DW | Amharic - News

News, Analysis and Service from Germany and Europe - in 30 Languages

Be sure to visit the podcast's website and support the creator: www.dw.com

Category

Uncategorized

Podcast website

www.dw.com

Latest episode

Nov 20, 2026

Where to listen?

Podcasts in the app Replaio Radio Coming soon

Podcasts are coming to the app soon. Install now and be the first to see a whole new take on podcasts

Get it on Google Play Install for free Android 10M+ downloads · 4.7+ rating iOS soon

Episodes

ሞያሌ፦ የይገባኛል ውዝግብ ከሚቀሰቅሰው ግጭት ያልተላቀቀች የኢትዮጵያ እና ኬንያ የንግድ ከተማ 28.10.2026

ለኢትዮጵያ እና ኬንያ ቁልፍ የንግድ ከተማ የሆነችው ሞያሌ ዳግም በግጭት ስትናጥ ወደ 50,000 የሚሆኑ ሰዎች ተሰደዋል። ሞያሌ የሰዎች፣ የአደንዛዥ እጽ እና የጦር መሣሪያ አዘዋዋሪዎች የሚያዘወትሯት ኹነኛ የገበያ ማዕከል ነች። የኦሮሚያ እና የሶማሌ ክልሎች በይገባኛል የሚወዛገቡባት ከተማ የግጭት ሰለባ ስትሆን የአሁኑ የመጀመሪያ አይደለም።

አይኮግ ላብስ ፤የኤአይ ቴክኖሎጂን ለሚሊዮኖች ተደራሽ ለማድረስ የሚሰራው ኩባንያ 28.10.2026

አዲስ አበባ የሚገኘው «አይኮግ ላብስ«የቴክኖሎጂ ማዕከል የኢትዮጵያውያንን ተሰጥኦና ዕውቀት በመጠቀም የሰውሰራሽ አስተውሎት ቴክኖሎጂ ምርምር እና ልማት ላይ በማተኮር ይሰራል።«አይኮግ ላብስ« በምስራቅ አፍሪቃ የመጀመሪያው በሰውሰራሽ አስተውሎት ምርምር ላይ የተሰማራ ኩባንያ ሲሆን፤ ለዓለም አቀፍ ገበያዎች ተግባራዊ የኤአይ መፍትሄዎችን ያቀርባል።

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲን በቅዱስ ሲኖዶስ በኩል ባሰማችው የሀዘን መግለጫ፤ በሰሞነኛው በአርሲ ዞን ሁለት ወረዳዎች "ግፍን በተሞላ ጭካኔ" 60 ምዕመናን መገደላቸውን ገልጻለች። 28.10.2026

በኢትዮጵያ ኦሮሚያ ክልል ደቡብ ምስራቃዊ ዞን አርሲ ውስጥ በተደጋጋሚ በሚከሰት የሰላማዊ ዜጎች ግድያ በርካታ የሰብኣዊ ተቋማት ማሳሰቢና የሃማኖት ድርጅቶች አቤቱታ ተሰምቷል። በተለይም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲን “ምዕመናኖቼ እየተገደሉብኝ ነው” በማለት ተደጋጋሚ የጸጥታው ጥበቃ ጥሪን ለሚመለከተው የመንግስት ተቋማት ጥሪ አሰምታለች።

በጸጥታ ችግር በአማራ ክልል የተከሰተው የባንክ አገልግሎቶች መስተጓጎልና ከፍተኛ የጥሬ ገንዘብ እጥረት 28.10.2026

ባለፉት ሦስት ዓመታት በአማራ ክልል በመንግሥትና በፋኖ ኃይሎች መካከል የሚካሄደው ጦርነት አንድ ጊዜ ቀዝቀዝ ሌላ ጊዜ ደግሞ ሞቅ እያለ በቀጠለበት በዚህ ጊዜ ጦርነት በተካሄደባቸው አካባቢዎች ያሉ የማህበረሰብ ክፍሎች በሰሜን ሸዋ፣ ደቡብና ሰሜን ወሎ ከፍተኛ የጥሬ ገንዘብ እጥረት በማጋጣሙ ለግብይት መቸገራቸውን ነዋሪዎች ይገልፃሉ።

