DW | Amharic - News
News, Analysis and Service from Germany and Europe - in 30 Languages
Be sure to visit the podcast's website and support the creator: www.dw.com
Where to listen?
Podcasts in the app Replaio Radio Coming soonPodcasts are coming to the app soon. Install now and be the first to see a whole new take on podcasts
Episodes
የፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ የአጋማሽ የስልጣን ዘመን ምርጫ እና አንድምታዉ 02.11.2026
በዩናይትድ ስቴትስ፣ የፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ የአጋማሽ የስልጣን ዘመን ወይም የአማካይ ወቅት ምርጫ እና ዉጤቱ በጉጉት እየተጠበቀ ነዉ። ምርጫዉ የሚካሄደዉ ነገ ማክሰኞ ኖቬምበር 3 ወይም ጥቅምት 24 ነዉ። የምርጫዉ ዝግጅት ምን ይመስላል?-የቅድመ ትንበያ ዉጤቶችስ ምን ያሳያሉ?
የስፖርት ዘገባ፦ የጥቅምት 23 ቀን፣ 2019 ዓ.ም ፦ 02.11.2026
በኢትዮጵያ አትሌቲክስ ዘርፍ የሕገወጥ ኃይል ሰጪ ንጥረ ነገር ጉዳይ አሳሳቢ ደረጃ መድረሱ ተነግሯል፥ ቃለ መጠይቅ ይኖረናል ።ማንቸስተር ሲቲ ሽንፈት አስተናግዶ መሪነቱን አስረክቧል። አርሰናል ትናንት ሊቨርፑልን በአንፊልድ የገዛ ስታዲየሙ በደጋፊው ፊት አንድ ለዜሮ በመርታት የፕሬሚየር ሊጉ መሪነት ተቆናጥጧል ።
መንግስት ዜጎቹን ከተደጋጋሚ ጥቃት መታደግስ እንደምን ተሳነው ? ማንስ ኃላፊነቱን ይውሰድ ? 01.11.2026
በአዲሱ የኦሮሚያ ክልላዊ አደረጃጀት በደቡብ ምስራቅ ኦሮሚያ ዞን የቀድሞው የአርሲ ዞን የተለያዩ ወረዳዎች ባለፈው ሳምንት በተለይ የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን ምዕመናንን ዒላማ ያደረጉ ጥቃቶች መፈጸማቸው ተሰምቷል
ፍልሰት በሊቢያ እንዴት የሥልጣን ማጠናከሪያ የንግድ ሞዴል ለመሆን በቃ? 31.10.2026
በሊቢያ ሰዎች ማዘዋወር፣ ሥልጣን እና ትርፍ ማጋበስ አንዳቸው ከሌላቸው ተሣሥረዋል። ሰዎች ማዘዋወር ከአገሪቱ “የግጭት ኢኮኖሚ” በመቀናጀቱ ታጣቂ ቡድኖች መደበኛ ያልሆኑ ገበያዎችን እና የጉዞ መሥመሮችን በመቆጣጠር ኢኮኖሚያዊ ጥቅም እና ፖለቲካዊ ተጽዕኖ ያገኛሉ።
ሩሲያ በአፍሪካ ያላት ተጽዕኖ ምን ያክል ጠንካራ ነው? 31.10.2026
ሩሲያ ከአራት ዓመታት በፊት ዩክሬንን በመውረሯ ከምዕራባውያኑ ያስከተለው መቃቃር ፊቷን ወደ አፍሪካ እንድታዞር አድርጓታል። የሩሲያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ማሪያ ዛክኻሮቫ “ታሪካዊ መመለስ” ብለውት ነበር። ለመሆኑ ሩሲያ በአፍሪካ በጦር መሣሪያ ሽያጭም ይሁን በኢኮኖሚ ያላት ተጽዕኖ ምን ያህል ጠንካራ ነው?
