DW

ዜና መጽሔት

News AM ↓ Epizody: 189

በዐበይት የኢትዮጵያ፣ የአፍሪካ፣ የአውሮፓ እና የዓለም ጉዳዮች ላይ ዜናዎች፣ ቃለ-መጠይቆች እና ጥልቅ ትንታኔዎች ይቀርባሉ። በዐበይት የኢትዮጵያ፣ የአፍሪካ፣ የአውሮፓ እና የዓለም ጉዳዮች ላይ ዜናዎች፣ ቃለ-መጠይቆች እና ጥልቅ ትንታኔዎች ይቀርባሉ። ኢትዮጵያን ጨምሮ በተለያዩ የዓለም ክፍሎች የሚገኙ የዶይቼ ቬለ ዘጋቢዎች የሚያጠናቅሩት ዜና መፅሔት ከሰኞ እስከ አርብ ከዓለም ዜና ቀጥሎ ይቀርባል። የዶይቼ ቬለን ሥርጭት በራዲዮ፣ በሳተላይት እና በፌስቡክ በቀጥታ ማድመጥ ይቻላል። በአፕል ፖድካስት እና በስፖቲፋይ የዶይቼ ቬለን ዜና መጽሔቶች ያዳምጡ።

Určitě navštivte web podcastu a podpořte jeho tvůrce: www.dw.com

Autor

DW

Kategorie

News

Web podcastu

www.dw.com

Nejnovější epizoda

12. lis 2026

Kde poslouchat?

Podcasty v aplikaci Replaio Radio Už brzy

Podcasty míří do aplikace už brzy. Nainstaluj si ji teď a jako první uvidíš úplně nový pohled na podcasty

Stáhnout z Google Play Nainstaluj zdarma Android téměř 10 mil. stažení · hodnocení 4,7+ iOS už brzy

Epizody

የመጋቢት 7 ቀን፣ 2018 ዓ.ም ዜና መጽሔት 16.03.2026

በዜና መጽሔት -በኢትዮጵያ የነዳጅ አጠቃቀም በቁጠባ እንዲሆን ማሳሰቢያ መሰጠቱ ፣ - በሰሜን ወሎ ዞን ሙጃ ወረዳ በውጊያ ምክንያት መንገዶች መዘጋታቸው በነዋሪዎች ላይ ያስከተለው ማኅበራዊ ቀውስ - የሆርሙዝን ወሽመጥ ለማስጠበቅ የአሜሪካን ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ያቀረቡት የእርዳታ ጥሪና የአውሮጳ ኅብረት እንዲሁም የጀርመን የምርጫ ስርዓትና ጠቃሚ ልምዶች በተሰኙት ርዕሶች ስር የተቀናበሩ ዘገባዎች ይቀርባሉ።

የዐርብ መጋቢት 4 ቀን፣ 2018 ዓ.ም ዜና መጽሔት 13.03.2026
የመጋቢት 3 ቀን 2018 ዓ.ም. የዜና መጽሔት 12.03.2026

በዜና መጽኄት የ«ፋይዳ» ዲጂታል መታወቂያ፡ በቴክኖሎጂ እድገት እና በዜጎች መብት መካከል ያለው ሚዛን፤ የጦርነት ስጋት ያዣበበባት ትግራይ ክልል እና የህወሓት አስገዳጅ የገንዘብ ማሰባሰብያ ፤ በአዲስ አበባ እና ደሴ መንገድ የአሽከርካሪዎችና ተጓዦች የደኅንነት ሥጋት ማየሉ፤ ነጻ ሚዲያ የሚኖረው ሚና ትኩረት እንዲሰጠው መጠየቁ፤ እንዲሁም የጀርመን የፌዴራሊዝም ሥርዓት አተገባበር እና ልዩ መገለጫው ይሰኛሉ ዘገባዎቹ ።

የመጋቢት 2 ቀን 2018 የዜና መፅሔት 11.03.2026

የዓለም ዜናን በሚከተለው የዜና መጽሔት በኢትዮጵያ ህዝባዊ እምቢተኝነትን አሰመልክቶ የተሰጠ ጋዜጣዊ መግለጫ፣ በጋሞ ዞን በናዳና ጎርፍ የሞቱት ሰዎች ቁጥር ቢያንስ 64 መድረሱ፣ የነዳጅ ዋጋ ጭማሪው እና የኑሮው ጫና እንዲሁም በፖላንዱ የዓለም የቤት ውስጥ አትሌቲክስ ሻምፕዮና የሚሳተፈው የኢትዮጵያ አትሌቶች ቡድን ያጋጠመው የቪዛ ችግርን ይዳስሳል።

