DW | Amharic - News

News, Analysis and Service from Germany and Europe - in 30 Languages

Be sure to visit the podcast's website and support the creator: www.dw.com

Category

Uncategorized

Podcast website

www.dw.com

Latest episode

Nov 22, 2026

Where to listen?

Podcasts in the app Replaio Radio Coming soon

Podcasts are coming to the app soon. Install now and be the first to see a whole new take on podcasts

Get it on Google Play Install for free Android 10M+ downloads · 4.7+ rating iOS soon

Episodes

የኤርትራ ወታደሮች ወደ ኢትዮጵያ ግዛት ገቡ የተባሉባቸው የትግራይ አካባቢዎች የትኞቹ ናቸው? 09.10.2026

የኤርትራ ወታደሮች በትግራይ ክልል ሦስት ዞኖች በኩል ድንበር ተሻግረው ወደ ትግራይ ክልል እንደገቡ የገለጹት ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቲዮስ ኢትዮጵያ ራሷን የመከላከል ተፈጥሯዊ መብቷን እንደምትጠቀም ለጸጥታ ጥበቃው ምክር ቤት አባላት አስታውቀዋል። ውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ወታደሮቹ ከ30-60 ኪሎ ሜትር ወደ ኢትዮጵያ ግዛት እንደገቡ ጠቅሰዋል።

ነዋሪዎቹ ከተማዋን የተቆጣጠሩ የፀጣታ ሃይሎች ፖሊስን ለመሳሰሉ የፀጣታ መዋቅሮች ጥሪ እያቀረቡ እንዳሉም አመልክተዋል፡፡ 09.10.2026

በሰሜን ኢትዮጵያ ዳግም ያገረሸውን ጦርነት ተከትሎ በትግራይ ክልል የሚገኙ ከተሞች እና አከባቢዎች አሁንም በተለያዩ ይዞታዎች ላይ ይገኛሉ።

ሰሜን ኢትዮጵያ ያለው ኹኔታ ጦርነት ሳይሆን «የትጥቅ ግጭት» በሚል የሚገለጽ ነው: ኢሰመኮ 09.10.2026

በትግራይና አዋሳኝ የአማራና የአፋር ክልሎች ያለውን ኹኔታ እስካሁን ባለው ደረጃ «የትጥቅ ግጭት» አድርጎ እንደሚመለከተው የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን ገለፀ። ኮሚሽኑ በተለይ በትግራይና አማራ ክልሎች ያለውን ኹኔታ በዓለም አቀፍ ብያኔ «ጦርነት» ሳይሆን «በግጭት ዐውድ ላይ የሚገኙ አካባቢዎች» አድርጎ እንደሚወስዳቸው አስታውቋል።

ሰሜን ወሎ በተፈናቃዮች መጠለያ በማኅበረሰቦች ግጭት ሰዎች መጎዳታቸው ተገለጸ። 09.10.2026

በአማራ ክልል ሰሜን ወሎ ዞን በሚገኘው የጃራ ተፈናቃዮች መጠለያ ጣቢያ ላይ በተፈጸመ ጥቃት ሁለት ተፈናቃዮች በጽኑ መቁሰላቸውን የመጠለያው ነዋሪዎች እና አስተባባሪዎች ገለጹ።

ተመድ ለኤርትራ ወረራ ምላሽ ይስጥ ስትል ኢትዮጵያ ጠየቀች 09.10.2026

የኢትዮጵያ መንግሥት፣ ግብፅ፣ ሱዳንና ኤርትራ ታጣቂዎችን ይረዳሉ በማለት ሲወነጅል ቆይቷል። ሰሞኑን ደግሞ፣ የኤርትራ ወታደሮች ድንበር ጥሰው ገብተዋል፣ ግልፅ ወረራም ፈጽመዋል በማለት ከሷል።

ደቡብ አፍሪቃዊትዋ ዳና ናቫኔተም በአጭሩ ስማቸዉ "ናቪ" ፒላይ የዘንድሮዉን የጎርጎሮሳዉያን 2026 የኖቤል የሰላም ሽልማት አሸነፉ። 09.10.2026

