Leoul Zewelde
Sost kilo
Stories.https://linktr.ee/sostkilo
Où écouter ?
Les podcasts dans l'appli Replaio Radio Bientôt disponibleLes podcasts arrivent très bientôt dans l'appli. Installe-la dès maintenant et découvre en avant-première une toute nouvelle façon de vivre les podcasts
Épisodes
የራህባን ጭስ 20.08.2023 11:18
#Spotify #Sostkilo #shortstory
ሮዛ ሮዚና 14.05.2023 10:38
ሮማናት – ናሽናል ካፌ . . . ሮዝ አገሯ ያለ ካፌ ስትቀጥረኝም ሆነ ቀጥራኝ ስትቆይ ለመጀመሪያ ግዜ ነው ። እንደደረስኩ ወፍራም የማሽን ቡና አዝዤ እሱን እየጠጣሁ ጥበቃዬን ጀመርኩ ። ካፌው ውስጥ ዝንቦች እንዳያስቸግሩ በሚል በየጠረጴዛው የሊም ቅጠል ተነጥፏል ። ውስጥ የሚተራመሰውን ሰው ...
የመንታ እናት ፖለቲካ ! 05.05.2023 12:40
የ መ ን ታ ፡ እ ና ት ፡ ፖ ለ ቲ ካ [ ል ዑ ል ፡ ዘ ወ ል ደ ] ለማበጠር ጀምራው ከነበር ፀጉሯ ውስጥ እጇን ወትፋ "ዋ………ይ"ብላ ጮኸች ። እሪታዋ ርዝመቱ በመሃል ቅላፄዋ እስኪለዋወጥ ነበር ። ጩኸቷን ተከትሎ ቤቱ ውስጥ ፀውታ (*ፀጥታ + ክውታ) ሰፈነ ። የድንገት ጩኸቷ ከሷ በፊት ሲርገበገቡ የነበሩ ሁለት የመንትዬ እንጥሎችን አርግቧል ። ሣራ ያለግዜ የመጣችባት ፅጌዋ(*ፔሬዷ) ምቾት ነስታት ድምፅ የሚባል ነገር መስማት አስጠልቷታል። አንዴ አግና በለቀቀችው ጩኸቷ ያሰፈነችውን ፀውታ ቶሎ ለመጠቀም አሰበች ። ከጆንያ ላይ ሃባ ክር መዛ ልጆቿ የተጣሉበትን ፊኛ የኮመዲኖው ጠርዝ ላይ ቋጠረችው። ድምር ለቅሷቸው ሲያስጨንቃት...
የአላውያን ሣልዮን | Good Friday 14.04.2023 0:42
Leoul Zewelde የሮም ወታደሮች እየተዟዟሩ ሶስቱ ዛይሎኖች ላይ ቅናዋት ሲወቅሩ ይታየናል በሩቅ … ከካህናት ዕሠይ ፤ ካይሁድ ጉርምርምታ አልፎ የሚረብሽ የአንዲት ሴት ስቅስቅታ ይሠማናል ከሩቅ … ለተጓዥ አላውያን መንፈቅ ትርዒት ፥ ከሩቅ ለምናየው …የአርብ መንገድ አድክሞን ከመስቀሉ ጀርባ ተጋርደን ለቆምነው … ክርስትና ርዕዮት ነው !
ያልተላኩ አምስት ቴክስቶች - Message 3 | Part II 18.02.2023 10:36
ያልተላኩ አምስት ቴክስቶች - Message 3 | Part II
ዛሬ ፥ ጨረቃዋን አይተሻታል ? ... ፩. አዲስ አበባ ፥ ካምፕ አስመራ 15.01.2023 3:08
ያልተላኩ አምስት ቴክስቶች ፤ Message 3
ኪ ሣ ኬ ሣ ፥ አ ዱ ሬ ን ፡ ቢ ኔ ሳ 17.11.2022 9:56
ራቢራ ሱራ ነኝ ። ቢራዬን እንደትኩስ ሻይ ...
