DW | Amharic - News
News, Analysis and Service from Germany and Europe - in 30 Languages
Be sure to visit the podcast's website and support the creator: www.dw.com
Where to listen?
Podcasts in the app Replaio Radio Coming soonPodcasts are coming to the app soon. Install now and be the first to see a whole new take on podcasts
Episodes
የጋምቤላ ተፈናቃዮች፦ ከ4ሺ በላይ አባወራዎች ወደቀያቸው መመለሳቸውን የክልሉ አደጋ ስጋት ስራ አመራር አስታወቀ 06.11.2026
ባለፉት ሦስት ሳምንታት በጋምቤላ ከተማ ተከስቶ በነበረው ግጭት በርካታ ሰዎች ከቤት ንብረታቸው ተፈናቅለዋል። ከተፈናቃዮቹ መካከል 4444 የሚሆኑት አባወራዎች ወይም ወደ 16ሺ 1መቶ 29 ሰዎች ወደየቀያቸው መመለሳቸውን የክልሉ አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን አስታዉቋል። ከምቤላ ከተማ ወደ ወረዳዎች የተፈናቀሉ ግን እስካሁን አልተመለሱም።
የህጻናትን እና ወጣቶች የወደፊት እጣ ፈንታን እየነጠቀ ያለዉ የኢትዮጵያዉ ግጭት እና ጦርነት 06.11.2026
ኢትዮጵያ ውስጥ በበፊቱም ይሁን አሁን ባገረሸው ጦርነት እንዲሁም በተለያዩ አካባቢዎች ባሉ ግጭቶች ምክንያት አሁንም በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ወጣቶች እና መምህራን ከትምህርት ገበታ እንደራቁ ናቸው። መፍትሔው ምን ይኾን?
የማኅበረሰቡን እንቅስቃሴ የገታዉ እያወደመዉ ያለዉ ጦርነት በአማራ ክልል 06.11.2026
በአማራ ክልል ላለፉት ሦስት ዓመታት ሲካሄድ የቆየውና በቅርብ ጊዜያት መጠናከር ያሳየው ጦርነት የማህበረሰቡን ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ህይወት ክፉኛ ከመጉዳቱም በላይ፣ የሞት ዜናን በቀላሉ ከመልመድ እስከ ወላጆች ልጆቻቸውን ወደ ትምህርት ቤት ለመላክ እስከመሰጋት የደረሰ አዲስና አስፊ ህይወት እንዲለማመዱ ማስገደዱንየአካባቢው ነዋሪዎች ገለጹ።
ዲፕሎማቶች ከህወሓት የተማረኩ የተባሉ የጦር መሣሪያዎችን ጎበኙ 06.11.2026
በህወሓት እና በኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት መካከል ሰሜን ኢትዮጵያ መስከረም 13 ቀን 2019 የተጀመረውን ጦርነት ተከትሎ፣ ከህወሓት የተማረኩ የተባሉ የጦር መሣሪያዎች ኢትዮጵያ ውስጥ በሚገኙ የዲፕሎማቲክ ማኅበረሰብ አባላት ተጎበኙ። ኢትዮጵያ ከፍተኛ ውስጣዊና ቀጣናዊ የሰላምና ደኅንነት ችግሮች እየተጋፈጠች ትገኛለች"
