DW | Amharic - News
News, Analysis and Service from Germany and Europe - in 30 Languages
Be sure to visit the podcast's website and support the creator: www.dw.com
Where to listen?
Podcasts in the app Replaio Radio Coming soonPodcasts are coming to the app soon. Install now and be the first to see a whole new take on podcasts
Episodes
ዳግም የተቀጣጠለው ጦርነት ለቀጣናው ስጋት ይሆን? 30.09.2026
በሰሜን ኢትዮጵያ ከመስከረም 12 ቀን 2019 ዓ.ም. ጀምሮ ዛሬ ስምንተኛ ቀኑን የደፈነው ዳግም የተቀሰቀሰው ጦርነት ዛሬም ድረስ እንደቀጠለ ነው።
የሕዝብ መገናኛ ብዙኃን ስላገረሸው ጦርነት ምን ያህል ለሕዝብ መረጃ እየሰጡ ነው? 30.09.2026
ሰሞኑን ዳግም የተቀሰቀሰው የሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት ከመጀመሩ አስቀድሞ፣ የሕዝብ በሚባሉት መገናኛ ብዙኃን እና ህወሓት በሚቆጣጠራቸው መገናኛ ዐውታሮች መካከል ግልፅ መወነጃጀል፣ መካሰስ እና መወጋገዝ በሥፋት ይስተናገድባቸው ነበር።
ጎብኙዎቿ ቁጥር የቀነሰው ላሊበላ ያገረሸው ጦርነት ያስከተለባት ስጋት 30.09.2026
ከኮቪድ-19 ወረርሽኝና ከሰሜኑ ጦርነት ወዲህ በላሊበላ አካባቢ በቀጠለው ግጭትና የበረራ መቋረጥ ምክንያት የቱሪስት ቁጥር በመቀነሱ፣ የአስጎብኚዎችና የሆቴል ባለቤቶች የኑሮ መሠረትና ህልውና አደጋ ላይ ወድቋል።
የኢትዮጵያ የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሐኑ ጁላ ኤርትራ፣ ሱዳንና ግብፅ ህዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት)ን ይደግፋሉ በማለት በቅርቡ ወንጅለዉ እንደነበር የሚታወስ ነዉ። 30.09.2026
ሁለቱ የኤርትራ መንግሥት ተቃዋሚ ሁለት የአፋር ድርጅቶች፤ የኤርትራ መንግሥት ጦር ሰራዊት የኢትዮጵያን ድንበር ዘልቆ መግባቱን አስታወቁ። ሁለቱ ድርጅቶች በየተናጠል ይፋ ባደረጉት መግለጫ፤ ኤርትራ በኢትዮጵያ ጉዳይ ጣልቃ ገብታለች፤ በሃገሪቱ ዉስጥ ያለዉን ግጭትንም በማባባስ ጉዳይ እጅዋ አለበት ሲሉ ከሰዋል።
የሰው ሠራሽ አስተውሎት ከቁጥጥር ውጭ ሊሆን ይችላል ? 30.09.2026
የሰው ሠራሽ አስተውሎት (AI)፣ የሰው ልጆች ህልውና ላይ አደጋ ጋርጧል። ቴክኖሎጂው የሰው ልጆችን በማገዝ ኑሮን በማቅለል እየተወደሰ ባለበት ሁኔታ የዕድገቱ ግስጋሴ አሳሳቢ ሆንዋል።
አሳሳቢው የሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት ዳግም ቀጥሏል፥ የዶይቸ ቬለ የቀጥታ ጡመራ (Live Blog) ዘገባ 30.09.2026
ውድ ተከታታዮቻችን! በኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት እና በአጭሩ «ትብብር ለሕልውና» በተባለው ጥምረት መካከል መስከረም 12 ቀን፣ 2019 ዓ.ም የጀመረው ጦርነት በተለያዩ ከተሞች እየተጠናከረ መኾኑ ተዘግቧል ። በዚህ የቀጥታ ጡመራ (Live Blog) ዘገባ ጦርነቱን በተመለከተ ዶይቸ ቬለ አዳዲስ መረጃዎችን ለእናንተ ያቀርባል ።
የዩናይትድ ስቴትስ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማርኮ ሩቢዮ በኢትዮጵያ የበረታውን ውጥረት ለማርገብ እርምጃ እንዲወስዱ የአሜሪካ ሴናተሮች ጥሪ አቀረቡ 29.09.2026
