DW

ዜና መጽሔት

News AM ↓ 189 episoder

በዐበይት የኢትዮጵያ፣ የአፍሪካ፣ የአውሮፓ እና የዓለም ጉዳዮች ላይ ዜናዎች፣ ቃለ-መጠይቆች እና ጥልቅ ትንታኔዎች ይቀርባሉ። በዐበይት የኢትዮጵያ፣ የአፍሪካ፣ የአውሮፓ እና የዓለም ጉዳዮች ላይ ዜናዎች፣ ቃለ-መጠይቆች እና ጥልቅ ትንታኔዎች ይቀርባሉ። ኢትዮጵያን ጨምሮ በተለያዩ የዓለም ክፍሎች የሚገኙ የዶይቼ ቬለ ዘጋቢዎች የሚያጠናቅሩት ዜና መፅሔት ከሰኞ እስከ አርብ ከዓለም ዜና ቀጥሎ ይቀርባል። የዶይቼ ቬለን ሥርጭት በራዲዮ፣ በሳተላይት እና በፌስቡክ በቀጥታ ማድመጥ ይቻላል። በአፕል ፖድካስት እና በስፖቲፋይ የዶይቼ ቬለን ዜና መጽሔቶች ያዳምጡ።

Husk at besøge podcastens hjemmeside og støtte skaberen: www.dw.com

Forfatter

DW

Kategori

News

Podcastens hjemmeside

www.dw.com

Seneste episode

12. nov. 2026

Hvor kan du lytte?

Podcasts i appen Replaio Radio Kommer snart

Podcasts kommer snart til appen. Installer nu, og vær den første til at se en helt ny tilgang til podcasts

Hent den på Google Play Installer gratis Android næsten 10 mio. downloads · 4,7+ i bedømmelse iOS snart

Episoder

የሐምሌ 23 ቀን 2018 ዓ/ም የዜና መጽሔት 30.07.2026

1, የሀገራዊ ምክክር ጉባኤ የመረጃ ተደራሽነት ላይ የተሰጡ አስተያየቶች 2, የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ጉባኤና የሌሎች ሀገሮች ተሞክሮ 3, በትግራይ የተመናመነው ሰብዓዊ ድጋፍ እና የተፈናቃዮች እሮሮ 4, የአዳሪ ትምህርት ቤት ግንባታ በድሬደዋ 5, ጣና ሐይቅን እየፈተነ ያለዉ የእምቦጭ አረም //እንዲሁም 6, አፍሪካ ኀብረት በሶማሊያ ያለው ሚና ወደ ፖለቲከዊ ተልዕኮ እንዲሸጋገር መጠየቁ

የሐምሌ 22 ቀን 2018 የዜና መጽሔት 29.07.2026

በዜና መጽኄት አምስት ዘገባዎችን እናስተነትናለን ። ግድያና ጥቃትን የተመለከቱ የምርመራ ውጤቶች ትኩረት አግኝተዋልን? ሲል የሚጠይቀው ቀዳሚው ዘገባችን ነው ። ከ90 ሺህ በላይ ተፈናቃዮች በ4 ጣቢያዎች ለብርቱ ዝናምና ጎርፍ ተጋልጠዋል መባሉ፤ የኢትዮጵያ አየር መንገድ የዓመቱ ስኬቶች እና ያጋጠሙት ፈተናዎች፤ IOM ምስራቅ አፍሪቃውያን በዓለም አቀፍ ወንጀል እንዲሳተፉ እየተገደዱ ነው ማለቱ እንዲሁም የሰው ሠራሽ አደጋ በማጃንግ ዞን ጥብቅ ደን ላይ አደጋ ደቅኗል ይሰኛሉ ዘገባዎቹ

የዜና መጽሔት፤ ሐምሌ 21 ቀን 2028 ዓ.ም ማክሰኞ 28.07.2026

የዜና መጽሔት ጥንቅራችን ዩናይትድ ስቴትስና ኢትዮጵያ በጋራ ያዘጋጁትን ሲምፖዚየም አላማ ፤ትግራይ ክልል ለ2019 በጀት ዓመት 65 ቢሊዮን ብር ማፅደቁ ከመቀሌ ሲነገር፣ በክልሉ ይደረጋል ያሉትን ወታደራዊ ምልመላና ጦርነት ያሰጋቸዉ ወጣቶች በብዛት መሸሻቸዉ ከአማራ ክልል ተዘግቧል።የደቡብ ኢትዮጵያ አስተዳደር በአደጋ ለተፈናቀሉ ነዋሪዎች ቤት መስራቱ እንዲሁም የአፍሪቃ ሕብረት የዉጪ ጉዳይ ሚንስትሮችን ስብሰባ በአዲስ አበባ የተሰኙ ዘገባዎችን አካቷል።