በአፍሪካ ቀንድ ያሉ ግጭቶች መጨመር ለቀጠናው የሚሰጠው ትኩረት መበታተን 28.10.2026

የሰሜን ኢትዮጵያው ግጭት ማገርሸት፣ ዓለምአቀፉ ማኀበረሰብ በቀጠናው ላሉ ግጭቶች የሚሰጠውን ትኩረት እንደሚበታትነው የፖለቲካና የፀጥታ ጉዳይ ተመራማሪዎች ገልፀዋል። በቀጠናው ላሉ ግጭቶች የሚሰጠው ትኩረት በፊትም ውስን መኾኑን የጠቀሱት ተመራማሪዎቹ፣ ሌላ ግጭት መጨመሩ ደግሞ የበለጠ እንደሚያሳንሰው አመልክተዋል።

የህወሓት "ካድሬዎች" በፖሊስ ጣቢያዎች እንዲመዘገቡ መጠየቁ "የሕብረተሰቡን በሰላም፣ ተቻችሎ የመኖር ዕሴት የሚሸረሽር ነው" 28.10.2026

የትግራይ ሰላም ኃይል የተባለው የትጥቅ ቡድን የህወሓት "ካድሬዎች" በየአካባቢያቸው ባሉ ፖሊስ ጣቢያዎች ቀርበው እንዲመዘገቡ ሲል መጠየቁ ሕገ-ወጥ ተግባር ነው በሚል ተቃውሞ ቀረበበት።ቅድሚያ ለሰብአዊ መብት ኢትዮጵያ "ደኅንነትና ፀጥታን ማስጠበቅ የመንግሥት ኃላፊነት" እንጂ ሕጋዊ መሠረት የሌላቸው የትጥቅ ቡድኖች አይደለም ሲል ውድቅ አድርጓል።

ጀርመን በቀድሞ ቅኝ ግዛትዋ በናሚብያ ለተፈጸመው የዘር ማጥፋት ወንጀል እውቅና እንድትሰጥ የሚደረግባት ግፊት 27.10.2026

የሀምቡርግ ዩኒቨርሲቲ የታሪክ ምሁር ዩርገን ዚመርማን ፣ በርሳቸው አስተያየት የጀርመን የህዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤትም ሆነ መንግሥት የራሳቸውን ያለፈ ታሪክ በቁም ነገር ለመጋፈጥ ፈቃደኛ አይደሉም ብለዋል ። ዚመርማን ለዶቼቬለ እንደተናገሩት ፈቃደኝነቱ ካለ የሚፈለገው በጣም በፍጥነት እውን ሊሆን ይችላል።

በኦሮሚያ ክልል አርሲ ዞን ሺርካ ወረዳ በተፈጸመው ጥቃት ከቆሰሉ ሰዎች መካከል የተወሰኑት ሕይወታቸው እንዳለፈ የአካባቢው ነዋሪዎች ተናገሩ። 27.10.2026

በኦሮሚያ ክልል ደቡብ ምስራቃዊ ዞን አርሲ-ሺርካ ወረዳ ቢርቦና ጮሌ ቀበሌ ቅዳሜ ጥቅምት 14 ቀን 2019 ዓ.ም. በተፈጸመው ጥቃት ከቆሰሉ ሰዎች መካከል የተወሰኑት ሕይወታቸው እንዳለፈ የአካባቢው ነዋሪዎች ተናገሩ። በጥቃቱ ምክንያት ከቀያቸው ተፈናቅለው በአብያተ ክርስቲያናት ተጠልለው እንደሚገኙ ዶቸ ቬለ ያነጋገራቸው ነዋሪዎች ገልጸዋል።

ብርቱ ውግዘት እና የሕግ ከለላ ጥያቄ ያስከተለው በኦሮሚያ ክልል የተፈፀመው ግድያ 27.10.2026

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ በአርሲ ዞን ሁለት ወረዳዎች መስከረም 10 እና 14 ቀን 2019 "ግፍን በተሞላ ጭካኔ" 60 ምዕመናን መገደላቸውን ገልጿል። ውስን የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ ድርጊቶቹን አውግዘው፣ የዜጎችን ሕይወትና ደኅንነት፣ የሃይማኖት ነፃነትና ፍትሕ ማስከበር ነበረበት ያሉትን መንግሥት ተጠያቂ አድርገዋል።

የኩላሊት ታማሚዎች ህክምና እና ማህበራዊ ህይወታቸው 27.10.2026

ወጣት አስመላሽ ግርማ በሀዋሳ ከተማ የኩላሊት አጥበት /ዲያሊሲስ/ በማድረግ ላይ ከሚገኙ ህመምተኞች መካከል ነው ፡፡ ወጣት አስመላሽን ጨምሮ የዲያሊሲስ ህክምና ለማግኘት ወደ ሀዋሳ ሜሪ ጆይ የህክምና ማዕከል ከመጡት ታማሚዎች መካከል አብዛኞቹ በወጣት የዕድሜ ክልል ውስጥ የሚገኙ ናቸው ፡፡

