DW | Amharic - News

News, Analysis and Service from Germany and Europe - in 30 Languages

Be sure to visit the podcast's website and support the creator: www.dw.com

Category

Uncategorized

Podcast website

www.dw.com

Latest episode

Nov 22, 2026

Where to listen?

Podcasts in the app Replaio Radio Coming soon

Podcasts are coming to the app soon. Install now and be the first to see a whole new take on podcasts

Get it on Google Play Install for free Android 10M+ downloads · 4.7+ rating iOS soon

Episodes

ጠቅላይ ሚንስትሩ በአርባምንጭ የኮንፈረንስ ሪዞርት ምረቃ ላይ ምን አሉ? 04.07.2026

በአርባ ምንጭ ሪዞርት የመረቁት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ “አላስፈላጊ ሽኩቻ ከልማት እንዳያስቀረን” ሲሉ ተደምጠዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ቱሪዝም የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ኹነኛ ምሰሶ እንዲሆን ፍላጎት እንዳላቸው በተደጋጋሚ ገልጸዋል። ዶይቼ ቬለ ያነጋገራቸው የቱሪዝም ባለሙያ ግን የጸጥታ ችግሮችን በማስወገድ ሰላም ማስፈን እንደሚያስፈልግ ተናግረዋል።

በሆሮ ጉዱሩ ወለጋ አሙሩ ወረዳ ታጣቂዎች በከፈቱት 13 ሰዎች ገደሉ 02.07.2026

አስተያየታቸውን ለዶይቼ ቬለ የሰጡ የከተማዋ ነዋሪዎች እንደሚሉት ጥቃቱን የከፈቱት በአጎራባች ወረዳ ኪረሙ እና በዙሪያው በሚንቀሳቀሱ ታጣቂዎች ናቸዉ፡፡

የዐቢይ መንግሥት ለኢትዮጵያ ሕዝብ “መጥፎ” በተባለ ሥምምነት ወደ ንግድ ብድር ሊመለስ ነው? 01.07.2026

ውድ ወለድ የሚከፈልባቸው የንግድ ብድሮች እንዳቆሙ በተደጋጋሚ ምለው የሚገዘቱት የኢትዮጵያ ባለሥልጣናት ቃላቸው የሚፈተንበት ሥምምነት ከቦንድ ባለቤቶች ጋር አድርገዋል። ሥምምነቱ ኢትዮጵያ እስከ 9% ወለድ የሚከፈልበት ቦንድ እንድታወጣ የሚያደርግ ነው። ኢትዮጵያ ቦንዱን ካላወጣች ለግል አበዳሪዎቿ እስከ 90 ሚሊዮን ዶላር ለመክፈል ትገደዳለች።

ማሕደረ ዜና፣ የ7ኛዉ አጠቃላይ ምርጫ ዉጤት፣ እድምታዉና የኢትዮጵያ ተጨባጭ ሁኔታ 22.06.2026

በኢትዮጵያ የቅርብ ይሁን የሩቅ ዘመን ታሪክ የተደረጉ ለዉጦች በሙሉ የተደረጉት በምርጫ ሳይሆን በቤተ መንግሥት ሴራ፣ በመፈንቅለ መንግሥት፣በጦርነትና በሕዝባዊ አመፅ ነዉ።ምክንያቱ ብዙ ነዉ።ፕሮፌሰር መረረ «መሠረታዊ ችግራችን» የሚሉት ይጠቅሳሉ።

ኢሰመኮ - አርሲ ዞን የተፈፀመዉን ጥቃት ክትትል እና ምርመራ እያደረገ መሆኑን ገለፀ 08.06.2026

በኦሮሚያ ክልል አርሲ ዞን አሰኮ ወረዳ ከሳምንት በፊት የተፈጸመው የንጹሃን ግድያን በተመለከተ መንግሥት ተገቢውን ምርመራ በማካሄድ ተጠያቂነትን እንዲያረጋግጥ የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) አሳሰበ፡፡ ኢሰመኮ መንግስት ተጎጂዎችን ለመካስና ለማቋቋም የሚያስችሉ እርምጃዎችን ሊወስድ ይገባልም ብሏል፡፡