የሐምሌ 20 ቀን 2018 ዓ.ም የዜና መፅሄት 27.07.2026

የዛሬው የዜና መ።ፅሄት፤ ለአማራ እና ለትግራይ ምኁራን የቀረቡ የትብብር ጥሪዎችና ያላስማሙ ተቃርኖዎች፣በምስራቅ ወለጋ ዞን በታጣቂዎች የደረሰው ጥቃት፣የደቡብ አፍሪቃዉ መጤ ጠል ጥቃትሃገሪቱን ከአፍሪቃ ማቃረኑ እንዲሁም የኢትዮጵያ የፊልም ፌስቲቫል በፓሪስ የተሰኙ ርዕሶችን ያስተነትናል።

የዕለተ ዐርብ ሐምሌ 17 ቀን፣ 2018 ዓ.ም ዜና መጽሔት 24.07.2026

የዓለም ዜናን የሚከተለዉ የዜና መጽሔት፤ -በኢትዮጵያ ሕዝብ ላይ እየደረሰ ነው ያለው የዘር ማጥፋት እና የእርስ በርስ ጦርነት እንዲቆም፣ ሲል ጥሪ ያቀረበዉ የኢትዮጵያውያን ትብብር ንቅናቄ -በትግራይ ክልል እየተደረጉ ያሉ ሰሞነኛ ስብሰባዎችና የነዋሪዎች ኹኔታ - በቀይ ባሕር በሁቲ ታጣቂዎች የተፈፀ የመርከቦች ጥቃትን የአፍሪካ ኅብረት ማዉገዙ -የኢትዮጵያ የስደተኞች እና ተመላሾች አገልግሎትን ለማስተሳሰር ያለመ አዲስ ፍኖተ-ካርታ ይፋ መሆኑ - እንዲሁም ተግባራዊ የሆነው ተንቀሳቃሽ ማህበረሰብ አቀፍ የጤና ፕሮግራም በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የተሰኙ ርዕሶችን ይዟል።

የሐምሌ 16 ቀን 2018 ዓ.ም. የዜና መጽሔት 23.07.2026

በዜና መጽኄት አምስት ዘገባዎችን እናስተነትናለን ። ዘገባዎቹ፦ አገራዊ ምክክር ኮሚሽን፦ የምክክር ጉባኤ ተሳታፊዎች በሚያቀርቡት ሐሳብ እንዳይጠየቁ ኃላፊነት እወስዳለሁ ማለቱ፤ የድሮን ጥቃት በአባይ ገዳመ አስቄጤስ አቡነ አረጋዊ እና ቅድስት አርሴማ አንድነት ገዳም፣ የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት (ኦነሰ) ከሌሎች ታጣቂዎች ጋር ስለመተባበር ምን አለ? ደቡብ አፍሪቃ፡ ኢትዮጵያውያን በፈቃደኝነት ወደ አገራቸው የተመለሱ ነዉ፤ እንዲሁም የአሜሪካ ሕግ አውጪ ምክር ቤት ስለ ኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት፤ ይሰኛሉ ዘገባዎቹ ።

የሐምሌ 15 ቀን 2018 የዜና መፅሔት 22.07.2026

ዜና መፅሔቱ፣ በሀገራዊ ምክክር ጉባኤ የሲቪል ማሕበራት ተሳትፎ እና የታዛቢነት ሚና፣ ደብረብርሀን መጠለያ ውስጥ የሚገኙ ተፈናቃዮች ሮሮ ፣ የግብፅ የህዳሴ ግድብ ውንጀላና የኢትዮጵያዊው ተደራዳሪ ምላሽ፣ እንዲሁም በትግራይ የሰላሙ ተስፋ ምን ይመስላል? በተሰኙ ርዕሶች ስር የተቀናበሩ ዘገባዎች ይቀርቡበታል

የዜና መጽሔት፤ ሐምሌ 14 ቀን 2018 ዓ.ም ማክሰኞ 21.07.2026
የሐምሌ 13 ቀን 2018 ዓ.ም. የዜና መጽሔት 20.07.2026

