DW | Amharic - News
News, Analysis and Service from Germany and Europe - in 30 Languages
Be sure to visit the podcast's website and support the creator: www.dw.com
Where to listen?
Podcasts in the app Replaio Radio Coming soonPodcasts are coming to the app soon. Install now and be the first to see a whole new take on podcasts
Episodes
የትግራይ ክልል ህዝብ አስተዳዳሪዎቹን መምረጡ መረጋጋቱን ያረጋግጥለት ይሆን? 14.10.2026
በትግራይ ክልል የአካባቢ መስተዳድሮች መዋቀር እና ወቅታዊ ሁኔታ
የቀጠለው የደቡብ ወሎና የሰሜን ሸዋ ውጊያ 14.10.2026
በአማራ ክልል ደቡብ ወሎ እንዲሁም ሰሜን ሸዋ በመንግሥት ኃይሎች እና በፋኖ ታጣቂዎች መካከል ውጊያ ተጠናክሮ መቀጠሉን የአካባቢው ነዋሪዎች ለዶቼ ቬለ ገለጹ።
የሶማሌ ላንድ ለዶናልድ ትራምፕ ንግግር የሰጠችው መልስ እና አንድምታው 14.10.2026
የሶማሌ ላንድ ለረዥም ጊዜ ስትጠብቅ የነበረው ዓለማቀፍ ዕውቅና ቀርቦ ይኾን?
በአማራ ክልል በሶስት ዞኖች የሚደረገዉ ዉጊያ ቀጥሏል 13.10.2026
ሌላው የወገልጤና ከተማ ነዋሪም ጦርነቱ በወገልጤና ከተማ ውስጥ መሆኑን ገልጸው ተዋጊዎቹ ማህበረሰቡን ከተማ ለቆ እንዲወጣ ጥሪ ማቀረባቸውን ይናገራሉ። ትናንት በመጀመርያው ጦርነትም በተባራሪ ጥይት የተመቱ ሰዎች መኖራቸውና ጉዳቱ ግን የከፋ አለመሆኑን ተናግረዋል።
የዩናይትድ ስቴትስና ብሪታንያ ወደ ኢትዮጵያ ለሚጓዙ ዜጎቻቸዉ አዲስ ማሳሰቢያ አወጡ 13.10.2026
ትናንት ባወጣው የጉዞ ማሳሰቢያ የተለያዩ ምንጮችን የጠቀሰው በኢትዮጵያ የአሜሪካ ኤምባሲ፣ የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት እና የትግራይ የሰላም ኃይሎች ትግራይ ክልል ውስጥ አዲግራት፣ አድዋ እና ሽሬን ጨምሮ አቢ አዲ ከተሞችን መቆጣጠራቸውን፣ ከሰሜን አፋር አካባቢ የታጠቁ የተቃዋሚ ኃይሎችን ማስወገዳቸውንም አመልክቷል።
የአዉሮጳ ሕብረት የዉጪ ጉዳይ ሚንስትሮች ሥብሰባ ዉሳኔዎች 13.10.2026
ፕረዝዳንት ትራምፕ ባለፈው ዓርብ በማዕቀብ ውስጥ ካለችው ሩሲያ ናፍታ ለማስገባት ከፕሬዝዳንት ፑቲን ጋር መስማምታቸውን ማስታወቃቸው ከዩክሬን ብቻ ሳይሆን ከህብረቱ አገሮችም ተቃውሞ የተሰማበት ሲሆን፤ ሚኒስትሮቹ ግን በስብሰባቸው በሩሲያ ላይ ይልቁንም ከፍተኛ የተባለውን የማዕቀብ ውሳኔ ያሳለፉ መሆኑን ውይዘሮ ካያ ካላይ አስታውቀዋል
የፍልሰተኛችን ሞት ለመቀነስ መደበኛ መስመሮች እንዲስፋፉ አንድ ባለሙያ ጠየቁ 13.10.2026
ከአፍሪካ ቀንድ ተነስቶና ቀይ ባህርን አቋርጦ ወደ የመን የሚዘልቀውና ምስራቃዊው የጉዞ መስመር የሚባለው የፍልሰተኛች መሄጃ አቅጣጫ እንኾ ገዳይነቱ ቀጥሏል። ባለፈው ሳምንት መጨረሻ በደረሰ የጀልባ መገልበጥ አደጋ እስካሁን 139 ሰዎች መሞታቸውን አለምአቀፉ የፍልሰት ድርጅት- አይአኤም አስታውቋል።
የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ) «ቀይ ባሕር ለኢትዮጵያ ሕዝብ ይገባል» አለ 13.10.2026
“ቀይ ባህር ለዚህ አገር ህዝብ የተገባ ነው” የሚል ርዕስ ሰጥቶት ትናንት ባወጣው መግለጫ የኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦንግ)፤ “ኤርትራ እና ሕዝባዊ ወያኔ ኃርነት ትግራይ (ህወሓት) የደርግ ወታደራዊ መንግስት ውድቀትን ተከትሎ በነበራቸው ስልታዊ የፖለቲካ ትስስር ኢ-ፍትሃዊ በሆነ መንገድ በኢትዮጵያ ላይ የባህር በር መውጫን ዘግተዋል” ሲል ተችቷል፡
የዓይን ጤና ንጽሕናውን ከመጠበቅ ይጀምራል 13.10.2026
ኢትዮጵያ ውስጥ በተለይ የዓይን ማዝ የበርካታ ሰዎች ዓይን የጤና ችግር እንደሆነ የዘርፉ የህክምና ባለሙያዎች ይናገራሉ። የዓይን ንጽሕና በመጠበቅ እና በቀላል የህክምና እርዳታ ሊድን በሚችለው በዚህ የዓይን የጤና ችግር ብዙዎች የዓይን ብርሃናቸውን ሊያጡ ይችላሉ።
ማሕደረ ዜና፣ የኢትዮጵያ ጦርነት፣ የኢትዮ-ኤርትራ ፍጥጫ መቆሚያዉ መቼ ነዉ? 12.10.2026
የኢትዮጵያና የኤርትራ መንግሥታት ጠብ በናረበት በዚሕ ወቅት የኢትዮጵያ የሥለላ መስሪያ ቤት ኃላፊ፣ሌሎች ባለሥልጣናት፣ የጦር ጄኔራሎችና የተባባሪዎቹ ኃይላት የጦር አዛዦች ሥልታዊቱን ከተማን አዲግራትን የመጎብኘታቸዉ ፖለቲካዊ መልዕክት ከደብረፂዮን እኩል ለኢሳያስ አፈወርቂ መሆኑ ግልፅ ነዉ።
ባለፉት ሦስት ሳምንታት ግድም በሰሜን ኢትዮጵያ ትግራይ ክልል ግጭቶች ካገረሹ በኋላ በግጭቱ የሚከሰተው የሰብዓዊ ቀውስ በእጅጉ ስጋት ቀስቅሷል። 12.10.2026
በሰሜን ኢትዮጵያ ዳግም ያገረሸውን ጦርነት ተከትሎ በትግራይ ክልል ከሚገኙ ከተሞች በፌፌራል የጸጥታ ሃይሎች ስር በገቡ ከተሞች ለኢትዮጵያ ፌዴራል መንግስት አመራሮች አቀባበል ተደርጓል፡፡ በትናንቱ የአመራሮች አቀባበል ወቅት በርካታ የማህበረሰብ አካላት ደስታቸውን ብገልጹም፤ ስጋቶችም ግን እስካሁን ሙሉ በሙሉ አለመወገዳቸው እየተነገረ ነው፡፡
በአማራ ክልል በሚካሄደዉ ጦርነት ምክንያት በሸቀጦች ላይ ከፍተኛ የዋጋ ጭማሪ ተከሰተ። በክልሉ በሰሜን፤ ደቡብ ወሎና ሰሜን ሸዋ ጦርነት ዳግም አገርሽቷል። 12.10.2026
በአማራ ክልል በተሽከርካሪ መስተጓጎል ምክንያትበሸቀጦችና በግብርና ምርቶች ላይ ከፍተኛ የዋጋ ጭማሪ ተከሰተ። በአማራ ክልል በመንግሥትና በፋኖ ኃይሎች መካከል ባለፉት ሦስት ዓመታት እየተካሄደ የሚገኘው ጦርነት ባለፉት 14 ቀናት እንደ አዲስ አገርሽቶ በሰሜን ወሎ፣ ደቡብ ወሎና ሰሜን ሸዋ ጦርነቱ በተለያዩ ቦታዎች ቀጥሏል።
ማንኛውም ክልል ለሕገ መንግሥቱ መጣስ ራሱ ክልሉ ተጠያቂ የሚሆንበት ማንኛውም ድርጊት በክልሉ ሲፈፀም የፌዴራል መንግሥት ያለ ክልሉ ፈቃድ እና ይሁንታ በፌደሬሽን ምክር ቤት አዛዥነት ጣልቃ የሚገባበት ሥርዓት ተዘርግቷል።" 12.10.2026
