DW

ትኩረት በአፍሪቃ | Deutsche Welle

News AM ↓ 63 episoder

አፍሪቃን የሚመለከቱ ጉዳዮች ይታዩበታል።

Husk å besøke podkastens nettsted og støtte skaperen: www.dw.com?maca=amh-podcast_amh_fokus_afrika-13603-xml-mrss

Forfatter

DW

Kategori

News

Siste episode

1. nov 2026

Hvor kan du lytte?

Podkaster i appen Replaio Radio Kommer snart

Podkaster kommer snart til appen. Installer nå, og bli den første som ser en helt ny tilnærming til podkaster

Last ned på Google Play Installer gratis Android nesten 10 mill. nedlastinger · 4,7+ i vurdering iOS snart

Episoder

ትኩረት በአፍሪቃ፣ የባሕረ ሰላጤዉ ጦርነት መዘዝ በሶማሊላንድ፣ ደቡብ አፍሪቃ-ወርሮበላን ለመምታት ጦር ሠራዊት 14.03.2026

ታዛቢዎች እንደሚገምቱት የእስራኤል ጦር ገና ካሁኑ ሶማሊላንድ ዉስጥ በሚገኘዉ የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች ጦር ሠፈር ዉስጥ ሳይሰፍር አልቀረም።ጦሩ ሶማሊላንድ የሰፈረዉ የሁቲ አማፂያንን ከቅርብ ርቀት ለማጥቃት ነዉ

ትኩረት በአፍሪቃ፤አሜሪካ እና እስራኤል ከኢራን ጋር የሚያደርጉት ጦርነት በአፍሪቃ ምን ተፅዕኖ ያሳድራል? 07.03.2026
ትኩረት በአፍሪቃ፤አሜሪካ እና እስራኤል ከኢራን ጋር የሚያደርጉት ጦርነት በአፍሪቃ ምን ተፅዕኖ ያሳድራል? 07.03.2026

የኢራን ጦርነት ዓለም አቀፍ ንግድን እያስተጓጎለ ነው። የንግድ መርከቦች ከሱዌዝ ቦይ ይልቅ አፍሪካ ወደሚገኘው ኬፕ ኦፍ ጉድ ሆፕ ለመሄድ ይገደዳሉ። ይህም ወጪን ይጨምራል፤በነዳጅ እና በሌሎች ሸቀጦች የዋጋ ጭማሪ ያስከትላል። ጦርነቱ በውጭ አገር ተቀጥረው ለሚሠሩ አፍሪቃውያንም የኢኮኖሚ መዘዝ አለው።

ትኩረት በአፍሪቃ፤ኬንያ በመካከለኛው ምስራቅ ጦርነት ለምን ስጋት ገባት? 07.03.2026

ከ400,000 በላይ ኬንያውያን እንደ ሳውዲ አረቢያ፣ የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ እና ኳታር ባሉ የባህረ ሰላጤው ሀገራት ይሰራሉ። ብዙዎቹ በቤት ውስጥ ሥራ፣ በግንባታ፣ በእንግዳ ተቀባይነት እና በአቪዬሽን ዘርፍ ተቀጥረው ይሰራሉ።የመካከለኛው ምስራቅ ውጥረት እነዚህን ኬንያውያን ስጋት ውስጥ ከቷል።

ትኩረት በአፍሪቃ፤ኬንያ በመካከለኛው ምስራቅ ጦርነት ለምን ስጋት ገባት? 07.03.2026
ትኩረት በአፍሪቃ፤አሜሪካ እና እስራኤል ከኢራን ጋር የሚያደርጉት ጦርነት በአፍሪቃ ምን ተፅዕኖ ያሳድራል? 07.03.2026
ትኩረት በአፍሪቃ -የደቡብ ሱዳን አለመረጋጋት እና የቻድ ሚና በሱዳን ጦርነት 28.02.2026
በሱዳን ጦርነት የጎረቤት ቻድ ሚና 28.02.2026

