DW | Amharic - News

News, Analysis and Service from Germany and Europe - in 30 Languages

Be sure to visit the podcast's website and support the creator: www.dw.com

Category

Uncategorized

Podcast website

www.dw.com

Latest episode

Nov 22, 2026

Where to listen?

Podcasts in the app Replaio Radio Coming soon

Podcasts are coming to the app soon. Install now and be the first to see a whole new take on podcasts

Get it on Google Play Install for free Android 10M+ downloads · 4.7+ rating iOS soon

Episodes

ማሕደረ ዜና፣ የኢትዮጵያ ጦር መቀሌን ተቆጣጠረ፣ጦርነቱ አላባራም፣አካባቢያዊዉን ማስጋቱም ቀጥሏል 05.10.2026

ከየካቲት 1981 ጀምሮ መቀሌ ከህወሓት እጅ ስትወጣ ያሁኑ ሁለተኛዋ ነዉ።የመጀመሪያዉ የፌደራሉ መንግሥት ህዳር 2013 ከተማይቱን ሲቆጣጠር ነበር።ግን ከሰባት ወር በላይ አልቆየም።ህወሓት መልሶ ተቆጣጠራት።ዘንድሮም ከመቀሌ ድል-ሽንፈት በኋላ ጦርነቱ ቦታ-ይቀይር እንጂ አላባራም

የመስከረም 25 ቀን 2019 የስፖርት መሰናዶ 05.10.2026

የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የ2019 የእግር ኳስ ውድድር ዘመን በተያዘው ሳምንት ይጀመራል። ቡንደስ ሊጋን ጨምሮ ዋና ዋናዎቹ የአውሮፓ ሊጎችም አርብ እና ቅዳሜ ወደ ውድድር ይመለሳሉ። ሐና ደምሴ ያዘጋጀችው የዛሬው የስፖርት መሰናዶ እነዚህን ጨምሮ አትሊቲክስ እና ሜዳ ቴኒስን የተመለከቱ ዘገባዎች አካቷል።

በአማራ ክልል የጻግብጅ እና አበርገሌ ወረዳ ተፈናቃዮች ወደቀያቸው መመለስ ጀመሩ 05.10.2026

በአማራ ክልል ዋግህምራ ብሄረሰብ ዞን አበርገሌ እና ፃግብጂ ወረዳዎች ከወራት በኋላ የመንግሥት መዋቅር በመመለሱ ተፈናቃዮች ወደ ቀያቸው መመለስ ቢጀምሩም፣ ከፍተኛ የትራንስፖርት እጥረት፣ የሰው ሕይወት መጥፋት ያሳደረው ሀዘን እንዲሁም የረሃብና የደህንነት ስጋት እንደተቀነባቸው ነዋሪዎች ገለጹ።

የፌዴራል መንግስት ኃይሎች መቀሌን ከተቆጣጠሩ በኋላ የከተማዋ ሁኔታ 05.10.2026

በሰሜን ኢትዮጳያ ዳግም ጦርነት ካገረሸ በኋላ ባሳለፍነው ቅዳሜ መስከረም 23 ቀን 2019 ዓ.ም. የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊትና አጋሮቹ የትግራይ ክልል መዲና መቀሌን መቆጣጠራቸው ተረጋግጧል፡፡ ይህንን ተከትሎ በትናንትናው እለት የቴሌኮም አገልግሎት ሙሉ በሙሉ ፤ በኢንተርኔት የተደገፈ የባንክ ስርዓት ደግሞ በከፊል መመለሱን ነዋሪዎች ገልፀዋል።

ዛሬ የተመሠረተው መንግሥት የሚጠብቁት አንገብጋቢ የፀጥታ እና ቀጣናዊ ጉዳዮች 05.10.2026

ግንቦት 24 ቀን 2018 ዓ.ም. በተካሄደው ጠቅላላ ምርጫ ያሸነፈው ብልጽግና ፓርቲ ያቋቋመው መንግሥት ዛሬ መስከረም 25 ቀን 2019 ተመስርቷል። የተቋቋመው መንግሥት ከውስጥ አንገብጋቢ የፀጥታና የደኅንነት እንዲሁም፣ ከብሔራዊ ጥቅም አንፃር ከጎረቤት ሀገራት ብርቱ ቀጣናዊ መፍትሔ የሚሹ ጉዳዮች የሚጠብቁት ነው።

የአፍሪቃ ቀንድን የተመለከተው የኤርትራ ፣ሶማሊያ ፣ሱዳን እና ግብፅ መሪዎች የጋራ መግለጫ 05.10.2026

የግብጽ፤ ሱዳን፤ ኤርትራና ሶማሊያ መሪዎች ባለፈው ሳምንት መጨረሻ ቀናት በግብጽ በኤል አላሜይን የወደብ ክተማ ከተካሄደው የግብጽና አፍሪካ ቢስነስ ጉባኤ ጎን ባካሂዱት የአራትዮሽ ስብሰባ፤ በአፍሪካ ቀንድና የቀይ ባህር ደህንነት ላይ የጋራ መግለጫ አውተዋል።