በትግራይ ክልል ምርጫ እስኪደረግ ድረስ ክልሉ የፌደራል መንግሥት በሚያቋቁመው የዕዝ ማዕከል ወይም ኮማንድ ፖስት እንደሚመራ አቶ ጌታቸው ረዳ ተናገሩ። የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የምስራቅ አፍሪካ ጉዳዮች አማካሪ ይህንን ያሉት፣ የህወሓት አመራሮች ከመቀሌ ከተማ መውጣታቸውንና መከላከያ ሠራዊት የትግራይ ከተሞችን መቆጣጠር መጀመሩን ተከትሎ ነው።
የአፋር አንድነትን በማጠናከር የራስን ዕድል በራስ የመወሰን መብትን በጋራ ትግል ማረጋገጥና ቀጣናዊ ሰላምና መረጋጋት እንዲረጋገጥ ጥሪ ማቅረብ የሚሉ ሀሳቦችም በአቋም መግለጫው ተካቷል፡፡፡ 12.10.2026
የኤርትራ ተቃዋሚ ድርጅት የሆነው የቀይ ባህር ዓፋር ዲሞክራሲያዊ ድርጅት በዛሬው እለት በኢትዮጵያ አፋር ክልል ሰመራ ከተማ ህዝባዊ ጉባኤ ማካሄዱን አስታወቀ፡፡ ዛሬ ጥቅምት 02 ቀን 2019 ዓ.ም በሰመራ ተካህዶ የዋለው የጉባኤው ዋና ዓለማ እየተለዋወጠ በመጣው የቀይ ባህር ቀጣና ህዝቡን በተለይም ወጣቱን ለትግል ለማነሳሳት ያለመ ነው ተብሏልም፡፡
የጥቅምት 2 ቀን 2019 የስፖርት ዘገባ 12.10.2026
በአሜሪካ ቺካጎ በተካሄደው የማራቶን ውድድር አትሌት ሀዊ ፈይሳ አሽናፊ ሆናለች።የ2019ኝ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ በሜዳና ከሜዳ ውጭ በደማቅ ሁኔታ ተጀምሯል።የሳምንቱ መጨረሻ የጀርመን ቡንደስሊጋ ጨዋታዎች እና የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ መርሃ ግብሮች በርካታ ግቦችን፣ አስገራሚ ውጤቶችን እና ከፍተኛ ትኩሳትን የፈጠሩ ጨዋታዎችን አስተናግደዋል።
ትግራይ፦ የኢትዮጵያ እና የኤርትራ መፋለሚያ? 11.10.2026
በትግራይ ክልል እየተደረገ የሚገኘው ውጊያ በኢትዮጵያ እና ኤርትራ ፍጥጫ ወደ ሌላ የግጭት ምዕራፍ ሊሸጋገር ዳር ዳር እያለ ነው። በመቶ ሺሕዎች የተገደሉባቸው ሁለት የጦርነት ታሪኮች ያላቸው አገራት ፍጥጫ ምን ያክል አስጊ ነው? ሦስት እንግዶች የተሳተፉበት ውይይት የውጊያውን አደጋ፤ ለሰላማዊ ሰዎች የሚያስከትከትለው መዘዝ ይፈትሻል።
በጂቡቲ የባህር ዳርቻ በደረሰ የጀልባ አደጋ ከ100 በላይ ስደተኞች ህይወት አለፈ 11.10.2026
ዓለም አቀፉ የስደተኞች ድርጅት እንደገለፀው በጂቡቲ የባህር ዳርቻ በደረሰ የጀልባ አደጋ 109 ስደተኞች ህይወታቸው አልፏል።ከሟቾቹ መካከል 15ቱ ህፃናት ናቸው። ከአደጋው 80 ኢትዮጵያውያን በሕይወት የተረፉ ሲሆን፣ 116 ሰዎች ደግሞ የት እንዳሉ አይታወቅም።
የሰሜን ኢትዮጵያው ጦርነት እና መልስ የሚሻው የርዳታ አቅርቦት ፍላጎት 10.10.2026
የተመድ ዋና ጸሐፊ በሰሜን ኢትዮጵያ ሶስት ክልሎች ዳግም የተቀሰቀሰው ግጭት በእጅጉ እንዳሳሰባቸው ገልጸዋል
ኢትዮጵያ ሕገ-ወጥ የሰዎች ዝውውርን በማስወገድ አሁንም ደረጃ 2 ላይ ናት ተባለ 10.10.2026
መንግሥት ከቀደመው ጊዜ ጋር ሲነጻጸር በአጠቃላይ እየጨመረ የመጣ ጥረት አሳይቷል ቢባልም ደረጃዋ ግን የነበረበት 2 ላይ ሆኗል።