ዉይይት፤ ቅድመ ምርጫ፣ ምርጫ እና ድኅረ ምርጫ በጋዜጠኞች ዕይታ 07.06.2026

ባሳለፍነው ሳምንት መጀመሪያ በኢትዮጵያ 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ተካሂዷል። ግንቦት 24 ቀን 2018 ዓ.ም. በተካሄደው በዚህ ምርጫ ፤ዋዜማው፣ የምርጫው ዕለት እና ድህረ ምርጫ በጋዜጠኞች ዕይታ ምን ይመስላል።?7ኛውን ጠቅላላ ምርጫ፤ ከዘገቡ የዶቼ ቬለ ጋዜጠኞች መካከል አራቱን አነጋግረናል።

መንግስት አፋጣኝ ጸጥታን በማስከበር ዘላቂ መረጋጋት እንዲያመጣ ተጠየቀ 05.06.2026

ዘጠኝ ሲቪል ዜጎች እና ሁለት የመንግስት ጸጥታ ሃይሎች በደለታ ጨፋ ቀበሌ በእሁድ እና ሰኞው ጥቃት መገደላቸውን የሚያረጋግጡት አስተያየት ሰጪው የግጭቱ ሰለባ፤ አሁን ላይ በርካታ ዜጎች በሱንቴ ቅድስት ማሪያም እና እሬቻ ቅዱስ ሚካኤል ቤትክርስቲያን እንደተጠለሉ ናቸው ብለዋል፡፡

ስለ መገናኛ ብዙኃን ምኅዳር የመንግሥት፣ የባለሙያዎች እና አጥኚዎች ዕዉነት 08.05.2026

ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ "ባለፉት 8 ዓመታት የመገናኛ ብዙኃን ምኅዳሩን በዲሞክራሲያዊ አውድ ለመዋጀት መንግሥታቸው በወሰደው"ርምጃ ለሀገር ግንባታ የሚረዳ መሠረት መጣሉን ገልፀዋል። IMS በጥናቱ 2025 ዓ.ም. በኢትዮጵያ በመገናኛ ብዙኃን ባለሙያዎች ላይ "ሰፊ እሥራቶች፣ አፈናዎችና ትንኮሳዎች የተጋረጡበት ወቅት ተብሎ ሊገለጽ ይችላል" ብሎ ነበር

በአርሲ ዞን ሮቤ ዲዳዓ ወረዳ በንጹሐን ላይ የተፈጸመው ጥቃት 24.04.2026

በኦሮሚያ ክልል አርሲ ዞን ሮቤ ዲዳዓ ወረዳ ባሳለፍነው ሰኞ ሚያዚያ 12 ቀን 2018 ዓ.ም. አንድ የቤተ ክርስቲያን አገልጋይ ከሁለት ወንድሞቻቸው ጋር ባልታወቁ ታጣቂዎች መገደላቸውን ቤተሰቦች እና የቤተክስቲያን አገልጋዮች ገለጹ።

በአማራ ክልል ያለው የነዳጅ ዘይት እጥረትና ድብቅ ገበያ 25.03.2026

ነዳጅ ከማደያዎች ውጪ በሊትር ደሴ 350 ብር፣ በዳባት 900 ብር መሸጡን አሽከርካሪዎች ለዶይቼ ቬለ ተናግረዋል። በጎንደር እና ባሕር ዳር በነዳጅ ማደያዎች ለወረፋ ከ2,000 እስከ 10,000 ብር የተከፈለባቸው ቀናት አሉ። በአማራ ክልል የነዳጅ እጥረት እና የዋጋ ለውጥ በግብርና እና በኢንዱስትሪ ምርቶች መሸጫ ላይ ጭማሪ አስከትሏል።

እንወያይ፤ የነጻ ፕሬስ እና የጋዜጠኞች ፈቃድ መሰረዝ ተጽኖ በኢትዮጵያ 08.03.2026

ኢትዮጵያ ሰባተኛዉን አገራዊ ምርጫ ለማካሄድ ሽር ጉድ እያለች ባለችበት በአሁኑ ወቅትም ይሁን አስቀድሞ ጥቂት የማይባሉ የመገናኛ ብዙኃን ባለሞያዎች እና ጋዜጠኞች እንዲሁም በአመዛኙ "ነጻ" የሚባሉ ብዙኃን መገናኛ ዐውታሮች ፈቃዳቸው እየተሰረዘ፣ ጋዜጠኞቻቸውም የሥራ ፈቃዳቸዉን እየተነጠቁ ነዉ።

በኢትዮጵያ ሀሳብን የመግለጽ ነጻነት ሠፋ ወይስ ጠበበ? 23.02.2026

ሀሳብን የመግለጽ ነጻነት፤ የሚዲያ አስተዳደር እና ቁጥጥር በኢትዮጵያ" በሚል ርዕስ 3ኛውን የፖሊሲ ዉይይት በሀዋሳ ከተማ ተካሄደ ፡፡ የሀዋሳ ዪኒቨርሲቲ ባዘጋጀው በዚሁ መድረኩ ላይ በዘርፉ የሚታዩ ተግዳሮቶችና የመፍትሄ አማራጮች ተነስተው ውይይት ተደርጎባቸዋል፡፡ በኢትዮጵያ ሀሳብን የመግለጽ ነጻነት ሠፋ ወይስ ጠበበ?

