DW | Amharic - News

News, Analysis and Service from Germany and Europe - in 30 Languages

Be sure to visit the podcast's website and support the creator: www.dw.com

Category

Uncategorized

Podcast website

www.dw.com

Latest episode

Nov 20, 2026

Where to listen?

Podcasts in the app Replaio Radio Coming soon

Podcasts are coming to the app soon. Install now and be the first to see a whole new take on podcasts

Get it on Google Play Install for free Android 10M+ downloads · 4.7+ rating iOS soon

Episodes

የአዉሮጳ ከተሞችን ያጥለቀለቀዉ ተቃዉሞ ሰልፍ ምክንያት 23.10.2026

ስጳኝ፣ ፈረንሳይ፣ አልባኒያ፣ ኢጣሊያ፣ ፖርቱጋል፣ ቤልጂግ፣ ኦትሪያና ጀርመን በየከተሞቹ አደባባይ የሚወጣዉ ሕዝብ የየሐገሩ መንግሥታት የህዝቡን ችግርና ጥያቄ ከቁብ አልቆጠሩትም በማለት እየተቃወመ ነዉ

በሞያሌ ከተማ የቀጠለው አለመረጋጋት 23.10.2026

ከሰኞ እስከ ረቡዕ በሶማሌ ክልል እና በኦሮሚያ ክልል አዋሳኝ አከባቢ በቦታ ይገባኛል የተጀመረው ውዝግብ ከትናንት ሓሙስ ጀምሮ ወደ መሣሪያ መታኮስ ተሸጋግሮ ቢያንስ የአስር ሰዎች ህይወት ማለፉንም አንድ ነዋሪ ገልጸዋል፡፡ ትናንት ከማለዳው 12 ሰዓት በሞያሌ በሁለቱ ክልሎች አዋሳኝ ስፍራ ዳሙቅ ላይ የተጀመረው የተኩስ ልውውጥ ዛሬም ቀጥሎ ውሏል፡፡

በቡርጂ ዞን አምስት ሰዎች በታጣቂዎች ተገደሉ፣ ከብቶች ተዘረፉም 23.10.2026

የቡርጂ ዞን ፖሊስ ኮሚሽነር ኮማንደር ዘመዴ ባንቶሪ ዝርዝር ማብራሪያ ከመሥጠት ቢቆጠቡም ጥቃቱ ሥለመፈጸሙ ግን በሰጡት አጭር ምላሽ አረጋግጠዋል ፡፡በደቡብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ቡርጂ ዞን በሶያማ ዙሪያ ወረዳ ነደሌ ቀበሌ ሰዎች በታጣቂዎች መገደላቸውን የቡርጂ ዞን መስተዳድር ጽህፈት ቤት ባወጣው መግለጫ አስታውቋል

ሱዳን ግብፅና ኤርትራ ታጣቂዎችን ይደግፋሉ ስትል ኢትዮጵያ በድጋሚ ወነጀለች 23.10.2026

በኢትዮጵያ ብሔራዊ መከላከያ ኮሌጅ እና በዉጭ ጉዳይ ኢንስቲትዩት በጋራ በተዘጋጀ የፖሊሲ ውይይት ላይ ገላጻ ያደረጉት የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር የምስራቅ አፍሪካ ጉዳዮች አማካሪ ሚኒስትር ጌታቸው ረዳ፣ በአካባቢው ያሉ የተለያዩ ሀገራት ትብብር ለህልውና በሚል ለተደራጀው የተቃዋሚዎች ጥምረት ድጋፍ ያደርጋሉ በሚል ተናግረዋል

በትግራይ ክልል ማህበራዊ አገለግሎቶችን መልሶ የማስጀመር ጥረት 23.10.2026

በትግራይ ክልል በተቀሰቀሰው ግጭት ክፉኛ የማህበራዊ ቀውስ ከተጋረጠባቸው የማህበራዊ አገልገሎት ዘርፎች አንዱ የትምህርት ዘርፍ ነው፡፡ አስተያየት ሰጪ የመቀሌ ከተማ ነዋሪ ዛሬ ለዶይቼ ቬለ እንደነገሩት በከተማዋ አሁንም ሙሉ በሙሉ ስጋቶች ባይወገዱም የተሸለ መረጋጋት መኖሩን አስረድተዋል