ደቡብ አፍሪቃዊትዋ ዳና ናቫኔተም በአጭሩ ስማቸዉ "ናቪ" ፒላይ የዘንድሮዉን የጎርጎሮሳዉያን 2026 የኖቤል የሰላም ሽልማት አሸነፉ። ደቡብ አፍሪቃዊቷ ዳኛ "ናቪ" ፒላይ፣ የዘንድሮውን የኖቤል የሰላም ሽልማት ያሸነፉት፤ ለሰላም እና ለዓለም አቀፍ ህግ መከበር ላደረጉት ጥረት መሆኑን የሽልማት ኮሚቴዉ ዛሬ ኖርዌይ መዲና ኦስሎ ላይ ይፋ አድርጓል።

የካቢኔ ሽግግር እና ሹመቶችን ተከትሎ የካቢኔ መጠነኛ ለውጥ መደረጉ ላይ ያለዎት አስተያየት ምንድን ነው? ዶቼ ቬለ የተለያዮ አስተያየቶችን አሰባስቧል። 08.10.2026

መንግሥት በ 22ቱ የሚኒስቴር መሥሪያ ቤቶች ላይ ያደረገው የካቢኔ ሽግግርና አዳዲስ ሹመቶች በህዝብ ዘንድ የተለያዩ አስተያየቶችን እያስከተለ ይገኛል። በተለይም በኢኮኖሚው መስክ እንደ ፋይናንስ፣ ገቢዎች፣ እንዲሁም ንግድ እና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር ያሉ ዋና ዋና የፖሊሲ መሥሪያ ቤቶች በሴት መሪዎች መያዙ አዲስ አቀራረብ ነው ተብሎዋል።

የሚኒስትሮች ሹመትና የምክር ቤቱ ምላሽ፤ ይህ መንግሥት ከፊቱ ምን ይጠብቀዋል? 08.10.2026

የምክር ቤት አባል ሚኒስትሮች የተሰሩትን በጎ ሥራዎች ብቻ ሳይሆን የተገኙ ድክመቶችንም ለማረም የሚያሳዩት ቁርጠኝነት መታየት አለበት ብለዋል።ድክመት ለምን ታነሳላችሁ የሚል ችግት ይገጥማቸው እንደነበርና እንዲህ ያሉ ነገሮች ሲነሱ የፖለቲካ ሽፋን መስጠትና እነሱን ለማጥቃት የተደረገ ጥረት የማስመሰል ችግር እንደነበር ጠቅሰው ሊታረም ይገባል ብለዋል

ዐቢይ አሕመድ ባዋቀሩት የመንግሥት ካቤኔ አባላት ሹመቱ ውስጥ 11 የቀድሞ ሚኒስትሮች በሌሎች ተተክተዋል። በአዲሱ ካቢኔ 9ኙ ሴቶች ናቸው። 08.10.2026

በሳምንቱ መጀመርያ ሰኞ የጀመረው 7ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ያቀረቧቸውን 23 የካቢኔ አባላት ሹመት ዛሬ ሐሙስ አፅድቋል። የካቤኔ አባላት ሹመቱ 11 የቀድሞ ሚኒስትሮችን በሌሎች የተካ ሲሆን፣ በአዲስ ከተዋቀረው የአስፈፃሚ አካል ዝርዝር ውስጥ 9 ኙ ሴቶች ናቸው።

የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊትና አጋሮቹ የመቀሌ ከተማን ከተቆጣጠሩ በኋላ የነዋሪው እንቅስቃሴ ከቀን ወደ ቀን እየተሻሻለ መጥቷል 08.10.2026

