DW | Amharic - News
News, Analysis and Service from Germany and Europe - in 30 Languages
Where to listen?
Podcasts in the app Replaio Radio Coming soonPodcasts are coming to the app soon. Install now and be the first to see a whole new take on podcasts
Episodes
አሜሪካ ፤ኢራን የሆርሙዝ ጥቃቶችን ለማስቆም በይፋ ቃል እንድትገባ መፈለጓን ባለስልጣናት ገለፁ 11.07.2026
ዋሽንግተን ቴህራን በሆርሙዝ ስትራቴጂካዊ የባህርት ወሽመጥ ላይ በሚጓዙ መርከቦች ላይ የሚሰነዘሩትን ጥቃቶች ለማስቆም በይፋ ቃል እንድትገባ መፈለጓን ዘገባዎች አመልክተዋል። በሌላ በኩል ዶናልድ ትራምፕ ኢራን እሳቸውን ለመግደል ከሞከረች ሀገሪቱን ሙሉ በሙሉ እንደሚያወድሟት ዝተዋል።1000 ሚሳይሎች ወደ ኢራን አነጣጥረው ተቀምጠዋል። ሲሉም ዝተዋል።
ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ወቀሳ የህወሓት ምላሽ 10.07.2026
ሕወሓት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ከኤርትራና ሱዳን ጋር በመስራት ያቀረቡበትን ክስ አጣጣለ ። ፓርቲው ምላሹን የሰጠው ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ፤ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የማጠቃለያ መድረክ ላይ ባደረጉት ንግግር ሕወሓት፣ ኤርትራ እና ሱዳንን የኢትዮጵያን መንግስት ለመዋጋት ተጣምረዋል በማለት በጠንካራው መተቸታቸውን ተከትሎ ነው፡፡
የኢሰመኮ የአምስት ዓመት ዕቅድ የመብት ጥሰቶችን ይቀንስ ይሆን? 10.07.2026
ኢትዮጵያ ውስጥ «ግጭት፣ የፀጥታ ችግርና መፈናቀል፣ ሕገ ወጥ የሲቪል ሰዎች ግድያ እና የአካል ጉዳት፣ የዘፈቀደ እና የተራዘመ እስር» የሰብአዊ መብት ጥበቃ ሥጋት ሆነው እንደሚቀጥሉ የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን ገለጠ። በሰብአዊ መብት ጥበቃ ላይ የሚሠራ አንድ ሀገር በቀል ሲቪክ ድርጅት የኢሰመኮን ሥጋት እንደሚጋራ ጠቅሷል ።
በአፍሪቃ የሚካሄዱ ምርጫዎች ዳያስፖራውን ማሳተፍ እንደለባቸው ተገለፀ 10.07.2026
የዳያስፖራ አባላት የብሔራዊ ምርጫ ተሳትፎ በተለያዩ የአፍሪካ ሃገራት ያለበት ደረጃ ተመሳሳይ አለመኾኑን የገለፀው የአፍሪካ ኀብረት፣ አባል ሃገራት ቁርጠኝነት እንዲያሳዩ ጥሪ አቅርቧል። በርካታ ሃገራት በተለያዩ የውጭ ሃገራት የሚገኙ ዜጎቻቸው በምርጫ እንዲሳተፉ የሚያስችሉ የሕግ ማሻሻያዎች ማድረጋቸውን ገልፀዋል።
በአርሲ አሰኮ በግጭት የተፈናቀሉ ነዋሪዎች የድጋፍ ጥያቄ 10.07.2026
በኦሮሚያ ክልል አርሲ ዞን አሰኮ ወረዳ በተለያዩ ቀበሌዎች ግንቦት 23 እና 24 ቀን፣ 2018 ዓ.ም በተፈጸመ ጥቃት የተፈናቀሉ ነዋሪዎች በርዳታ አቅርቦቶች መቋረጥ መቸገራቸውን ገለጹ። ተፈናቃዮቹ በጥቃቱ ወቅት በደረሰባቸው የቤት ቃጠሎና የንብረት ውድመት ወደ መኖሪያቸው ቀየያቸው ለመመለስም ከፍተኛ ድጋፍ እንደሚያስፈልጋቸው ተናግረዋል ፡፡
በእሥር ላይ ስለሚገኙ ፖለቲከኞች መፈታት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ የሰጡት ፍንጭ 10.07.2026
የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በልዩ ልዩ ፖለትካዊ ምክንያቶች በእሥር ላይ የሚገኙ ኢትዮጵያዊያን ከእሥር ሊለቀቁ የሚችሉበት ዕድል ስለመኖሩ ፍንጭ ሰጡ። መንግሥታቸው "የሃይማኖት አባቶችን እና ትልልቅ ሰዎችን" ተጠቅሞ "በተቻለ መጠን በእሥር ላይ ያሉ ሰዎችን ለመፍታት" ፍላጎት እንዳለው ጠቁመዋል ።
አንድነት ላይ ያተኮረው የኔቶ ጉባኤ 10.07.2026