“ታላቁ ሕዳሴ ግድብ ከቀዳሚ አጀንዳዎቼ አንዱ ነው” ዶናልድ ትራምፕ 17.01.2026

የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ የአባይ ውሃ ባለድርሻነት ለዘለቄታው እልባት እንዲያገኝ በሚል፤ ግብጸጽ እና ኢትዮጵያን ዳግም ወደ ድርድር ለስገባት አገራቸው አሜሪካ ቁርጠኛ መሆኗን አስታወቁ፡፡ትራምፕ ይህንን ያሉት ለግብጹ ፕሬዝዳንት አብዱፈታ አልሲሲ ብለው ትሩዝ ሶሻል በሚባለው የማህበራዊ መገናኛ ዘዲያቸው ላይ ባጋሩት ደብዳቤ ነው።

የግብፅ አስገዳጅ የውኃ ክፍፍል ውል ጥያቄ "የአስተሳሰብ ለውጥ የሚያሻው ነው" - ባለሙያ 22.12.2025

የግብፁ ፕሬዝዳንት አብደል ግብፅ በናይል ውኃ ላይ አለኝ የምትለው መብት በአስገዳጅ የውል ስምምነት እንዲታሰር ተሰምቷል። ኢትዮጵያ በአንፃሩ ይህ ጉዳይ በናይል ተፋሰስ ሀገራት ማዕቀፍ ውስጥ መታየት ያለበትና ከሕዳሴ ግድብ ጉዳይ ያለፈ ሀሳብ መሆኑን በመጥቀስ ፍትሐዊ ክፍፍል መደረግ አለበት በሚል የግብፅን አቋም ውድቅ ስታደርግ ቆይታለች።

በምሥራቅ ወለጋ ኪረሙ ወረዳ ታጣቂዎች ባደረሱት ጥቃት አራት ሰላማዊ ሰዎች ተገደሉ 05.11.2025

በምስራቅ ወለጋ ዞን ኪረሙ ወረዳ በደረሰ የታጣቂዎች ጥቃት 4 ሰላማዊ ሰዎች ተገድለው ሌሎች አራት መቁሰላቸውን ነዋሪዎች ተናገሩ ። ነዋሪዎቹ እንዳሉት ከጥቃቱ በተጨማሪ ታጣቂዎቹ በርካታ የቁም እንስሳት ዘርፈዋል። ስለ ኹኔታው ለዶቼ ቬለ አስተያየየታቸውን ለዶቼ ቬለ የሰጡ ነዋሪዎች የመንስግ የጸጥታ ኃይሎች ሊከላከሉልን አልቻሉም ሲሉ ወቅሰዋል።

ለትግራይ የመንግስት ሰራተኞች ውዝፍ ደሞዝ ክፍያ 20 ቢልዮን ብር ያስፈልጋል መባሉ 05.09.2025

የመንግስት ሰራተኞች ውዝፍ ደሞዝ ለመክፈል 20 ቢልዮን ብር እንደሚያስፈልገው የትግራይ ግዚያዊ አስተዳደር አስታወቀ። ውዝፍ ደሞዝ በአንድ ግዜ መክፈል እንደማይችል የገለፀው ግዚያዊ አስተዳደሩ፥ ከአዲሱ በጀት ዓመት ብያንስ 5 በመቶ በጀት ለውዝፍ ደሞዝ ለመክፈል መወሰኑን ገልጿል።

የፖለቲካ ፓርቲ አባል የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን የቦርድ አባል መሆኑን የሚፈቅድ አዋጅ ፀደቀ 17.04.2025

በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የዴሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አዋጅ ቁጥር 1238/2013 የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን የዕለት ተዕለት ሥራውን እንዳያከናዉን ለተቋሙ ቦርድ የተሰጠው ሥልጣን "የሕግ ክፍተት ያለበት በመሆኑ" እና ያንን ለተቋሙ ሥራ አስፈፃሚ መመለስ አስፈላጊ በመሆኑ ማሻሻል እንዳስፈለገ ገልጿል።