የእውነት እውነት ፥ እወድሻለሁ ! 17.10.2022 1:55
ውብትሽን ከሩቅ ለሚያይ 'ፍዝ' ነው ። ሎሚ እንዳቤዠው ሻይ ፥ ካልቀመሱት የአይን ስህተት ነው ። ይሄን ብዥታ እንደሀቅ ተቀብለው ፥ ይገፉሻል ። ለእኔ ግን ፥ ጣዕምሽን አውልዬ ለማውቀው ፥ ለሰው ብዬ አይደለም ! ከሰው መጥቶ አይደለም ! የእውነት ነው ። ከማታውቂው አገር ብትኮምሪ ፥ የቤትሽ የመጨረሻ ሰካራም ፥ እኔ ነው ምሆነው ። ትተሽ ብታዘምሪ ፥ ጭራ ልጌ አጅባለው ። ለእኔ ? ጣዕምሽን አውልዬ ለማውቀው ፥ ለሰው ብዬ አይደለም ! ከሰው መጥቶ አይደለም ! የእውነት ነው ። በፀጋ ሆነ ቅባት ፥ ብቻ ከአንዱ ሆነሽ ብትነፍቂ ፥ ጥላ ጥለትሽን ይዤ እከተልሻለው ። አንቺ በምታምኚው ፥ እኔ እታነመናለሁ ። ውርስ ሥጋዬ ለስደትሽ...
ሽ ፍ ደ ት ፡ በ አ ይ ን ፡ ይ ገ ባ ል ... 21.07.2022 15:10
የተንጣለለው አስፋልት በሚረግፈው የዳመና ቡትርፍ እየታጠበ ነው ። አቶ 'ሀ' ( ይቅርታ ፤ ስሙን ስለማላውቀው ነው) ጭር ባለው ጎዳና እየተዘነበበት ወደቤቱ ያቀናል ። ተበታትኖ የሚወርደው የጨፈጨፍ ናዳ ሲያርፍ ይዘልና ሌላ ቀድሞ የወረደ ጨፍ እየያዘ ወደዳር ይንቆረቆራል ። ተርታውን ያቀረቀሩት የመንገድ ዳር መብራቶች ገና ሳይመሽ በስህተት ብርሃናቸውን ወልተዋል ...
ኦቾሎኒ - አለንጋና ምስር | 1985 ሆላንድ 17.07.2022 59:01
ለአዳም ረታ - የልደት ማስታወሻ
አስኩቲን በትኩሱ:) 03.07.2022 1:29
የችኮላ ሥራ ሲገጥመኝ ትዝ የምትለኝ ነገር ነች። ቄራ ላይ የሆነ ነው ፥ ያው እንደጨዋታ ። አስኩቲ የሚባል እሳት ሞተረኛ ...
ከ ሀ - ፐ ስንት ኪሎሜትር ነው ? 24.06.2022 4:10
Excerpt : ድምቡሎ ጎዳና | Short story.
አንቺ የወደድሽው ፥ እኔ የማልሆነው ••• 20.06.2022 1:28
ጀግና የወደድሽ ሰሞን ፤ ጀግና አሳድዳለው ። ጎሽ ገድዬ ኮልባ ሎቲ እቀርፃለው ። ከነብር ገላ ላይ ለአንገት በርኖስ እላጫለሁ •••
ብዥ 01.06.2022 7:56
በመሃል እራት አለመብላቴ ትዝ ብሎኝ ደሞ በባዶ ሆዴ ተከዝኩ ። ችግሮቼ በጣም ስለሚወዱኝ ብቻዬን አይተውኝም ፥ አንዱ እንኳ ሲሄድ አንዱን ተክቶ ነው ....
ዝንየት ሦስት : ተፃብዖ (ሰማያዊና ቀይ ኮላዥ) 04.05.2022 9:37
ይሄኔ ነው ትርዒቱ የተለኮሰው ። መጀመሪያ የበረንዳው አምፖል ላምባ እንደጨረሰ ኩራዝ ጥር ጥር ሲል ቆይቶ ዚግዛጉ እስኪታይ ድረስ ከሰመ ። ተደፍቶ በስንፍናዬ ያልወለወልኩት ውሃን ወለሉ ሲመጠውና ጠቦ ጠቦ ሲጠፋ አየሁ ። በድንጋጤ እግሮቼን ወንበሬ ላይ ሰበሰብኩ ። የግቢያችን መታጠፊያ ሾላ ዛፍ ላይ የተከመሩ ወፎች ተበተኑ ። እነሱን ተከትለው የዛፉ ፍሬዎች ሿ ብለው ረገፉ ....
