DW | Amharic - News
News, Analysis and Service from Germany and Europe - in 30 Languages
Be sure to visit the podcast's website and support the creator: www.dw.com
Where to listen?
Podcasts in the app Replaio Radio Coming soonPodcasts are coming to the app soon. Install now and be the first to see a whole new take on podcasts
Episodes
የጥቅምት 09 ቀን፣ 2019 ዓ.ም ሣምንታዊ የስፖርት ዘገባ 19.10.2026
ኢትዮጵያ የአፍሪቃ ዋንጫን ለማስተናገድ ጥያቄ አቅርባለች ። የዛሬው ስፖርት ዝግጅታችን ዋነኛ ትኩረት ነው ። ቃለ መጠይቅ አድርገናል ። ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በተለያዩ የዓለማችን ክፍሎች በተደረጉ የሩጫ ፉክክሮች ድል መቀዳጀታቸውን የሚያበስር የአትሌቲክስ እንዲሁም የእግር ኳስ ዘገባዎችንም አካትተናል ። ሙሉ ዘገባውን በድምፅና በጽሑፍ ይከታተሉ ።
በትግራይ ክልል ላይ ባለው የሰብአዊ መብት አያያዝ ላይ አተኩሮ የሚሠራው ቅድሚያ ለሰብአዊ መብቶች ኢትዮጵያ በክልሉ አሁንም ጦርነት ቆሟል ለማለት የሚያስደፍር ተጨባጭ ለውጥ የለም። 19.10.2026
በትግራይ ክልል የመከላከያ ሠራዊትና የትግራይ ሰላም ኃይል በህወሓት ላይ እየወሰዱት ነው የተባለ እርምጃ በኅብረተሰቡ ዘንድ ድጋፍ ያገኘ መሆኑን በክልሉ የሚንቀሳቀሱ ሁለት የፖለቲካ ፓርቲዎች ገለፁ። ፓርቲዎቹ ለዚህ ማሳያ ያቀረቡት ህወሓት በአጭር ጊዜ ጥቂት ከማይባሉ የክልሉ ከተሞች ተገፍቶ በመዉጣቱና ድርጅቱን ከሕዝብ ለመነጠል በተሰራዉ ስራ ነዉ።
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ የኢትዮጵያ መንግሥት የጦርነት ሂደት ያለ ተጠያቂነት እንዲያስቀጥል ያደርጋል ያለው ጥምረቱ፣ አሜሪካ ጉዳዩን በሚመለከት ሚዛናዊና ገንቢ አቋም እንዲኖራት ጠይቋል። 19.10.2026
የፌዴራል መንግሥትን በኃይል ለመጣል የተመሠረተው ትብብር ለሕልውና የተባለው የፖለቲካ እና የትጥቅ ቡድኖች ስብስብ ቅዳሜ ዕለት በአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የተሰጠውን አስተያየት ተቃወመ። ማሮኮ ሩቢዮ ስም ሳይጠቅሱ "ተገንጣይ" ባሉት ኃይል በአዲስ አበባ እና በቢሾፍቱ የድሮን ጥቃቶች መፈፀማቸውን አረጋግጠዋል።
ውይይት፤ የኢትዮጵያ እና ኤርትራ ፍጥጫ ወዴት? 18.10.2026