ማህበራዊ አገለግሎቶች እየተጀመረበት ያለው ትግራይ ክልል 31.10.2026
ተደጋጋሚ የድሮን ጥቃቶች በሚፈጸሙበት የትግራይ ክልል ትምህርትና ጤናን ጨምሮ ተቋርጠው የነበሩ አገልግሎቶችን ለማስመለስ ጥረት እየተደረገ ነው። የክልሉ ባለደአራ አስተዳደር “በጦርነት ምክንያት የተጎዱ መሠረተ ልማቶችን በመጠገን” “ፈጥነው ወደ ሥራ እንዲገቡ ማድረግ” እና “ተቋርጠው የነበሩ ማኅበራዊ አገልግሎቶች” ማስቀጠል ይጠበቅበታል።
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ጉራጌ ዞን ወልቂጤ ከተማ ከተገደሉት ሦስት ሰዎች አንዱ የሆነው የኪነ ጥበብ ባለሙያ ዐይን እና ደረቱን በጥይት እንደተመታ ወዳጆቹ ተናገሩ 31.10.2026
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ጉራጌ ዞን ወልቂጤ ከተማ አንድ ኪነ ጥበብ ባለሙያን ጨምሮ ሦስት ሰዎች ተገደሉ ፡፡ ባለሙያው ግድያው የተፈጸመበት ለሥራ በወጣበት መሆኑን ለዶቼ ቬለ የተናገሩት የሟች ጓደኞች እና የቅርብ ዘመዶች በተሞላበት ሁኔታ በጥይት ተደብድቦ ነው ህይወቱ ያለፈው ›› ብለዋል ፡፡
በአማራ ክልል ዋግ የዋግ ኽምራ ዞን ውስጥ በሚገኙ ወረዳዎች በተከሰተው ድርቅ ምክንያት ሰዎች መሞታቸውን የአካባቢው ነዋሪዎች ለዶቸ ቬለ ተናገሩ። 31.10.2026
በአማራ ክልል ዋግ ኽምራ ዞን ውስጥ በሚገኙ ወረዳዎች በተከሰተው ድርቅ ምክንያት ሰዎች መሞታቸውን የአካባቢው ነዋሪዎች ለዶቸ ቬለ ተናገሩ። አንድ የጻግብጂ ወረዳ ነዋሪ በሚኖሩበት አካባቢ ለምግብ የሚሆን አስር ጣሳ ማሽላ እንኳ እንደጠፋ አስረድተዋል። በጦርነት እና በድርቅ በተጎዱት አካባቢዎች ሕጻናት፣ አረጋውያን እና እመጫቶች ለረሐብ ተጋልጠዋል።
በሶማሊያ የተባበሩት መንግሥታት ፖለቲካዊ ተልዕኮ ከ30 ዓመታት ገደማ በኋላ በይፋ ተዘጋ 31.10.2026
ከ30 ዓመታት በላይ የዘለቀው በሶማሊያ የተባበሩት መንግሥታት ፖለቲካዊ ተልዕኮ ዛሬ ቅዳሜ በይፋ ተዘግቷል። የተልዕኮው ኃላፊነቶች ወደ ሶማሊያ መንግሥት ተቋማት ወይም በአገሪቱ ወደሚገኘው የተባበሩት መንግሥታት ቢሮ ተሸጋግረዋል።
የደቡብ ሬዲዮ እና ቴሌቪዥን ድርጅትን ማን ይታደገው ? 30.10.2026
የደቡብ ሬዲዮ እና ቴሌቪዥን ድርጅት ባጋጠመው አስተዳደራዊና የፋይናንስ ቀውስ የተነሳ የህልውና ፈተና ውስጥ መውደቁን የድርጅቱ ሠራተኞች እየገለጹ ይገኛሉ ፡፡ ተቋሙ የሥርጭት መሣሪያዎችን ለመጠገንም ሆነ ለሠራተኖቹ ደሞዝ መክፈል ባለመቻሉ ቀጣይ ህልውናው አሳሳቢ ደረጃ ላይ መድረሱ ነው የተነገረው ፡፡
የወንዶች መሰወር እና አፈሳ በኢትዮጵያ: መታወቂያ የሌለው ይታፈሳልን? 30.10.2026