በእስራኤል ከፍተኛ ግምት የተሰጠው ምክር ቤታዊ ምርጫ ሲካሔድ ዋለ 27.10.2026

ዛሬ ሲካሔድ የዋለው የክነሰት ምክር ቤታዊ ምርጫ እስራኤልን ለረዥም ዓመታት በመምራት ቀዳሚ በሆኑት ጠቅላይ ሚኒስትር ቤኒያሚን ኔታንያሁ ላይ የሚሰጥ ሕዝበ-ውሳኔ ተደርጎ እየታየ ነው። ኔታንያሁ ከዋና ተቀናቃኛቸው እና የቀድሞው የእስራኤል ጦር ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ጋዲ አይዘንኮት ጋር አንገት ለአንገት ተናንቀው እንደሚገኙ አሶሼትድ ፕሬስ ዘግቧል።

በአበሽጌ ወረዳ ከሐሙስ ወዲህ ሦስት ሰዎች ሲገደሉ 20 ሰዎች ታግተው መወሰዳቸውን የአካባቢው ነዋሪዎች ተናግረዋል 27.10.2026

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ጉራጌ ዞን አበሽጌ ወረዳ የሚፈጸመው የንጹሃን ግድያ እና እገታ እየተባባሰ መምጣቱን ነዋሪዎች ገለጹ፡፡ ከባለፈው ሐሙስ ወዲህ ብቻ በወረዳው ሦስት ሰዎች በታጣቂዎች ሲገደሉ 20 ሰዎች ታግተው ተወስደዋል፡፡ የክልሉ መንግስት ነባር አገር በቀል እሴቶችን በመጠቀም የአካባቢውን ሰላም ለማስፈን እንደሚሰራ አስታውቋል ፡፡

የፕሬዝደንት ቭላድሚር ፑቲን መንግሥት ውጥረት ውስጥ የገቡትን የኢትዮጵያ እና የኤርትራ ባለሥልጣናት በሩሲያ አፍሪካ የመሪዎች ጉባኤ ማገናኘት ይፈልጋል 26.10.2026

ኃይለኛ ፍጥጫ ውስጥ የገቡትን የኢትዮጵያ እና የኤርትራ ባለሥልጣናት የፕሬዝደንት ቭላድሚር ፑቲን መንግሥት በዚህ ሣምንት በሦስተኛው የሩሲያ-አፍሪካ የመሪዎች ጉባኤ ማገናኘት ይፈልጋል። በቀይ ባሕር በኩል ኢትዮጵያ ወደብ ለማግኘት የምታደርገው ግፊት ከታላቁ ህዳሴ ግድብ ድርድር “ምንም ዐይነት ግንኙነት” እንደማይኖረው ግብጽ አስታውቃለች።

"ግጭቱን የአጠቃላይ የማህበረሰቡ ለማድረግ የሚጥሩ አካላት አሉ ጉዳዩ የማይመለከታቸውን ንጹሃን ጭምር እየሞቱ ነው" 26.10.2026

በነፍስ ወከፍ መሳሪያ ታጅቦ በተደጋጋሚ የሚነሳው ግጭት ባለፉት 10 ዓመታት ውስጥ የ200 በላይ ሰዎችን ህይወት ቀጥፏል። በ2017 ዓ.ም በሁለቱ ብሄሮች መካከል የተደረገውን የእርቅ ስምምነት የሚያስፈጽም የመንግስት የጸጥታ አካል ባለመኖሩና ችግሩ በቸልተኝነት በመታየቱ ግጭቱ ሊቆም እንዳልቻለ የአካባቢው ነዋሪዎች እና የአገር ሽማግሌዎች ገልጸዋል።

በሁሉም ግንባር "ጠላት" ባለው የፌዴራል መንግሥት ላይ "ከፍተኛ ጉዳት እያደረሰ" እንደሆነም ባወጣው መረጃ ጠቅሷል። 26.10.2026

የኢትዮጵያ የፖለቲካና የጦር መሪዎች መስከረም 13 ቀን 2019 ትግራይ ክልል ውስጥ የተጀመረው ጦርነት በህወሓት ሽንፈት መጠናቀቁን ደጋግመው እየገለፁ ነው። የጦር ኃይሎች ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ ሠራዊቱ ህወሓትን ባቻ ሳይሆን ትብብር ለሕልውና የተባለውን ጭምር ማሸነፉን ገልፀዋል።