በሱዳን የሚካሄደው ጦርነት ወደ ጎረቤት ቻድም እየተቃረበ ነው። ያለፈው ሳምንት መጨረሻ የሱዳን ጦር እና አጋሮቹ በድንበር ላይ ከሚገኙት የሱዳን ፈጥኖ ደራሽ ሀይል በእንግሊዝኛው ምህፃሩ የRSF ሚሊሻዎች ጋር ተጋጭቷል። የቻድ መንግስትም ከሱዳን ጋር የሚያዋስነውን 1,300 ኪሎ ሜትር ርዝመት ያለው ድንበር ዘግቷል።

ፕሬዝዳንት ኪር ደቡብ ሱዳንን ማረጋጋት ይችሉ ይሆን? 28.02.2026

የደቡብ ሱዳን ፕሬዝዳንት ሳልቫ ኪር ሰሞኑን ባለስልጣኖቻቸውን ከስልጣን ማባረር ይዘዋል። ተንታኞች እንደሚሉት የሰሞኑ የፕሬዚዳንቱ እርምጃ በሀገሪቱ እየጨመረ የመጣውን አለመረጋጋት የሚያባባስ ነው። በሙስና፣ በጎሰኝነት እና በብልሹ አስተዳደር የሚተቸው የሳልቫኪር መንግስት ምክትላቸውን ሪክ ማቻርን ካሰሯቸው ወዲህ በሀገሪቱ አለመረጋጋት ተባብሷል።

አሜሪካ እጇን ያስገባችበት የኮንጎ የሰላም ስምምነት ይጸና ይኾን? 21.02.2026

በምሥራቃዊ ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ለዓመታት የዘለቀው ደም መፋሰስ እንዲቆም አዲስ የተስፋ ጭላንጭል አሳይቷል። ባለፈው ረቡዕ የካቲት 11 ቀን 2018 ዓ/ም ተግባራዊ እንዲሆን የታቀደው የተኩስ አቁም ስምምነት፤ «ለመጨረሻ ጊዜ የተገኘ የሰላም ዕድል ይሆን?» የሚለው ጥያቄ የአለም አቀፍ ዲፕሎማቶችን ትኩረት ስቧል።

ደቡብ አፍሪካ ፊቷን ከአሜሪካ ወደ ቻይና አዙራ ይኾን ? 21.02.2026

በሁለቱ የዓለማችን ልዕለ ኃያላን የንግድ እና ዲፕሎማሲያዊ ፍጥጫ መሃል የገባችው ደቡብ አፍሪካ ፊቷን ወደ ምሥራቅ ታዞር ይኾን? የሚለው ጥያቄ አሁን የበርካቶችን ትኩረት የሳበ መስሏል። ላለፉት 20 ዓመታት ደቡብ አፍሪካ በዋሽንግተን እና በቤጂንግ መካከል ያለውን ግንኙነት በሚገርም ብልሃት ሚዛኑን ጠብቃ ማቆየቷ ነው የሚነገርላት።

የየካቲት 14 ቀን 2018 ዓ/ም የትኩረት በአፍሪቃ ዝግጅት 21.02.2026
የሱዳን ጦርነት ከኤል ፋሸር እስከ በኒ ሻንጉል፤ የአፍሪቃ ሕብረት ጉባኤና የአሕጉሪቱ ሠላም 14.02.2026

የብሪታንያዉ ዜና አገ,ልግሎት ሮይተርስ በያዝነዉ ሳምንት መጀመሪያ ላይ የሱዳን ፈጥኖ ደራሽ ጦር ተዋጊዎች የሚሰለጥኑበት ጦር ሠፈር ኢትዮጵያ ዉስጥ መግንባቱን ከዘገበ ወዲሕ ጉዳዩ ብዙዎችን እያነጋገረ ነዉ።