የአሜሪካ ሴናተሮች ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ እና ህወሓት በኢትዮጵያ የተፈጠረውን “ውጥረት የሚያረግቡ እርምጃዎች መውሰድ” እንዳለባቸው አሳሰቡ። የተባበሩት መንግሥታት እና የአፍሪካ ኅብረት የሰላም እና ደሕንነት የጋራ ግብረ ኃይል በኢትዮጵያ የተቀሰቀሰውን ግጭት አንዳች “የተሳሳተ ስሌት” የበለጠ እንደሚያባብስ አስጠንቅቋል።
የሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት ሲቀሰቀስ የኮረም፣ አላማጣና ሽሬ ሆስፒታሎች ከ720 በላይ በጦርነት የቆሰሉ ሰዎች መቀበላቸውን ድንበር የለሽ የሐኪሞች ቡድን ገለጸ 29.09.2026
በኮረም፣ አላማጣ እና ሽሬ የሚገኙ ሆስፒታሎች በድምሩ ከ720 በላይ በጦርነት የቆሰሉ ሰዎች የሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት ከተቀሰቀሰበት ቀን ጀምሮ ባሉት ጥቂት ቀናት መቀበላቸውን ድንበር የለሽ የሐኪሞች ቡድን ገለጸ። ድርጅቱ የሰሜን ኢትዮጵያ “ወቅታዊ ሁኔታ እጅግ አሳሳቢ” ደረጃ ላይ እንደሚገኝ አስጠንቅቋል።
ዉይይት፣ የኢትዮጵያ የአዲስ መንግሥት ምሥረታ ዝግጅትና የጦርነት እልቂት 27.09.2026
በኢትዮጵያ ፌደራላዊ መንግሥትና በህዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) መካከል የሚደረግ ያሉት ጦርነትን ሥለጀመረዉ ወገን ማንነት ተፋላሚ ኃይላት አንደሚጠበቀዉ አንዳቸዉ ሌላቸዉን እየወነጀሉ ነዉ።ዉጊያዉ ግን ቀጥሏል
በኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊትና በትግራይ ኃይሎች መካከል በዛሬው እለት በተለያዩ ግንባሮች ከባድ ውጊያ መካሄዱን የፈረንሳይ ዜና አገልግሎት ዘገበ 25.09.2026
በፌደራል መንግሥት እና በትግራይ ኃይሎች መካከል ሦስት ቀናት ያስቆጠረዉ ውጊያ በትግራይ ክልልና በአማራ ክልል አንዳድ ከተሞች የኢንተርኔት እና የስልክ አገልግሎት ዛሬ አርብ መታጎሉን ተጠቃሚዎች አስታዉቀዋል። የሰሜን ኢትዮጵያዉ ጦርነት የሚያስከትለዉ ሰብዓዊ ቀዉስ ምን ሊሆን ይችላል?
ኢትዮጵያ ዉስጥ የተቀሰቀሰው ጦርነት ኤርትራን እና ሱዳንን ያሳትፍ ይሆን? 25.09.2026
ህወሓት ብቻ ሳይሆን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የሚመሩትን ፌድራል መንግሥት የማስወገድ ዓላማ ካነገበው “ትብብር ለሕልውና” ጥምረት መሥራቾች መካከል የተወሰኑት በአንድም ይሁን በሌላ መንገድ ከኤርትራ ጋር ግንኙነት ነበራቸው። ጥምረቱ በተመሠረተ በቀናት ልዩነት የተቀሰቀሰው ውጊያ ኤርትራ እና ሱዳንን ሊያሳትፍ ይችላል የሚል ሥጋት አለ።
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ላሊበላ የሚደረጉ በረራዎች መሰረዙ ተዘገበ 24.09.2026
በአማራ ክልል በምትገኘው ላሊበላ ከተማ ዛሬ ሐሙስ “በአራቱም አቅጣጫ እየተተኮሰ” እንደነበር አንድ የከተማው ነዋሪ ለዶቸ ቬለ ተናግረዋል። በከተማዋ የሚገኙት አብያተ ክርስቲያናት በከባድ መሣሪያ ጉዳት ሊደርስባቸው ይችላል የሚል ሥጋት አለ። የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ላሊበላ የሚያደርጋቸውን በረራዎች እንዳቋረጠ ሬውተርስ ዘግቧል።
የአውሮፓ ኅብረት በኢትዮጵያ የተቀሰቀሰውን ጦርነት “በአፋጣኝ ማርገብ” እንደሚያስፈልግ አሳሰበ 24.09.2026
