዲህ ይደረግለታል!" በሚል ርዕስ በአስቴር ምዕራፍ 6 ላይ ተመሥርቶ የቀረበ የእግዚአብሔር ቃል መልዕክት ነው:: የመልዕክቱ ማዕከላዊ አሳብ ንጉሥ ሲወድ በንጉሥ አቅም ልክ መሆኑን ለማስገንዘብና እኛም በእግዚአብሔር የተወደድነው ለመረዳት ከአቅም በላይ በሆነ የእግዚአብሔር ፍቅር መሆኑን ማስገንዘብ ነው::
29_የእግዚአብሔር ክብር 29.12.2018 50:38
"የእግዚአብሔር ክብር" በሚል ርዕስ በፓስተር ዮሴፍ ፈንታው በ2ኛ ዜና 7:1-10 ባለው ክፍል ላይ ተመሥርቶ የቀረበ የእግዚአብሔር ቃል መልዕክት ሲሆን በመልዕክቱም የእግዚአብሔር ክብር ሲመጣ የሚሆኑ 4 መሠረታዊ ነገሮች ተዳስሰዋል::
28_ምርኮው ይመለሳል! 23.12.2018 44:32
ይህ የእግዚአብሔር ቃል መልዕክት "ምርኮው ይመለሳል" በሚል ርዕስ በ1ሳሙኤል ምዕራፍ 30 ላይ ተመሥርቶ በወንጌላዊ ዘገዬ መኮንን የቀረበ ሲሆን የመልዕክቱ ማዕከላዊ አሳብ "ነገራችን በጠላት ሲወሰድብንና የሚናደርገው ግራ ሲገባን 1) ልባችንን በእግዚአብሔር ማበርታት አለብን 2) ማድረግ የሚገባንን እንዲያሳውቀን እግዚአብሔርን በጸሎት መጠየቅ አለብን 3) ምርኮአችንን ለመመለስ እግዚአብሔር አድርጉ የሚለንን ማድረግ አለብን" የሚል ነው::
027_ህዝቡን ከኃጢአታቸው ያድናቸዋል! 16.12.2018 43:57
ይህ የእግዚአብሔር ቃል መልዕክት "ህዝቡን ከኃጢአታቸው ያድናቸዋል" በሚል ርዕስ የገና በዓልን አስመልክቶ በወንጌላዊ ዘገዬ መኮንን የቀረበ ሲሆን የመልዕክቱ ዋና ማዕከላዊ ትኩረት ኢየሱስ ክርስቶስ ወደ ምድር የመጣበትን ዋና ዋና ዓላማዎች መተንተን ነው::
026_ምንጭ 09.12.2018 48:05
ይህ የእግዚአብሔር መልዕክት "ምንጭ" በሚል ርዕስ በወንጌላዊ ዘገዬ መኮንን የቀረበ ሲሆን የካሌብ ሴት ልጅ በነበረችው በአክሳ ህይወት ላይ ተመሥርቶ የቀረበ ነው:: የመልዕክት ዋና መልዕክት ስለምንጭ አስፈላጊነት ነው [ኢያ. 15.16-19ና መሳ. 1:11-15]:: ምንጭ ለአንድ የእርሻ መሬት ፍሬያማነት አስፈላጊ እንደሆነ ሁሉ መንፈስ ቅዱስም በአንድ ሰው ህይወት ውስጥ ላለ የእግዚአብሔር ጸጋ ፍሬያማነት እጅግ አስፍላጊ ነው::
025_ምን አላችሁ? ምን ይዛችኋል? 02.12.2018 48:37
ይህ መልዕክት "ምን አላችሁ? ምን ይዛችኋል?" በሚል ርዕስ በእህት ለምለም ጌታቸው የቀረበ ሲሆን የመልክቱ ማዕከል እግዚአብሔር ባልተጠበቀ ሁኔታ ወስጥ ባልተጠበቁ ሰዎች ሌሎችን መርዳት እንደምችል የሚያስረግጥ መልዕክት ነው:: ለምሳሌ: 1) አንድ ህጻን ልጅ በያዘው ዳቦና ዓሣ አምስት ሺህ ህዝብ መመገቡ 2) በሰታፕታ መንደር እፍኝ ዱቀት ብቻ በነበራት ባልተት ኤልያስን መመገቡና 3) ባዶ የሚመስል የዘይት ማድጋን ተጠቅሞ የነቢይ ሚስት የነበረችን ባልቴት ባለዕዳ ልጆቿን እንዳይወስድባት መርዳቱ::
24_እግዚአብሔርን መከተል 25.11.2018 56:39
ይህ "እግዚአብሔርን መከተል" በሚል ርዕስ በወ/ዊ ዘገዬ መኮንን የቀረበ የእግዚአብሔር ቃል መልዕክት ነው:: መልዕክቱ በኦሪት ዘኁልቁ ምዕራፍ 13 ላይ የተመሠረተ ሲሆን ማዕከላዊ አሳቡም እግዚአብሔርን በመከተል ሂዴት ውስጥ ትኩረታችን መሆን ያለበት ዙሪያችን ላይ በሚታየው ላይ ሳይሆን እግዚአብሔር በሰጠን የተስፋ ቃል ላይ ነው የሚል ነው::
023_የመንግሥተ ሰማያት መክፈቻዎች 18.11.2018 1:08:23
"የመንግሥተ ሰማያት መክፈቻዎች" በሚል ርዕስ በወንጌላዊ ዘገዬ መኮንን የቀረበ የእግዚአብሔር ቃል መልዕክት:: ይህ መልዕክት "ቤተ ክርስቲያን" በሚል ርዕስ እየቀረበ ያለው ተከታታይ ትምህርት ክፍል ነው:: የመልዕክቱ ጭብጥ በእግዚአብሔር መንግሥት ውስጥ ሥራ ለመሥራት የሚረዱ ቁልፎች 1) የእግዚአብሔር ቃል 2) የኢየሱስ ስም 3) ጸሎትና 4) መንፈስ ቅዱስ መሆናቸውን ማስገንዘብ ነው::
Similar podcasts
Replaio is not a podcast publisher; show names, artwork and audio belong to their authors and are distributed through public RSS feeds.