DW | Amharic - News

News, Analysis and Service from Germany and Europe - in 30 Languages

Be sure to visit the podcast's website and support the creator: www.dw.com

Category

Uncategorized

Podcast website

www.dw.com

Latest episode

Nov 20, 2026

Where to listen?

Podcasts in the app Replaio Radio Coming soon

Podcasts are coming to the app soon. Install now and be the first to see a whole new take on podcasts

Get it on Google Play Install for free Android 10M+ downloads · 4.7+ rating iOS soon

Episodes

የሩሲያ፤ ዩክሬንና አሜሪካ የሦስትዮሽ የሰላም ውይይት በአቡዳቢ 11.11.2026

በአሜሪካ አደራዳሪነት በተባበሩት አረብ ኤሚሪትስ አቡዳቢ ከተማ ከትናንት ጀምሮ ለሁለት ቀናት ሲካሄድ የቆየው የሩሲያና ዩክሬን የሰላም ድርድር ተጠናቀቀ።

በአርሲ ጥቃቶች የተፈናቀሉ ዜጎች የእርዳታ ጥያቄ 11.11.2026

በኦሮሚያ ክልል ደቡብ ምሥራቅ ዞን በተለያዩ ወረዳዎች በተለያዩ ጊዜያት የተፈናቀሉ ዜጎች በእርዳታ እጦት መቸገራቸውን አመለከቱ።

ሰሀላ ወረዳ፤ ድርቅ፤ ረሀብና ወባ ወረርሽኝ ያስከተሉት የከፋ ሰብአዊ ቀውስ 11.11.2026

በአማራ ክልል የዋግምራ ብሔረሰብ አስተዳደር ዞን ሰሀላ ወረዳ የደረሰው ከባድ ድርቅና የወባ በሽታ መዛመት ከረሀብ ጋር ተዳምሮ ነዋሪዎችን ለከፋ ሰብአዊ ቀውስና ለሞት እየዳረጋቸው መሆኑ ተገለጸ።

በጅማ በተፈጠረው ግጭት የሰው ሕይወት ማለፉ 11.11.2026

በኦሮሚያ ክልል ደቡብ ምዕራብ ዞን ጅማ ከተማ ቦሬ ተብሎ በሚታወቅ ቀበሌ አካባቢ ባለፉት ሁለት ቀናት በአካባቢው ማኅበረሰብ እና የአካባቢው የጸጥታ አካላት መካከል በተፈጠረው አለመግባብት የሰው ሕይወት ማለፉ ተነገረ።

በ2013 ዓ.ም. ወደትውልድ አካባቢያቸው ፖለቲካ የተመለሱት አይግነር በግዛቲቱ ጠ/ሚ ኽርስት ዜሆፈር የስልጣን ዘመን በባቫርያ የኤኮኖሚ ሚኒስትር ነበሩ። በወቅቱም ዜሆፈር አይግነር እርሳቸውን እንዲተኩ ሙከራ አድርገው ነበር። 10.11.2026

የጀርመን መራኄ መንግሥት ፍሪድሪሽ ሜርስ የክርስቲያን ሶሻል ኅብረት ፓርቲ ፖለቲከኛ ኢልዘ አይግነርን ትናንት በይፋ ለሀገሪቱ ፕሬዝዳንትነት በእጩነት አቅርበዋቸዋል። የሶሻል ዴሞክራቶቹ ፓርቲም በአይግነር እጩነት ሲስማማ ከአረንጓዴዎቹ ፓርቲም ይሁንታ አግኝተዋል። አማራጭ ለጀርመን ግን የአይግነርን ለፕሬዝዳትነት መታጨት ተቃውሟል።

አንዲት የአምቦ ዩኒቨርስቲ ተማሪ ድንገት መሞቷ ያስከተለዉ ድንጋጤና ጥርጣሬ 10.11.2026

ስለሟች ተማሪዋ የጊቢው ህይወት አስተያየቱን ያከለው ተማሪ ኢዘዲን፤ “መሰረት እጅግ ተግባቢና ተጨዋች እንደነበች ነው የምትታወቀው” በማለት ለዚህ የሚበቃት ነገር ያለባት አይመስልም ነበር ብሏል፡፡