የሰኞ ጥቅምት 16 ቀን 2019 ዓ/ም የስፖርት ዝግጅት 26.10.2026

ዝናባማ ና ነፋሻማ በሆነ የአየር ሁኔታ በተካሄደው የፍራንክፈርት ማራቶን የሴቶችውድድር ዘይነባ ይመር በ2:19:45 ሰከንድበሆነ ሰአት አሸናፊ ሆናለች ። ጀርመናዊቷ ብላንካ ዶርፌል የመጀመሪያ ማራቶኗን በሮጠችበት ውድድር በ2:20:46ሰከንድ በሆነ ሰአት ርቀቱን ሁለተኛ ሆና ጨርሳለች

"ባዱ ተኩስ በሁለቱ ክልሎች የጸጥታ አካላት እና በታጠቁ ማህበረሰብ አካላት ጭምር ሓሙስ ጀምሮ ዓርብም ቀጥሎ ሌሊትን ግን የቀጠለው የተኩስ እሩምታ እንቅልፍም የሚነሳ እንደነበር ተገልጿል፡፡" 26.10.2026

በኦሮሚያ እና ሶማሌ ክልል አዋሳኝ ላይ በምትገኘው የደቡባዊ ኢትዮጵያ ጠረፍ ከተመዋ ሞያሌ ከአንድ ሳምንት በፊት የተነሳው ግጭት አድማሱ ሰፍቶ ከፍተኛ ውድመት እና ሰብዓዊ ቀውስ እያስከተለ መሆኑ ተነግሯል፡፡ ባልረገበው ግጭቱ ምክንያት ከድንበር ከተማዋ ሞያሌ ወደ ኬንያ የሚሻገሩ ተሰዳጅ ሰላማዊ ሰዎች ቁጥርም በከፍተኛ መጠን መጨመሩ ነው የተሰማው፡፡

የሶማሌ ፌደራሊስት ፓርቲ፤ በሞያሌ ከተማ ግጭት የፌደራል መንግስት ጣልቃ እንዲገባ ጠየቀ 26.10.2026

ኦሮሚያ እና ሶማሌ ክልል በሚዋሰኑባት ሞያሌ ከተማ ከቀናት በፊት ለተቀሰቀሰው ግጭት የፌደራል መንግስት ጣልቃ ገብቶ እልባት እንዲሰጥ የሶማሌ ፌደራሊስት ፓርቲ ጠየቀ። የፓርቲዉ ሊቀመንበር የአካባቢው ግጭት "ተደጋጋሚ እና አሳሳቢ" እየሆነ መምጣቱን ተናግረዋል።

የአርሲ- ሺርካው የጅምላ ጥቃት፤ ከንጹሃን በጠጨማሪ ሰላማዊውን ህዝብ የሚጠብቁ የቀበሌ ታጣቂዎችም አልቀዋል 26.10.2026

በቅዳሜው የአርሲ-ሺርካ ቢርቦና ጮሌ ቀበሌው አስከፊ የዜጎች ጥቃት ከአንድ ቤት ሙሉ ቤተሰብ ያለቀባቸው ሳይቀር እጅግ ከፍተኛ የሆነ “ዘግናኝ” ክስተት ነው የተፈጠረው ሲሉ አስተያየታቸውን የሰጡ የአይን እማኞችና ተጎጂ ቤተሰብ እንዲህ ያለ የከፋ ነገር በአከባቢው ታይቶም ተሰምቶም አይታወቅም ብለዋል።

የትግራይ ክልል ጦርነት ፤ የአማራ ክልል ውጊያ ፤ የኢትዮጵያና የኤርትራ የቃላት ጦርነት ወዴት ያመራሉ? 25.10.2026

ህወሓትን ጨምሮ የኢትዮጵያ መንግሥትን የሚወጉትን ኃይሎች ትደግፋለች በምትባለው በኤርትራና በኢትዮጵያ መካከል የቃላት ጦርነቱ ቀጥሏል። የኢትዮጵያው ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የኤርትራ መንግሥት «የኢትዮጵያ ጠላቶች መሣሪያ ሆኗል" በማለት ኤርትራ ለአማፅያን የምትሰጠውን ድጋፍ ከቀጠለች «ከባድ መዘዝ» ይጠብቃታል በማለት አስጠንቅቀዋል።