የሁለቱ መንግሥታት ውዝግብ ምንም እንኳ በአሁኑ ወቅት ወደለየለት ጦርነት ባይሸጋገርም በአፍሪቃው ቀንድ አጠቃላይ ጦርነት እንዲቀሰቀስ የሚያደርግ ወታደራዊ እንቅስቃሴ በሰሜን ኢትዮጵያ እና በኤርትራ ድንበር አካባቢ መታየቱ እየተነገረ ነው።ጉዳዩ ያሳሰባቸው ሀገራት እና ዓለም አቀፍ ድርጅቶችም ጉዳዩን በውይይት እንዲፈቱ እያሳሰቡ ነው።
የአየር ንብረት ለውጥና የአውሮፕላን ጥቃት ያባባሰው ሰብአዊ ቀውስ በሱዳን 17.10.2026
የረድኤት ድርጅቶች ሱዳን ውስጥ ከቤት ንብረታቸው ለተፈናቀሉት አገልግሎት የሚሰጡ የጤና ተቋማት ሙሉ ለሙሉ ከሥራ ውጪ ሊሆኑ እንደሚችሉ እያስጠነቀቁ ነው። ሱዳን ውስጥ በሰሜን ኮርዶፋን እና በብሉ ናይል ግዛት አንዳንድ አካባቢዎች በሱዳን ጦር እና በፈጥኖ ደራሹ ኃይል መካከል የሚካሄደው ውጊያ ተጠናክሯል።
ኬንያ ራይላ ኦዲንጋ የታገሉለትን ዴሞክራሲያዊ ምህዳር ማስጠበቅ ትችል ይሆን? 17.10.2026
ኬንያውያን ባለፈው ዓመት በዚህ ወቅት ከዚህ ዓለም በሞት የተለዩት የቀድሞው የሀገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ራይላ ኦዲንጋ ለፖለቲካው ያበረከቷቸውን ጉዳዮች የሰሞኑ መነጋገሪያ አድርገዋቸዋል።
የኢትዮጵያ ፌድራል መንግሥት ባለአደራ አስተዳደር ሲመሰርት የትግራይ የሰላም እና ለውጥ ምክር ቤት ለምን ፈረሰ? 17.10.2026
ህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይን ከሥልጣን ለማስወገድ የተመሠረተው የትግራይ የሰላም እና ለውጥ ምክር ቤት ከአምስት ወራት ገደማ በኋላ መፍረሱን ትላንት አርብ ጥቅምት 06 ቀን 2019 አስታውቋል። የትግራይ የሰላም እና ለውጥ ምክር ቤት አባል የነበሩ ፓርቲዎች“የምርጫ ቦርድ ሕግ በሚፈቅደው መሠረት የጋራ ትግላቸውን” እንደሚቀጥሉ ተገልጿል።
መንግሥት በትግራይ ስላቋቋመው ባለአደራ አስተዳደር ህወሓት ምላሽ ሰጠ 17.10.2026
ህወሓት የፌዴራል መንግሥት በትግራይ ክልል ለ6 ወር ያቋቋመውን ባለአደራ አስተዳደር "ሕጋዊነት ወይም ተፈጻሚነት እንደሌለው" በማለት ተቃውሟል። ከፌዴራሉ መንግሥት ጋር ግጭት ዉስጥ የገባው ህወሓት ከተቋቋመው ባለአደራ አስተዳደር ጋር የሚተባበር ማንኛውም ድርጅት የመንግሥት አካል ተደርጎ እንደሚቆጠር እና ተጠያቂ እንደሚሆን አሳስቧል።
የአሜሪካ አጋማሽ ዘመን ምርጫ 17.10.2026
የአሜሪካ ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ በሥልጣናቸው አጋማሽ የሚካሔደው ምርጫ ሲቃረብ ለሪፐብሊካን ዕጩዎች ድጋፍ ለማሰባሰብ ባደረጓቸው ንግግሮች የኢትዮጵያ፣ ታላቁ የህዳሴ ግድብ እና የሶማሊያን ጉዳይ አንስተዋል። ከሁለት ሣምንት ገደማ በኋላ የሚካሔደው ምርጫ የሕግ አውጪ ምክር ቤቶች፤ የግዛት አስተዳዳሪዎችና ከንቲባዎች የሚመረጡበት ነው።
የሚዲያ ነፃነትን የሚጋፉ "በርካታ" አሳሳቢ ጉዳዮች ተለይተዋል - የኢሰመኮ ዓመታዊ ሪፖርት 16.10.2026