ሞያሌ ዉስጥ የሚደረገዉ ዉጊያ እንደቀጠለዉ ነዉ 10.11.2026

ግጭቱን ሽሽት ወደ ተለያዩ አቅጣጫዎች የተበታተነው የሞያሌ ማህበረሰብ ከፍተኛ ችግር ውስጥ መውደቁንም የሚገልጹ ነዋሪዎቹ ከፊል ህዝብ ወደ ኬንያ ሲሻገር ሌሎች ደግሞ ወደ መሃል አገር መሸሹንም ነው ያመለከቱት፡፡

የደቡብ ኢትዮጵያ ራዲዮና ቴሌቪዥን ሠራተኞች የማሕበራዊ መገናኛ ዘዴ ዘመቻ 10.11.2026

ሠራተኞቹ የማህበራዊ መገናኛ ዘዴዎችን በመጠቀም ዘመቻ ለማድረግ የተገደዱት የድርጅቱ ቀጣይ ህልውና አሳሳቢ ደረጃ ላይ በመድረሱ መንግሥት ትኩረት እንዲሰጠው ድምጻቸውን ለማሰማት መሆኑን የሠራተኞቹ ተወካዮች ተናግረዋል

ሱዳንና ግብጽ የሕዳሴ ግድብ ያደርሳል ያሉትን ጉዳት ሊመረምሩ ነዉ 10.11.2026

የሁለቱ የናይል የታችኛው ተፋሰስ ሀገራት ባለሥልጣናት የሰሞኑን የግብጽ ስብሰባቸውን ካጠናቀቁ በኋላ ሰጡት በተባለው የጋራ መግለጫ፣ ማንኛውንም የአንድ ወገን እንቅስቃሴ ውድቅ ማድረጋቸውን በድጋሚ ማረጋገጣቸው ተዘግቧል

COP31 ዓመታዊው የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ 10.11.2026

የተመድ ዓመታዊ ዓለም አቀፍ የአየር ንብረት ለውጥ ተከታታይ ጉባኤ በአጭሩ COP በመባል የሚታወቀው 31ኛ ዙር አንታሊያ ቱርክ ላይ ትናንት በይፋ ተጀምሯል። ለሁለት ሳምንት የሚዘልቀው ይህ ዓለም አቀፍ ጉባኤ የእስከዛሬውን ውይይትና የተገባውን ቃል ወደ ተግባር ለመለወጥ የሚያስችል ወሳኝ እርምጃ ይጠበቅበታል።

ማሕደረ ዜና፣ የዲሞክራቶች ድል የትራምፕን መርሕ ይቀይር ይሆን 09.11.2026

ትራምና ኔታንያሁ የጫሩት እሳትና አፀፋዉ ኢራንን፣ሊባኖስን፣የመንን፣እስራኤልን፣ ከኢራቅ እስከ ኩዌት የሚደርሱ የፋርስ ባሕረ ሠላጤ ሐገራትን ክፉኛ ጎድቷል።ኢራኖችን ግን ዛሬም አልተሸነፉም።ጥቅምት 29 ቀን 2026 እስራኤል፣ በአራተኛ ቀኑ ዩናይትድ ስቴትስ ላይ በተደረገዉ ምርጫ ግን የኔታንያሁና የትራምፕ የፖለቲካ ፓርቲዎች ተሸንፈዋል።

ዲፕሎማቶችን የማባረር 'ርምጃ በመንግሥታት ግንኙነት ያለው ትርጉም 09.11.2026

ኢትዮጵያ ሁለት ወር ባልሞላ ጊዜ ውስጥ የሁለት ጎረቤት አገራት ዲፕሎማቶች አገር ለቅቀው እንዲወጡ አድርጋለች። የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የኢትዮጵያን ብሔራዊ ደኅንነት አደጋ ላይ በሚጥሉ ጠብ አጫሪ ተግባራት እና እንቅስቃሴዎች ውስጥ መገኘት 10 የኤርትራ ዲፕሎማቶች ከአንድ ወር በፊት ከአዲስ አበባ እንዲባረሩ ምክንያት መሆኑን ጠቅሷል።

በድርቅ እና በጦርነት ምክንያት በዋግ ኸምራ ዞን የተከሰተዉ ከፍተኛ ረሃብ 09.11.2026

በአማራ ክልል ዋግምራ ብሔረሰብ አስተዳደር ዞን በተከሰተው ድርቅ የሰው ሕይወት ማለፉንና በርካቶች ለከፍተኛ ችግር መዳረጋቸዉን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የዋግምራ ብሔረሰብ አስተዳደር ዞን ሃገረ ስብከት እና የወረዳው ነዋሪዎች አስታወቁ። በዞኑ ሰሀላ ሰየምት ወረዳ በድርቅ ምክንያት የአምስት ሰዎች ህይወት ማለፉ ተገልጿል።