ሩስያና አሜሪካ፥ አፍሪቃን ለመቆጣጠር ሩጫ 07.02.2026

ሩሲያ ቀድማ እግሯን ባደላደለችባቸው የሣኅል አገራት ጎዳና ላይ ዩናይትድ ስቴትስም መገስገስ ትሻለች ። ከማሊ፣ ከኒጀር እና ከቡርኪናፋሶ ላይ ያላትን አቀራረብም ከወታደራዊ ኹንታው ጋር ቢሆንም እንደገና እያስተካከለች ነው ።

ትኩረት በአፍሪቃ 07.02.2026
በአማጺው M23 ስር ያለችው የዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎዋ ከተማ ጎማ ከአንድ ዓመት በኋላ 31.01.2026

ከአንድ ዓመት በኋላ፣ ጎማ ለጦርነት ክፍት የሆነች ከተማ አይደለችም። የጸጥታ ሁኔታ ተሻሽሏል። ገበያዎች እንደገና ተከፍተዋል፣ትምህርት ቤቶችም ተከፍተዋል። ሆኖም የኢኮኖሚ ሁኔታው ​​አሁንም አስቸጋሪ ነው። ከተማዋ አሁንም በአማፂያን ቁጥጥር ስር ነች። ከሁሉም በላይ፣ ስነልቦናዊ መዘዞች በስፋት አሉ። ጭንቀት የብዙዎች የዕለት ተዕለት እውነታ ነው።

የዩጋንዳ ምርጫ ወዴት? 17.01.2026

ከ40 ዓመታት በላይ ሐገሪቱን ያስተዳደሩት የ81 አመቱ የኡጋንዳ ፕረዚደንት ዩዌሪ ሙሰቨኒ ሐሙስ ዕለት በተካሄደም ምርጫ ማሸነፋቸውን የሐገሪቱ የምርጫ ኮሚሽን ዛሬ ይፋ አደረጓል። ዩጋንዳ ውስጥ ሐሙስ በተከናወነው አገር አቀፍ ምርጫ ከ81 ዓመቱ ፕሬዝዳንት ዮዌሪ ሙሴቬኒ ጋር ሰባት እጩዎች ተፎካክረው ነበር ።

የሱዳን ስደተኞች ብርቱ ሥጋት ተጋርጦባቸዋል፦ ተመድ 17.01.2026

በርስ በርስ ጦርነት በምትታመሰው ሱዳን አፋጣኝ የምግብ ርዳታ ባፋጣኝ ካልቀረበ ክምችቱ የፊታችን መጋቢት ወር ማገባደጃ ላይ ሊሟጠጥ እንደሚችል የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ይፋ አድርጓል የተመድ ከፍተኛ የሰብአዊ መብት ኮሚሽነር ፎልከር ቱይርክ ሱዳን ውስጥ ከ50 በላይ የሲቪል ማኅበረሰብ ተወካዮች እና መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶችን አወያይተዋል ።

የጥር 2 ቀን 2018 ዓ.ም፤ ትኩረት በአፍሪካ 10.01.2026

ቻይና ለአፍሪካ ሐገራት ያለፖሊሲ ጫናና በቀላል የቢሮክራሲ ውጣውረድ በገፍ የምታቀርበውን ብድር የሐገራቱን መጻኢ ዕድል በቻይና ስር እንዲወድቅ ያደርጋል የሚል መከራከሪያ የሚያቀርቡ የፖለቲካ ተንታኞችም ይደመጣሉ።

የእስራኤል የሶማሊያ ላንድ አገርነት እውቅና የፈጠረው ውዝግብ እና የጊኒ ምርጫ 03.01.2026

ባለፈው ሳምንት አርብ የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስተር ቢንጃሚን ናትናያሁ ባለፉት ሶስት አስርት አመታት ከሶማሊያ ተነጥላ እራሷን ነጻ አገር በማወጅ ዕውቅና ስትሻ የቆየችውን፤ ግን በማንም ጥያቄዋ ተቀባይነት አግንቶ የማያውቀውን ሶማሊያ ላንድን እስራኤል ዕውቅና የሰጠችና በነጻ- ሉላዊ አገርነት የተቀበለቻት መሆኑን ማሳወቃቸው ውዝግብ ቀስቅሷል