በተጠናቀቀው በጀት ዓመት የሚዲያ ነፃነትን የሚጋፉ "በርካታ" ያላቸው አሳሳቢ ጉዳዮች መለየታቸውን የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን ባለፈው ሳምንት ይፋ ባደረገው ዓመታዊ የምርመራ ዘገባው አመለከተ። "የሚዲያ ምኅዳሩ ሕግን፣ ሀገራዊ እሴቶችን እና ፍላጎቶችን ባከበረ መልኩ እንዲንቀሳቀስ ይደርጋል" መባሉ ይታወሳል።
የጋምቤላ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን በደረሰው የጸጥታ ችግር የሰው ህይወት ማለፉን ገልጸው የሰዓት እላፊ ገደብ ጥለዋል፡፡ በዛው እለትም በከተማው የሰው እንቅስቃሳ እንደለለና ተቋማት ዝግ መሆናቸው ተገልጸዋል፡ 16.10.2026
በጋምቤላ ክልል ዋና ከተማ ባለፈው ማክሰኞ ምሽት ባልታወቁ ሰዎች ደርሰዋል በተባለው ጥቃት የአራት ሰዎች ህይወት ማለፉ ተከትሎ ትናንት እሰከ ማታ ድረሰ የተኩስ ድምጽ ሲሰማ ነበር ተብለዋል፡፡ በርካቶች ጥቃቱን በማውገዝ ወደ ክልሉ ምክር ቤት በመሄድ ድምጻቸውን ማስማታቸውን ያጋርናቸው የከተማወ ነዋሪዎች ተናግረዋል፡፡
በቆቦ ከተማ የሚገኙ ከስድስቱ የራያ አካባቢዎች የተፈናቀሉ ነዋሪዎች፣ በአካባቢያቸው የሚካሄደው ጊዜያዊ የሽግግር አስተዳደር የምርጫ ሂደት አካታችነትና ገለልተኛነት የጎደለው ነው በማለት እንዲቆም በሰላማዊ ሰልፍ ጠየቁ። 16.10.2026
ባለፈው አንድ ዓመት የማንነት ጥያቄ ካላቸው ስድስቱ የራያ አካባቢዎች ተፈናቅለው በቆቦ ከተማ የሚኖሩ የተሾመዉ ጊዜያዊ የሽግግር አስተዳደር ምርጫ እኛን ያገለለ ነዉ ሲሉ በሰላማዊ ሰልፍ ጠየቁ፡፡ በሰላማዊ ሰልፉ ተሳፊዎች የአላማጣ ዎፍላ ባላ ራያ አላማጣ ዛታና ኮረም ተፈናቃዮች እየተካሄደ ሁኔታ አካታችነትና ገለልተኛነት የጎደለው ነው ብለዋል፡፡
የኢትዮጵ መንግስት የትግራይ ክልልን የሚያጸና ያለውን የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር እንዲቋቋም የሚስችል ውሳኔ አስተላልፏል። አስተያየት ሰጪ የክልሉ ነዋሪዎች ከመስተዳድሩ መሰየም ጋር ተያይዞ ተስፋም ስጋትም እንዳላቸው ገልጸዋል፡፡ 16.10.2026
በትግራይ ክልል“በህወሓት ዕንቅፋትነት የተነሣ ሳይሳካ ቀርቷል” ያለው የኢትዮጵያ መንግስት የትግራይ ሕዝብ የራቀውን ሰላም እንዲጎናጸፍ፣ ራስን በራስ የማስተዳደር መብቱ እንዲረጋገጥ እንዲሁም ከሌሎች የኢትዮጵያ ሕዝቦች ጋር በኅብረ-ብሔራዊ አንድነት ጸንቶ እንዲኖር ለማስቻል የባለአደራ አስተዳደር መመስረቱን ዛሬ አስታውቋል፡፡
የፌዴራል መንግሥት በምን በምን ጊዜ ወደ ክልሎች ጣልቃ ይገባል? 16.10.2026
ከፌዴራል መንግሥት በሚሰጠው አቅጣጫና መመሪያ መሠረት ትግራይ ክልልን ለሚቀጥሉት 6 ወራት የሚያስተዳድር አሥር ተግባራት ያሉት ባለ አደራ አስተዳደር ተመሠረተ። ይህ ባለ አደራ አስተዳደር፣ ክልሉ ሰላሙን ማስከበር እንዲችል፣ ትኩረቱን በልማት ላይ እንዲያደርግ እና በአንድነት ጸንቶ መኖር እንዲችል ይሠራል ተብሏል።