«የመንግስት ኃይል ወረዳው ላይ የለምና ሬሳ ማንሳት አልተቻለም፤ የሞቱትም ሲቪሎች ናቸው፤ 6 ሰዎች ዛሬ አግኝተን ቀብረናል ፣ 3 ቁስለኞችም አግኝተናል፤ የት እንደገቡ እስካሁያልታወቀው እጅግ በርካታ ማህበረሰብ አለና እየተፈለጉ ነው” 05.11.2026
በምዕራብ ኦሮሚያ ዞን ኪረሙ ወረዳ ጉዲና ጅሬኛ ቀበሌ ጥቅምት 25 ቀን 2019 ዓ.ም. ከማለዳው ጀምሮ ታጣቂዎች ባደረሱት ጥቃት የበርካታ ንጹሀን ሕይወት ማለፉንና ከፍተኛ የንብረት ውድመት መድረሱን ነዋሪዎች ለዶይቼ ቬለ ገልጸዋል፡፡
የሰብአዊ መብት ድርጅቶችና ዓለም አቀፍ ተቋማት በሰላማዊ ሕዝብ ላይ ተፈፅሟል ያለውን "የጅምላ ግድያ" እንዲያወግዙና ተጠያዎች ለፍርድ እንዲቀርቡ እንዲተባበሩ ህወሓት ጠይቋል። 05.11.2026
ህወሓት "አገዛዝ" ብሎ የሚጠራው የፌዴራል መንግሥት "በከባድ የጦር መሳሪያዎች፣ አውሮፕላኖች እና ድሮኖች በሲቪሎች ላይ በሚያነጣጠሩ ቀጣይነት ባላቸው ጥቃቶች ንፁሃን ሰዎችን እየገደለ ነው" ሲል ከትናንት በፊት ከሷል። የፌዴራሉ መንግሥትም ኾነ መከላከያ ሠራዊት ግን ስለዚህ ጉዳይ ምንም ያሉት ነገር የለም።
በአፍሪካ ሕብረት ኮሚሽን የፖለቲካ ጉዳዮች፣ የሰላምና ደህንነት ኮሚሽነር አምባሳደር ባንኮሌ አዶዬ፣ ትናንት ጥቅምት 25 ቀን 2019 ዓ/ም ለጋዜጠኞች ሲናገሩ፣ ውጥረቱን የማብረድ ጥረቱ በተለያያ ደረጃ እየተካሄደ ነው ብለዋል። 05.11.2026
የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት ጉዳዩን አስመልክቶ ባወጣው መግለጫ፣ በኹለቱ ሀገራት መካከል እየጨመረ የመጣው ውጥረት በቀጠናው በሙሉ ጉዳት የማድረስ አቅም እንዳለው አስታውቋል። የአፍሪካ ቀንድ ሌላ ግጭትና ሰብአዊ ቀውስ መቋቋም አይችልም ብሏል። ሌሎች ሀገራትና ዓለም አቀፍ ተቋማትም ተመሳሳይ የሰላም ጥሪ ሲያቀርቡ ቆይተዋል።
በትግራይ ክልል ራማ እና በአማራ ክልል ጃራ ህጻናትን ጫምሮ በርካታ ሲቪሎች ህይወታቸው ማለፉን ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሃኖም ገልጸው፣ በድሮን ጥቃት በኢትዮጵያ በተለያዩ አከባቢዎች ሲቪሎች ላይ ጉዳቶች እየተከሰቱ መሆኑንም ተናግረዋል፡፡ 05.11.2026
የክልሉ ነዋሪዎች የቀጠለው ግጭት ከፍተኛ ጉዳት ከማስከተሉም በላይ የተናፈቀው ሰላምና መረጋጋት ቅርብ እንዳልሆነ ምናልባትም ፍንጭ የሚሰጥ ነው ይላሉ፡፡ አንድ የመቀሌ ነዋሪ እንዳሉት “ከሰሞኑ በተለይም ከትናንት ወዲያ በአዲአፍሮም ከፍተኛ ውጊያ መኖሩን” መስማታቸውን ገልጸው በዚህም ከፍተኛ መስዋእትነት ተከፍሏል ተብሎ እንደሚታመን ተናግረዋል።
በትላላቆቹ የፈረንሳይ ከተሞች ፣በፓሪስ ፣በሊዮ በማርሴይና በሌሎችም የፈረንሳይ ከተሞች የተካሄደውን ሰልፍ በመቶ ሺህዎች የሚቆጠሩ አባላት ያሉት የሠራተኛ ማኅበርም ተቀላቅሏል። 05.11.2026
ለተወሰኑ ቀናት ተቋርጦ የነበረው የፈረንሳዩ ተቃውሞ ዛሬ በፈረንሳይ የተለያዩ ከተሞች ቀጥሏል። በትላላቆቹ የፈረንሳይ ከተሞች ፣በፓሪስ ፣በሊዮ በማርሴይና በሌሎችም የፈረንሳይ ከተሞች የተካሄደውን ሰልፍ በመቶ ሺህዎች የሚቆጠሩ አባላት ያሉት የሠራተኛ ማኅበርም ተቀላቅሏል።