የዜና መጽሔት ዝግጅታችን ፣ የኦሮምያ ክልል ምክር ቤት ጨፌ ስለክልሉ የፀጥታው ሁኔታ መምከሩን፣ -በሀገራዊ ምክክር ሂደቱ በአዲስ ጉባኤዉን የተቀላቀሉ የፖለቲካ ፓርቲዎች አሉ መባሉን፣ -በደቡብና ሰሜን ወሎ በመሰረተ ልማቶች ላይ የሚፈጸም ዝርፍያ መባባሱ፣ -የአፍሪቃ ቀንድን የበለጠ ስጋት ዉስጥ የጣለዉ የአሜሪካ እና የኢራን ዳግም ግጭት የተሰኙ ርዕሶችን በስፋት ይዳስሳል

የሐምሌ 10 ቀን፣ 2018 ዓ.ም ዜና መጽሔት 17.07.2026

የዓለም ዜናን የሚከተለዉ የምሽቱ የዜና መጽሔት፤ በአማራ ክልል በሴቶች ላይየሚደርሰው ወሲባዊ አካላዊና ጥቃት ተባብሷል መባሉ፤ በጊምቢ ወደ ቀያቸው የተመለሱ ዜጎች ቅሬታ፣በኢትዮጵያ የዩናይትድ ስቴትስ አምባሳደር የሰሜን ኢትዮጵያ ጉብኝቶች፣በትግራይ የሰላምና ለውጥ ም/ቤት በአዲስ አበባ የተጠራው ሰላማዊ ሰልፍ እንዲሁም በአሜሪካ ምርጫ ቻይና ጣልቃ ገብታለች ሲሉ ቻይናን የከሰሱት ዶናልድ ትራምፕ የተሰኙ ርዕሶችን በስፋት ይዳስሳል።

የሐሙስ ሐምሌ 9 ቀን፣ 2018 ዓ.ም ዜና መጽሔት 16.07.2026

ዜናውን በሚከተለው የዜና መጽሔት፦ ትናንት ስለተጀመረው የኢትዮጲያ ብሔራዊ የምክክር ጉባኤ የተሳታፊዎች አስተያየት ፣ በሀገራዊ ምክክር ጉባኤው መጀመር፣ አካሄድ እና ውጤቱ ላይ የፖለቲካ ፓርቲዎች አስተያየት በምክክሩ የሚሳተፉ ተወካዮቻቸውን የላኩት ተፈናቃዮች ከጉባኤው የሚጠብቁት፤ እንዲሁም የኢትዮጵያ የወደብና የቀይ ባህር ወሰን ጥያቄ ፣ አሜሪካ ኢትዮጵያውያን ስደተኞችን በተመለከተ የወሰደችው የፖሊሲ ለውጥ የዓለም እግር ኳስ የግማሽ ፍጻሜና የፍጻሜ ጨዋታዎች የዛሬው የዜና መጽሔት ዝግጅታችን የሚያስቃኘን ጉዳዮች ናቸው።

የሐምሌ 8 ቀን 2018 ዓ.ም. የዜና መጽሔት 15.07.2026

የዜና መጽሔት ቀዳሚው ዘገባ ዛሬ በይፋ የተጀመረውን ብሔራዊ ምክክር ጉባኤ ይመለከታል፤ የአየር ንብረት መዛባት በክረምቱ ግብርና ላይ የደቀነው ስጋት፤ የአሜሪካው አምባሳደር የመቀለ ጉብኝት፤ አሜሪካ ኢትዮጵያውያን ስደተኞችን በተመለከተ የወሰደችው የፖሊሲ ለውጥ እንዲሁም የትናንቱን የፈረንሳይ ስፔን ጨዋታ እና የዛሬውን የዓለም ዋንጫ ተጋጣሚዎች የሚመለከቱ ዘገባዎችን አካቷል

የዜና መጽሔት፤ ሐምሌ 7 ቀን 2028 ዓ.ም ማክሰኞ 14.07.2026

በዜና መጽኄት ስድስት ዘገባዎችን ይዟል- የዓለም ዋንጫ የግማሽ ፍጻሜን በተለመለከተ ቃለ መጠይቅ ነው ። ነገ ስለሚጀመረው የሀገራዊ ምክክር ጉባኤ ሰዎች ምን ይላሉ?፣ ነገ ስለ ሚጀረው የአገራዊ ምክክር ጉባኤ ምን ተባለ?፣ በአማራ ክልል የተፈናቃዮች የድረሱልን ጥሪ፤ የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽን አገራዊ ውይይት በጅግጅጋ እንዲሁም የጊምቢ- ኖሌካባ እና ሜቱ መንገድ ግንባታ መጓተት የሚሉ ዘገባዎችን ያስተነትናል።

