Leoul Zewelde

Sost kilo

Fiction AM ↓ 38 episodes

Stories.https://linktr.ee/sostkilo

Author

Leoul Zewelde

Category

Fiction

Podcast website

t.me

Latest episode

Aug 20, 2023

Where to listen?

Podcasts in the app Replaio Radio Coming soon

Podcasts are coming to the app soon. Install now and be the first to see a whole new take on podcasts

Get it on Google Play Install for free Android almost 10M downloads · 4.8 rating iOS soon

Episodes

አሁን ምን ያደርጋል የሴት ወየው ባይ፣ ወሎ የመጣው ሞት ሸዋ የለም ወይ? 14.12.2021

Leoul zewelde | Podcaster : Yeab Dems ምክንያት ይሰጡት እንጂ ፥ ሞት አይቀርም ። ተዘጋጅተው አይጠብቁት ነገር ደግLምክንያትዳ እንጂ ሙሽራ አይደለም ። በጦርነት ግፎች እንደሚሞት ሁሉ በሰላም ውስጥ ተኹኖም ይሞታል ። በረሃብ አረንቋ እንደሚሞት ፥ በጥጋብና አለቅጥ ውፍረትም ይሞታል ። ኤሊያሶች አይደለን አንዳናርግ ፥ ሮሙለስ አይደለን አንሠወርም ። ለማን እንደራራው - ለማን እንደሳሳው ይተወናል ? በአንድ ወቅት የሸዋረጋ ምኒሊክ ፥ የንጉሥ ሚካኤል ባለቤት ፥ ከወሎ አገር መከተሟን ሸዋዎች አልወደዱም ነበር ። ይህ አለመውደዳቸው ከወሎና ሸዋ ባላንጣነት ፥ ማለትም ከልጅ እያሱ መፈንቀለ መንግስት ጋር ይገናኛል...

የ አ ረ መ ኔ ፡ ክ ር ስ ት ያ ኖ ች ፡ ዘ ር ፡ ማ ጥ ፋ ት 31.10.2021

በመካከለኛው ዘመን ፥ አውሮጳ ግሪጎሪ ፱ኛ የተባለ ድመት ጠል ጳጳስ ትቀባለች ። ይህ እብሪተኛ ሰው በትረ ሙሴውን በጨበጠ ማግስት በፀሊም ድመቶች ላይ የዘር ማጥፋት (*Pogrom) አወጀ ። ይሄ አሰቃቂ የእልቂት አዋጅ በድመታውያን ታሪክ በክርስትያኖች የተፈፀመባቸው ትልቁ በደል ነው ። ነገሩ የሆነው እንዲህ ነው ። ተራማጅ እንደሆነ በአንደበቱ የሚናገረው ጳጳስ የጵጵስና ማዕረጉን ያገኘው በልጅ እግሩ በሰማንያ ዕድሜው ነበር ። መንበሩን እንደተቀበለም እረፍት አጥቶ ቀኖናዎችን ያሻሽል ገባ ። መታተሩንና እረፍት ማጣቱን ያዩ ሮማውያን የለውጥ ሐዋርያቸው አድርገው ተቀበሉት ። ለፍቅርና እምነት የተቀባው ጳጳስ ግን ነገረ ሥራው በየዓው...