ኢትዮጵያ ውስጥ የሚታየዉ የፖለቲካ ቀዉስ አንዳንዶች እንደሚገልጹት የትናንት ሳይሆን 50 ዓመታትን ያለፈ፤ በዉይይት መፍትሄን የማግኘት ብስለት የራቀው፤ አልያም መረዳት ያልፈለገ፤ የእልህ መንፈስ የተጸናወተው አካሄድ ነው። 05.11.2026
የኢትዮጵያ የፖለቲካ ቀዉስ አንዳንዶች እንደሚገልጹት የትናንት ሳይሆን 50 ዓመታትን ያለፈ፤ በዉይይት መፍትሄን የማግኘት ብስለት የራቀው፤ አልያም መረዳት ያልፈለገ፤ የእልህ መንፈስ የተጸናወተው አካሄድ ነው። የቀዉሱ መነሻ የት ነዉ? አንዳንዶች የምሁራኑን ሚና ተጠያቂ ያደርጋሉ። ለሌሎች ደግሞ እየተሸረሸረ የሄደው ማኅበራዊ እሴት ውጤት ነዉ ይላሉ።
የብሔራዊ ባንክ የወርቅ ግዢ በኢትዮጵያ የዋጋ ግሽበትን እያባባሰ ነው? 04.11.2026
የጥቅምት ወር አጠቃላይ የዋጋ ግሽበት 14.6 በመቶ ሆኖ እንደተመዘገበ የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት አስታውቋል። ዳቦ፣ እንጀራ እና አትክልት ከ10 በመቶ በላይ፤ ሥጋ እና እንቁላል በአንጻሩ ከ20 በመቶ በላይ የዋጋ ጭማሪ ታይቶባቸዋል። የዋጋ ግሽበቱ በሚቀጥሉት ስድስት ወራትም ወደ ነጠላ አሐዝ ይወርዳል ተብሎ አይጠበቅም።
በአውሮፓ የምግብ ማቀዝቀዣዎች ላይ የተፈጸመው የሰሞኑ የሳይበር ጥቃት 04.11.2026
በሳይበር ምኅዳር ውስጥ የሳይበር ጥቃት የተለመደ ሲሆን፤ በአብዛኛው በባንኮች፣ በመንግሥታዊ ተቋማትና በትላልቅ ድርጅቶች ላይ የሚከሰት ነው። ሰሞኑን በአውሮፓ የተከሰተው የሳይበር ጥቃት ግን በምግብ ማቀዝቀዣዎች ላይ ያነጣጠረ በመሆኑ እያነጋገረ ነው። ለመሆኑ ይህ የሳይበር ጥቃት እንዴት ተከሰተ? ለምን አሳሳቢ ሆነ? መፍትሄውስ?
የጉራጌ ዞንን የፀጥታ መታወክ ለማስወገድ የሽምግልና ጥረት ተጀመረ 04.11.2026
በሁለቱ ጉራጌ ዞኖች የሚስተዋለው የፀጥታ ችግር ሁለት መልክ ያለው መሆኑን ነዋሪዎች ይናገራሉ ፡፡ በአንድ በኩል ከኦሮሚያ ክልል የሚነሱ ታጣቂዎች፣በሌላ መልኩ የአበሽጌ ወረዳ ውስጥ ደግሞ ከዛው ማህበረሰብ ወጥተው የሸፈቱ ታጣቂዎች በጫካ እንደሚንቀሳቀሱ መረጃዎች ይጠቁማሉ
የኢትዮ- አሜሪካውያን ድርጅቶች ስለቀጠለው አሩሲ ዞን ጥቃት 04.11.2026
የኢትዮጵያ አሜሪካውያን የሲቪል ድርጅቶች፣ ለሰላማዊ ዜጎች ጥበቃ፣ ለፍትሕና ለተጠያቂነት የሚያደርጉትን እንቅስቃሴ አጠናክረው እንደሚቀጥሉ አስታወቁ።
በዩናይትድ ስቴትሱ የአጋማሽ ዘመን ምርጫ የዲሞክራቶች ድል 04.11.2026
የተቃዋሚዉ የዲሞክራቲክ ፓርቲ ፖለቲከኞች ለሐገሪቱ የህዝብ ተወካዮች (ህግ-መምሪያ) ምክር ቤት፣ ለሴኔት (ህግ-መወሰኛ ምክር ቤት)፣ ለግዛቶች አገረ-ገዢነት በተደረገዉም ዉድድር አሸናፈዋል
አውሮፓ በ2026 የአሜሪካ አጋምሽ ምርጫ 04.11.2026
