DW

ስፖርት | Deutsche Welle

Games AM ↓ Episoade: 70

ት እንቅስቃሴ የሚታይበት ዝግጅት ነው።

Vizitează neapărat site-ul podcastului și susține-i creatorul: www.dw.com?maca=amh-podcast_amh_sportmagazin-13629-xml-mrss

Autor

DW

Categorie

Games

Cel mai nou episod

12 oct. 2026

Unde asculți?

Podcasturi în aplicație Replaio Radio În curând

Podcasturile ajung în curând în aplicație. Instaleaz-o acum și fii primul care descoperă o abordare complet nouă a podcasturilor

Descarcă din Google Play Instalează gratuit Android aproape 10 mil. descărcări · nota 4,8 iOS în curând

Episoade

ሣምንታዊ የስፖርት ዘገባ 15.06.2026
የሰኔ 8 ቀን፣ 2016 ዓም የስፖርት ዘገባ 15.06.2026

ተጠባቂው የዓለም ዋንጫ በድምቀት ተጀምሯል ። የጀርመን ብሔራዊ የእግር ኳስ ቡድን እስካሁን ከተደረጉ ግጥሚያዎች በአጠቃላይ በአንድ ጨዋታ በርካታ ግቦችን ከመረብ በማሳረፍ ቀዳሚ ብሔራዊ ቡድን ኾኗል ። አትሌቲክስ እና ሌሎች ዘገባዎችንም አካትተናል ።

የሰኔ 1 ቀን 2018 ዓ.ም የስፖርት ዘገባ 08.06.2026

ያሳለፍነው ሳምንት መጨረሻ በዓለም አቀፍ የአትሌቲክስ መድረኮች ላይ የኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ ከፍ ብሎ የበራበትና የአትሌቶቻችን የበላይነት የታየበት ሆኖ አልፏል። በሩሲያ እና በኢጣሊያ በተደረጉ ታላላቅ ውድድሮች ላይ አትሌቶቻችን ድንቅ ስኬት አስመዝግበዋል።በሌላ በኩል እንደ አውሮፖውያኑ አቆጣጠር 2026 የሚካሄደው የዓለም ዋንጫ ሀሙስ ይጀምራል።

የሰኔ 1 ቀን 2018 ዓ.ም የስፖርት ዘገባ 08.06.2026
የግንቦት 17 ቀን፣ 2018 ዓ.ም የስፖርት ዘገባ 25.05.2026
የግንቦት 17 ቀን፣ 2018 ዓ.ም የስፖርት ዘገባ 25.05.2026

ኢትዮጵያውያን እና የምስራቅ አፍሪካ አትሌቶች ደምቀው የዋሉበት የተለያዪ የአትሌቲክስ ውድድሮች ተካሂደዋል። የአፍሪካ ኬፕ ታውን ማራቶን የኢትዮጵያውያን ድርብ ድል የተሰራበት ነበር። በሌላ በኩል የእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ ትላንት ምሽት የአርሰናል ዘውድ መጫን፣ የዌስትሃም መውረድ እና የስንብት እንባዎች አስተናግዶ ተጠናቅዋል።

የግንቦት 10 ቀን፣ 2018 ዓ.ም የስፖርት ዘገባ 18.05.2026

ጋና አክራ ውስጥ በተከናወነው የአፍሪቃ አትሌቲክስ ፉክክር ኢትዮጵያ በሜዳሊያ ብዛት በ3ኛ ደረጃ አጠናቅቃለች ። ኤርትራ በ1 ብቸኛ ግን ደግሞ በወርቅ ሜዳሊያ 16ኛ ደረጃ አግኝታ የወርቅ ሜዳሊያ ማግኘት የተሳናት አስተናጋጇ ጋናን በልጣለች ። በፕሬሚየር ሊጉ ዛሬ ማታ መሪው አርሰናል እንዲሁም ነገ ተከታዩ ማንቸስተር ሲቲ ወሳኝ ጨዋታ አላቸው ።

ሣምንታዊ የስፖርት ዘገባ 18.05.2026
የግንቦት 3 ቀን፣ 2018 ዓ.ም የስፖርት ዘገባ 11.05.2026

ሞሮኮ ውስጥ ትናንት በተከናወነው የራባት ማራቶን ውድድር ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በወንድም በሴትም መድረኩን ሙሉ ለሙሉ ተቆጣጥረው በአስደናቂ ውጤት ለድል በቅተዋል ። አርሰናል የማታ ማታ ከጉድ ወጥቷል ። በቡንደስሊጋው ወራጅ ቀጠና ቡድኖች ግብግቡ ቀጥሏል ። ሌሎችንም ጨምሮ ሙሉ ዘገባውን በድምፅና ጽሑፍ ከማገኛኛው ይከታተሉ።