ዝንየት ሁለት - ምርጫ ቀረበልኝ ፤ ከእውነት እና ፍቅር ? 27.03.2022 5:58
በሩ ሁለቴ ተንኳኳ ። ስከፍት የበሩን የውጭ ማዕዘን ተደግፋ ቆማለች ። ሰላምታ ሳትሰጠኝ አልፋኝ ገባችና ዘግቼው ወደሷ እስክዞር ጠብቃ " አርግዣለሁ " አለቺኝ ። ደንግጬ አየኌት ....
ዝንየት አንድ ፤ EP01 16.03.2022 10:04
የለበሰችው እጅጌ ሙሉ ፒትልስ ወልቆ ምኔ እርቃኗን እንደቀረች አታውቅም ። የተጨመታተረው አንሶላው ሀሩር ገላዋን እየነካ ሲቆጠቁጣት ገልፍፋ ጣለችው ....
ለምን ግን ትልቅ ሆነ ? 08.03.2022 6:14
ከትናንት ወዲያ ማታ ለት እናቴ እሪሪ ብላ እያለቀሰች ገረፈቺኝ ፤ እያነቡ እስክስታ ነገር ። ከደቂቃ በፊት ( ደብተሬ ላይ ጭረት እስካይና እስክጠይቃት) አገር ጎረቤት ሰላም ነው ብለን ስለ ሙሉ ቁጥሮች ተካፋይ ስታስረዳኝ ነበር ። ድንገት ተነስታ ጫማዋን አውልቃ አናት አናቴን እየጠፈጠች < ኧረ ሰዎች አቃተኝ ምናባቴ ላርገው ? > ብላ ለአገላጋዮቼ ታሳጣኛለች ፤ ሁለተኛ በደል ። ባህሪዋ ለማንም ግራ የሚገባ አይነት ነው ። እስኪ ልፈትናት ብዬ ሁለት ቀን የሚያስቅ ቀልድ ባወራት ራሱ ትንሽ ፈገግ ሳትል ወደ ጠብደል ምክር ትለውጠዋለች ። ምክሯ ከመብዛቱ የተነሳ አንዳንዴ እንዲሁ < ዛሬ አመክሪኝም ኣ ? > እላታለው ። በራሷ ስቃ...
#saynotowar 14.02.2022 2:52
... ረጅም የስደት ሰልፍ ፥ ሰሌን አናቷ ላይ ጠቅልላ የምትጓዝ እናት ፥ የታረዙ ብላቴኖች ፥ የተደፈሩ መበለት ፥ የተገፈፉ ክብሮች ፥ የከተማ ምሽጎች ፥ የተበሳሱ መስኮቶች ፥ የሚነዱ ቲያትር ቤቶች ፥ ከሰማይ የሚዘንቡ አረሮች ፥ በየቀጠናው የተማገዱ ጎረምሶች ፥ ባንጋ የቀላቸው አናቶች ፥ የሰቀቀን እሪታዎች ፥ ጆፌ የሚዞረው አንገት ፥ የልጁን ሬሳ የሚያናግር አባት ፥ ረጅም የእሾህ አጥር ፥ የስጋት ድንኳኖች ፥ ፈንጂ ዶሿቸው የሚደሁ ገላዎች ፥ እሳት አከፋፋይ ኦራሎች ፥ የነፍሴ አውጪኝ ትርምስ ፥ የሚያለቅሱ ቄሶች ፥ ሚናራቸው የወደቀ መስጂዶች ፥ የተጨነቁ ሩሆች ፥ የማይታይ ነጭ ባንዲራ ...