ትራም ከኢራን ጋር የገቡበት ጦርነትና የሆርሙዝ ሰርጥ መዘጋት፤ ለአሜሪካ ብቻ ሳይሆን ለአለም በሙሉ፤ለጋዝ ዋጋ መጨምር መክኒያት መሆኑ ይነገራል ። ሆኖም ግን ፕሬዝዳንት ትርምፕ የተሸንፉት በስልጣን ላይ ላይ ያለ ፓርቲ መሸነፉ የተለመደ በመሆኑ እንጂ በሌላ እንድላሆነ ነው ከምርጫው ውጤት በኋላ ሲናገሩ የተሰሙት
በመላ ጀርመን በተካሄዱት በነዚህ ሰልፎች ላይ በተነሱት አመጾች በርካታ የፖሊስ መኮንኖችም ቆስለዋል። 03.11.2026
ሰልፎቹ ርዕሰ ከተማይቱን በርሊንን፣ የፋይናንስ ማዕከሏን ፍራንክፈርትን፣ የወደብ ከተማዋን ሐምቡርግንና ኮሎኝን ጨምሮ ከ30 በላይ የጀርመን ከተሞች ነው የተካሄዱት። ዓላማቸውም ለትምህርት የሚሰጠው ድጎማ ከፍ እንዲል በየስራ ዘርፉ የሚካሄድ የበጀት ቅነሳ እንዲቆም ለኑሮ ውድነትምመፍትሔ እንዲፈለግና አጥብቆ መጠየቅ ነበር።
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያንን ጨምሮ ስድስት ጥንታዊ የክርስቲያን አብያተ ክርስቲያናት ቤተሰብ የሆነው የኦሬንታል ኦርቶዶክስ አብያተ ክርስቲያናት ቋሚ ጉባኤ በበኩሉ ግድያውን "ታላቅ አሳዛኝ ክስተት" ብሎታል። 03.11.2026
ኦሮሚያ ክልል አርሲ ውስጥ የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ክርስትያኖችን አነጣጥረው መስከረም 10 እና 14 ቀን 2019 ዓ.ም ሁለት ወረዳዎች ላይ "ግፍን በተሞላ ጭካኔ" ተፈፀሙ በተባሉ አሰቃቂ ጥቃቶች 60 ምዕመናን መገደላቸው መገለፁ የፍትሕ እና የተጠያቂነት ጥሪ ዛሬም ከተለያየ አቅጣጫ እንዲሰማ አድርጓል።
30ኛ ዓመት የምስረታ በዓሉን ከወራት በፊት ያከበረው ሪፖርተር አማርኛ፣ ዘ - ሪፖርተር እንግሊዝኛ እና የድርጅቱ የበይነ መረብ ሥርጭት አገልግሎት ከትናንት ሰኞ ጥቅምት 23 ቀን 2019 ዓ.ም ጀምሮ "ላልተወሰነ ጊዜ" ታግዷል። 03.11.2026
ከጥቂት ዓመታት በፊት ተቆጣጣሪ መሥሪያ ቤቱ የኢትዮጵያ ብሮድካስት ባለሥልጣን በሚባልበት ወቅት ዋና ዳይሬክተር የነበሩት ዶክተር ጌታቸው ድንቁ ይህ 'እርምጃ "ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የሚዲያ ምኅዳሩ ከመንግሥት አካባቢ ከሚወጣው መረጃ እና ትርክት የተለዩ ሐሳቦችን በነፃነት የማንሸራሸር ዕድሉ እየጠበበ እንደመጣ ጠቋሚ መሆኑን ለዴቼ ቬለ ገልፀዋል።
ኢትዮጵያዊ አሜሪካውያንን ለዘንድሮው የአጋማሽ ዘመን ምርጫ የሚሰጡት ትኩረት 03.11.2026
በተለምዶ ወደ ዴሞክራት ፓርቲ እንደሚያዘነብሉ የሚነገርላቸው ኢትዮጵያዊ-አሜሪካውያን፣ በ2024ቱ የፕሬዚዳንት ምርጫ በሃይማኖታዊ፣ ማኅበራዊና ባህላዊ እሴቶች ሳብያ ወደ ድጋፋቸው ወደ ሪፐብሊካን ፓርቲማመዘኑ ታይቷል።ታዲያ ከሁለት ዓመታት በኋላ የእነዚህ መራጮች አቋም ምን ይመስል ይሆን? በዘንድሮው ምርጫስ የውሳኔያቸው ዋነኛ መሠረት ምንድን ነው?