የዜና መጽሔት፤ መጋቢት 1 ቀን 2018 ማክሰኞ 10.03.2026
የየካቲት 30 ቀን 2018 ዓም የዜና መጽሔት 09.03.2026

--በጦርነት ግጭት ዉስጥ የሴቶች ከፍተኛ ተጋላጭነት እልባት ያሻዋል ሲል የኦሮሞ ፌዴራላዊ ኮንግሬስ (ኦፌኮ)መግለጫ ማዉጣቱ --የአፍሪካ ሕብረት የሴቶችን ውክልና የበለጠ እንዲያሳድግ መጠየቁ --የሲቪል ነዋሪዎች ደህንነት እንዲጠበቅ የጠየቀዉ ጎጎት ለጉራጌ አንድነትና ፍትህ ፓርቲ --በደላንታ ወረዳ የኦፓል ማዕድን አምራቾች በሰላም እጦት ምክንያት ስጋት ውስጥ ነን ማለታቸዉ እንዲሁም -መዲና በርሊን የሚገኘዉ የጀርመን የዉጭ ጉዳይ ሚኒስትር የኢትዮጵያ እና የጀርመንን ግንኙነት የተመለከተዉ ስብሰባ

የየካቲት 27 ቀን 2018 ዓ.ም. የዜና መጽሔት 06.03.2026

ዓለም አቀፉ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅት አምነስቲ -ኢንተርናሽናል የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊትን ፣ሴቶችን በጅምላ የመድፈርና የማሰቃየት ወንጀሎችን ጨምሮ በበርካታ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች መክሰሱ ፣ -ነገ ስለሚጀመረው የመራጮች ምዝገባ የተሰበሰቡ የህዝብ አስተያየቶች፣ -በኢትዮጵያ በኬንያና በሶማሊያ የሚገኙ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ሰዎች ለድርቅ መጋለጣቸው -ኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ የዓለም አትሌቲክስ የ"አንድ ቀን ውድድር" እንደምታዘጋጅ መገለጹ

የየካቲት 26 ቀን 2018 ዓ.ም. የዜና መጽሔት 05.03.2026

የዛሬው የዜና መጽሔት ዝግጅታችን 41 ሐገሮች በኢትዮጵያ ያለውን የመናገር ነጻነትና የሰብዓዊ መብት ጥሰት እንዳሳሰባቸው መግለጻቸውን፤ የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሞሽን በአርሲ ስለተገደሉ ዜጎች ያወጣውን መግለጫ፤ ከራያ አላማጣ፣ ኮረምና ኦፍላ ዛታ የተፈናቀሉ ወገኖች የዕርዳታ ጥሪ፤ በምዕራባዊ የሐገሪቱ ክፍል ከመደበኛ በላይ ጎርፍ ሊከሰት እንደሚችል ማስጠንቀቂያ መሰጠቱን፣ በኢትዮጵያ የተከሰተው የነዳጅ ዕጥረት እንዲሁም የድሬደዋ ስታድየም - የኢትዮጵያ ብሔራዊ እግር ኳስ ቡድን ከሳኦቶሜ እና ፕሪንስፔ ጋር የሚያደርገውን የቅድመ ማጣሪያ ጨዋታ እንዲያስተናግድ መወሰኑ" የተሰኙትን ጉዳዮች ያስቃኘናል

የየካቲት 25 ቀን 2018 ዓ/ም የዜና መጽሔት 04.03.2026

በሆሮ ጉዱሩ ወለጋ ዞን አቤደንጎሮ ወረዳ ያገረሸው ጸጥታ ችግር፤ በአማራ ክልል የሚካሄደው ውጊያ ወጣቶች ላይ ያስከተለው ተጽዕኖ፤ ምርጫ ቦርድ በ5 የምርጫ ክልሎች ጉዳይ ለቀረበበት ክስ ለፍርድ ቤት ምላሽ ማቅረቡ፤ የሱዳን መከላከያ በኢትዮጵያ ላይ ያቀረበው ክስ አንድምታ

የማክሰኞ የካቲት 24 ቀን 2018 ዓ.ም የዜና መፅሄት 03.03.2026

በዛሬው የዜና መፅሔት ዝግጅታችን፣በመጪዉ ግንቦት ሊደረግ ለታቀደዉ ምርጫ የፖለቲካ ፓርቲዎችንና የሲቪክ ማሕበራት ድርጅቶችን ዝግጅቶች የሚቃኙ ሁለት ዘገባዎችን ፣ የአድዋ ድል 130ኛ ዓመት ዝክር በፓሪስ የሚመለከት ዘገባ የእስራኤልና የአሜሪካ ድብደባና የኢራን አፀፋን የሚመለከት አጭር ቃለ መጠይቅም ተካቷል።