ጦርነቶችና የአየር ንብረት ቀውስ ከጊዜ ወደ ጊዜ በርካታ ሰዎችን፣ በተለይም አፍሪቃን እየጎዳ ነው። ውጤቱም፡ ስደት፣ መፈናቀልና ረሃብ ሆንዋል። ሁለት ዘገቦች እንደሚያመለክቱት ለዓለም ማህበረሰብ እውነታዎችን እና ምክረ ሀሳቦችን ያቀርባሉ። 24.10.2026

ከፍተኛ የሆነ አጣዳፊ የምግብ ዋስትና እጦት ካጋጠማቸው ሰዎች ቁጥር አንጻር፣ በዓለም ላይ ብዙ ሰዎችን የያዙት አስር ሀገራት ዝርዝር በአብዛኛው የአፍሪቃ ሀገራትን ያካተተ ነው። ናይጄሪያ፣ ኮንጎ እና ሱዳን ግንባር ቀደም ናቸው። ደቡብ ሱዳንም ለመጀመርያ ጊዜ ተካታለች። ከህዝቧ ከ80 በመቶ በላይ የሚሆነው የሰብአዊ እርዳታ ጥገኛ ነዉ።

ወደ ሁከት እና ንብረት ውድመት ያመራው የፈረንሳይ ተቃውሞ 24.10.2026

የተሻሉ የትምህርት መገልገያዎችን፣ ተጨማሪ መምህራንን እና በሀገሪቱ የትምህርት ስርዓት ላይ ሌሎች ማሻሻያዎችን በመጠየቅ በቅርቡ በተማሪዎች የተጀመረው የፈረንሳይ ተቃውሞ ፣ ወደ አጠቃላይ የኑሮ ውድነትን የተመለከተ የህዝብ ቁጣ ተቀይሯል።

የቀይ ባሕር ደህንነት ጉዳይ ለጥቂት ሀገራት ብቻ የሚተው አይደለም ስትል ኢትዮጵያ አስታወቀች 24.10.2026

የቀይ ባሕር ደህንነት ጉዳይ ለጥቂት ሀገራት ብቻ የሚተው አይደለም ስትል ኢትዮጵያ አስታወቀች።የአፍሪካ የደህንነት ጉባኤ የኾነው ጣና ፎረም ባዘጋጀው መድረክ ላይ የብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን፣ ኢትዮጵያ የደህንነት ሰጋቶችን የማስወገድና የንግድ መርከቦቿን የመጠበቅ አስፈላጊ ኃላፊነት አለባት ብለዋል።

የስራ ዘመኑን ያጠናቀቀው አገራዊ ምክክር ኮሚሽን እና ውጤቱ 24.10.2026

ከአራት አመት በላይ በስራ ላይ የቆየው የኢትዮጵያ አገራዊ የምክክር ኮሚሽን ዛሬ በህግ የተሰጠውን የስራ ዘመኑን አጠናቋል፡፡የአገራዊ ምክክር ኮሚሽኑ 8 ዋና ዋና አገራዊ አጀንዳዎች እና የውሳኔ ምክረ ሐሳቦችንም አስቀድሞ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት፣ ለፌደራል እና ለክልል መንግሥታት አስረክቧል፡፡ ለመሆኑ የኮሚሽኑ ስራና ውጤቱ እንዴት ይገመገማል?

ፈረንሳይ በሳምንቱ መጨረሻ ለሚካሄዱ ተቃውሞዎች 70,000 የፖሊስ መኮንኖችን ለማሰማራት ወሰነች 24.10.2026

በአሁኑ ቅዳሜ እና እሁድ በፈረንሳይ የሚካሄዱ የተቃውሞ ሰልፎችን ተከትሎ የዓመፅና የዘረፋ ጥሪዎች በበይነመረብ እየተስፋፉ መሆናቸውን የሀገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስትር ሎረንት ኑኔዝ አስጠንቅቀዋል። የሚደርሰውን ጉዳት ለመከላከል እና በመላ አገሪቱ ሥርዓትን ለማስጠበቅ 70,000 የፖሊስ መኮንኖችን ለማሰማራት ሚንስትሩ ቃል ገብተዋል።

Listen to the DW | Amharic - News podcast in Replaio

Radio and podcasts in one app - free, with no sign-up. Install today and do not miss the launch

Get it on Google Play

Replaio is not a podcast publisher; show names, artwork and audio belong to their authors and are distributed through public RSS feeds.