አዲስ የሚመሰረተዉ የኢትዮጵያ መንግሥት ሀገሪቱ ከገባችበት ቀዉስ ሊያወጣ የሚችል መፍትሄን ያገኝ ይሆን? 04.10.2026

የጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ ብልፅግና ፓርቲ፤ አዲስ መንግሥት የሚመሰርተዉ፤ ሰሜን ኢትዮጵያ ዉስጥ በአዲስ ጦርነት ተቀሰቀሰ ከተባለ በኃላ ነዉ። ጦርነቱ የጀመረዉ በፌደራል መንግሥት እና በህወሓት፤ የአማራ ፋኖ፤ የኦሮሞ ነጻ አዉጭ ሰራዊትን ጨምሮ 7 አማፂ ኃይላት መንግሥትን ለመጣል የጋራ ጥምረት በመሰረቱ በሁለተኛዉ ቀን መሆኑ ነዉ።

የመብራትና የስልክ መሰረተ ልማቶች በላሊበላ አገልግሎት መስጠት ጀመሩ 03.10.2026

በአማራ ክልል በጦርነቱ ምክንያት ተጎድተዉ የነበሩ የመብራትና የስልክ መሰረተ ልማቶች በላሊበላ አገልግሎት መስጠት ጀመሩ በላሊበላ የነበሩ የውጭ ሀገር ቱሪስቶችን በአየርና በየብስ የማስወጣት ስራዉ ሲቀጥል በደቡብ ወሎ እና አላማጣ አካባቢዎች ደግሞ አዳዲስ ግጭቶችና የሸቀጦች ዋጋ ንረት መከሰታቸው ተመልክቷል።

በኢትዮጵያ እና ኤርትራ መካከል ባገረሸው የዲፕሎማሲ መካረር የህዝብ አስተያየት 03.10.2026

በኢትዮጵያ እና ኤርትራ መካከል የዲፕሎማሲ ግንኙነት መሻከሩን ተከትሎ በሁለቱ አገራት መካከል ጦርነት እንዳያስነሳ ስጋት አሳድሯል፡፡

ጉብኝቱ ኢትዮጵያ የኤርትራ አሥር፣ የግብጽ አንድ ዲፕሎማቶች በ48 ሰዓታት ከሀገር እንዲወጡ ትዕዛዝ በሰጠች ማግስት የተደረገ ነው 03.10.2026

የአፍሪካ ቀንድ ቀጣና በዓለም አቀፍ የግንኙነት መርህ ጉልህ የዲፕሎማሲ እርምጃዎች የተስተዋሉበት ሳምንት እያሳለፈ ነው።የኤርትራው ፕሬዝዳንት ኢሳይያስ አፈወርቂ ቀይ ባሕርን፣ የአደንና የአረብ ባህረ-ሰላጤን እንዲሁም የናይል ተፋሰስን ያካተተውን ቀጣና በሚመለከቱ ጉዳዮች ለመወያየት ዛሬ ጥዋይ ካይሮ ገብተዋል።

በመቐለ የተፈጸመው ከፍተኛ ዝርፊያና የስምረት ፓርቲ መግለጫ 03.10.2026

ሕዝቡ በህወሓት አገዛዝ ከፍተኛ በደል ሲደርበት እንደነበረ የገለጹት አቶ ሓለፎም «ይሁን እንጂ አጥፊዎች መጠየቅ ያለባቸው በሕግ ቻ ነው፤ሕዝቡ ልጆቹን በኃይል ለውትድርና ሲወስዱበት የነበሩ በየደረጃው ያሉ አመራሮችን የዘፈቀደ የበቀል እርምጃ መውሰድ አይገገባም» ብለዋል።

የኢሬቻ ሆራፊንፊኔ በዓል አከባበር 03.10.2026

ዛሬ መስከረም 23 ቀን 2019 ዓ.ም. በመዲናዋ አዲስ አበባ ኢሬቻ ሆራ-ፊንፊኔ በዓል ለተከታታይ 8ኛ ጊዜ ተከብሮ ውሏል፡፡በበዓሉ ላይ የታደሙ ተሳታፊዎች ለዶይቼ ቬለ በሰጡት አስተያየት ሰላምና እና አንድነትን አጉልተው አንስተዋል።

