DW | Amharic - News
News, Analysis and Service from Germany and Europe - in 30 Languages
Be sure to visit the podcast's website and support the creator: www.dw.com
Where to listen?
Podcasts in the app Replaio Radio Coming soonPodcasts are coming to the app soon. Install now and be the first to see a whole new take on podcasts
Episodes
የኢትዮጵ መንግስት የትግራይ ክልልን የሚያጸና ያለውን የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር እንዲቋቋም የሚስችል ውሳኔ አስተላልፏል። አስተያየት ሰጪ የክልሉ ነዋሪዎች ከመስተዳድሩ መሰየም ጋር ተያይዞ ተስፋም ስጋትም እንዳላቸው ገልጸዋል፡፡ 16.10.2026
በትግራይ ክልል“በህወሓት ዕንቅፋትነት የተነሣ ሳይሳካ ቀርቷል” ያለው የኢትዮጵያ መንግስት የትግራይ ሕዝብ የራቀውን ሰላም እንዲጎናጸፍ፣ ራስን በራስ የማስተዳደር መብቱ እንዲረጋገጥ እንዲሁም ከሌሎች የኢትዮጵያ ሕዝቦች ጋር በኅብረ-ብሔራዊ አንድነት ጸንቶ እንዲኖር ለማስቻል የባለአደራ አስተዳደር መመስረቱን ዛሬ አስታውቋል፡፡
የፌዴራል መንግሥት በምን በምን ጊዜ ወደ ክልሎች ጣልቃ ይገባል? 16.10.2026
ከፌዴራል መንግሥት በሚሰጠው አቅጣጫና መመሪያ መሠረት ትግራይ ክልልን ለሚቀጥሉት 6 ወራት የሚያስተዳድር አሥር ተግባራት ያሉት ባለ አደራ አስተዳደር ተመሠረተ። ይህ ባለ አደራ አስተዳደር፣ ክልሉ ሰላሙን ማስከበር እንዲችል፣ ትኩረቱን በልማት ላይ እንዲያደርግ እና በአንድነት ጸንቶ መኖር እንዲችል ይሠራል ተብሏል።
በሰሜን ኢትዮጵያ አለመረጋጋት በሰፈነበት በአሁን ወቅት በኦሮሚያ ክልል አንዳንድ ቦታዎች ጸጥታ ችግሩ እንደቀጠለ መሆኑ ተናግረዋል። የክልሉ ነዋሪዎች እንዳመለከቱት የጸጥታው ስጋት አሁንም አልፎ አልፎ ስጋት መደቀኑን እንቀጠለ ነው፡፡ 16.10.2026
የኖኖ ወረዳ ነዋሪ “ባለፈው ሳምንት ውስጥ በድሬ እንጪኒ ወረዳ በመንግስት የጸጥታ ሃይሎች እና በኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት መካከል በነበረው ግጭት በርካታ ሰዎች ተገድለዋል። ከኖኖ ወረዳ እዛ ተመድበው የነበሩ ሦስት የጸጥታ አካላት መሞታቸዉንም አስታውቃለሁ” ብለዋል፡፡ ዶይቼ ቬለ ከባለስልጣናት መረጃዎችን ለማግኘት ያደረገው ጥረት አልተሳካም፡፡
ኢትዮጵያ ዉስጥ የጦርነቱ ዋነኛ ሰለባዎች ሴቶችና ህጻናት ናቸው-ግን ታዲያ i,ሴቶች ድምፅ በየመድረኩ ለምን ቀነሰ? 15.10.2026
በአገር ዉስጥ በሚቀሰቀስ ጦርነት፤ ሴቶችና ታዳጊ ህጻናት የመጀመርያ ተጎጅዎች ናቸዉ። በጦርነት ወቅት ሴቶች ላይ የሚደርሱ ዋና ዋና ጉዳቶች፤ ፆታዊ ጥቃትን እንደ መሳርያ መጠቀም፤ የሥነ ልቦና ጉዳት፤ መፈናቀል እና የኑሮ ዉድነት፤ የጤና አገልግሎት እጦትን መጥቀስ ይቻላል። ኢትዮጵያ ዉስጥ የሴቶች ድምፅ በየመድረኩ ለምን ቀነሰ መጣ? ጦርነት ይቁም!