ከተለያዩ አካባቢዎች በተደጋጋሚ የሚፅፉልን የዝግጅታችን ተከታታዮች ወጣት ወንዶች በድንገት እና በግድ ከመንገድ እየታፈሱ ለውትድርና እየተመለመሉ እንደሆነ ይናገራሉ። ከዚህ ጋር በተያያዘ በተለያዩ ከተሞች ያሉ ወጣቶች ያላቸው ስጋት ምን ይመስላል? በዛሬው የወጣቶች ዓለም ዝግጅት አጠያይቀናል።
ተባብሶ በቀጠለው በየመኑ ጦርነት መሀል አትዮጵያውያን ወደ ሀገሪቱ እየፈለሱ ነው 30.10.2026
በየመን ያለው ጦርነት ተባብሶ በቀጠለበት በዚህ ወቅትም፣ ኢትዮጵያውያን ፍልሰተኛች በብዛት ወደ ሀገሪቱ መጓዛቸውን እንዳላቆሙ ዓለምአቀፉ የፍልሰት ድርጅት- IOM እና በዚያ የሚገኙ ዜጎች ገልፀዋል። በ2025 ዓ.ም ወደ የመን ከገቡት የአፍሪካ ቀንድ ፍልሰተኛች 97 በመቶ የሚኾኑት ኢትዮጵያውያን መኾናቸውን ድርጅቱ አስታዉቋል።
ለሰሞኑ ጥቃት የቀጠለው የፍትሕ ጥሪ፤ የመንግሥትና መገናኛ ዐዉታሮች ምላሽ 30.10.2026
በኦሮሚያ ክልል አርሲ ዞን ለተፈፀመው ግድያ ፍትሕና ተጠያቂነት እንዲሰፍን ማሕበረ ቅዱሳን ጠየቀ። ማሕበሩ በኢትዮጵያ ሕዝብ ግብር የሚተዳደሩ ያላቸው መገናኛ ዐውታሮች በተደጋጋሚ ተፈጽሟል ያለውን ጥቃት እንዳልሰሙ ማለፋቸውን አጥብቆ አውግዟል።የፖለቲካ ድርጅቶች ግለሰቦችና ይመለከተናል ያሉ ኹሉ ግድያውን እንዲቆም ተጠያቂነትም እንዲኖር እየጠየቁ ነው።
በሺርካው ጥቃት ለተጎጂዎች የደረሱ መታሰራው ቅሬታ ማስነሳቱ 30.10.2026
በኦሮሚያ ክልል ደቡብ ምስራቃዊ ዞን አርሲ-ሺርካ ወረዳ ባሳለፍነው ቅዳሜ በቢርቦና ጮሌ ቀበሌ በታጣቂዎች የደረሰውን ጥቃት ተከትሎ ከወረዳዋ ከተማ ወደ ጥቃቱ ስፍራው በመጓዝ ቦታው ላይ ተገኝተው ቀብር ካስፈጸሙ በርካቶች መታሰራቸው ቅሬታ ፈጥሯል፡፡ የታሰሩት ሰዎች ለተጎጂዎች ደርሰው ወገንተኝነት ከማሳየት ውጪ ጥፋታቸው አልተብራራም።
የሞያሌዉን ግጭት የሶማሌ ክልል የሰላም እና አንድነት ካውንስል አወገዘ 30.10.2026
በህብረተሰብ ሰላም እና አንድነት ጉዳይ ላይ እንደሚሰራ የተገለፀው የሶማሌ ክልል የሰላም እና አንድነት ካውንስል በሞያሌ እየተካሄደ ያለውን ለቀናት የዘለቀ ግጭት የሚያውገዝ መግለጫ አወጣ። ለረዥም ዓመታት ሁለቱም ክልሎች ከተማውን ሲያስተዳድሩ እንደነበር እና ግጭት ለመቀስቀስ የሚያበቃ የተለየ አዲስ ነገር የለም" ሲል ድርጅቱ ገልጿል።
በደቡብ ወሎ፤«ቱርክ» የሀገር ውስጥ ተፈናቃዮች መጠለያ ጣቢያ በደረሰ ድሮን ጥቃት 16 ሰዎች ተገደሉ ፤ 29 ሰዎች ጉዳት ደረሰባቸዉ 30.10.2026
በደቡብ ወሎ ዞን ተሁለደሬ ወረዳ በሚገኘው «ቱርክ» የሀገር ውስጥ ተፈናቃዮች መጠለያ ጣቢያ ላይ ጥቅምት 19 ቀን 2019 ዓ.ም. በተፈጸመ የድሮን ጥቃት ሕይወታቸው ያለፈ ንጹሐን ሰዎች ቁጥር 16 መድረሱን እና 29 ሰዎች በጽኑ መቁሰላቸውን የመጠለያ ጣቢያው አስተባባሪና ነዋሪዎች ገለጹ።