ዓለም አቀፍ ትኩረት የተነፈገው የሱዳን ጦርነት 20.12.2025

በሱዳን የሚፈጸሙ ወንጀሎችን በሳተላይት የሚከታተለው የየል ዩኒቨርስቲ የሰብዓዊ ጉዳዮች ጥናት ላቦራቶሪ የፈጥኖ ደራሹ ኃይል ሚሊሻያዎች የፈጸሟቸውን የጅምላ ግድያዎች ማስረጃዎች እያወደሙና እየደበቁ መሆናቸውን የሚያስረዳ ማስጠንቀቂያ የካተተ ዘገባ አቅርቧል።ሂዩመን ራይትስ ዋች በሱዳን ጦር እስር ቤቶች ሰዎች እየሞቱ ነው የሚሉ ዘገባዎች ደርሰውታል።

ትኩረት በአፍሪቃ 201225 ዓለም አቀፍ ትኩረት የተነፈገው የሱዳን ጦርነት ፤ በአፍሪቃ የተካሄዱት መፈንቅለ መንግሥታት 20.12.2025

ትኩረት በአፍሪቃ በሱዳኑ ውጊያ ፣ እጅግ አሰቃቂ የሰብዓዊ መብቶች ጥሰቶች እየተፈጸሙ ቢሆንም ለነዚህ በዓለማችን እጅግ አስከፊ ለሚባሉ የሰብዓዊነትና እና የመፈናቀል ቀውሶች የሚሰጠው ዓለም አቀፍ ትኩረት አሁንም አነስተኛ ነው። በቅርብ ጊዜያት በሁለት የአፍሪቃ ሀገራት መፈንቅለ መንግሥታት ፣በአንድ ሌላ ሀገር ደግሞ የመፈንቅለ መንግሥት ሙከራ ተደርጓል። ተከታታዮቹ መፈንቅለ መንግስታትና የመፈንቅለ መንግሥት ሙከራ ምን ያመለክታሉ? የዛሬው ትኩረት በአፍሪቃ በእነዚህ ሁለት ጉዳዮች ላይ ያተኩራል ኂሩትመለሰ አጠናቅራዋለች።

የታኅሣሥ 4 ቀን 2018 ዓ.ም. ትኩረት በአፍሪቃ 13.12.2025
ትኩረት በአፍሪቃ ኅዳር 20 ቀን 2025 ዓ.ም. 29.11.2025
የሱዳኑ ፈጥኖ ደራሽ ኃይል በኤልፋሺር ይፈጽማል የሚባለው ግፍ 15.11.2025

በጀርመኑ ዓለም አቀፋዊና እና አካባቢያዊ ጥናቶች ተቋም የሱዳን ጉዳዮች አዋቂ ሀገር አሊ እንደተናገሩት አሁን በአልፋሺር በሚካሄደው ጭፍጨፋ የጭካኔው መጠን በጣም አስደንጋጭ ወደሆነ አዲስ ደረጃ ላይ ደርሷል ። በበቂ ሁኔታ በጋለ ስሜት የማይደግፋቸው፣ ከእነሱ ጋር መቀላቀል የማይፈልግ ወይም ማንኛውንም ተዋጊ የሚያደናቅፍ ሰው አደጋ ላይ ይወድቃል።

Hør på podkasten ትኩረት በአፍሪቃ | Deutsche Welle i Replaio

Radio og podkaster i én app - gratis og uten registrering. Installer i dag, og ikke gå glipp av lanseringen

Last ned på Google Play

Replaio er ikke podkastutgiver; programnavn, omslag og lyd tilhører opphavspersonene og distribueres via offentlige RSS-feeder.