DW | Amharic - News
News, Analysis and Service from Germany and Europe - in 30 Languages
Be sure to visit the podcast's website and support the creator: www.dw.com
Where to listen?
Podcasts in the app Replaio Radio Coming soonPodcasts are coming to the app soon. Install now and be the first to see a whole new take on podcasts
Episodes
የሞያሌ ግጭት እና የኢትዮጵያ ፌድራሊዝም ጉድለቶች 22.11.2026
የሞያሌ ውዝግብ ለዘመናት የዘለቀ ጠንካራ ትሥሥር ያላቸውን የኦሮሞ ቦረና እና የሶማሌ ገሪ ጎሳዎች ለደም አፋሳሽ ግጭት ዳርጓቸዋል። ዳግም ያገረሸው ግጭት የኢትዮጵያ የፌድራሊዝም ሥርዓት በፈጠራቸው ክልሎች መካከል የሚገኙ ወሰኖች መፋለሚያ ሆነው መቀጠላቸውን ያሳየ ነው። ዶቸ ቬለ ሦስት እንግዶች በመጋበዝ በግጭቱ ላይ ውይይት አካሒዷል።
የሳውዲ አረቢያ የሰብአዊ መብት ይዞታ ማሽቆልቆሉ ቀጥሏል፤ ባለፉት 12 ወራት ቢያንስ 211 ሰዎች ለሞት ተዳርገዋል፣ የአካል ቅጣቶችም ተፈጽመዋል፣ ትችት የሚያሰሙ ወገኖች ላይ የሚወሰደው እርምጃም ተጠናክሮ ቀጥሏል። 21.11.2026
AFP እንደዘገበው በሞት ከተቀጡት 211 ሰዎች መካከል 100ዎቹ የሳዑዲ አረቢያ ዜጎች ሲሆኑ፣ የተቀሩት ደግሞ ኢትዮጵያውያንን ጨምሮ የሌሎች አገራት ዜጎች ናቸው። ሂዩማን ራይትስ ዎች እንዳሳወቀው፣ በሐምሌ ወር የሳዑዲ ባለስልጣናት ከአደንዛዥ ዕፅ ጋር በተያያዙ ወንጀሎች አምስት ኢትዮጵያዊያን ስደተኞችን በሞት ቀጥተዋል።
የኢትዮጵያ የቅርስ ጥበቃ ከአሜሪካው ቶሌዶ ሙዚየም ጋር ቅርሶችን ማስመለስ የሚያስችል ስምምነት ተፈራረመ 21.11.2026
ሰሞኑን ሁለት የኢትዮጵያ ታሪካዊ የብራና ጽሑፎች እና ሦስት የብረት መስቀሎች ከለንደን ወደ ኢትዮጵያ እንዲመለሱ የሚያግዝ ስምምነት ተደርሷል። በኢትዮጵያ ቅርስ ባለሥልጣን፣ በአሜሪካው ቶሌዶ ሙዚየም እና በግል ቅርስ በሚሰበስቡት ባለሀብት ሮበርት ማካርቲ መካከል የተደረሰው ይህ ስምምነት በቀጣይም ሌሎች ቅርሶች እንዲመለሱ የሚያግዝ ነው ተብሏል።
የፊንጫ ስኳር ፋብሪካ ሰራተኞች ጥሪ 21.11.2026
ከሶስት ሺ በላይ የሚሆኑ የፍንጫ ስኳር ፋብሪካ ቋሚ እና ጊዜያዊ ሰራተኞች በፋብሪካው ላይ የሚደርሱ ተደጋጋሚ ጥቃቶችን በሰላማዊ ሰልፍ አወገዙ፡፡ አብዛኛው ህይወታቸውን በፋብሪካው ስራ ላይ የመሰረቱት ሰራተኞቹ መሰረተ ልማቶች የጥቃት ዒላማ መሆን እንደለለባቸው በመጥቀስ በፋብሪካው ይዞታ ውስጥ የሚደረጉ የትጥቅ ግጭቶችን አውግዘዋል።