በአርሲ ሮቤ ዲዳዓ እንደቶ የደረሰዉ ጥቃት እና ያስከተው ስጋት 09.11.2026

ባሳለፍነው ሓሙስ በኦሮሚያ ክልል በቀድሞ አርሲ ዞን ሮቤ-ዲዳዓ ወረዳ እንደቶ ከተማ ታጣቂዎች ከፈቱ በተባለ ጥቃት የተገደሉ ሰዎች ቁጥር 40 መድረሱን የዓይን እማኞች ለዶይቼ ቬለ ተናገሩ። አስተያየት ሰጪዉ የዓይን እማኞች እና ነዋሪዎች አንዳሉት ከተገደሉት 40 ሰዎች መካከል፤ የ36 ሰዎች አስከሬን በእንደቶ ቅድስት ማርያም ቤተክርስቲን ተቀብሯል፡፡

የስፖርት ዘገባ፦ የሰኞ ጥቅምት 30 ቀን፣ 2019 ዓ.ም 09.11.2026

በዛሬው የሳምንታዊ የስፖርት ዘገባ፦ ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ድል ስለተቀዳጁበት የሩጫ ፉክክር፤ በሴኔጋል በመካሄድ ላይ ስላለው የወጣቶች ኦሎምፒክ እንዲሁም ዓለም አቀፍ የእግር ኳስ ዘገባዎችን እንዳስሳለን ።

እንወያይ፤ ሰላም የራቃት ኢትዮጵያ እጣ ፈንታ 08.11.2026

በሰሜን የሀገሪቱ ክፍል በትግራይ እና አማራ ክልል የለየለት ጦርነት እየተካሄደ ነው። በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች በጋምቤላ፤ በወለጋ፤ አርሲ፤ በጉራጌ እና ሞያሌ የበርካቶች ሕይወትን የቀጠፉና እየቀጠፉ ያሉ ግጭት ጥቃቶች አላባሩም።

በሴኔጋል የባህር ዳርቻ በደረሰ የጄልባ አደጋ ቢያንስ 21 ስደተኞች ህይወታቸው አለፈ 08.11.2026

የፈረንሳይ ዜና አገልግሎት አጃንስ ፍራንስ ፕሬስ እንደዘገበው አደጋው የተከሰተው በሰሜን ምዕራብ ሴኔጋል የባህር ዳርቻ፣ ከኬቤመር አካባቢ ነው። እንደ ሴኔጋል የሀገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስቴር ገለጻ፣ ከጀልባ አደጋው አንድ ሰው ብቻ ተርፏል። 21 አስከሬኖች ደግሞ ተገኝተዋል።

የምገባ መርኃ ግብሩ ውጤታማ የሆነው በአመዛኙ በለጋሾች እርዳታ ነው። ሁለት ሦስተኛው ድጋፍ ከለጋሾች ሲገኝ መንግስትም መርኃ ግብሩን ይደጉማል። የናይሮቢ አስተዳደር ድጋፍ ስለሚያደርግ፣ ወላጆች የሚከፍሉት በጣም አነስተኛ ገንዘብ ብቻ ነው። 07.11.2026

በኬንያ በአሁኑ ጊዜ ቁጥራቸው 2.6 ሚሊዮን የሚደርስ ህጻናት በመንግሥት ወይም መንግስታዊ ባልሆኑ ድርጅቶች መርኃ ግብሮች አማካኝነት በትምህርት ቤት ምሳ ይበላሉ። የናይሮቢ ከተማ አስተዳደር ለምገባው የተወሰነ ድጎማ ያደርጋል። ምገባው የሚካሄድባቸው የናይሮቢ ትምህርት ቤቶች የተማሪዎች የትምህርት አፈጻጸምና በትምህርት ቤት መገኘት መሻሻል አሳይቷል።

AFP ያነጋገራቸው በሺር ግጭቱ በሚካሄድበት አካባቢ« ማንም ሰው አልቀረም፤ የታጠቁ ሰዎች ብቻ ናቸው ያሉት፤እርስ በርስ እየተታኮሱ ነው" ብለዋል። 07.11.2026