የአውሮፓ ኅብረት “በበርካታ አካባቢዎች የሚደረጉ ወታደራዊ እንቅስቃሴዎችን” ጨምሮ “በፍጥነት እያሽቆለቆለ የሚገኘው” የሰሜን ኢትዮጵያ ሁኔታ “በጥልቅ” እንደሚያሳስበው ሥጋቱን ገልጿል። ኅብረቱ የኢትዮጵያ ፌድራል መንግሥት እና ህወሓት ወደ ተፈራረሙት ግጭት የማቆም ሥምምነት ለመመለስ “ጊዜው አልረፈደም” የሚል አቋም አለው።
በትግራይ ክልል በሰው አልባ አውሮፕላን «ተከታታይና የተጠናከረ» ጥቃት መኖሩን ህወሓት መግለፁ 09.09.2026
በትግራይ ክልል በተለይ ካለፉት ሦስት ሳምንታት ወዲህ በሰው አልባ አውሮፕላን (ድሮን) «ተከታታይ እና ተጠናክሮ የቀጠለ» ጥቃት እየተፈፀመ መኾኑን ህወሓት ገለፀ። የድርጅቱ ቃል ዐቀባይ እንዳሉት የድሮን ጥቃቶቹ በሰዎች መኖሪያ ቤቶች፣ በትምህርት ቤቶች፣ በአርሶ አደር መንደሮች እና ንጹሐን ሰዎች በሚኖሩበት አካባቢ ነው።
በአቤዶንጎሮ ወረዳ በግጭት ምክንያት የተፈናቀሉ ዜጎች ቅሬታ 25.08.2026
በምዕራብ ኦሮሚያ ባለፉት 3 ዓመታት በሆሮ ጉዱሩ ወለጋ ዞን አቤዶንጎሮ እና አሙሩ ወረዳ፣ ከምስራቅ ወለጋ ዞን ደግሞ ኪረሙ እና ጊዳ አያና ወረዳዎች ከፍተኛ ሰብአዊ ጉዳት የደረሰባው ወረዳዎች ናቸው፡
የግብፅ የህዳሴ ግድብ ውንጀላና የኢትዮጵያዊው ባለሙያና ተደራዳሪ ምላሽ 22.07.2026
የግብፅ ውጭ ጉዳይ ሚኒስተር ግብፅና ሱዳን ስለህዳሴ ግድብ የደህንነት ደረጃ ወይም አካባቢያዊ ተጽዕኖ የደረሰን የጥናት ውጤት የለም ብለዋል። የሕዳሴ ግድብ የኢትዮጵያ ተደራዳሪ ቡድን አባልና በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የሃይድሮ ፖለቲክስ ተመራማሪ ፕሮፌሰር ያዕቆብ አርሳኖ ግን የግብፅ አስተያየት የተለመደና በመረጃ ላይ ያልተመሰረተ መኾኑን ይናገራሉ።
አሜሪካ ፤ኢራን የሆርሙዝ ጥቃቶችን ለማስቆም በይፋ ቃል እንድትገባ መፈለጓን ባለስልጣናት ገለፁ 11.07.2026
ዋሽንግተን ቴህራን በሆርሙዝ ስትራቴጂካዊ የባህርት ወሽመጥ ላይ በሚጓዙ መርከቦች ላይ የሚሰነዘሩትን ጥቃቶች ለማስቆም በይፋ ቃል እንድትገባ መፈለጓን ዘገባዎች አመልክተዋል። በሌላ በኩል ዶናልድ ትራምፕ ኢራን እሳቸውን ለመግደል ከሞከረች ሀገሪቱን ሙሉ በሙሉ እንደሚያወድሟት ዝተዋል።1000 ሚሳይሎች ወደ ኢራን አነጣጥረው ተቀምጠዋል። ሲሉም ዝተዋል።
ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ወቀሳ የህወሓት ምላሽ 10.07.2026
ሕወሓት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ከኤርትራና ሱዳን ጋር በመስራት ያቀረቡበትን ክስ አጣጣለ ። ፓርቲው ምላሹን የሰጠው ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ፤ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የማጠቃለያ መድረክ ላይ ባደረጉት ንግግር ሕወሓት፣ ኤርትራ እና ሱዳንን የኢትዮጵያን መንግስት ለመዋጋት ተጣምረዋል በማለት በጠንካራው መተቸታቸውን ተከትሎ ነው፡፡
የኢሰመኮ የአምስት ዓመት ዕቅድ የመብት ጥሰቶችን ይቀንስ ይሆን? 10.07.2026
ኢትዮጵያ ውስጥ «ግጭት፣ የፀጥታ ችግርና መፈናቀል፣ ሕገ ወጥ የሲቪል ሰዎች ግድያ እና የአካል ጉዳት፣ የዘፈቀደ እና የተራዘመ እስር» የሰብአዊ መብት ጥበቃ ሥጋት ሆነው እንደሚቀጥሉ የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን ገለጠ። በሰብአዊ መብት ጥበቃ ላይ የሚሠራ አንድ ሀገር በቀል ሲቪክ ድርጅት የኢሰመኮን ሥጋት እንደሚጋራ ጠቅሷል ።