ትግራይ ክልል በኤርትራ ድንበር አካባቢ የሚገኙ ነዋሪዎች በጦርነት ስጋት አካባቢውን እየለቀቁ ነው 21.11.2026
በትግራይ ክልል በኢትዮጵያ እና ኤርትራ ድንበር አከባቢዎች ላይ የሚስተዋለውን የጦርነት ስጋት በመሸሽ በርካታ ሰዎች እየተፈናቀሉ ነው ተብሏል፡፡ተፈናቃዮቹ ትራንስፖርት እና እርዳታ በማይደርስባቸው ስፍራ ላይ በመሆናቸው ብርቱ ፈተና እየገጠማቸው መሆኑም ተገልጿል።
በተባበሩት መንግስታት የተካሄደው 'ገዳይ ሮቦቶች'ን የማገድ ውይይት ያለ ውጤት ተጠናቀቀ 21.11.2026
በጄኔቫ ሲውዘር ላንድ ለአንድ ሳምንት በተባበሩት መንግስታት የተካሄደው በሰው የማይታዘዙ'ገዳይ ሮቦቶች'ን የማገድ ውይይት ያለ ስምምነት ተጠናቋል።ሆኖም ግን ከሁለት ዓመት በኋላ አዳዲስ ደንቦችን ለማዘጋጀት እና ተጨማሪ ውይይቶችን ለማድረግ ስምምነት ላይ ተደርሷል።
በማያንማር የዘር ማጥፋት ወንጀል ላይ የተሰጠው ውሳኔr፦ ሮሂንጋዎች ለፍትህ የሚያደርጉት ትግል አላበቃም ይላሉ 20.11.2026
የዓለም አቀፉ የጦር ወንጀል መዳኛ ፍርድ ቤት (ICJ) ምያንማር በሮሂንጊያ ላይ የዘር ማጥፋት ወንጀል ፈጽማለች የሚለዉን ፍርድ የሮሂንጊያ ሙስሊም አናሳ ተወካዮች በደስታ ተቀበሉት። ዓለም አቀፉ የጦር ወንጀሎች መዳኛ ፍትህ ፍርድ ቤት (ICJ) ምያንማር በሮሂንጊያ አናሳ ህዝብ ላይ የዘር ማጥፋት ወንጀል ፈጽሟ ሲል ፈርጇል።
ያልተቋጨው የሞያሌው ግጭት 20.11.2026
ደቡባዊ የኢትዮጵያ ጠረፍ ከተማዋ ሞያሌ ቀጠለው ግጭት አሁንም ዘላቂ እልባት አለማግኘቱን ነዋሪዎች ገልፀዋል።፡እንደነዋሪዎቹ ገለፃ ፡በዚህ ሳምንት ግጭቱን ለማቆም የፌዴራል ኃይሎች መሀል ላይ ገብተው የነበረ ቢሆንም እሱም ጥረት ከሶስት ቀናት በላይ የመሳሪያ ድምጽ ማዘጋት ባለመቻሉ ከትናንት ሓሙስ አመሻሽ በኋላ ግጭቱ መቀጠሉን ገልጸዋል፡፡
ኤርትራዊ-አሜሪካዊው ጆ ንጉሴ በአሜሪካ የተወካዮች ምክር ቤት ምክትል አፈ-ጉባኤ ሆነው ተመረጡ 20.11.2026
ኤርትራዊ-አሜሪካዊው ጆ ንጉሴ በአሜሪካ የተወካዮች ምክር ቤት ምክትል አፈ-ጉባኤ ሆነው ተመርጠዋል። ለመሆኑ ተመራጩ ምክት አፈ ጉባኤ ማን ናቸው? ሹመቱስ ምን በአሜሪካ ፖለቲካ ምን ያህል ትልቅ ነው?ይህ ምርጫስ አሜሪካ ለሚኖሩ ለትውልደ አፍሪቃውያን ምን ፋይዳ አለው?
የትግራይ ባለአደራ አስተዳደር እስካሁን ምን አከናወነ? 20.11.2026
ከተቋቋመ አንድ ወር ያለፈው የትግራይ ክልል ባለአደራ አስተዳደር መቀሌን ጨምሮ በተለያዩ የክልሉ ከተሞች ውይይቶችን እያደረገ ነው። አስተዳደሩ በክልሉ የፈረሰውን የመንግሥት መዋቅር ለማቋቋም ልዩ ልዩ ምደባዎችን እና ሹመቶችንም ሲሰጥ ቆይቷል።ተፈናቃዮችን የመመለስጨምሮ በርካታ ኃላፊነቶች ያሉበት ይህ አስተዳደር እስካሁን ምንምን ተግባራትን አከናወነ?