የዜጎች በሕይወት የመኖር መብት ይከበር - ኢሰመጉ 23.10.2026

የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ጉባኤ (ኢሰመጉ) "የዜጎች በሕይወት የመኖር መብት ሊከበር ይገባል" ሲል ትናንት ባወጣው መግለጫ እንዳለው፣ ታጣቂዎች ባሉባቸው የተለያዩ አካባቢዎች በየጊዜዉ ከሚቀሰቀሱ ግጭቶች ጋር ተያይዞ "ንፁሃን ዜጎች ለሞት፣ ለአካል ጉዳት፣ ለእገታ፣ ለንብረት ውድመት እና መፈናቀል ተዳርገዋል።"

በዓለም ላይ በማንኛውም ቦታ የሚከሰት ግጭት ሁልጊዜም የሚያሳዝን ነው፤ ነገር ግን ይህ በተለይ በኢትዮጵያ ሲታይ ይበልጥ ያሳዝናል። 22.10.2026

ኢትዮጵያ በሌሎች አፍሪቃዉያን ዘንድ የነጻነት የኩራትና የጥንታዊ ስልጣኔ ተምሳሌ ተደርጋ ትታወቃለች። ሀገሪቱ ዉስጥ ከስምንት ዓመታት በላይ የሆነዉን የፖለቲካ ቀዉስ የጎሳ ግጭት፤ የሃይማኖት አለመቻችል፤ አፈናና ግድያ፤ በዓለም አደባባይ ዜና ከሆነ ሰነባበተ። የኢትዮጵያን ጥንታዊነትና ታሪኮች የሚያዉቁ የዉጭ ዜጎች ምን ነካቸዉ ማለታቸዉ አልቀረም።

የቅድመ ምርጫ መድረክ ላይ ዶቼ ቨለ ያነጋገራቸው አላን አብራሞቪትዝ ፣ የፖለቲካ ሳይንስ ኤሚሪተስ ፕሮፌሰር ናቸው።የአጋማሽ ዘመን ምርጫውን ውጤት አዝማሚያ በተመለከተም ተከታዩን አስተያየት ሰጥተውናል። 22.10.2026

ሊካሄድ ጥቂት ቀናት የቀረው፣ የአሜሪካ አጋማሽ ዘመን ምርጫ፣ሃገሪቱ ከሌሎች ሃገሮች ጋር ያላትን ግንኙነት፣በቀጣይ ጊዜያት የመለወጥ አንደምታ እንደሚኖረው ባለሙያዎች አመለከቱ። ምርጫውን የሚወስኑ ጉዳዮች ላይ የመከረ የባለሙያዎች ውይይት፣አትላንታ ጆርጂያ ውስጥ ተካሄዷል።

በጋምቤላ ከተማ ከዛሬ ጀምሮ የመንግስ ተቋማት ስራ እንዲጀምሩ ማሳሰቢያ ተሰጥቷል። በግጭቱ የአብዛኞች ተፈናቃዮች መኖሪያ ቤት መፍረሱ ተመልክቷል። 22.10.2026

በጋምቤላ ከተማ በጥቅምት 4/2019 ዓ.ም በተከተሰው ግጭት ውስጥ ተሳፈዋል ተብለው የተጠረጠሩ 9 ግለሰቦች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን አስታውቋል፡፡ በዚህ ግጭት ውስጥ መደበኛ ፖሊሶች መሳተፉቸውን እና ሦስቱ በቁጥጥር ስር ከዋሉት መካከል ናቸው ተብሏል፡፡ ከተጠርጣሪዎቹ መካከል የፖሊስ አባላት ይገኙበታል።