አሜሪካን ጨምሮ ብዙዎች እንዲናገሩ እያደረገ ያለው የኢትዮጵያና የኤርትራ ውጥረት 15.10.2026
የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማርኮ ሩቢዮ በአፍሪካ ቀንድ አካባቢ የሚገኙ ሁሉም ሃገራት የጎረቤቶቻቸውን «ሉዓላዊነትና የግዛት አንድነት ማክበር» እንዳለባቸው ተናገሩ።
በሰሜን ኢትዮጵያ የሰብዓዊ ድጋፍ አቅርቦት 15.10.2026
የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰብዓዊ እርዳታ ማስተባበሪያ ድርጅት (UN-OCHA) በሰሜን ኢትዮጵያ የሰብዓዊ አቅርቦት መሻሻል ማሳየቱን አስታወቀ። የተባበሩት መንግሥታት ደግሞ ከአስቸኳይ እርዳታ ምላሽ ማዕከሉ (CERF) በሰሜን ኢትዮጵያ ለሕይወት አድን እርዳታ 8.5 ሚሊየን ዶላር መመደቡን ነው አመልክቷል።
በጦርነት በምትታመሰው የመን የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ተማጽኖ 15.10.2026
በየመን የሚገኙ የኢትዮጵያ ስደተኞች አሳሳቢ ሰብአዊ ሁኔታ ላይ ስለምንገኝ ድምፃችን እንዲሰማ ሲሉ ጥሪ አቀረቡ። እነዚህ ወገኖች ለዶቼ ቬለ በጻፉት የተማጽኖ ደብዳቤ፤ «በየመን ውስጥ የምንኖር የኢትዮጵያ ስደተኞች በእጅጉ አስከፊ የሰብአዊ፣ የጤና እና የደኅንነት ችግር ውስጥ እንገኛለን» ብለዋል።
በሰሃላ ሰየምት ወረዳ የተከሰተው አስከፊ ድርቅ 15.10.2026
በዋግህምራ ብሔረሰብ አስተዳደር ዞን ሰሃላ ሰየምት ወረዳ በ13 ቀበሌዎች ከ66 ሺህ በላይ ሰዎች ሲኖሩ ከእነዚህም ውስጥ ከ58 ሺህ በላይ ሰዎች የረሃብ ተጠቂ መሆናቸውን የወረዳው ግብርና ጽሕፈት ቤት መረጃ ያመለክታል።
በትግራይ የሚካሄደው ውጊያ እንዲቆም መጠየቁ 15.10.2026
በትግራይ ክልል የሚካሄደው ግጭት ቆሞ ወደ ሰላም የሚያመራ እውነተኛ መንገድ እንዲጀመር የትግራይ ማኀበረሰብ ዳያስፖራ ድርጅቶች ጥሪ አቀረቡ።
ቃለ መጠይቅ፣ «ያልተጠናቀቀ ፍቺ፣ ያልተሳካ ጉርብትና-የኤርትራና የኢትዮጵያ ጉዳይ» አቶ የሱፍ ያሲን 1991 15.10.2026
ታዛቢዎች ኋላ እንዳሉት የጠቅላይ ሚንስትር ዓብይ አሕመድና የፕሬዝደንት ኢሳያስ አፈወርቂ ወዳጅነት አንደኛ፣- በግልፅ፣ በሕግና በሕዝብ ይሁንታ የተደገፈ አልነበረም።ሁለተኛ፣- የጋራ «ጠላት» የሚሉትን ህዝባዊ ወያኔ ሓርነትን ትግራይ (ህወሓት)ን ለመዉጋት ሥለነበር የሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት በሰላም ሥምምነት ሲያበቃ ወዳጅነቱም ወደጠላትነት ተቀይሯል
የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ድርቅ የተደመረበትን የጦርነት ጫና መሸከም ይችላል? 14.10.2026
ከ2019 የኢትዮጵያ 2.4 ትሪሊዮን ብር በጀት ውስጥ 96.3 ቢሊዮን ብር የሚሆነው ለመከላከያ ተመደበ ነው። ይሁንና ጦርነት የሚያስፈልገው ከፍተኛ ገንዘብ በመንግሥት ወጪ እና የበጀት ጉድለት ላይ ጫና ሊያሳድር ይችላል። በምንዛሪ ሥርዓት ለውጥ እየተዳከመ የሔደው ብር ጭምር እና የዋጋ ግሽበት ድርቅ በተደመረበት የጦርነት ዳፋ መፈተናቸው አይቀርም።