በሰሜን ወሎ፣ በጃራ መጠለያ ካምፕ የሚገኙ ተፈናቃዮች፣ የልጆቻቸው ትምህርት መቋረጡን ገለፁ 20.11.2026
በአማራ ክልል በሰሜን ወሎ፣ በጃራ መጠለያ ጣቢያ የሚገኙ ተፈናቃዮች፣ ልጆቻቸው ከትምህርት ገበታ ውጭ መሆቸውን ተናገሩ ።በመጠለያ ጣቢያው የሚገኙ ልጆች ትምህርታቸው የተቋረጠው በመምህራን እጥረትና በበጀት እጦት ምክንያት መሆኑ ተገልጿል።
በዋግ ህምራ ዞን የዝቋላ ወረዳ ድርቅ አስከፊ ጉዳት እያደረሰ ነው 19.11.2026
በአማራ ክልል የዋግምራ ዞን የዝቋላ ወረዳ በባለፈው ክረምት በቂ ዝናብ ባለመገኘቱ በተከሰተ ከፍተኛ ድርቅ ምክንያት የሰውና የእንስሳት ህይወት እያለፈ መሆኑን የአካባቢው ነዋሪዎችና ባለሙያዎች ተናገሩ። በወረዳው 15 ቀበሌዎች ውስጥ በተደረገ ግምገማ 74,162 ሰዎች የአስቸኳይ ጊዜ የምግብ ድጋፍ እንደሚያስፈልጋቸው ተገልጿል።
ማሕበራዊ መገናኛ ዘዴዎች የወጣቶችን ቀልብ በገዙበት ዘመን ድሬደዋ የንባብ ባሕልን ለማዳበር እየጣረች ነው 19.11.2026
ፌስቡክ እና ቲክቶክን የመሳሰሉ ማኅበራዊ መገናኛ ዘዴዎች የወጣቶችን ቀልብ ሰንገው በያዙበት ወቅት ድሬደዋ የንባብ ባህልን ለማዳበር እየጣረች ነው። የድሬደዋ ወጣቶች እና ተማሪዎች “በእውቀት እና በክህሎት ዳብረው ብቁ እና ተወዳዳሪ” እንዲሆኑ እመርታ ቤተ-መጻሕፍትን የመሳሰሉ ተቋማት ፋይዳ እንደሚኖራቸው ኃላፊነቱ የተጣለባቸው ባለሥልጣናት ያምናሉ።
በኤርትራ ድንበር አቅራብያ የድሮን እና ከባድ መሳሪያ ድምጽ በተደጋጋሚ እየተሰማ ነው መባሉ 19.11.2026
በሰሜን በሰሜን ምዕራብ ትግራይ በኩል በኢትዮጵያ እና ኤርትራ ድንበር አቅራቢያ ከትናንት ከሰዓት ጀምሮ ከባባድ የጦር መሳሪያ ድምጽ እና የአየር ጥቃቶች መደረጋቸውን የአከባቢው ነዋሪዎች ገለጹ፡፡ ከባድ የጦር መሳሪያዎች ተኩስ የሚሰማባቸው አከባቢዎች ከኤርትራ ድንበር ባድሜ 15 ኪሎሜትር ግድም ብቻ የሚርቅ ነው ተብሏል፡፡
ህወሓት ዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብት እና የእርዳታ ድርጅቶች ይህንን "ሕገ- ወጥ" ያላቸውን ድርጊቶች እንዲያስቆሙ ጠይቋል። 19.11.2026
መንግሥት ከ600 በላይ የትግራይ ተወላጆችን በአዋሽ አርባ "በዘፈቀደ አስሯል" ሲል ህወሓት ገለጠ። እሥረኞቹ ኢ-ሰብአዊ፣ አዋራጅና ለሕይወት አስጊ በሆነ ኹኔታ ውስጥ እንደሚገኙ የጠቀሰው ህወሓት ኹኔታው የታሳሪዎችን ሰብአዊ መብት የጣሰ ነው ብሏል። በጉዳዩ ላይ ከመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ማብራሪያ ለመጠየቅ ጥረት ብናደርግም ምላሽ አላገኘንም።
በቤሮ ወረዳ 10 ሰዎች በታጣቂዎች ተገደሉ 19.11.2026
በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል ምዕራብ ኦሞ ዞን ቤሮ ወረዳ ዘጠኝ የፀጥታ አባላትና አንድ የሲቪል ሠራተኛ በታጣቂዎች መገደላቸውን የአካባቢው ነዋሪዎች ገለጹ። ታጣቂዎቹ በወረዳው ጋሮ ቀበሌ በሚገኝ አንድ የወርቅ ማምረቻ ድርጅት ላይ አደረሱት በተባለው ጥቃት ዶዘሮችና ግሬደሮችን ጨምሮ ንብረቶችን በእሳት ማቃጠላቸውን የአይን እማኞች ተናግረዋል።
በአቤደንጎሮ ወረዳ ተደጋጋሚ ጥቃት የተፈናቀሉ ዜጎች ቅሬታ 19.11.2026
በአቤዶንሮ ወረዳ አራት ቀበሌዎች በተከሰተው የጸጥታ ችግር የተፈናቀሉ ዙጎች በሰብአዊ እርዳታ እጦት ለከፋ ችግር እየተጋለጡ እንደሚገኙ አስታወቁ፡፡ በወረዳው ከጥቅምት 24/2019 ዓ.ም ለሁለት ቀናት በቆየው የታጣቂዎች ጥቃት ሆማ ጋለሳ የተባውን ስፍራን ጨምሮ ከአራት ቀበሌዎች ከ20ሺየሚደርስ ሰዎች መፈናቀላቸው ያነጋርናቸው ነዋሪዎች ገልጸዋል፡፡
የከባድ መኪና አሽከርካሪዎችን ማገትና ማዋከብ ቀነሰ ወይስ ጨመረ? 19.11.2026
የኢትዮጵያ ከባድ መኪና አሽከርካሪዎች ማህበር ታጣቂዎች አልፎ አልፎ ለማደሪያ እና የሚዛን በሚል አሽከርካሪ እያስቆሙ ገንዘብ መጠየቅ አሁንም ሊቆሙ ያልቻሉ ችግሮች መሆናቸውን ገልጿል። ሰሞኑን ዱከም ከተማ ላይ አንድን አሽከርካሪ አስቁመው ከመኪናው እንዲወርድ ሲያስገድዱ የነበሩ መሣሪያ የታጠቁ የመንግሥት ተሿሚዎች ጉዳይ በሕግ እንዲያዝ ተደርጓል።
የሦስት ዓመቱ ግጭት በአማራ ክልል ኢኮኖሚና ማህበራዊ ሕይወት ላይ የፈጠረው ጥልቅ ስብራት 18.11.2026
ከሦስት ዓመት በላይ የዘለቀ ግጭት፣ የብር መዳከም እና የኑሮ ውድነትን የመሳሰሉ ችግሮች ተደራርበው የአማራ ክልል ነዋሪዎችን በኃይል እየተፈታተኑ ይገኛሉ። ሸቀጦች የሚያጓጉዙ ተሽከርካሪዎች የሚጠይቁት የጭነት ዋጋ ጨምሯል። ነዋሪዎች በግዳጅ ከደመወዝ የሚቆረጥ መዋጮ እና ድርቅን የመሳሰሉ ችግሮች ተጽዕኖ ከባድ እንደሆነ ለዶቸ ቬለ ተናግረዋል።
በአፋርና በሶማሌ ክልሎች ድንበር አዋሳኝ አካባቢዎች በሁለቱ ክልሎች ማህበረሰቦች መካከል ግጭት መቀስቀሱ ተሰማ። በአርጋአቶ ሀሩካ እና አቢዳ አካባቢዎች በተከሰተው የድንበር ይገባኛል ግጭትንጹሃን ዜጎች ላይ ጉዳት መድረሱ ተገልጿል። 18.11.2026
በአፋር ክልልና በሶማሌ ክልል አዋሳኝ አካባቢዎች የተቀሰቀሰው ግጭት አንድ ወር ማስቆጠሩን የነገሩን አስተያየት ሰጪ ለተወሰነ ጊዜ ተቋርጦ የነበረ ቢሆንም ከቆይታ በኋላ ማገርሸቱን ይናገራሉ።
አምስት የዴሞክራቲክ ፓርቲ ሴናተሮች በጎርጎሮሳዊው በቅርቡ ለአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማርኮ ሩቢዮ በላኩት ደብዳቤ፣ በኢትዮጵያ እና በአፍሪካ ቀንድ እየሰፋ የመጣውን ግጭት ለመከላከል አስቸኳይ የዲፕሎማሲ ጥረት እንዲጠናከር ጠይቀዋል። 18.11.2026