የጋዜጠኞች፣ የሞያ እና የተቋማቱ ደኅንነት በኢትዮጵያ 02.04.2025

ኢትዮጵያ ውስጥ በአንድ ዓመት ጊዜ ውስጥ ብቻ 43 ጋዜጠኞች ተይዘው ለእሥር እና ለአፈና መዳረጋቸውን በጋዜጠኞች ደኅንነት ላይ የሚሠራው የኢንተርናሽናል ሚዲያ ሳፖርት (IMS) ጥናት አመለከተ ። ኢትዮጵያ ውስጥ የቀጠሉ ግጭቶች ጋዜጠኞችን ከመንግሥትም፣ ከታጣቂዎችም ለሚቃጣ እሥር፣ እገታ፣ ማስፈራራት፣ ማዋከብ እና ጥቃት ተጋላጭ አድርጋቸዋል ብሏል ።

በማንነት ላይ ያነጣጠር ጥቃት ቀጥሏል መባሉ 06.12.2023

በኦሮሚያ ክልል በወለጋና በአርሲ ዞኖች ምእመኖቻቸዉ እና አገልጋዮቻቸዉ በታጣቂዎቸ በግፍ እንደተገደሉ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስትያን እና የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ ክርስትያን ገለፁ። ሰሞኑን በኦሮሚያ ክልል በአርሲ ዞን ዘጠኝ ምእመኖች እንዲሁም በቄለም ወለጋ 9 አገልጋዮቿ መገደላቸዉን ተገልጿል።

በኢትዮጵያ እየደበዘዘ ነው የተባለው የሚዲያ ሚና እና ሙያዊነት 12.03.2022

አስተያየታቸውን ለዶይቼ ቬለ የሰጡ የሚዲያ ባለሙያዎች ዘርፉ ለአገር እድገትና ግንባታ የሚጫወተውን ሚና ከፍ ለማድረግ የሙያውን ነጻነት መጠበቅና በመርህ መምራት ይገባልም ነው ያሉት፡፡ 

የኖቤል ሽልማቱ ከሸክም ይልቅ ጌጥ እንዲሆን ምን ይደረግ? 13.12.2019

ኢትዮጵያ በዘመኑ ቋንቋ ስትደመር ስትቀነስ ይኸው ሁለት ዓመት ሊሞላት ነው። ሰሞኑን ብዙ ሰዎች መልሰው የተደመሩበት ሰሞን ነበር። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የኖቤል ሽልማት ሲቀበሉ ከሞላ ጎደል የነበረው ስሜት ጮቤ የመርገጥ ነበር። ስሜቱ ብሔርተኝነት በጣም የተጫነው ስለሆነ ድጋፉ ዘላቂ ይሁን አይሁን ለመገመት ይቸግራል።

ስለ ኖቤል ሽልማቱ ኤርትራዊያን ምን አሉ? 12.12.2019

የኢትዮጵያው ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አህመድ የዓለም የሰላም የኖቤል ሽልማት ተሸላሚ መሆናቸው በኢትዮጵያ እና በኤርትራ መካከል የተጀመረውን ሁሉ አቀፍ ግንኙነት ከተቀዛቀዘበት አንድ እርምጃ ወደፊት ያራምደዋል የሚል እምነት እንዳላቸው በኢትዮጵያ የሚኖሩ ኤርትራዊያን ተናገሩ።

ስለ ዐብይ ሽልማት የዛላምበሳ ነዋሪዎች አስተያየት  12.12.2019

ጠቅላይ ሚኒስቴር አብይ አሕመድን ለኖቤል የሰላም ሽልማት ያስመረጣቸው በኢትዮጵያና ኤርትራ መካከል ሰላም ለማውረድ ያደረጉት ጥረት ሂደት ህጋዊ እና ተቋማዊ ቅርጽ ይዞ እንዲቀጥል የብዙዎቹ ፍላጎት መሆኑን የመቀሌው ወኪላችን ሚሊዮን ኃይለ ሥላሴ ዘግቧል። 

Listen to the DW | Amharic - News podcast in Replaio

Radio and podcasts in one app - free, with no sign-up. Install today and do not miss the launch

Get it on Google Play

Replaio is not a podcast publisher; show names, artwork and audio belong to their authors and are distributed through public RSS feeds.