የክብ መጨረሻ | Book: ጉራማይሌ 07.10.2021

የክብ መጨረሻ ፥ መጀመሪያው ነው ።

ያን ቀን ባታቆላምጪኝሥ? | ያልተላኩ አምስት መልዕክቶች ፥ መልዕክት - 2 23.09.2021

ያ ን ፡ ቀ ን ፥ ባ ታ ቆ ላ ም ጪ ኝ ስ ? [ ል ዑ ል ፡ ዘ ወ ል ደ ] ከወፍራም ብርጭቆ ላይ እያበረደች የምትቀምሰው ወተት የከንፈሯን ዳር በስልባቦት ይኩላል ። የአፏን ወተት ለመግፈፍ እጄን ሰድጄ ግልፋፊውን በጣቴ አስቀረሁ ። ያስቀረሁትን ቀመስኩ ። የላስኩትን ኬሚስትሪ ጣዕም ለማስረዳት ይቸግራል ። ሀይድሮጅን ደርድረው በቦንድ ቢስሉት ዘርፉ ከአሮጌ ዋርካ ይገዝፋል። ቤሎንዥ ፥ ዛሬ ንጋት ላይ ከፓሪስ-ቻርል የገባች ነው ። ስለሚደክም ፥ ችላ የምትመጣም አልመሰለኝም ነበር ። ለገሃር ሳባ ኬክ ቤት ተገናኘን ። ሳፊ ወተት ጋበዝኳት ። ግብዣው የይቅርታ ነው ። ከአምስት ቀን መዘጋጋት በኋላ የሀቅ ኩርፊያዬን ካድኩ ። ጥፋቱ...

ች ግ ራ ች ን ፡ ም ን ፡ ነ በ ር ? 16.09.2021

ሌላ ያልነገርኩሽ ፥ የልደትሽ ቀን አበባ ገዝቼ ነበር ። አዎ ! እኔ ። የሚገርምሽ ባገሩ እንደጠፋ ሁሉ የትናየት ሄጄ መሰለሽ ? መጨረሻ ላይ ወሰን ምናምን እሚሉት ሰፈር ትንሽዬ ኪዮስክ ውስጥ ትልቅ መቀስ የያዘች ሻጭ አየሁ ፤ ፈንታቸው መርገፍ የሆኑ ቅጠሎችን እየከረከመች። እንዲሁ ልጅ ሳለሁ ፥ ከትምህርት መልስ ሙሽራ የሚሉትን አበባ ከሰው አፀድ ቀጥፌ ወደቤቴ እሮጥልሻለሁ ። ቤት ልደርስ 'ከባቢ እጄ ከአበባው ተሻሽቶ ኖሮ ፥ ወየበ ። ከቆረጡት ኋላ ቶሎ የሚሞት አይነት ዘር ሆኖም ይሆናል ። ብቻ እጄ ላይ ከስሞ ፥ ነደደኝ ። የቀጠፍኩት እንዲያ እንዳማረበት ለ'ናቴ ልሰጣት ነበር ። ያም ሆኖ አልተውኩትም ። ከስራ መምጫዋን ጠብ...

Intala mootii 11.08.2021

አባት ሆይ … ! ፀልዬ አላውቅም - ብዙ እንዳትታዘበኝ ፤ ዛሬን ብቻ… ጆሮ ዳባ ሳትል … ለሥጋዬ ውሉድ ፥ አንዲት ማቲ ዋጀኝ ። 'ሴት' ሆና የማምናት ፤ ካለ ሚስት አለናት ፥ አባት 'ምሆናት ። አንዲት ልዕልት ማቲ ሳይጋሩኝ የምወዳት - ሳትጋራ የምትወደኝ አቤቱ - በረቂዮትህ ዋጀኝ ። ጡት ብነሳ እንደማልጋ ላም ባላግት ፥ ወተት ባላደማም ጀባ'ኝ እንጂ ፥ እንደ'ዶሮ ጭሬ አፀድቃታለው ህይወቴ የሷ መንግስት ነው ። አባት ሆይ … ፀልዬ አላውቅም - ብዙ እንዳትታዘበኝ ፤ ዛሬን ብቻ… ጆሮ ዳባ ሳትል … ለሥጋዬ ውሉድ ፥ አንዲት ማቲ ዋጀኝ ።