የየካቲት 23 ቀን 2018 ዓ.ም. የዜና መጽሔት 02.03.2026

130ኛው የአድዋ ድል በዓል ዛሬ በድሉ መታሰቢያ ማዕከል ተከብሯል፤ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን በኦሮሚያ ክልል አርሲ ዞን ሺርካ ወረዳ ጃዊ ቀበሌ በንጹሃን ዜጎች ላይ የደረሰውን የጅምላ እልቂት አውግዛለች፣  አሜሪካና እሥራኤል በኢራን ላይ የከፈቱት ጦርነትና የኢራንን አጸፋንና አውሮጳን እንዲሁም ጦርነቱ የአፍሪካን ኢኮኖሚ በቀጥታ ሊጎዳ ይችላሉ መባሉ

የየካቲት 20 ቀን 2018 ዓ.ም. የዜና መጽሔት 27.02.2026

በዛሬው የዜና መጽሔት "በንጹሓን ላይ የሚሰነዘር" ያለው ጥቃት "እያደር ከብዷል" ሲል ትብብር ለኢትዮጵያ አንድነት መግለጫ ማዉጣቱ፣ በአማራ ክልል በኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር ዞን እና ሰሜን ሸዋ አዋሳኝ ወረዳዎች፣ በተለይም በኤፍራታ ግድም እና ጅሌ ጥሙጋ ወረዳ የተከሰተ ግጭት ፣ በሚሉ ርዕሶች ስር የተቀናበሩ ዘገባዎች ይቀርባሉ። በኦሮምያ ክልል ስለመጭዉ ምርጫ ምን አስተያየት አላቸዉ ነዋሪዎችን አነጋግረናል። አሜሪካ በኢራን ላይ ልትፈጸም የምትችለው ጥቃት የምሽቱ ዜና መጽሔት የያዘዉ ሌላዉ ጉዳይ ነዉ።

የየካቲት 19 ቀን 2018 ዓ.ም የዜና መፅሔት 26.02.2026

በዛሬው መጽሔታችን አምስት ርዕሰ ጉዳዮችን በትንታኔ እናስደምጣለን ፤ ብሔራዊ ምርጫ በ5 የምርጫ ክልሎች ላይ ያሳለፈው ውሳኔ "ለጊዜው ታግዶ እንዲቆይ" መታዘዙ፤ ክራይሲስ ግሩፕ ለኢትዮጵያና ኤርትራ ውዝግብ ያቀረበው ምክረ-ሀሳብ፤ 2025 በኢትዮጵያ ጋዜጠኞች ላይ "ሰፊ እሥራቶች፣ አፈናዎች እና ትንኮሳዎች የተጋረጡበት" ነበር መባሉl ፤ «የምግብ ድጋፍ ተነፈግን» ያሉ ተፈናቃዮች ለከፋ ስቃይ ተዳርገናል ማለታቸው ፤ በዝርዝር ይደመጣሉ።

የየካቲት 18 ቀን 2018 የዜና መጽሔት 25.02.2026

-የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣንት ፍቃዱን የሰረዘበት አዲስ ስታንዳርድ ሥራዉን አለማቋረጡን አስታወቀ።የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን ትናንት ባሰራጨዉ ደብዳቤ የአዲስ ስታንዳርድ የምሥክር ወረቀት መሰረዙን አሰታዉቆ ነበር።--የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ ትናንት ያደረጉት ዓመታዊ የመርሕ ንግግር በአብዛኛዉ ሐሰትን ከዕዉነት የቀየጠ መሆኑን አጥኚዎችና ተንታኞች አስታወቁ።ትራምፕ በኢራን ላይ የሰነዘሩት ዛቻም ከቴሕራን ጠንካራ አፀፋ ገጥሞታል። --በግሪጎሪያኑ አምና 2025፣ 129 ጋዜጠኞች መገደላቸዉን የጋዜጠኞች መብት ተሟጋቹ ኮሚቴ CPJ አስታወቁ።አብዛኞቹን ጋዜጠኞች የገደለችዉ እስራኤል ናት።

Poslouchej podcast ዜና መጽሔት v Replaio

Rádio a podcasty v jedné aplikaci - zdarma a bez registrace. Nainstaluj si ji ještě dnes a nepropásni premiéru

Stáhnout z Google Play

Replaio není vydavatelem podcastů; názvy pořadů, obálky a audio patří jejich autorům a šíří se přes veřejné RSS kanály