የኢትዮጵያ ኃይሎች የኤርትራ ድንበር አቅራቢያ የምትገኝ ከተማ መድረሳቸው ተገለፀ 14.10.2026
የኢትዮጵያ ፌደራል መንግሥት ኃይሎች እና ተባባሪዎቹ ከኤርትራ ድንበር አቅራቢያ ከምትገኘው ዛላንበሳ ከተማ መድረሳቸውን እማኞች ገልፀዋል።አንድ የአካባቢው ነዋሪ ለዶቼ ቬለ እንደገለፁት የኤርትራ ሠራዊት ዛላአምበሳ ከተማ ላይ የሚገኝ ቢሆንም በዙሪያው በሚገኙ የገጠር ቀበሌዎች ግን የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት መግባቱን ገልፀዋል።
በትግራይ ክልል ከሚንቀሳቀሱ የፖለቲካ ፓርቲዎች አንዱ ሳልሳይ ወያነ ያወጣው መግለጫ ምን ይላል? 14.10.2026
በትግራይ ክልል የተከሰተው ረሃብ እና የተፈናቃዮች ሁኔታ ቅድሚያ እንዲሰጥ ተጠየቀ
የትግራይ ክልል ህዝብ አስተዳዳሪዎቹን መምረጡ መረጋጋቱን ያረጋግጥለት ይሆን? 14.10.2026
በትግራይ ክልል የአካባቢ መስተዳድሮች መዋቀር እና ወቅታዊ ሁኔታ
የቀጠለው የደቡብ ወሎና የሰሜን ሸዋ ውጊያ 14.10.2026
በአማራ ክልል ደቡብ ወሎ እንዲሁም ሰሜን ሸዋ በመንግሥት ኃይሎች እና በፋኖ ታጣቂዎች መካከል ውጊያ ተጠናክሮ መቀጠሉን የአካባቢው ነዋሪዎች ለዶቼ ቬለ ገለጹ።
የሶማሌ ላንድ ለዶናልድ ትራምፕ ንግግር የሰጠችው መልስ እና አንድምታው 14.10.2026
የሶማሌ ላንድ ለረዥም ጊዜ ስትጠብቅ የነበረው ዓለማቀፍ ዕውቅና ቀርቦ ይኾን?
በአማራ ክልል በሶስት ዞኖች የሚደረገዉ ዉጊያ ቀጥሏል 13.10.2026
ሌላው የወገልጤና ከተማ ነዋሪም ጦርነቱ በወገልጤና ከተማ ውስጥ መሆኑን ገልጸው ተዋጊዎቹ ማህበረሰቡን ከተማ ለቆ እንዲወጣ ጥሪ ማቀረባቸውን ይናገራሉ። ትናንት በመጀመርያው ጦርነትም በተባራሪ ጥይት የተመቱ ሰዎች መኖራቸውና ጉዳቱ ግን የከፋ አለመሆኑን ተናግረዋል።
የዩናይትድ ስቴትስና ብሪታንያ ወደ ኢትዮጵያ ለሚጓዙ ዜጎቻቸዉ አዲስ ማሳሰቢያ አወጡ 13.10.2026
ትናንት ባወጣው የጉዞ ማሳሰቢያ የተለያዩ ምንጮችን የጠቀሰው በኢትዮጵያ የአሜሪካ ኤምባሲ፣ የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት እና የትግራይ የሰላም ኃይሎች ትግራይ ክልል ውስጥ አዲግራት፣ አድዋ እና ሽሬን ጨምሮ አቢ አዲ ከተሞችን መቆጣጠራቸውን፣ ከሰሜን አፋር አካባቢ የታጠቁ የተቃዋሚ ኃይሎችን ማስወገዳቸውንም አመልክቷል።
የአዉሮጳ ሕብረት የዉጪ ጉዳይ ሚንስትሮች ሥብሰባ ዉሳኔዎች 13.10.2026
ፕረዝዳንት ትራምፕ ባለፈው ዓርብ በማዕቀብ ውስጥ ካለችው ሩሲያ ናፍታ ለማስገባት ከፕሬዝዳንት ፑቲን ጋር መስማምታቸውን ማስታወቃቸው ከዩክሬን ብቻ ሳይሆን ከህብረቱ አገሮችም ተቃውሞ የተሰማበት ሲሆን፤ ሚኒስትሮቹ ግን በስብሰባቸው በሩሲያ ላይ ይልቁንም ከፍተኛ የተባለውን የማዕቀብ ውሳኔ ያሳለፉ መሆኑን ውይዘሮ ካያ ካላይ አስታውቀዋል
የፍልሰተኛችን ሞት ለመቀነስ መደበኛ መስመሮች እንዲስፋፉ አንድ ባለሙያ ጠየቁ 13.10.2026