የፖለቲካ ኢኮኖሚው ተንታኝ ሸዋፈራሁ ሽታሁን የኢትዮጵያ መሰል ዘመናዊና ውድ የጦር መሳሪያዎች ግዢ መፈጸም የሚኮነን ባይሆንም ጎን ለጎን ግን ኢኮኖሚውም ላይ አብዝቶ መስራት ይጠይቃል ብለዋል፡፡ 29.10.2026
አቶ ባይሳ የጦር መሳሪያ የሚገዛው ለውጊያ እንጂ ለእርሻ እንዳልሆነ ግልጽ ቢሆንም” ዘመናዊ መሣሪያ መታጠቅ ኢኮኖሚውንም እንደመከላከል ሊቆጠር የሚችል ነው ብለዋል። የፖለቲካ ኢኮኖሚው ተንታኝ ሸዋፈራሁ ሽታሁን ግን ኢትዮጵያ ዘመናዊና ውድ የጦር መሳሪያዎች ግመግዛትዋ የሚኮነን ባይሆንም ከዚሁ ጎን ኢኮኖሚውም ላይ አብዝቶ መስራት ይጠይቃል ብለዋል፡፡
ይህ ሴሚናር፤ ወደፊት በሚኖሩ የትብብር ፕሮግራሞችና የፖሊሲ አቅጣጫዎች ላይ አስተዋጾ ይኖረዋልም ተብሏል። 29.10.2026
ኢትዮጵያና ቤልጅየም ዘንድሮ የዲፕሎማሲ ግንኙኑነት የጀመሩበት 120ኛ ዓመት ደፈነ ። ቤልጅየም ከአድዋ ድል በኋላ እ.እ.እ በ1906 ዓ.ም ከኢትዮጵያ ጋር የዲፕሎማሲ ግንንኙነት ከጀመሩት ጥቂት አገሮች አንዷ ነች። ሁለቱ አገሮች ባለፉት 120 ዓመታት በፖለቲካ፤ ኢኮኖሚ እና በትምህርት ልዩ ልዩ ደረጃዎች ሲተባበሩና ልምድ ሲለዋወጡ ዘልቀዋል።
የሞያሌውን ግጭት አለመረጋጋት ተከትሎ ወደ ኬንያ ብቻ የተፈናቀሉት ከ50 ሺህ በላይ መሆኑን የዓለማቀፍ የመብት እና የሰብዓዊ ተቋማት እየገለጹ ነው። 29.10.2026
በኦሮሚያ እና ሶማሊ ክልሎች አዋሳኝ ሞያሌ ከተማ ውስጥ በተከሰተው ግጭትና አለመረጋጋት የተፈጠረው ሰብዓዊ ቀውስ ሊቆም እንደሚገባው ተጠየቀ። አስተያየታቸውን ከተለያዩ አከባቢዎች ለዶይቼ ቬለ የሰጡ ኢትዮጵያውያን እንዳሉት በግጭቱ ዙሪያ በመንግስት በኩል በቂ ማብራሪያ እና የምፍተሄ አቅጣጫ ለህዝቡ አለመሰጠቱ የሚነቀፍ ተግባር ነው ።
ፑቲን በጉባኢው መክፈቻ ላይ ሩሲያ ከአፍሪካ ጋር የቆየ የወዳጅነት ግንኙነቷን እንደምትቀጥልና በንግድ ቴክኖሎጂ ትምህርትና ግብርና ትብብርን እንደምታስፋፋ አስታውቀዋል 29.10.2026
ጠ/ሚኒስተር ዐቢይ አህመድ ባደረጉት ንግግር አገራቸው ትኩረት ሰጥታ እየሰራችባቸው ባሉ መስኮች ሩሲያ የበኩሏን እንድታደርግ ፍላጎታቸው መሆኑን አስገንዝበዋል። በምግብ የኃይል አቅርቦችትና በትምህርት ላይ ትክረት ሰጥተን እየሰራን ነው ያሉት ዐቢይ በምግብ በኩል ዋናው ትኩረታችን ህዝባችንን መመገብና የግብርናውን ኢኮኖሚ ማሳደግ ነው ብለዋል።
የሳዩ ኖሌ ወረዳ ፖሊስ ኃላፊ ኮማንደር አሰቤ ቡልቲ በወረዳው ከወቅታዊ ጉዳዮች ጋር በተያያዘ እና በወንጀል የተጠረጠሩ ሰዎች ጉዳያቸው በኮማንድ ፖስት እየታየ እንደሆነ አብራርተዋል፡፡ 29.10.2026