የኤርትራ ወታደሮች ወደ ኢትዮጵያ ግዛት ገቡ የተባሉባቸው የትግራይ አካባቢዎች የትኞቹ ናቸው? 09.10.2026
የኤርትራ ወታደሮች በትግራይ ክልል ሦስት ዞኖች በኩል ድንበር ተሻግረው ወደ ትግራይ ክልል እንደገቡ የገለጹት ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቲዮስ ኢትዮጵያ ራሷን የመከላከል ተፈጥሯዊ መብቷን እንደምትጠቀም ለጸጥታ ጥበቃው ምክር ቤት አባላት አስታውቀዋል። ውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ወታደሮቹ ከ30-60 ኪሎ ሜትር ወደ ኢትዮጵያ ግዛት እንደገቡ ጠቅሰዋል።
ነዋሪዎቹ ከተማዋን የተቆጣጠሩ የፀጣታ ሃይሎች ፖሊስን ለመሳሰሉ የፀጣታ መዋቅሮች ጥሪ እያቀረቡ እንዳሉም አመልክተዋል፡፡ 09.10.2026
በሰሜን ኢትዮጵያ ዳግም ያገረሸውን ጦርነት ተከትሎ በትግራይ ክልል የሚገኙ ከተሞች እና አከባቢዎች አሁንም በተለያዩ ይዞታዎች ላይ ይገኛሉ።
ሰሜን ኢትዮጵያ ያለው ኹኔታ ጦርነት ሳይሆን «የትጥቅ ግጭት» በሚል የሚገለጽ ነው: ኢሰመኮ 09.10.2026
በትግራይና አዋሳኝ የአማራና የአፋር ክልሎች ያለውን ኹኔታ እስካሁን ባለው ደረጃ «የትጥቅ ግጭት» አድርጎ እንደሚመለከተው የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን ገለፀ። ኮሚሽኑ በተለይ በትግራይና አማራ ክልሎች ያለውን ኹኔታ በዓለም አቀፍ ብያኔ «ጦርነት» ሳይሆን «በግጭት ዐውድ ላይ የሚገኙ አካባቢዎች» አድርጎ እንደሚወስዳቸው አስታውቋል።
ሰሜን ወሎ በተፈናቃዮች መጠለያ በማኅበረሰቦች ግጭት ሰዎች መጎዳታቸው ተገለጸ። 09.10.2026
በአማራ ክልል ሰሜን ወሎ ዞን በሚገኘው የጃራ ተፈናቃዮች መጠለያ ጣቢያ ላይ በተፈጸመ ጥቃት ሁለት ተፈናቃዮች በጽኑ መቁሰላቸውን የመጠለያው ነዋሪዎች እና አስተባባሪዎች ገለጹ።
ተመድ ለኤርትራ ወረራ ምላሽ ይስጥ ስትል ኢትዮጵያ ጠየቀች 09.10.2026
የኢትዮጵያ መንግሥት፣ ግብፅ፣ ሱዳንና ኤርትራ ታጣቂዎችን ይረዳሉ በማለት ሲወነጅል ቆይቷል። ሰሞኑን ደግሞ፣ የኤርትራ ወታደሮች ድንበር ጥሰው ገብተዋል፣ ግልፅ ወረራም ፈጽመዋል በማለት ከሷል።
ደቡብ አፍሪቃዊትዋ ዳና ናቫኔተም በአጭሩ ስማቸዉ "ናቪ" ፒላይ የዘንድሮዉን የጎርጎሮሳዉያን 2026 የኖቤል የሰላም ሽልማት አሸነፉ። 09.10.2026
ደቡብ አፍሪቃዊትዋ ዳና ናቫኔተም በአጭሩ ስማቸዉ "ናቪ" ፒላይ የዘንድሮዉን የጎርጎሮሳዉያን 2026 የኖቤል የሰላም ሽልማት አሸነፉ። ደቡብ አፍሪቃዊቷ ዳኛ "ናቪ" ፒላይ፣ የዘንድሮውን የኖቤል የሰላም ሽልማት ያሸነፉት፤ ለሰላም እና ለዓለም አቀፍ ህግ መከበር ላደረጉት ጥረት መሆኑን የሽልማት ኮሚቴዉ ዛሬ ኖርዌይ መዲና ኦስሎ ላይ ይፋ አድርጓል።
Replaio is not a podcast publisher; show names, artwork and audio belong to their authors and are distributed through public RSS feeds.