በሰሜን ኢትዮጵያ ዳግም ያገረሸውን ጦርነት ተከትሎ በትግራይ ክልል የሚገኙ ከተሞች እና አከባቢዎች በተለያዩ ይዞታዎች ላይ ይገኛሉ፡፡ በመቀሌ እና ውቅሮ ከተሞች የሰው እንቅስቃሴ በተሸለ መልኩ ተመልሷል ሲባል አዲግራት እና ወደ ዛላንበሳ የስልክ መስመሮችም በስፋት እየሰሩ አለመሆኑ ከአከባቢው ቤተሰብ ያላቸው እየገለጹት ነው፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ 11 አዳዲስ ሚኒስትሮችን በመሾም አዲሱን ካቢኔያቸውን ዛሩ ሐሙስ ይፋ አድርገዋል። በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በተካሄደው ጉባኤ ሹመታቸው የፀደቀላቸው 23 ሚኒስትሮች ሲሆኑ ከመካከላቸው ዘጠኙ ሴቶች ናቸው። 08.10.2026

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ 11 ሚኒስትሮችን በመሾም አዲሱን ካቢኔያቸውን ይፋ አድርገዋል። በሕዝብ ተወካዮች ም/ ቤት ሹመታቸው ከፀደቀላቸው 23 ሚኒስትሮች መካከል ዘጠኙ ሴቶች ናቸው።

በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን መንዝ አካባቢዎች (መሀል ሜዳ፣ ዘመሮ እና ሞላሌ) በመንግስትና በፋኖ ኃይሎች መካከል በተካሄደ ከባድ ግጭት የሰዎች ህይወት አለፈ፤ በንፁሃን ላይ ጉዳት ደረሰ። 08.10.2026

በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን መንዝ አካባቢዎች (መሀል ሜዳ፣ ዘመሮ እና ሞላሌ) በመንግስትና በፋኖ ኃይሎች መካከል በተካሄደ ከባድ ግጭት የሰዎች ህይወት ማለፉንና በንፁሃን ላይ ጉዳት መድረሱን የአካባቢው ነዋሪዎች ለዶቼቨለ ገለጹ። ደቡብ ወሎ መካነ ሰላም ከተማ ትናንት ከተሰማ የከባድ መሳሪያ ተኩስ በኋላ ዛሬ ሰላማዊ እንቅስቃሴ መኖሩ ተጠቅሷል።

የ2026 የኖቬል ሽልማት ፤ከሰዎች አእምሮ እስከ ጠፈር ምርምር 07.10.2026

የ2026 በየዓመቱ የላቀ ስራ ላበረከቱ ግለሰቦች በግል እና በጋራ ሽልማት የሚሰጠው የኖቤል ኮሚቴ በዚህ ሳምንትም በተለያዩ ዘርፎች የኖቬል አሸናፊዎችን ይፋ አድርጓል።ለመሆኑ ዘንድሮ በተፈጥሮ ሳይንስ ዘርፍ የትኞቹ ምርምሮች ተሸላሚ ሆኑ?

በውቅሮ ከተማ አቅራቢያ የከባድ መሳሪያ ድምጽ እየተሰማ እንደሚገኝ የከተማዋ ነዋሪ ለዶቼ ቬለ ተናገሩ 07.10.2026

የከተማዋ ነዋሪ ደግሞ የኤርትራ ወታደሮች ዛሬ ጠዋት በከተማዋ ውስጥ አቋርጠው ወደ መቀሌ አቅጣጫ ሲጓዙ መመልከታቸውን ተናግረዋል

የኤርትራ ጦር የኢትዮጵያ ድንበርን አቋርጦ መዝለቁን ተነገረ 07.10.2026

ስማቸው እንዳይጠቀስ የገለጹት የትግራይ የሰላም አዛዥ እንደሚሉት ዕዳጋ ሓሙስ ከገቡት የኤርትራ ወታደሮች ወደ አፅቢ ወንበርታ አቅጣጫ በ2 የጭነት መኪኖች ተጭነው በሚጓዙበት ወቅት በድሮን ተመተዋል። ከመከላከያ ሠራዊቱ ጎን ተሰልፎ የሚዋጋው ታጣቂ ቡድን አመራር ተፈጽሟል ያሉትን የድሮን ጥቃት ዶይቼ ቬለ በገለልተኝነት አላረጋገጠም።