ዝ ም ታ ህ ን ፡ ማ ረ ኝ 04.08.2021

በያንዳንዱ የእምነት ክሬ እንደሹራብ ተተርትሬ እንዳልጣፍ እንዳልሰፋ ሆኛለው የቀረኝ ጨርቅ ከቅዳጄ ያነሰ ነው ። የሲዖል መልህቅ ከግሬ ታስሯል እፍግ ሰንሰለቱ እሄድኩት ድረስ ይረዝማል ቁርጭሚቴ ካልቦ ያለረፍት ይንቋቋል ህልው ምልክቴ ጠፍረ ባርያ ሆኗል ። * * * ቀደም . . .በሌት ግርማ ታውሬ ስቀይርህ ሳፈስህ ከደምስሬ በፋኑዔል ክንፍ ሰበዝ ደምቀለም ነክሬ ነብሴን ላውሬ ስቤዥ ዝም ብለኸኛል ! በካሚዮን ከሚንቦገቦገው በጥፍሮቹ ምድርን ቧጦ ከከበበው አይሆኑ ውዬ ለሌጊዮን ግዞት ስሸጥ በፊርማዬ ደግመህ ዝም ብለኸኛል ! በዚ ዝምታህ ዘላለምን ንቄ ቀቢፅ አፍታን ቃረምኩ ባይኖር ነው ብዬ ውድ ነብሴን ገበርኩ ። * * * ጌታዬ አ...

Excerpt : እና ፥ እየዘነበ ነው . . . 27.07.2021

ብዙ ግዜ እግሮቼን ይዞ የሚያስቀረኝን ማጥ የማቦካው እኔ ራሴው ነኝ ። ለዚህም ነው ድብርቴን ያመጣው ጭጋጉ ይሁን ጭጋጉ የመጣው በኔ ድብርት እርግጠኛ ያልሆንኩት ። በየግዜው የሚነሱብኝን ወጀቦችን እያሳለፍኩ እቆያለሁ - እኖራለሁ ለማለት እንኳ ትንሽ ይከብደኛል ። በአጭሩ ህይወቴ በረከት ርቋት ድንገት የሚወርድ ሲሳይ መጠበቅ ከጀመርኩ ቆየሁ ። ሰማዩ ገና ማስገምገም ሲጀምር ከጀርባዬ ያለውን መጋረጃ ለሁለት ከፍዬ ወደላይ አንጋጠጥኩ - ዳመናው ፅልመት አዝሏል ። አከታትሎ መብረቅ ወረደ ። ሁሌ አይቶ እንደማያውቅ ያስበረግገኛል ። ፀሃፊዬ " ድምፁ እኮ ዘግይቶ ነው የሚደርሰው ፤ መፍራት ያለብህ ብርሃኑን ነው " ስትለኝ ይሰማኛል ።...

'ወድሃለሁ ስትይ - ስሜቱን ግን ታውቂዋለሽ ? 09.04.2021

. . . ምልዓተዓለም ፀጥ እንደሚል ፤ ልቤ የምር እንደምትታፈን ፤ እግሬ እንደሚቀዳደም ፤ ብሌኖቼ እንደሚሰፉ ፤ ሳይታዘዝ ጉንጬ እንደሚፈግግ ፤ እየሄድኩ መቆም እንደሚያምረኝ ፤ እየቆምኩ መሄድ እንደሚያሰኘኝ ። ዝለል ዝለል እንደሚለኝ ፤ ሸራ ጫማዬን ፈትቼ እንደማስር ፤ ስልኬን አውጥቼ ሳልደውል መልሼ እንደምከተው ፤ ሽቶሽ ከየትም እንደሚሸተኝ ፤ የት መሄዱን ሳላውቅ ታክሲ እንደምሳፈር ፤ በውጥንቅጥ መሀል አንቺን ብቻ እንደማስብ ፤ የምጠላው ሙዚቃ እንደሚመስጠኝ ፤ አልፎ - ደንስ ደንስ እንደሚለኝ ። ሀይል ገላዬን እንደሚወር ፤ ደረቴ እንደሚረበሽ ፤ ላለፈ ለማኝ ሁሉ መቶ ብር ስጥ-ስጥ እንደሚለኝ ፤ በቀን እንደማልም ፤ ይለወ...

ታኂሬ- Bonus episode - Mar08. 08.03.2021

...