በሰሜን ኢትዮጵያ አለመረጋጋት በሰፈነበት በአሁን ወቅት በኦሮሚያ ክልል አንዳንድ ቦታዎች ጸጥታ ችግሩ እንደቀጠለ መሆኑ ተናግረዋል። የክልሉ ነዋሪዎች እንዳመለከቱት የጸጥታው ስጋት አሁንም አልፎ አልፎ ስጋት መደቀኑን እንቀጠለ ነው፡፡ 16.10.2026
የኖኖ ወረዳ ነዋሪ “ባለፈው ሳምንት ውስጥ በድሬ እንጪኒ ወረዳ በመንግስት የጸጥታ ሃይሎች እና በኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት መካከል በነበረው ግጭት በርካታ ሰዎች ተገድለዋል። ከኖኖ ወረዳ እዛ ተመድበው የነበሩ ሦስት የጸጥታ አካላት መሞታቸዉንም አስታውቃለሁ” ብለዋል፡፡ ዶይቼ ቬለ ከባለስልጣናት መረጃዎችን ለማግኘት ያደረገው ጥረት አልተሳካም፡፡
ኢትዮጵያ ዉስጥ የጦርነቱ ዋነኛ ሰለባዎች ሴቶችና ህጻናት ናቸው-ግን ታዲያ i,ሴቶች ድምፅ በየመድረኩ ለምን ቀነሰ? 15.10.2026
በአገር ዉስጥ በሚቀሰቀስ ጦርነት፤ ሴቶችና ታዳጊ ህጻናት የመጀመርያ ተጎጅዎች ናቸዉ። በጦርነት ወቅት ሴቶች ላይ የሚደርሱ ዋና ዋና ጉዳቶች፤ ፆታዊ ጥቃትን እንደ መሳርያ መጠቀም፤ የሥነ ልቦና ጉዳት፤ መፈናቀል እና የኑሮ ዉድነት፤ የጤና አገልግሎት እጦትን መጥቀስ ይቻላል። ኢትዮጵያ ዉስጥ የሴቶች ድምፅ በየመድረኩ ለምን ቀነሰ መጣ? ጦርነት ይቁም!
አሜሪካን ጨምሮ ብዙዎች እንዲናገሩ እያደረገ ያለው የኢትዮጵያና የኤርትራ ውጥረት 15.10.2026
የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማርኮ ሩቢዮ በአፍሪካ ቀንድ አካባቢ የሚገኙ ሁሉም ሃገራት የጎረቤቶቻቸውን «ሉዓላዊነትና የግዛት አንድነት ማክበር» እንዳለባቸው ተናገሩ።
በሰሜን ኢትዮጵያ የሰብዓዊ ድጋፍ አቅርቦት 15.10.2026
የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰብዓዊ እርዳታ ማስተባበሪያ ድርጅት (UN-OCHA) በሰሜን ኢትዮጵያ የሰብዓዊ አቅርቦት መሻሻል ማሳየቱን አስታወቀ። የተባበሩት መንግሥታት ደግሞ ከአስቸኳይ እርዳታ ምላሽ ማዕከሉ (CERF) በሰሜን ኢትዮጵያ ለሕይወት አድን እርዳታ 8.5 ሚሊየን ዶላር መመደቡን ነው አመልክቷል።
በጦርነት በምትታመሰው የመን የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ተማጽኖ 15.10.2026
በየመን የሚገኙ የኢትዮጵያ ስደተኞች አሳሳቢ ሰብአዊ ሁኔታ ላይ ስለምንገኝ ድምፃችን እንዲሰማ ሲሉ ጥሪ አቀረቡ። እነዚህ ወገኖች ለዶቼ ቬለ በጻፉት የተማጽኖ ደብዳቤ፤ «በየመን ውስጥ የምንኖር የኢትዮጵያ ስደተኞች በእጅጉ አስከፊ የሰብአዊ፣ የጤና እና የደኅንነት ችግር ውስጥ እንገኛለን» ብለዋል።