በሰሜን ጎንደር ዞን ጠለምት ደጃች ሜዳ ወረዳ ድርቅ “የከፋ ረሐብ” እንዳስከተለ ነዋሪዎች ተናገሩ 07.10.2026

በሰሜን ጎንደር ውስጥ በሚገኘው ጠለምት ደጃች ሜዳ ወረዳ ድርቅ ባስከተለው ረሐብ የሰዎች ሕይወት ማለፉን የአካባቢው ነዋሪዎች ተናገሩ። ወረዳው ባለፉት ሁለት ተከታታይ ክረምቶች በቂ ዝናብ አላገኘም። ዶይቸ ቬለ ያነጋገራቸው አንድ የአካባቢው ነዋሪ እንደሚሉት ወረዳው ዘንድሮ የገጠመው በ1977 ከተከሰተው አስከፊ ድርቅ የሚመሳሰል ነው።

ከዚህ በፊት የነበሩት 22 የአስፈፃሚ መሥሪያ ቤቶች ቁጥር ባሉበት ይቀጥላሉ 07.10.2026

የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት ዛሬ ተወያይቶ ያፀደቀው የፌዴራል መንግሥት የአስፈፃሚ አካላት ስያሜ፣ አደረጃጀት፣ ስልጣንና ተግባር ለመወሰን የቀረበ ረቂቅ አዋጅ፣ የባሕል እና ስፖርት እንዲሁም የቱሪዝም በሚል ተዋቅረው የነበሩ ሁለት ተቋማት የባሕል እና ቱሪዝም ሚኒስቴር ተብለው እንዲደራጁ አድርጓል።

የመን ውስጥ የተባባሰው ውጊያ 07.10.2026

የመን ውስጥ በመንግሥት እና በሁቲ አማጽያን መካከል ውጊያው ተባብሷል። ዓለም አቀፉ እውቅና ያለው የየመን መንግሥት በሁቲዎች ላይ የሚያደርገውን ጥቃት አጠናክሯል

«የቆሰሉና የሞተው ታዳጊ ወጣት ግን ምንም የማያውቁ ንጹሃን ናቸው» 07.10.2026

«የጉምሩክ ጥበቃ ላይ የሚሰሩ የፌዴራል ፖሊስ አባላት ወደ ጉቢቻ ቀበሌ ልዩ ስሙ አባይነሽ በሚባል ስፍራ አንድ ባጃጅ የጫነችው ኮንትሮባንድ ሊባል የማይችል እቃ ይዘናል በሚል ደርሰው በከፈቱት ተኩስ ወደ ስፖርት የሚሄድ ልጅና ተማሪዎችን ወደ ትምህርት ቤት በማድረስ ላይ የነበረች የእድሜ ባለጸጋን ጨምሮ አምስት ስድስት ሰዎች በጥይት ተመተዋል፡»

ርእሠ ብሔር ታዬ መንግሥት ስለሚከተላቸው አቅጣጫዎች የሰጡት ገለፃ 06.10.2026

የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ርእሠ ብሔር ታዬ አፅቀ ሥላሴ ዛሬ ማክሰኞ መስከረም 26 ቀን 2019 ዓ.ም የሕዝብ ተወካዮች እና የፌዴሬሽን ምክር ቤቶች የሥራ ዘመን መክፈቻ ላይ ባደረጉት ንግግር፣ የምክር ቤቶቹ ዋና የትኩረት አቅጣጫዎችን ዘርዝረዋል። የሕዝብን ሰላምና ደኅነትን ማፅናት አንዱ መሆኑንም በዚሁ ወቅት ጠቅሰዋል።

በአማራ ክልል ደቡብ ወሎ ዞን ውስጥ በምትገኘው መካነ ሰላም በመንግሥትና በፋኖ ኃይሎች መካከል ትላንት ሰኞ ከባድ ውጊያ መደረጉን ነዋሪዎች ገለጹ 06.10.2026