የሐምሌ 6 ቀን 2018 ዓ/ም የዜና መፅሔት 13.07.2026
የሐምሌ 3 ቀን 2018 ዓ.ም. የዜና መጽሔት 10.07.2026

የዓለም ዜናን በሚከተለው በዛሬው የዜና መጽሄት ፣ በእሥር ላይ ስለሚገኙ ፖለቲከኞች መፈታት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ የሰጡት ፍንጭ፤ በአርሲ አሰኮ በግጭት የተፈናቀሉ ነዋሪዎች የድጋፍ ጥያቄ፤ የኢሰመኮ የአምስት ዓመት ዕቅድ የመብት ጥሰቶችን ይቀንስ ይሆን?፤ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ወቀሳ የህወሓት ምላሽ፣ በአፍሪቃ የሚካሄዱ ምርጫዎች ዳያስፖራውን ማሳተፍ እንደለባቸው መገለጹ እንዲሁም አንድነት ላይ ያተኮረው የኔቶ ጉባኤ ይሰኛሉ ዘገባዎቹ ። የወጣቶች ዓለም መሰናዶ ዝምታ ሰባሪ አዳጊ ሴቶች፦ የመረጃ ሰጪ መተግበሪያዎች የንባብ ባህልን እያዳከሙ ይሆን? በሚል ርእስ ተቀናብሯል ።

የሐሙስ ሐምሌ 2 ቀን፣ 2018 ዓ.ም ዜና መጽሔት 09.07.2026
የዜና መጽሔት፤ ሐምሌ 1 ቀን 2018 ረቡዕ 08.07.2026
የማክሰኞ ሰኔ 30 ቀን፣ 2018 ዓ.ም ዜና መጽሔት 07.07.2026

የዜና መጽሔት ጥንቅራችን፣ ጠቅላይ ሚንስትር ዓብይ አሕመድ ህዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ ለጦርነት እየተዘጋጀ ነዉ ሲሉ፣ -የዚያዉ ከትግራይ ክልል ወጣቶች ደግሞ አፈሳና የጦርነት ዝግጅት እንዳሳሰባቸዉ እያስታወቁ ነዉ።የዳግም ጦርነት ዝግጅት፣ ወቀሳና ሥጋቱን ዜና መጽሔቱ በሁለት ዘገቦች ያስተነትናል።የኢትዮጵያ ምርጫ የጥቃት ኢላማ እንደነበር፣ የሐገሪቱ ምጣኔ ሐብት ግን ዘንድሮም በ10.2 በመቶ አድጓል መባሉ ከወደ አዲስ አበባ ተሰምቷል።ሌላዉ የዜና መፅሔት ርዕስችን በሱዳንዋ ሥልታዊ ከተማ አል-ዑቤይድ የተፈፀመዉ የመብት ጥሰትና ይደርሳል የተባለዉ ተጨማሪ ጥፋት የተባበሩት መንግሥታት የሰብአዊ ኮሚሽንን እያባተለ መሆኑን ይቃኛል።

DW Amharic የሰኔ 29 ቀን 2018 ዜና መጽሔት 06.07.2026

በአፍሪቃ ቀንድ እየጨመረ የመጣው የጦርነት ስጋት፣ የፀጥታ ሥጋት ያጋጠመው የጋሞ ዞን ዛይሴ አካባቢ፣ የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተናን ያልተቀመጠዉ የትግራይ ክልል ቅሬታ

የሰኔ 26 ቀን 2018 የዜና መጽሔት 03.07.2026

እቅዱን አሳክቷል የተባለው የኢትዮጵያ የቡና ገቢ ፣ በአሜሪካ የትግራይ ማኅበረሰብ አባላት፣ስለትግራይ ክልል ወቅታዊ ሁኔታ የሰጡት አስተያየት ፣በድሬደዋ የተማሪ ህፃናት ምገባን በተደራጃ መንገድ ማከናወን ያስችላል የተባለ ፕሮጀክት በይፋ መጀመሩ እንዲሁም የቀድሞ የኢራን ላዕላይ መሪ አያቶላህ አሊ ኻሚኒ አስከሬን ሽኝት የተሰኙት ርዕሶች ይተነተናሉ።