«በርካታ ሰዎች ፣ዴሞክራቶች ኮንግረሱን በመቆጣጠራቸው የፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ የውጭ ጉዳይ ፖሊሲን እንዴት ይቀያራልሱሉ ይጠይቃሉ። ትራምፕ በተናጠል ሊወስዱ የሚችሉት እርምጃ አንዱ ነው። ከሪፐብሊካኑ ይልቅ ዴሞክራቶች ትራምፕን የበለጠ ተጠያቂ ሊያደርጉ ይችላሉ የሚል ነው።»በኤምሪ ዩኒቨርስቲ የፖለቲካ ሳይንስ ተባባሪ ፕሮፌሰር አንድራ ጊሊስፔን
አስተያየት ሰጪ የሞያሌ ነዋሪዎችም ግጭቱ ወደ ሌላ አከባቢ እንዳይዛመት ስጋት አላቸው፡፡ “አሁን በዚሁ አከባቢ ዋጭሌ እና ዳስ በሚባሉ ወረዳዎች ስጋቶች አሉ” ሲሉ አስተያየታቸውን አክለዋልም፡፡ 18.11.2026
የተመድ ሰብዓዊ እርዳታ አስተባባሪ ከተከሰተ አንድ ወር በደፈነው በኢትዮጵያ ሞያሌ በጋሪ እና ቦረና ማህበረሰብ ግጭትና አለመረጋጋት መዘዝ ከ60 ሺህ በላይ ህዝብ ተፈናቅለው ወደ ኬንያ መግባታቸውን ገልጿል። የተፈናቃሉት ቁጥርም ከተቀባዩ ማህበረሰቡ አቅም በላይ እየሆነ በመሄዱ ከፍተኛ የመሠረታዊ ፍላጎት አቅርቦትን ፈታኝ አድርጎታል ብሏል፡፡
ሀገራት የአየር ንብረት ለውጥን እንደቋቋሙ ለማስቻል የሚደረገው የገንዘብ ደጋፍ፣ የበለጠ የተጎዱትንና ለአየር ንብረት ለውጡ መከሰት አስተዋጽኦ ያላደረጉትን ከገንዛቤ ባስገባ መንገድ መኾን እንዳለበትም ዶ/ር ምህረት አሳሰበዋል። 18.11.2026
የጥናቱ ውጤት ይፋ የተደረገው ኬንያን፣ ሶማሊያንና፣ ደቡባዊውን የኢትዮጵያ ክፍል በመሳሰሉት አካባቢዎች ከጥቅምት እስከ ታህሳስ ባለው ጊዜ ውስጥ ከመደበኛ በላይ የኾነ ዝናብ እንደሚኖር የዘርፉ ባለሙያዎች በተነበዩበት፣ በአንዳንድ አካባቢዎችም ውጤቱ እየታየ ባለበት ወቅት ነው።
ኢትዮጵያ ወደ ከባቢ አየር ለሚለቀቅ ጋዝ ያላት ድርሻና የሚደርስባት ጉዳት 18.11.2026
ከኢትዮጵያ ከኃይል አጠቃቀም ጋር በተያያዘ በጎርጎሮሳዊው 2024 ወደ ከባቢ አየር የተለቀቀው 50.3 ሚሊዮን ቶን ካርቦን ዳይኦክሳይድ እንደነበር ዓለም አቀፉ የኢነርጂ ኤጀንሲ አስታውቋል። በከባቢ አየር ብክለት ያላት ድርሻ እጅግ በጣም አነስተኛ ቢሆንም ኢትዮጵያ ለአየር ንብረት ለውጥ ተጋላጭ ከሆኑ 10 አገራት አንዷ ናት።
ወደ 27ቱ አባል አገራት የሚመጡ ጥገኝነት ፈላጊዎችን ቁጥር ለመቀነስ እና የመቆየት መብት የሌላቸውን ስደተኞች ወደ አገራቸው እንዲመለሱ ለማድረግ የጋራ የፍልሰት ደንቦችን ለማጠናከር፣ ለዓመታት ሲሰራ ቆይቷል። 17.11.2026
ሀገራቸው መመለስ የማይችሉ ስደተኞችን ወደ ሩዋንዳ የመላክ ሂደት በጎርጎሮሳዊው 2027 ዓ.ም. መጀመሪያ ማለትም የፊታችን ጥር ላይ ይጀመራል ። ለዚህም ድርድሩ በፍጥነት መከናወን አለበት። በመራኄ መንግሥት ሽቶከር መግለጫ መሠረት የመመለሻ ማዕከላት መቋቋማቸው ጥቅሞች አሏቸው ይሁንና የመብት ተሟጋች ድርጅቶች ውሳኔው አጥብቀው ይቃወማሉ
Replaio is not a podcast publisher; show names, artwork and audio belong to their authors and are distributed through public RSS feeds.