በአፍሪቃ የሚካሄዱ ምርጫዎች ዳያስፖራውን ማሳተፍ እንደለባቸው ተገለፀ 10.07.2026
የዳያስፖራ አባላት የብሔራዊ ምርጫ ተሳትፎ በተለያዩ የአፍሪካ ሃገራት ያለበት ደረጃ ተመሳሳይ አለመኾኑን የገለፀው የአፍሪካ ኀብረት፣ አባል ሃገራት ቁርጠኝነት እንዲያሳዩ ጥሪ አቅርቧል። በርካታ ሃገራት በተለያዩ የውጭ ሃገራት የሚገኙ ዜጎቻቸው በምርጫ እንዲሳተፉ የሚያስችሉ የሕግ ማሻሻያዎች ማድረጋቸውን ገልፀዋል።
በአርሲ አሰኮ በግጭት የተፈናቀሉ ነዋሪዎች የድጋፍ ጥያቄ 10.07.2026
በኦሮሚያ ክልል አርሲ ዞን አሰኮ ወረዳ በተለያዩ ቀበሌዎች ግንቦት 23 እና 24 ቀን፣ 2018 ዓ.ም በተፈጸመ ጥቃት የተፈናቀሉ ነዋሪዎች በርዳታ አቅርቦቶች መቋረጥ መቸገራቸውን ገለጹ። ተፈናቃዮቹ በጥቃቱ ወቅት በደረሰባቸው የቤት ቃጠሎና የንብረት ውድመት ወደ መኖሪያቸው ቀየያቸው ለመመለስም ከፍተኛ ድጋፍ እንደሚያስፈልጋቸው ተናግረዋል ፡፡
በእሥር ላይ ስለሚገኙ ፖለቲከኞች መፈታት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ የሰጡት ፍንጭ 10.07.2026
የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በልዩ ልዩ ፖለትካዊ ምክንያቶች በእሥር ላይ የሚገኙ ኢትዮጵያዊያን ከእሥር ሊለቀቁ የሚችሉበት ዕድል ስለመኖሩ ፍንጭ ሰጡ። መንግሥታቸው "የሃይማኖት አባቶችን እና ትልልቅ ሰዎችን" ተጠቅሞ "በተቻለ መጠን በእሥር ላይ ያሉ ሰዎችን ለመፍታት" ፍላጎት እንዳለው ጠቁመዋል ።
አንድነት ላይ ያተኮረው የኔቶ ጉባኤ 10.07.2026
በዚህ ሳምንት ለሁለት ቀናት አንካራ ቱርክዬ ላይ የተካሄደው የሰሜን አትላንቲክ የጦር ቃል ኪዳን (ኔቶ) ጉባኤ የአባላቱ አንድነት አሁንም እንዳለ መሆኑን ለማሳየት ያለመ እንደነበር ነው ተንታኞች የሚናገሩት።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ “ጦርነት ሊቀሰቅሱ የሚችሉ ትንኮሳዎች በየጊዜው ትግራይ ባሉ ኃይሎች ይፈጸማል” ሲሉ ከሰሱ 07.07.2026
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ “ጦርነት ሊቀሰቅሱ የሚችሉ ትንኮሳዎች በየጊዜው ትግራይ ባሉ ኃይሎች ይፈጸማል” ሲሉ ወንጅለዋል። ዐቢይ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በሰጡት ማብራሪያ በገደምዳሜ ስለ ጽምዶ ጠቀስ አድርገዋል። ይሁንና ህወሓት፣ ኤርትራና ሱዳን ቢተባበሩ እንኳ ለኢትዮጵያ “ሉዓላዊነት ቅንጣት ታክል ሥጋት” እንደማይሆኑ ገልጸዋል።
እንወያይ፤ የትግራይ ክልል ቀዉስ ወዴት እያመራ ነዉ? መፍትሔዉስ? 05.07.2026
በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ መንግሥትና በህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ መካከል የሚደረገዉ ዉዝግብና ቁርቁስ አሁንም እንደቀጠለ ነዉ። ህወሓት በፕሪቶርያ ስምምነት መሰረት የተሰየመዉን የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ከተቆጣጠረ ወዲህ ከመንግሥት ጋር የነበረዉ ቂም እየተካረረ መምጣቱ እየተነገረ ነዉ። ህወሓትም ወጣቶችን ለዉትድርና እያስገደደ ነዉ ተብሏል።
Replaio is not a podcast publisher; show names, artwork and audio belong to their authors and are distributed through public RSS feeds.