ሣምንታዊ የስፖርት ዘገባ 11.05.2026
የሚያዝያ 26 ቀን፣ 2018 ዓ.ም የስፖርት ዘገባ 04.05.2026

በአውሮጳ ሻምፒዮንስ ሊግ እግር ኳስ በነገው ምሽት አርሰናል እና አትሌቲኮ ማድሪድ ይፋለማሉ ። የአትሌቲኮ ማድሪዱ አንቷን ግሪዝማን በሻምፒዮንስ ሊግ ፍጻሜ ያላጠናቀቀውን የቤት ሥራ ነገ ማታ አርሰናል ላይ ለመፈጸም ዝቷል ። የዕድሜ ጉዳይ በኢትዮጵያ አትሌቲክስ እጅግ አነጋጋሪ ኹኗል ። ሙሉውን ዘገባ በድምፅና በጽሑፍ በማገናኛው ማግኘት ይቻላል ።

ሣምንታዊ የስፖርት ዘገባ 04.05.2026
ማን ለዋንጫ ያልፍ ይሆን? ባዬርን ሙይንሽን ወይንስ ፓሪ ሳንጃርሞ? 28.04.2026

ዛሬ ማታ ከጥቂት ሰዓታት በኋላ ለአውሮጳ ሻምፒዮንስ ሊግ ግማሽ ፍጻሜ ፍልሚያ ፓሪስ ከተማ ውስጥ የጀርመኑ ኃያል ባዬርን ሙይንሽን እና ፓሪ ሳንጃርሞ ይገናኛሉ ። ማን ያሸንፍ ይሆን? የጀርመኑ ብሔራዊ ቡድን የቀድሞ ተሰላፊ ቶኒ ክሮስ ባዬርን፤ ፕሬዚደንት ኤማኑዌል ማክሮ ፓሪ ሳንጃርሞ ብለዋል ። ሙሉ ቃለ መጠይቁን በማገናኛው ማድድመጥ ይቻላል ።

የሚያዝያ 19 ቀን፣ 2018 ዓ.ም የስፖርት ዘገባ 27.04.2026

አዲስ አበባ ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ ስለተከናወነው አወዛጋቢ የድብልቅ ማርሻል አርት ፍልሚያ ሰፋ ያለ ቃለ መጠይቅ ይኖረናል ። በለንደን ማራቶን የወንዶች ፉክክር ከሁለት ሰዓት በታች በመግባት አዲስ የዓለም ክብረ ወሰን ተመዝግቧል ። የአትሌቲክስ፤ የእግር ኳስ እና ተጨማሪ የስፖርት ዘገባዎችንም አካተናል ። ሙሉ ዘገባውን ማገናኛው ማድመጥ ይቻላል ።

የሚያዝያ 12 ቀን፣ 2018 ዓ.ም የስፖርት ዘገባ 20.04.2026

በዛሬው የስፖርት መሰናዶ፦ አዲስ አበባ ውስጥ ስለተደረገው የመጀመሪያው ግራንድ ፕሪ ፉክክር ዘገባ ይኖረናል ። ባዬር ሙይንሽን ከወዲሁ ዋንጫውን ማንሳቱን ስላረጋገጠበት የጀርመን ቡንደስሊጋም ዳሰሳ ይኖረናል ። ማንቸስተር ሲቲ አርሰናልን ድል አድርጎ በነጥብ ተጠግቶታል ።

ሣምንታዊ የስፖርት ዘገባ 20.04.2026
ሣምንታዊ የስፖርት ዘገባ 13.04.2026
የሚያዝያ 5 ቀን፣ 2018 ዓ.ም የስፖርት ዘገባ 13.04.2026

አዲስ አበባ የመጀመሪያውን «የአዲስ አበባ ግራንድ ፕሪ» ፉክክር ልታሰናዳ ነው ። ቃለ መጠይቅ ይኖረናል ። እድሜያቸው ከ17ና ከ18 ዓመት በታች የኢትዮጵያ ብሔራዊ የሴቶች የእግር ኳስ ቡድኖች ድል ቀንቷቸዋል ። ሦስት የዓለማችን ምርጥ ቡድኖች ከሻምፒዮንስ ሊግ ሊሰጫፍ ላይ ደርሰዋል ። ሙሉ ዘገባውን በጽሑፍና ድምጽ በማገናኛው ማግኘት ይቻላል ።