የኢሬቻ በዓል ታዳሚዎች የሰላም ጥሪ 03.10.2026

ዛሬ በአዲስ አበባ የተከበረው የኢሬቻ ሆራ ፊንፊኔ በዓል በሠላም መከበሩን የከተማው የተቀናጀ የጸጥታ ግብረ ኃይል ገለፀ። ዾቼ ቬለ ያነጋገራቸው የክብረ በዓሉ ታዳሚዎች በዓሉን ማክበራቸው የፈጠረላቸው ደስታ እንዳለ ኾኖ፣ በሰሜን ኢትዮጵያ የተቀሰቀሰው ጦርነት በንግግር እንዲፈታ እና የእርስ በርስ ግጭት እንዲቆም ጠይቀዋል።

የኢሬቻ በዓልና የፀጥታ ቁጥጥር በአዲስ አበባ 02.10.2026

የዘንድሮዉ በዓል የሚዉለዉ ቢሾፍቱ ዉስጥ በ2009 በተከበረዉ በዓል ላይ የያኔዉን የኢትዮጵያ መንግሥት በሚቃወሙ የኦሮሞ ወጣቶች (ቄሮ)ና በፀጥታ አስከባሪዎች መካከል በተፈጠረ ግጭትና መረጋገጥ በርካታ ታደሚዎች በሞቱ በአሥረኛዉ ዓመት ነዉ።

ኢትዮጵያ፣ ኤርትራ እና ግብጽ - ከባዱ የዲፕሎማሲ 'ርምጃ ልውውጥ 02.10.2026

ኢትዮጵያ ከኤርትራ እና ግብጽ ጋር ባላት ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ጉልህ መነጋገሪያ የሆኑና በሁለቱ ሀገራት ፈጣን የአፀፋ 'ርምጃ ያስከተሉ ውሳኔዎችን ትናንት ሐሙስ መስከረም 21 ቀን 2019 ዓ.ም አሳልፋለች።

ጦርነት በሲቪሎች ላይ ያደረሰው ሞት፣ መፈናቀልና የደቀነው ሰብአዊ ቀውስ 02.10.2026

የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት እና መንግሥትን በኃይል ለመጣል ጥምረት መሰረትን ያሉት ኃይላት ጋር ከባድ አዉደ ውጊያ እየተደረገበት ነው በሚባለው የአላማጣ ግንባር፣ ከቆቦ እስከ ኩኩፍቱ 96 ሰዎች መገደላቸውን፣ ከነዚህም 52ቱ በአላማጣ ከተማ የተገደሉ መሆናቸውን የአካባቢው ነዋሪዎች ትናንት ለዶቸ ቬለ ተናግረዋል

የአፍሪቃ ሕብረት በኢትዮጵያ፣ ኤርትራና ግብፅ መካከል እየተባባሰ የመጣው ውጥረት እንዲረግብ ጥሪ ቀርቧል። 02.10.2026

ሐሙስ መስከረም 21 ቀን 2018 ዓ,ም ኢትዮጵያ አስመራ የሚገኝ ኤምባሲዋን በመዝጋት አዲስ አበባ ያሉ 10 የኤርትራ ዲፕሎማቶች በ48 ሰዓታት ከሀገር እንዲወጡ ትዕዛዝ አስተላልፋለች። በአፀፋዉ ኤርትራም ከኢትዮጵያ ጋር የነበራትን የዲፕሎማሲ ትስስር በሙሉ ማቋረጧን አስታውቃለች። የአፍሪቃ ሕብረት እየተባባሰ የመጣው ውጥረት እንዲረግብ ጥሪ ቀርቧል።

ለኢሬቻ በዓል አከባበር የተደረገው የጸጥታ ዝግጅት 02.10.2026

ነገ ቅዳሜ አዲስ አበባ ውስጥ የሚከበረውን የኢሬቻ ሆራ ፊንፊኔ እና እሑድ ደግሞ በቢሾፍቱ የሚከበረውን ኢሬቻ ሆራ ሀርሰዲ በሰላም እንዲጠናቀቁ አስፈላጊው የፀጥታ ቅድመ ዝግጅት መጠናቀቁ እየተገለጸ ነው።

ኢትዮጵያ ዉስጥ የተቀጣጠለዉ ጦርነት እንዲቆም የአዲስ አበባ እናቶች ጠየቁ 02.10.2026

አብዛኞቹ አነስተኛና መካከለኛ ገቢ ያላቸው የከተማዋ ነዋሪዎች፣ የዕለት ተዕለት ገቢያቸው ከፍ ካለው የኑሮ ውድነት ጋርሊጣጣምላቸው አልቻለም። ይህ ደግሞ በቤተሰብ የምግብ ዋስትና እና በልጆች የአመጋገብ ሁኔታ ላይ ቀጥተኛ ስጋት ደቅኗል።