በመቱ ዩኒቨርሲቲ የሕግ መምህር አቶ ኬነሳ ደገፋ በቅርቡ ወደ ወረዳው በመሄድ በጣቢያው የታሰሩትን ሰዎች የማየት እድል እንደነበራቸው ተናግረዋል፡፡ የሕግ መምህር ኬነሳ በሳዩ ኖሌ ወረዳ ጣቢያ ውስጥ የሚገኙ እስከ 30 እንደሚደርሱ ፣ከተያዙ አንድ እና ሁለት ወራት የሆናቸው እንዳሉና ጉዳየያቸው ፍ/ቤት ሳይቀርብ በጣቢያው መቆየታቸውን አመልክተዋል፡፡
የአፍሪካ ኀብረት ከዲፕሎማቶች መባረር ጋር በተያያዘ የተፈጠረውን ውዝግብ መፍታት ይችላል 29.10.2026
የአፍሪካ ኀብረት የኤርትራ ዲፕሎማቶች ከአዲስ አበባ እንዲወጡ ከመደረጋቸው ጋር በተያያዘ የተነሳውን ውዝግብ በሦሰትዮሽ ውይይት ሊፈታው እንደሚችል አንድ አንጋፋ የአለምአቀፍ ሕግ ባለሙያ ተናግረዋል። እንደዚህ አይነቱ ከሀገር የማስወጣት እርምጃ ብዙ ጊዜ የሚፈፀመው፣ ዲፕሎማቶቹ ተወካይ ለሆኑበት ተቋም በማሳወቅ ጭምር መኾኑንም ገልፀዋል።
ትብብር ለሕልውና በመንግሥት ላይ ያቀረበው ክስ - መንግሥት በጉዳዩ ላይ ምን አለ? 29.10.2026
የኢትዮጵያ ሕዝባዊ ኃይሎች ትብብር ለሕልውና በወለጋ፣ በአርሲ፣ በሞያሌና በጋምቤላ በንፁሃን ዜጎች ላይ ደረሰ ባለው ግድያ እና ስልታዊ ማፈናቀል፣ የመንግሥት መዋቅር "ቀጥተኛና ተዘዋዋሪ" ተሳትፎ ነበረው ሲል ከሰሰ። በምስራቅ ወለጋ ትናንሽ ከተሞችን እንደወደሙና "ከ80 ሺህ በላይ አማራዎች ያለ መጠለያ ቀርተዋል" ሲልም ወንጅሏል።
በሚቀጥለው ሳምንት በሚካሄደው የአሜሪካ አጋማሽ ዘመን ምርጫ፣ ዴሞክራቶች የማሸነፍ ሰፊ እድል እንዳላቸው እየተነገረ ነው። በምርጫው፣የሕግ መወሰኛውን ብቻም ሳይሆን የሕግ መምሪያው ምክር ቤትም ዴሞክራቶች ይቆጣጠሩታል እየተባለ ነው። 29.10.2026
በምርጫው ቁልፍ ናቸው ከተባሉት ግዛቶች አንዷ፣ እዚህ ጆርጂያ ውስጥ እየተካሄደ ባለው የቅድመ ምርጫ ሂደት፣ከዚህ በፊት ከነበረው ክብረ ወሰን የሰበረ መራጭ ወጥቶ ድምጽ መስጠቱ ተመዝግቧል። ምርጫው ሞቅ ደመቅ ባለባት ግዛቲቱ፣ሴናተር ጆን ኦሳፍ እና የሪፐብሊካን ተፎካካሪያቸው ማይክ ኮሊንስ የሴኔቱን መቀመጫ ለማግኘት ከፍተኛ ፉክክር ላይ ናቸው።
በርካታ ተበራሪ ጥይት እና በሚወሩ ከባባድ መሳሪያ የተጎዱ ሆስፒታል መግባታቸውንም የገለጹት እኚህ አስተያየት ሰጪ የሞያሌ ከተማ ነዋሪ የሆኑት የአይን እማኝ፤ “በርካቶች ሆስፒታል ገብተው እየታከሙ ነው፡፡ 28.10.2026
በኦሮሚያ እና ሶማሌ ክልሎች አዋሳኝ እና በኢትዮጵያ እናኬንያ ድንበር ላይ በምትገኘው ሞያሌ ከተማ ከተከሰተው አስር ቀናትን ያለፈው ግጭት አሁንም እልባት ሳያገን መቀጠሉን ነዋሪዎች ገለጹ፡፡ በግጭቱ መዘዝ ከቀዬያቸው ተፈናቅለው ወደ ኬንያ የሚሻገሩ ሰላማዊ ዜጎች ቁጥር ከ36 ሺህ በልጧል፡፡
Replaio is not a podcast publisher; show names, artwork and audio belong to their authors and are distributed through public RSS feeds.