በሰሜናዊ ኬንያ የጸጥታ ስጋት የደቀነው የሞያሌው ግጭት 03.11.2026
በኢትዮጵያ ደቡባዊ የድንበር ከተማዋ ሞያሌ ከሁለት ሳምንት በፊት የተከሰተው ግጭት በኬንያ ሰሜናዊ የጠረፍ ከተማ ሞያሌ የፀጥታ ስጋትን እየደቀነ ነው። በኢትዮጵያ ድንበር ውስጥ በሚካሄደው ግጭት ውስጥ የሚወረወሩ የከባድ መሳሪያዎች በራሪ ጥይት የሰው ሕይወት እየቀጠፈም ነው ተብሏል።
ማሕደረ ዜና፥ ኢትዮጵያ፣ ሸቀጥ የተወደደ፣ ሞት የረከሰባት ሐገር 02.11.2026
ኢትዮጵያ ዉስጥ ለሰዎች በጣሙን ለየዋሆች ሕይወት የሚጨነቅ አይደለም የሚያሳብ ፖለቲከኛ መገኘቱ እያጠራጠረ ነዉ።ወይም አስከሬን መቅበር፣ ተፈናቃይ መቁጠር፣ ለየጦርነት ግጭቱ «ጠላት» የሚባሉ ወገኖችን ማሳጣት፣ ሰበብ ምክንያት መደርደሩ ተለመደና አስጨናቂዉ ጥፋት የወትሮ ምግባር የሆነ ያክል ቀጠለ።
የአርሲ ሺርካው የንጹሐን ጥቃትና ዓለም አቀፍ ውግዘት 02.11.2026
በኦሮሚያ ክልል ደቡብ ምሥራቃዊ ዞን ሺርካ ወረዳ የተፈጸመውን የንጹሐን ጥቃት ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ እያወገዘው ነው። ዩናይትድ ስቴትስ እና ዩናይትድ ኪንግደም «አስደንጋጭ» ያሉትን ጥቃት አውግዘው አጥፊዎች ለፍትህ እንዲቀርቡ ጠይቀዋል።
የቀጠለው የሞያሌ ግጭት እና ሰብዓዊ ቀውስ 02.11.2026
የኦሮሚያ እና ሶማሌ ክልሎች አዋሳኝ ከተማዋ ሞያሌ ግጭት ከተከሰተ ከሁለት ሳምንታት በላይ ቢሆነዉም ግጭቱ ዛሬም ድረስ ተባብሶ መቀጠሉ እየተነገረ ነው። በአስተዳደር ወሰን ውዝግብ የጀመረው በከባባድ መሳሪያ ጭምር ታግዞ በቀጠለዉ ግጭት የሰዎች ህይወት ጠፍቷል ንብረት ወድሟል፤ በሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች ወደ ኬንያ ተፈናቅለዋል፡፡
ትብብር ለሕልውና የጀመረውን ትግሉ እንደሚያጠናክር መግለፁ 02.11.2026
ትብብር ለሕልውና የትጥቅ ቡድኖች ስብስብ "የጋራ ጠላት" ብሎ የፈረጀውን ፌዴራል መንግሥት መታገሉን እንደሚቀጥል በድጋሚ ገለፀ። የትብብሩ አባል ድርጅቶች መሪዎች በታዩበት ተንቀሳቃሽ ምስል ተደግፎ በቀረበው መግለጫ፣ መንግሥት "ጦርነትን የመግታት፣ ዘላቂ ሰላም የማምጣት፣ ሕግና ሥርዓትን የማስፈን አቅምም ኾነ ፍላጎት የሌለው" ሲል ወቅሷል።
Replaio is not a podcast publisher; show names, artwork and audio belong to their authors and are distributed through public RSS feeds.