ቃለ መጠየቅ፣ ኢትዮጵያ፣ ስምምነት ከሸፈባት፤ አዲስ ጦርነት ተጫረባት መፍትሔዉ ታገኝ ይሆን? 01.10.2026

አቶ ያሬድ እንደሚሉት አዲሱ ጦርነት እስከተጫረበት ጊዜ ድረስ የተደረጉት ሥምምነት፣ ድርድር፣ ሽምግልናና ዲፕሎማሲዎች የከሸፉት የኢትዮጵያን ተጨባጭ ሁኔታ በትክክል ተረድቶ መፍትሔ ለማቅረብ የሚችል ኃይል አለመኖር አንዱ ምክንያት ነዉ።«ሌለኛዉ ምክንያት ሐገሪቱ መዋቅራዊ ችግር ያለባት መሆንዋ ነዉ»

በአዲስ አበባ ስለተሰሙት ፍንዳታዎች ምን ይታወቃል? 01.10.2026

በአዲስ አበባ በሦስት የተለያዩ ቦታዎች ፍንዳታዎች እንደነበሩ አንድ ስማቸው እንዳይገለጽ የጠየቁ የኢትዮጵያ የስለላ መሥሪያ ቤት ባለሥልጣን እንደተናገሩ አሶሼትድ ፕሬስ ዘግቧል። በዋና ከተማዋ ፍንዳታ መሰማቱ የተገለጸው በአዲስ አበባ ድሮን ለማብረር ፈቃድ እንደማይሰጥ የኢትዮጵያ የስለላ መሥሪያ ቤት ባሳወቀ በሰዓታት ልዩነት ነው።

በሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት አላማጣ ግንባር ከቆቦ እስከ ኩኩፍቶ 96 ሰላማዊ ሰዎች መገደላቸውን ነዋሪዎች ተናገሩ 01.10.2026

ከባድ ውጊያ እየተደረገበት በሚገኘው የአላማጣ ግንባር ከቆቦ እስከ ኩኩፍቱ 96 ሰዎች መገደላቸውን የአካባቢው ነዋሪዎች ለዶቸ ቬለ ተናገሩ። በአላማጣ ከተማ ብቻ 52 ሰዎች ተገድለዋል። ከከባድ መሣሪያ ለመሸሽ የሞከሩ አምስት ሕጻናት አፉኝት የተባለ ወንዝ ወስዷቸው ህይወታቸውን አጥተዋል።

በሰሜን ኢትዮጵያ ዳግም የተቀጣጠለው ጦርነት በአፋር ክልል ያደረሰው ጉዳት 01.10.2026

በአፋር ክልል በኩል እየተደረገ በሚገኘው ውጊያ መከላከያ ሠራዊትና የአፋር ክልል ልዩ ኃይል ኤረቢቲ እና አብአላን እንዳስለቀቁ የአካባቢው ነዋሪ እና የአፋር ሰብዓዊ መብቶች ድርጅት ኃላፊ ተናግረዋል። በአፋር በኩል በሚገኙ አውደ ግምባሮች ባለፉት ሦስት ቀናት ከባድ ውጊያ ሲደረግ ነበር።

እስራኤል 45 ዜጎቿን ከሰሜን ኢትዮጵያ የጦርነት ቀጣና አስወጣች 01.10.2026

እስራኤል ወታደራዊ ግጭት እየተካሄደበት ከሚገኘው ሰሜን ኢትዮጵያ 45 ዜጎቿን ማስወጣቷ ተገለፀ። የእስራኤል የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በጉብኝት ላይ ነበሩ ያላቸው ዜጎቹ ግማሹ በሄሊኮፕተር ቀሪዎቹ በመከላከያ ሠራዊት እጀባ በተሽከርካሪ እንዲወጡ ተደርጓል። ዶቼ ቬለ መረጃው ተጨባጭ ስለመሆኑ ኢትዮጵያ ውስጥ ከሚገኘው የእስራኤል ኤምባሲ አረጋግጧል።

በትግራይ የተከፈቱ የባንክ ሒሳቦች ዕግድ “ትልቅ ጥሰት ነው” ቅድሚያ ለሰብአዊ መብቶች ኢትዮጵያ 30.09.2026

በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የትግራይ ክልል ቅርንጫፎች የተከፈቱ የባንክ ሒሳቦች ዕግድ “ትልቅ ጥሰት ነው” የሚል አቋም እንዳላቸው የቅድሚያ ለሰብአዊ መብቶች ኢትዮጵያ ዋና ዳይሬክተር ተናግረዋል። እርምጃው በትግራይ እና ከክልሉ ውጪ የሚገኙ ደንበኞች ገንዘባቸውን ማንቀሳቀስ እንዳይችሉ አድርጓል። ይህ የዕለት ተዕለት ወጪዎችን ለመሸፈን ችግር ፈጥሯል።

Listen to the DW | Amharic - News podcast in Replaio

Radio and podcasts in one app - free, with no sign-up. Install today and do not miss the launch

Get it on Google Play

Replaio is not a podcast publisher; show names, artwork and audio belong to their authors and are distributed through public RSS feeds.