ኤርትራ በአፍሪካ ቀንድ "እየተባባሰ የመጣ" ያለችው አለመረጋጋት ሙሉ በሙሉ በብልጽግና ፓርቲ "የታቀደና ለበርካታ ዓመታት የዘለቀ ጂኦፖለቲካዊ ጥቃት ውጤት ነው" ስትል ከሰሰች። ኤርትራ “አጥፊ ሚና" እየተከተለች ነው - አቶ ጌታቸው ረዳ 22.10.2026

ኤርትራ መከላከያ ኃይሏ ዓለም አቀፍ እውቅና ባለው ድንበሯ ውስጥ ብቻ ይገኛሉ ስትል ሠራዊቷ ኢትዮጵያ ውስጥ መግባቱን በሚመለከት የቀረበባትን ክስ ውድቅ አድርጋለች።

በትግራይ ክልል በቅርቡ የተከሰተውን ግጭት ተከትሎ የተቃወሰው የጤና ዘርፉ አሁን አሁን አገልግሎታቸውን መመለሳቸውን አስታውቋልም፡፡ 22.10.2026

በሰሜን ኢትዮጵያ የተከሰተውን ጦርነት ተከትሎ የሰብዓዊ ድጋፎች ማስተባበርን ስጋት ውስጥ ከቶት ቢሆንም የተለያዩ የተራድኦ ድርጅቶች የመድሃኒትና ምግብ ነክ እርዳታዎችን እያቀረቡ መሆኑን አስታወቁ፡፡ ድጋፉን የሚጠባበቁ የማህበረሰብ አካላትም እስካሁን ድረስ እጃቸው ላይ ባይገባም በሚሰሙትና በሚደረጉ ውይይቶች ተስፋቸው መለምለሙን ገልጸዋል፡፡

“በሁለቱም በኩል ሽማግሌዎች እና አስተዳዳሪዎች አብረው ተቀምጠው ተወያይተው እልባት ማስቀመጥ አለባቸው፡፡ በዚህ ውጥረት በከተማዋ እንቅስቃሴ በመቆሙ የደሃ ልጅ በርሃብ እየተቸገረ ይገኛል” 22.10.2026

በኦሮሚያ ክልል ሞያሌ ከተማ በሰንደቃላማ በተነሳው ውዝግብ በተቀሰቀሰ ግጭት የሰው ህይወት ማለፉን የአይን እማኞች። በሶማሌ እና ኦሮሚያ ክልሎች አዋሳኝ ላይ በምትገኘው ሞያሌ “ያለ ቦታው ተሰቀለ” በተባለ ባንድራ ላይ ቅሬታ ያላቸው የአከባቢው ነዋሪዎች ተቃውሞ አስነስተዉ በሁለቱ ክልሎች የጸጥታ ሃይሎች መሃል አለመግባባት ተፈጥሮም ነበር።

ጦርነት የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ዕድገት ላይ የሚያሳድረውን ተጽዕኖ “ለመገምገም ጊዜው ገና” እንደሆነ ዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት ገለጸ 21.10.2026

ዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት በኢትዮጵያ “የጸጥታ ውጥረት መጨመር” እና ግጭት በሚደረግባቸው አካባቢዎች በሚኖሩ “ማኅበሰረቦች ላይ የሚያሳድረው ተጽዕኖ” እንደሚያሳስበው አስታወቀ። የግጭቱ “ስፋትና የሚቆይበት ጊዜ” ስለማይታወቅ በኢኮኖሚ ዕድገት ላይ የሚያሳድረውን ተጽዕኖ “ለመገምገም ጊዜው ገና” እንደሆነ የድርጅቱ ቃል አቀባይ ለዶቸ ቬለ ገልጸዋል

የአፍሪቃ ቀንድ ሁኔታ በፓለቲካ ሳይንስ ምሁሩ ዕይታ 21.10.2026

የኢትዮጵያና የተቀረው የአፍሪቃ ቀንድ ሁኔታ ከመቼውም ጊዜ በላይ አስጊ መሆኑን አንድ የፖለቲካ ሳይንስ ምሁር ገለጹ።

በትግራይ ለተቋቋመው ባለአደራ አስተዳደር ሙሉ ድጋፍ እንደሚያደርግ የተመድ ገለፀ 21.10.2026

በቅርቡ ለ6 ወራት እንዲቆይ ሆኖ ለተመሠረተው የትግራይ ክልል ባለአደራ አስተዳደር ሙሉ ድጋፍ እንደሚያደርግ በኢትዮጵያ የተባበሩት መንግሥታት ጽሕፈት ቤት ገለፀ።