ለመውደቅ ግን ተሥፋ አለኝ • 07.03.2021

አንድ ልጇ ዱርዬ ሆኖ እንዳሸነፋት እናት … በካር ማህፀኗ ሌላ ዘር ሳይዝ … እሱኑ ስትል አሳድጋ… ሲያፄም ግዜ ከእጇ እንደወጣ… ደምላቧ ከንትቶ የምትኖርለት ሌላ ምክንያት እንዳጣች … ብዙ ብዙ ሄዶ እግዜርን ከቦታው እንዳጣ ቄስ … እድሜውን ሙሉ የቀራቸው መፃህፍት እርባን እንዳጡበት … ረፍዶ ከመመለስና ፣ ተሳስቶም ከመሄድ ምርጫ እንዳጣ … በሁለት የቂጡ ጉንጮች ሁለት ወንበር ላይ እንደተቀመጠ … … ተሥፋ አጥቻለው … አሳዳሪው አረጀህ ብሎ እንዳባረረው ውሻ ። እድሜ ዘመኑን በሳጥን ታጥሮ ኖሮ … ከግቢው ሲወጣ አቅም ከድቶት ቁጊያም እንደሆነ … የሰፈር ውሾች ሊነክሱ እንደሚያሳዱት … እድሜ ይፍታህ ታስሮ ድንገት በአመክሮ እንደ...

ጭንቀቴ መች ገባሽ 02.03.2021

…ጭንቀቴ… ድር እንዳጠመደው ዝንብ ነው ። ሸረሪቷ ካሁን አሁን መጣች እያለ እንደሚሳቀቅ … ክንፉን እያማታ… የትም እንደማይፈናፈን… …ጭንቀቴ…ለወር ታህል ቋጥራ እንደሚሾትልባት ነብሰጡር ነው ። ማህፀኗ አልረጋ እንዳላት … ዘጠኝ ወር ርቆ … የምልጃዋን ማርያም … ማርያም እንደምትል … ጭንቀቴ…ከእናት አባቱ ጥል አምልጦ እንደወጣ ህፃን ነው ። … የሚሮጥ መድረሻ የሌለው… ልጋጉን እየሳበ በለንባዳ አፉ እንደሚያለቅስ … …ጭንቀቴ … ፈረሰኞች በሌት መጥተው ጎተራውን እንዳነደደቡበት መጤ ነው ። ነጋጠባ ውጣልን እንደሚባል … ከአመድ ክምር ላይ ተቀምጦ… በለበቅ መሬት እንደሚጭር … …ጭንቀቴ… ደግመው ደጋግመው እንደደፈሯት ማቲ ነው...

•••ሥትናፍቂኝ 10.01.2021

ስ ት ና ፍ ቂ ኝ [ ል ዑ ል ፡ ዘ ወ ል ደ ] ስትናፍቂኝ … ባሏ ለዕድሜ ይፍታሕ ወህኒ እንደተወረወረባት ሴት ነው ። መልሳ ላታገኘው ነገር እሁድን እየጠበቀች እንደምትጠይቀው … ስትናፍቂኝ … ሲዖል ተኮራምቶ ገነትን እንደሚያልም ሠይጣን ነው ። ምህረት ሱሚ ሆኖበት በልቡ ማብከሪያ እንደሚለምን ። ጥፍሮቹን ቢከረክም'ም ርህራሄ ተነፍጎት ምናልባትን እንደያዘ… ስትናፍቂኝ … በምናብሽ የሚሄድ አስፋልት ሣይና በዛ ላይ በተቃራኒ አቅጣጫ የሚጓዝ ከንቱ ደሞ አስቢ ። እየሄደ የሚመስለው ግን አንድ ቦታ ላይ እንደቆመ ። ኃይሉ ሲሟጥ አስፋልቱ በራሱ አቅጣጫ እያንደባለለ እንደሚወስደው … ስትናፍቂኝ … ወደቀኝ እንደሚዞር ሽክርክር ሰዓት...

Listen to the Sost kilo podcast in Replaio

Radio and podcasts in one app - free, with no sign-up. Install today and do not miss the launch

Get it on Google Play

Replaio is not a podcast publisher; show names, artwork and audio belong to their authors and are distributed through public RSS feeds.