በሰሃላ ሰየምት ወረዳ የተከሰተው አስከፊ ድርቅ 15.10.2026
በዋግህምራ ብሔረሰብ አስተዳደር ዞን ሰሃላ ሰየምት ወረዳ በ13 ቀበሌዎች ከ66 ሺህ በላይ ሰዎች ሲኖሩ ከእነዚህም ውስጥ ከ58 ሺህ በላይ ሰዎች የረሃብ ተጠቂ መሆናቸውን የወረዳው ግብርና ጽሕፈት ቤት መረጃ ያመለክታል።
በትግራይ የሚካሄደው ውጊያ እንዲቆም መጠየቁ 15.10.2026
በትግራይ ክልል የሚካሄደው ግጭት ቆሞ ወደ ሰላም የሚያመራ እውነተኛ መንገድ እንዲጀመር የትግራይ ማኀበረሰብ ዳያስፖራ ድርጅቶች ጥሪ አቀረቡ።
ቃለ መጠይቅ፣ «ያልተጠናቀቀ ፍቺ፣ ያልተሳካ ጉርብትና-የኤርትራና የኢትዮጵያ ጉዳይ» አቶ የሱፍ ያሲን 1991 15.10.2026
ታዛቢዎች ኋላ እንዳሉት የጠቅላይ ሚንስትር ዓብይ አሕመድና የፕሬዝደንት ኢሳያስ አፈወርቂ ወዳጅነት አንደኛ፣- በግልፅ፣ በሕግና በሕዝብ ይሁንታ የተደገፈ አልነበረም።ሁለተኛ፣- የጋራ «ጠላት» የሚሉትን ህዝባዊ ወያኔ ሓርነትን ትግራይ (ህወሓት)ን ለመዉጋት ሥለነበር የሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት በሰላም ሥምምነት ሲያበቃ ወዳጅነቱም ወደጠላትነት ተቀይሯል
የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ድርቅ የተደመረበትን የጦርነት ጫና መሸከም ይችላል? 14.10.2026
ከ2019 የኢትዮጵያ 2.4 ትሪሊዮን ብር በጀት ውስጥ 96.3 ቢሊዮን ብር የሚሆነው ለመከላከያ ተመደበ ነው። ይሁንና ጦርነት የሚያስፈልገው ከፍተኛ ገንዘብ በመንግሥት ወጪ እና የበጀት ጉድለት ላይ ጫና ሊያሳድር ይችላል። በምንዛሪ ሥርዓት ለውጥ እየተዳከመ የሔደው ብር ጭምር እና የዋጋ ግሽበት ድርቅ በተደመረበት የጦርነት ዳፋ መፈተናቸው አይቀርም።
የኢትዮጵያ ኃይሎች የኤርትራ ድንበር አቅራቢያ የምትገኝ ከተማ መድረሳቸው ተገለፀ 14.10.2026
የኢትዮጵያ ፌደራል መንግሥት ኃይሎች እና ተባባሪዎቹ ከኤርትራ ድንበር አቅራቢያ ከምትገኘው ዛላንበሳ ከተማ መድረሳቸውን እማኞች ገልፀዋል።አንድ የአካባቢው ነዋሪ ለዶቼ ቬለ እንደገለፁት የኤርትራ ሠራዊት ዛላአምበሳ ከተማ ላይ የሚገኝ ቢሆንም በዙሪያው በሚገኙ የገጠር ቀበሌዎች ግን የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት መግባቱን ገልፀዋል።
በትግራይ ክልል ከሚንቀሳቀሱ የፖለቲካ ፓርቲዎች አንዱ ሳልሳይ ወያነ ያወጣው መግለጫ ምን ይላል? 14.10.2026
በትግራይ ክልል የተከሰተው ረሃብ እና የተፈናቃዮች ሁኔታ ቅድሚያ እንዲሰጥ ተጠየቀ
Replaio is not a podcast publisher; show names, artwork and audio belong to their authors and are distributed through public RSS feeds.