የመጋቢት 28 ቀን፣ 2018 ዓ.ም የስፖርት ዘገባ 06.04.2026

ባለፈው ቅዳሜ በፈንሳዊቷ ሊል ከተማ በተካሄደው የአምስት ኪሊሜትር ሩጫ ውድድር ኢትዮጵዉያን አትሌቶች ድል ቀንቷቸዋል።በሌላ በኩል አርሰናል እና ሊቨርፑል በኤፍኤ ካፕ የሩብ ፍፃሜ ያልተጠበቀ ሽንፈት አስተናግደዋል።

የመጋቢት 21 ቀን፣ 2018 ዓ.ም የስፖርት ዘገባ 30.03.2026

የኢትዮጵያ ብሔራዊ የእግር ኳስ ቡድን ከሳኦቶሜና ፕሪንሲፔ ቡድን ጋር ለአፍሪቃ ዋንጫ ማጣሪያ የቅድመ ማጣሪያ ሁለተኛ ጨዋታውን በነገው ዕለት በድሬዳዋ ስታዲየም ያከናውናል ። የጀርመን እግር ኳስ ቡድን በወዳጅነት ግጥሚያ ድንቅ ጨዋታ ዐሳይቶ የስዊትዘርላንድ አቻውን 4 ለ3 አሸንፏል ። ይህን ጨምሮ ሙሉ ዘገባው በድምፅና በጽሑፍ ከማገናኛው ይገኛል ።

የመጋቢት 14 ቀን፣ 2018 ዓ.ም የስፖርት ዘገባ 23.03.2026

በዓለም የቤት ውስጥ አትሌቲክስ ፉክክር ኢትዮጵያ እጅግ ደካማ ደረጃ ይዛ አጠናቅቃለች ።ቃለ መጠይቅ ይኖረናል ። በካራባዎ ፍጻሜ የማንቸስተር ሲቲ አርሰናል ላይ የተቀዳጀው ድል፣ የጀርመን ቡንደስ ሊጋ እና ሌሎች የስፖርት ዘገባዎችንም አካተናል ። ሙሉ ዘገባው በድምፅና በጽሑፍ ከማገናኛው ይገኛል ።

ሣምንታዊ የስፖርት ዘገባ 23.03.2026
የመጋቢት 7 ቀን 2018 ዓ/ም የስፖርት ዝግጅት 16.03.2026
የመጋቢት 7 ቀን 2018 ዓ/ም የስፖርት ዝግጅት 16.03.2026

በአትሌቲክስ ኢትዮጵያዉያን አትሌቶች በሳምንቱ የመጨረሻ ቀናት በተለያየ የዓለም ክፍል ታላላቅ ድሎች የተጎናጸፉባቸው ዉጤቶች ተመዝግበዋል። የኢትዮጵያ ታሌቲክስ ብሄራዊ ቡድን ፖላንድ በምታስተናግደው የዓለም አትሌቲክስ የቤት ውስጥ ውድድር ላይ የመሳተፉ ነገር ገና ርግጥ አልሆነም።

ዳግም የቪዛ ክልከላ በኢትዮጵያ አትሌቲክስ ቡድን ላይ 11.03.2026

የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ቡድን የፊታችን ዐርብ ፖላንድ ውስጥ በሚጀምረው የዓለም አትሌቲክስ ውድድር ለመሳተፍ የሚያስችለውን ቪዛ እስካሁን አላገኘም ። ፖላንድ ለመግባት የሚያስፈልገውን የሸንገን ቪዛ ለማመልከት 45 ቀናት እንደሚያስፈልግ የጠቆሙ አሰልጣኝ ይህንኑ ከሦስት ወራት በፊት ብናገርም ሰሚ አጥቻለሁ ብለዋል ።

Ascultă podcastul ስፖርት | Deutsche Welle în Replaio

Radio și podcasturi într-o singură aplicație - gratuit și fără înregistrare. Instaleaz-o azi și nu rata lansarea

Descarcă din Google Play

Replaio nu este editorul podcasturilor; numele emisiunilor, coperțile și materialul audio aparțin autorilor lor și sunt distribuite prin fluxuri RSS publice