ኬንያ የሚገኙት ተፈናቃዮች፣ በሌሊት የተኩስ እና የከባድ ውጊያ ድምጾችን እንደሚሰሙ ይናገራሉ። የድንበሩ አካባቢ ከኢትዮጵያም ከኬንያም በኩል ከዚህ ቀደም ብዙ እንቅስቃሴ ያለበት ነበር። ይሁንና አሁን ከሁለቱም ሀገራት በኩል የጭነት ተሽከርካሪዎች አይንቀሳቀሱም፤ ንግዱድም እንደተቋረጠ ነው።

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ በአሶሳ ዞን በደረሰ ጥቃት ከ30 በላይ የጸጥታ ኃይል አባላት መገደላቸው ተገለጸ 07.11.2026

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ በአሶሳ ዞን በደረሰ ጥቃት ሰላማዊ ሰዎች በሰቃቂ ሁኔታ መገደላቸው ተገልጿል

ሪፓርተር ጋዜጣ "ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ጥቅም ጋር የሚጻረሩ ይዘቶችን አሰራጭቷል" በሚል "ላልተወሰነ ጊዜ ሙሉ በሙሉ ታግዷል 07.11.2026

ሪፖርተር ጋዜጣ በመታገዱ ሦስት ዋና ዋና ዓለም አቀፍ የፕሬስ ነፃነት እና የሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች ርምጃውን አውግዘዋል

በኦሮሚያ ክልል በተለያዩ የድንበር አካባቢዎች ግጭቶች ተባብሰው በመቀጠላቸው እንዳሳሰበው ኦነግ አስታወቀ 07.11.2026

ኦነግ የኦሮሚያ ክልል አዋሳኝ አካባቢዎች ግጭቶች አሳስቦኛል አለ

አሳሳቢዉ የመቀሌ ፀጥታ ሁኔታና የተወሰዱ ያሉ እርምጃዎች 06.11.2026

በትግራይ ክልል ቀደም ሲል ሕዝባዊ ወያኔ ኃርነት ትግራይ (ህወሃት) የመሰረተው መንግስት ፈርሶ የአገር መከላከያ ሰራዊት እና የትግራይ ሰላም ኃይሎች ሁሉንም የክልሉ ዋና ዋና ከተሞች እና በርካታ ስፍራዎችን ተቆጣጥረዋል፡፡ የሀገር መከላከያ ሰራዊት የጸጥታ ስጋቱን ሙሉ በሙሉ ለመቅረፍ አዲስ ስልቶችን ትናንት ሓሙስ ይፋ አድርጓል፡፡

በኦሮሚያ የአርሲ ሮቤ-ዲዳ ጥቃትና ጥቃቱ ያሳደረው ስጋት 06.11.2026

በኦሮሚያ ክልል ደቡብ ምስራቅ ዞን ሮቤ ዲዳ ወረዳ እንደቶ ከተማ ትናንት ከማለዳው ጀምሮ ታጣቂዎች በፈፀሙት ጥቃት የበርካታ ሰዎች ሕይወት ማለፉ ተሰምቷል፡፡ በቅርብ ርቀት በሚገኘው ሺርካ ወረዳ በበኩሉ በቅርቡ የበርካታ ሰዎች ህይወት የቀጠፈው ጥቃትን ተከትሎ የደረሰው ይህ አደጋ አከባቢው ላይ ሰፊ ስጋት መፍጠሩንም ነዋሪዎች ገለፁ፡፡

የመንግሥት አመራሮች ወታደራዊ ሥልጠና፤ በፖለቲካ ተንታኝና በቀድሞ ወታደር ዕይታ 06.11.2026

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የመንግሥት አመራሮች በሁርሶ ወታደራዊ ማሠልጠኛ ሥልጠና እየወሰዱ መሆኑን ባለፈዉ ሳምንት ማጠናቀቅያ ገልፀዉ ነበር። አመራሩ "በአካል የዳበረ፣ በግብረ-ገብ የጠነከረ፣ በዕውቀት የተሳለ" እንዲሆን ይጠበቅበታል ያሉት ዐቢይ አመራሩ ግዴታዎቹን እንዲወጣ የሀገር አደራ ያለበት በመሆኑ ሥልጠናው ማስፈለጉን ገልፀዋል።

Listen to the DW | Amharic - News podcast in Replaio

Radio and podcasts in one app - free, with no sign-up. Install today and do not miss the launch

Get it on Google Play

Replaio is not a podcast publisher; show names, artwork and audio belong to their authors and are distributed through public RSS feeds.