በቀይ ባሕር ያለው የፀጥታ ችግር መቀጠል የኢትዮ-ኤርትራን ጦርነት የመነሳት እድል ይቀንሳል? 21.10.2026

በቀይ ባሕር አካባቢ የቀጠለው ውጥረት ኢትዮጵያና ኤርትራ ወደ ጦርነት እንዳይገቡ በኃያላን ሃገራት የሚደረገውን ጫና ሊያጠናክረው እንደሚችል የፀጥታ ተንታኛች አመለከቱ።

በአርሲ ቀጥሏል የተባለው ጥቃትና የሀገረ ስብከቱ አቤቱታ 21.10.2026

በአርሲ ሀገረ ስብከት በሚገኙ በሺርካና በሆንቆሎ ዋቤ ወረዳዎች በጥቅምት ወር 2019 ዓ.ም. በተፈጸሙ ጥቃቶች በርካታ ሰዎች መገደላቸውን፣ ሌሎች መታገታቸውን በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ የአርሲ ሀገረ ስብከት አመለከተ።

ኢትዮጵያዊው ፕሮፌሰር ዓለም አቀፍ የሳይንስ ሽልማትን አሸነፉ 21.10.2026

ሰሞኑን በስኮትላንድ ግላስጎው በተካሄደ ዓለም አቀፍ የሳይንስ ጉባኤ ኢትዮጵያዊው ፕሮፌሰር ሰለሞን ተፈራ የፓማላ ስክላር ዓለም አቀፍ የፈጠራ ሽልማት አሸናፊ ሆነዋል። ፕሮፈሰር ሰለሞን ለሽልማት የበቁት ከአእምሮ ጤና እክሎች አንዱ የሆነው የድባቴ በሽታ ከአፍሪቃውያን ዘረመል ጋር ያለውን ትስስር ለመረዳት ባደረጉት ጥልቅ ምርምር ነው።

በኬኒያ የኤቦላ ቫይረስ ተጠቂዎች ቁጥር ስምንት መድረሱ ተረጋግጠዋል። ከመስከረም ወር አጋማሽ ጀምሮ በአገሪቱ በተከሰተው የኤቦላ ቫይረስ የመጀመሪው ተጠቂ ነው የተባለው የ40 ዓመት ጎልማሳ ባለፈው ሳምንት በበሽታው ህይወቱ አልፏል ፡፡ 20.10.2026

ኢትዮጵያ ከኬኒያ በምትዋሰንባቸው ድንበሮች ላይ የኤቦላ ቫይረስ ሥርጭትን ለመከላከል የሚያስችል የጤና ባለሙያዎች ቡድን ማሰማራቷን የጤና ጥበቃ ባለሥልጣናት አስታወቁ ፡፡ የጤና ባለሙያ ቡድኖቹ ወደ አካባቢዎ የተንቀሳቀሱት በጎረቤት ኬኒያ በቫይረሱ የሚያዙ ሰዎች ቁጥር እየጨመረ መምጣቱን ተከትሎ ነው ፡፡

የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አሕመድ የኤርትራን መንግሥት ወቀሱ፣ አስጠነቀቁም 20.10.2026

ኤርትራ መንግሥት "ልማትንና ተቋማትን መገንባት ትቶ የኢትዮጵያ ጠላቶች መሣሪያ ሆኗል" ሲሉ የከሰሱት ዐቢይ አሕመድ ይህ ጉርብትናን ያበላሻል ብለዋል። አክለውም "ጥሩ ጉርብትና እና ወዳጅነት ብቻ" እንደሚያዋጣ፣ ከዚህ ውጭ ያለው አማራጭ እንደማይጠቅምም አብራርተዋል።