ከአፍሪካ ቀንድ ተነስቶና ቀይ ባህርን አቋርጦ ወደ የመን የሚዘልቀውና ምስራቃዊው የጉዞ መስመር የሚባለው የፍልሰተኛች መሄጃ አቅጣጫ እንኾ ገዳይነቱ ቀጥሏል። ባለፈው ሳምንት መጨረሻ በደረሰ የጀልባ መገልበጥ አደጋ እስካሁን 139 ሰዎች መሞታቸውን አለምአቀፉ የፍልሰት ድርጅት- አይአኤም አስታውቋል።
የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ) «ቀይ ባሕር ለኢትዮጵያ ሕዝብ ይገባል» አለ 13.10.2026
“ቀይ ባህር ለዚህ አገር ህዝብ የተገባ ነው” የሚል ርዕስ ሰጥቶት ትናንት ባወጣው መግለጫ የኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦንግ)፤ “ኤርትራ እና ሕዝባዊ ወያኔ ኃርነት ትግራይ (ህወሓት) የደርግ ወታደራዊ መንግስት ውድቀትን ተከትሎ በነበራቸው ስልታዊ የፖለቲካ ትስስር ኢ-ፍትሃዊ በሆነ መንገድ በኢትዮጵያ ላይ የባህር በር መውጫን ዘግተዋል” ሲል ተችቷል፡
የዓይን ጤና ንጽሕናውን ከመጠበቅ ይጀምራል 13.10.2026
ኢትዮጵያ ውስጥ በተለይ የዓይን ማዝ የበርካታ ሰዎች ዓይን የጤና ችግር እንደሆነ የዘርፉ የህክምና ባለሙያዎች ይናገራሉ። የዓይን ንጽሕና በመጠበቅ እና በቀላል የህክምና እርዳታ ሊድን በሚችለው በዚህ የዓይን የጤና ችግር ብዙዎች የዓይን ብርሃናቸውን ሊያጡ ይችላሉ።
ማሕደረ ዜና፣ የኢትዮጵያ ጦርነት፣ የኢትዮ-ኤርትራ ፍጥጫ መቆሚያዉ መቼ ነዉ? 12.10.2026
የኢትዮጵያና የኤርትራ መንግሥታት ጠብ በናረበት በዚሕ ወቅት የኢትዮጵያ የሥለላ መስሪያ ቤት ኃላፊ፣ሌሎች ባለሥልጣናት፣ የጦር ጄኔራሎችና የተባባሪዎቹ ኃይላት የጦር አዛዦች ሥልታዊቱን ከተማን አዲግራትን የመጎብኘታቸዉ ፖለቲካዊ መልዕክት ከደብረፂዮን እኩል ለኢሳያስ አፈወርቂ መሆኑ ግልፅ ነዉ።
ባለፉት ሦስት ሳምንታት ግድም በሰሜን ኢትዮጵያ ትግራይ ክልል ግጭቶች ካገረሹ በኋላ በግጭቱ የሚከሰተው የሰብዓዊ ቀውስ በእጅጉ ስጋት ቀስቅሷል። 12.10.2026
በሰሜን ኢትዮጵያ ዳግም ያገረሸውን ጦርነት ተከትሎ በትግራይ ክልል ከሚገኙ ከተሞች በፌፌራል የጸጥታ ሃይሎች ስር በገቡ ከተሞች ለኢትዮጵያ ፌዴራል መንግስት አመራሮች አቀባበል ተደርጓል፡፡ በትናንቱ የአመራሮች አቀባበል ወቅት በርካታ የማህበረሰብ አካላት ደስታቸውን ብገልጹም፤ ስጋቶችም ግን እስካሁን ሙሉ በሙሉ አለመወገዳቸው እየተነገረ ነው፡፡
በአማራ ክልል በሚካሄደዉ ጦርነት ምክንያት በሸቀጦች ላይ ከፍተኛ የዋጋ ጭማሪ ተከሰተ። በክልሉ በሰሜን፤ ደቡብ ወሎና ሰሜን ሸዋ ጦርነት ዳግም አገርሽቷል። 12.10.2026
በአማራ ክልል በተሽከርካሪ መስተጓጎል ምክንያትበሸቀጦችና በግብርና ምርቶች ላይ ከፍተኛ የዋጋ ጭማሪ ተከሰተ። በአማራ ክልል በመንግሥትና በፋኖ ኃይሎች መካከል ባለፉት ሦስት ዓመታት እየተካሄደ የሚገኘው ጦርነት ባለፉት 14 ቀናት እንደ አዲስ አገርሽቶ በሰሜን ወሎ፣ ደቡብ ወሎና ሰሜን ሸዋ ጦርነቱ በተለያዩ ቦታዎች ቀጥሏል።
Replaio is not a podcast publisher; show names, artwork and audio belong to their authors and are distributed through public RSS feeds.