አማራ ክልል በመካነ ሰላም ከተማ ዙሪያ በመንግሥት እና በፋኖ ኃይሎች መካከል በተደረገ ከባድ ውጊያ አንድ ታዳጊ ስትገደል፣ ቤተሰቦቿ መጎዳታቸውን ነዋሪዎች ገለጹ። በመካነ ሰላም እና ዙሪያዋ በነበረው ከባድ ውጊያ ትምህርት እና የንግድ እንቅስቃሴዎች ተስተጓጉለው የነበረ ቢሆንም፣ ዛሬ ከተማዋ ወደ ሰላማዊ እንቅስቃሴ መመለሷን ነዋሪዎች ተናግረዋል።

የፀጥታው ነገር፤ በቀጣዩ የመንግስት አቅጣጫ ሊሰጠው የሚገባው ትኩረት 06.10.2026

ሰላም እና ጸጥታ አዲስ በተመሰረተው የኢትዮጵያ መንግስት አንዱ ትልቅ ትኩረት ሊሰጠው የሚገባው ጉዳይ መሆኑን በተለያዩ አከባቢዎች በፀጥታው የተፈተኑ የማህበረሰብ አካላት ገልጸዋል፡፡ መንግስት በፊናው በቀጣይ ጊዜያት ልዩ ተባለው የፀጥታው ስምረት በማድረግ ዝግጅ ስለመኖሩ ነው የጠቆመው፡፡

የኢትዮጵያ ጦርነት እንዲቆም፣የኢትዮጵያና የኤርትራ ዉጥረት እንዲረግብ የአዉሮጳ ሕብረት ጠየቀ 06.10.2026

በሕብረቱ የዉጪ ግንኙነት ጉዳይ የበላይ ኃላፊ ሥም ዛሬ የወጣዉ መግለጫ በኢትዮጵያና በኤርትራ መካከል የተካረረዉ ዉጥረት መላዉን የአፍሪቃ ቀንድ ሊያዉከዉ እንደሚችል አስታዉቋል።የኢትዮጵያ መንግሥትና ህወሓት ዉጊያ ከገጠሙ ካለፈዉ መስከረም 13 ቀን 2019 ወዲሕ የአዉሮጳ ሕብረት ጦርነቱን በማስመልከት መግለጫ ሲያወጣ የዛሬዉ ሁለተኛ ነዉ

በትግራይ የሚገኝ የተመድ መጋዘን ዘረፋ እንደተፈፀመበት ድርጅቱ አስታወቀ 06.10.2026

እሳቸው እንዳሉት፣ በክልሉ የሚገኝ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት መጋዘን እንደዚሁም መንግሥታዊ ያልኾኑ አለምአቀፍና የሀገር ውስጥ ድርጅቶች መጋዘኖችና ሌሎች ተቋማት ተዘርፈዋል። በዚህም ምክንያት፣ ምግብን፣ ዘርን፣ ማዳበሪያንና የውሃ መሳቢያዎችን ጨምሮ፣ ሰብአዊ አቅርቦቶች መወሰዳቸውን አመልክተዋል

ከራስ አልፎ ለብዙዎች የተኖረ ሕይወት 06.10.2026

ከራሳቸው አልፈው ለብዙዎች የኖሩት የማትያስ ወንዱ የካንሰር ማኅበረሰብ መሥራችና ዳይሬክተር አቶ ወንዱ በቀለ ባለፈው ዓመት ሚያዝያ ወር በህመም ላይ ሆነው ያጋጠማቸውን የጤና እክል ገልጸውልን ነበር።

Listen to the DW | Amharic - News podcast in Replaio

Radio and podcasts in one app - free, with no sign-up. Install today and do not miss the launch

Get it on Google Play

Replaio is not a podcast publisher; show names, artwork and audio belong to their authors and are distributed through public RSS feeds.