በዚህ ሳምንት ለሁለት ቀናት አንካራ ቱርክዬ ላይ የተካሄደው የሰሜን አትላንቲክ የጦር ቃል ኪዳን (ኔቶ) ጉባኤ የአባላቱ አንድነት አሁንም እንዳለ መሆኑን ለማሳየት ያለመ እንደነበር ነው ተንታኞች የሚናገሩት።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ “ጦርነት ሊቀሰቅሱ የሚችሉ ትንኮሳዎች በየጊዜው ትግራይ ባሉ ኃይሎች ይፈጸማል” ሲሉ ከሰሱ 07.07.2026
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ “ጦርነት ሊቀሰቅሱ የሚችሉ ትንኮሳዎች በየጊዜው ትግራይ ባሉ ኃይሎች ይፈጸማል” ሲሉ ወንጅለዋል። ዐቢይ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በሰጡት ማብራሪያ በገደምዳሜ ስለ ጽምዶ ጠቀስ አድርገዋል። ይሁንና ህወሓት፣ ኤርትራና ሱዳን ቢተባበሩ እንኳ ለኢትዮጵያ “ሉዓላዊነት ቅንጣት ታክል ሥጋት” እንደማይሆኑ ገልጸዋል።
እንወያይ፤ የትግራይ ክልል ቀዉስ ወዴት እያመራ ነዉ? መፍትሔዉስ? 05.07.2026
በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ መንግሥትና በህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ መካከል የሚደረገዉ ዉዝግብና ቁርቁስ አሁንም እንደቀጠለ ነዉ። ህወሓት በፕሪቶርያ ስምምነት መሰረት የተሰየመዉን የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ከተቆጣጠረ ወዲህ ከመንግሥት ጋር የነበረዉ ቂም እየተካረረ መምጣቱ እየተነገረ ነዉ። ህወሓትም ወጣቶችን ለዉትድርና እያስገደደ ነዉ ተብሏል።
ጠቅላይ ሚንስትሩ በአርባምንጭ የኮንፈረንስ ሪዞርት ምረቃ ላይ ምን አሉ? 04.07.2026
በአርባ ምንጭ ሪዞርት የመረቁት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ “አላስፈላጊ ሽኩቻ ከልማት እንዳያስቀረን” ሲሉ ተደምጠዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ቱሪዝም የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ኹነኛ ምሰሶ እንዲሆን ፍላጎት እንዳላቸው በተደጋጋሚ ገልጸዋል። ዶይቼ ቬለ ያነጋገራቸው የቱሪዝም ባለሙያ ግን የጸጥታ ችግሮችን በማስወገድ ሰላም ማስፈን እንደሚያስፈልግ ተናግረዋል።
የዐቢይ መንግሥት ለኢትዮጵያ ሕዝብ “መጥፎ” በተባለ ሥምምነት ወደ ንግድ ብድር ሊመለስ ነው? 01.07.2026
ውድ ወለድ የሚከፈልባቸው የንግድ ብድሮች እንዳቆሙ በተደጋጋሚ ምለው የሚገዘቱት የኢትዮጵያ ባለሥልጣናት ቃላቸው የሚፈተንበት ሥምምነት ከቦንድ ባለቤቶች ጋር አድርገዋል። ሥምምነቱ ኢትዮጵያ እስከ 9% ወለድ የሚከፈልበት ቦንድ እንድታወጣ የሚያደርግ ነው። ኢትዮጵያ ቦንዱን ካላወጣች ለግል አበዳሪዎቿ እስከ 90 ሚሊዮን ዶላር ለመክፈል ትገደዳለች።
ማሕደረ ዜና፣ የ7ኛዉ አጠቃላይ ምርጫ ዉጤት፣ እድምታዉና የኢትዮጵያ ተጨባጭ ሁኔታ 22.06.2026
በኢትዮጵያ የቅርብ ይሁን የሩቅ ዘመን ታሪክ የተደረጉ ለዉጦች በሙሉ የተደረጉት በምርጫ ሳይሆን በቤተ መንግሥት ሴራ፣ በመፈንቅለ መንግሥት፣በጦርነትና በሕዝባዊ አመፅ ነዉ።ምክንያቱ ብዙ ነዉ።ፕሮፌሰር መረረ «መሠረታዊ ችግራችን» የሚሉት ይጠቅሳሉ።
ዉይይት፤ ቅድመ ምርጫ፣ ምርጫ እና ድኅረ ምርጫ በጋዜጠኞች ዕይታ 07.06.2026
ባሳለፍነው ሳምንት መጀመሪያ በኢትዮጵያ 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ተካሂዷል። ግንቦት 24 ቀን 2018 ዓ.ም. በተካሄደው በዚህ ምርጫ ፤ዋዜማው፣ የምርጫው ዕለት እና ድህረ ምርጫ በጋዜጠኞች ዕይታ ምን ይመስላል።?7ኛውን ጠቅላላ ምርጫ፤ ከዘገቡ የዶቼ ቬለ ጋዜጠኞች መካከል አራቱን አነጋግረናል።
Replaio is not a podcast publisher; show names, artwork and audio belong to their authors and are distributed through public RSS feeds.