የሰኔ 25 ቀን 2018 ዓ.ም. የዜና መጽሔት 02.07.2026

የዜና መጽሔት ዝግጅታችን ሆሮ ጉድሩ ወለጋ ዞን ታጣቂዎች 13 ሰዎች መግደላቸዉን የሚቃኝ ዘገባ ያስቀድማል።ዜና መፅሔቱ፣ ደቡብ ኢትዮጵያ የኮሬ ዞን አስተማሪዎች ተማሪዎችን ላለመፈተን ማደማቸዉን ከዞኑ አስተዳደር መልስ ጋር ያሰባጠረ ዘገባም አለዉ።የአዉሮጳ የሙቀት መጠን ማየልና የፖለቲካዊ መርሕ ለዉጥ ጥያቄ፣ የቻይና ኮሚንስት ፓርቲ 105ኛ ዓመት በአል፣ የዓለም የእግር ኳስ ግጥሚያ የአፍሪቃ ቡድናት ሽንፈት ያልናቸዉንም ርዕሶች ያስተነትናል።

የሰኔ 24 ቀን 2018 ዓ.ም. የዜና መጽሔት 01.07.2026

የዜና መጽሔት፤ አዲሱ የመኖሪያ ቤት የኪራይ ዋጋ ጥናት፤ በጋምቤላ ክልል ባህላዊ የግጭት አፈታት ዜዴዎች ዘላቂ ሰላም ለማስፈን ስለሚኖራቸው ሚና፤ የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ መልቀቂያ ፈተና መጀመሩ እንዲሁም የአሜሪካ ጠቅላይ ፍርድ ቤት እዚያ ስለሚወለዱ ልጆች ዜግነት ያሳለፈው ውሳኔን የሚያስቃኙ ዘገባዎችን አካቷል።

የሰኔ 23 ቀን 2018 ዓ.ም. የዜና መጽሔት 30.06.2026

የዜና መጽሔት ዝግጅታችን የኤርትራ የወደፊት ኅልዉና የፕሬዝደንቷ አገዛዝ ያልነዉን ርዕሥ ያስቀድማል። ዜና መፅሔቱ አዲስ አበባ ዉስጥ በተዘዋዋሪ አዉቶብሶች የዲጅታል የሕዝብ አገልግሎት መሰጠቱ፣ የደቡብ አፍሪቃ መጤ ጠል ቡድናት በከፈቱት ዘመቻ ላይ ሊነጋገር የነበረዉ የአፍሪቃ ሕብረት ስብሰባ መራዘምና የዓለም እግር ኳስ ዋንጫን የሚቃኙ ዘገቦችና ቃለ ምልልስን አካቷል።

DW Amharic የሰኔ 22 ቀን 2018 ዜና መጽሔት 29.06.2026

የሶማሊያው ፕሬዝዳንት ሀሰን ሼክ ሞሐመድ የኢትዮጵያ ጉብኝት፣ በትግራይ የወጣቶች አፈሳ ቀጥሏል መባሉና የአውሮፓ ህብረት ማስጠንቀቂያ፣ የቀነ ገደቡ መጠናቀቅ እና የፍልሰተኞች ሥጋት በደቡብ አፍሪካ

የዓርብ ሰኔ 19 ቀን፣ 2018 ዓ.ም ዜና መጽሔት 26.06.2026

ዜናዉን የሚለጥቀዉ የዜና መፅሔት ዝግጅታችን ህዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) አዲስ የደነገገዉን ሕግ እንዲሽር ሑማን ራይትስ ዋች ያቀረበዉን ጥያቄ ህወሃት ዉድማድረጉን የሚተነትነዉን ዘገባ ያስቀድማል።ዜና መፅሔቱ፣ የጋቤላ ብልፅግና ፓርቲ ፅሕፈት ቤት ከተቃዋሚዎች ጋር ተባብሮ ለመሥራት ቃል መግባቱ፣ ደቡብ አፍሪቃ የሚኖሩ ኢትዮጵያዉያን ጥቃት ይደርስብናል የሚለዉ ሥጋታቸዉ መናሩ፣ የመረጃ ጥቅም፣ የአፍሪቃ አቅምና ዝግጅት፣ እንዲሁም የዓለም የእግር ኳስ የዋንጫ ግጥሚያን የሚቃኙ ዘገቦችና አጭር ዉይይቶች አሉት።

Lyt til podcasten ዜና መጽሔት i Replaio

Radio og podcasts i én app - gratis og uden tilmelding. Installer i dag, og gå ikke glip af lanceringen

Hent den på Google Play

Replaio er ikke podcastudgiver; programmernes navne, coverbilleder og lyd tilhører deres ophavsmænd og distribueres via offentlige RSS-feeds.