በሱሉላ ፍንጫኣ ወረዳ ታጣቂዎች የሚሊሻ አባላትን ጨምሮ 5 ሰዎች ገደሉ 20.10.2026

በሱሉላ ፍንጫ ወረዳ ውስጥ የሚገኘው የፍንጫ ስኳር ፋብሪካ በተለያዩ ወቅቶች የጥቃት ሰለባ ሆኖ የቆየ ሲሆን ከ2015 ዓ.ም ወዲህ ትላንት ጠዋት በፋብሪካው ግቢ ውስጥ የደሰው ጥቃተ ከፍተኛ እንደሆነ ያነጋርናቸው የአካባቢው ነዋሪዎች ገልጸዋል፡፡

የትግራይ ክልል ነዋሪዎች ተስፋና ሥጋት 20.10.2026

የመቀሌ ከተማ ነዋሪ እንደነገሩን፤ “እዚህ እንከታተለዋለን በረራው ቀጥሏል፤ እንቅስቃሴውም ወደ መደበኛው ይዞታው የተመለሰ መስሏል” በማለት በቅርቡ ህወሓት አውጥቶት ከነበረው ማስጠንቀቂያ ጋርም ተያይዘው በሰጡት አስተያየት፤ “ማስጠንቀቂው አየርመንገዱ ወታደራዊ አገልግሎት መስጠት የለበትም” የሚል ይመስላል

ስለጡት ካንሰር የሰዎች ግንዛቤ እየተሻሻለ ይሆን? 20.10.2026

በየዓመቱ በጎርጎሪዮስ የዘመን ቀመር ጥቅምት ወር ላይ በዓለም አቀፍ ደረጃ ስለጡት ካንሰር የሰዎች ግንዛቤ ከፍ እንዲል የተለያዩ እንቅስቃሴዎች ይከናወናሉ። መገናኛ ብዙኃንም ስለጡት ካንሰር መረጃዎችን ለሕዝብ ያቀርባሉ። ይህ እንቅስቃሴ ኢትዮጵያም ውስጥ ይከናወናል። ለውጥ እያመጣ ይሆን?

ማሕደረ ዜና፣ ቀይ ባሕር፤ በደም ቀልቶ ደም የሚገበርለት ባሕር 19.10.2026

ኢትዮጵያና ኤርትራ አንድ ሐገር በነበሩበት ዘመን ይዋጉ ነበር።30 ዓመት። ሁለት ሐገርም ሆነዉ ይዋጋሉ።የአሥመራና የአዲስ አበባ መሪዎች ያልተዋጉበት ጊዜ ከነበረ-አንድም-በ1990ዎቹ እንዳየነዉ «የጋራ ጠላት» የሚሏቸዉን መንግሥትን ወይም በ2013 እንደሆነዉ የመቀሌ ገዢዎችን ለመዉጋት የተወዳጁበት-ሁለትም አንዱ የሌላዉን ጠላት የሚያደራጁበት ነበር።

ከተመዘገቡ መራጮች 51 ሚሊየን ገደማ ማለትም 95 በመቶ ያህሉ ወጥተው መምረጣቸውን ያመለከተው ጥናቱ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 90 በመቶ ያህሉን ገዢው ብልጽግና ፓርቲ ማሸነፉንም አስታውሷል፡፡ 19.10.2026

የኢትዮጵያ ሲቪል ማህበራት ድርጅት ህብረት ለምርጫ በ7ኛው የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምርጫ የትዝብት እና የሚዲያ ክትትል ሪፖርት ግኝቱን ይፋ አድርጓል። የሲቪል ተቋሙ ባዘጋጀው የውይይት መድረክ በምርጫው ቅድመ ዝግጅት ወቅት፣ በምርጫው እለት እና ከምርጫው በኋላ የታዘባቸውን ጉድለቶች እና ጥንካሬዎች ይፋ አድርጓል፡፡

Listen to the DW | Amharic - News podcast in Replaio

Radio and podcasts in one app - free, with no sign-up. Install today and do not miss the launch

Get it on Google Play

Replaio is not a podcast publisher; show names, artwork and audio belong to their authors and are distributed through public RSS feeds.