ሲመሽ ፤ ሲመሽ . . . ትዝ ይለኛል ! 09.02.2022 12:50
ሲመሽ – ፊት ላይ የሚለሰልስ ብርትኳናማ የፀሃይ ጨረር ሲፈናጠቅ – ከመስጂድ ሚናር የመግሪብ አዛን ሲሰማ – ህዝቤ ስራ ያንዠረገገው ሚስቶ ፊቱን ይዞ ወደቤቱ ሰከም ሰከም ሲል – የትራፊክና የፍሬቻ መብራቶች መድመቅ ሲጀምሩ – የእራት ወጥ ጢሶች ከየኩሽናው ወደሰማይ ሲወጡ . . . ሲመሽ ፤ ሲመሽ . . . ትዝ ይለኛል . . . !
ቻው ፡ ቻው | ጉራማይሌ መፅሐፍ 25.01.2022 11:23
እንደዛ ነው የሚያደርጉት ፤ ይሄዳሉ ። ምንም ሳይሉህ ይሄዳሉ ። እንደጨረቃ ሙላታቸው ይጎድላል - ይገምሳል - ይቀጥኑ ይቀጥኑና - በሆነ ቀን ቀና ስትል የሉም ። ለመከተያ እንኳ ዳና ሳይተውልህ - ልክ እንደ ወቅቶች ፤ እንዳምናዎች ፤ እንደትናንቶች ... ሄድን ሳይሉ ፥ ፍውው …! በዳ'ባድመ መሐል ጥለውህ ሄደውም እንዳልረሣሀቸው ማወቅ ይፈልጋሉ ። ይሄ መሻት እያደር ሲሞረሙራቸው ረፈዶ ከባቸ በኋላ 'ቻው' ይሉሃል ። ከሄዱ ከምናምን አመታት በኋላ አተኩሰው ይሰናበቱሃል ። ደሞ ቻው ሲሉህ . . . ቻው፡ቻው ! ያንተው ሃና ። …የደብዳቤው 31ኛ መስመር መቋጫ ላይ። ጠርዙን ቴምብር ካሽቆጠቆጠው ቅድ ፖስታ ውስጥ ለመጨረሻ ግዜ አው...
የተሸጠ ነብሥ ፥ አይመለስም••• 21.01.2022 9:23
ነብሴን በገዙኝ ማግስት የፀሓይን ሞት አረዱኝ ። በከባድ ምጥ ማለፏን እንደሰማሁ በዛለ ጀምበር ወደ ለቅሶው ሄድኩ። መቃብሯ የጀበል ቓፍ (*የምድር ጠርዝ) ኮረብቶች ላይ ነው ።ለቀሥተኛው እየተነዳዳ ወደ ቀብሩ ይግተለተላል። እንደህፃን እግር እየተከተልኩ መጓዝ ጀመርኩ። በገፍ ከሚጋዘዉ ለቀስተኛ እንባ የሚወጣኝ አንድ እኔ ነኝ ። ሌሎቹ የአይን መቅደሳቸው ተገልብጦ ከነጩ መቃድ የጠለሸ ደም ይፈሳል ። ዶቃ ብሌናቸው በቦታው የለም ። ወዮታቸውን ባልሰማም ከደረታቸው የሚነሳ ተደጋጋሚ ስቅታ ግን አለ። እየሄድን ነው ። ከፊቴ የቀደሙም ሆኑ ከጀርባ የተውኳቸው ለቀስተኞች አናታቸው የተመለጠ ሲሆን ከአናታቸው ዙርያ እንፋሎት ይጤሳል ። በተ...
የመጨረሻዋ እራት 10.01.2022 4:37
የተለያየነው የተገናኘን 'ለት ነው ። እንዲህ እልህ ፍቅራችንን ሳይወርስ በፊት አንዳችን የአንዳችን ደቅ ነበርን ። አሁን በነብስም በስጋም ተለያይተናል ። ሰው ስለይ ጎበዝ እንደሆንኩ እነግራት ነበር ። የትናንት እንጥፍጣፊ ውስጤ አላስቀርም ። ክፉንም ደግ ጠጠር እንደሞላው አቁፋዳ እንዲረሳ አድርጌ ከባህር እሰደዋለው ። አሁንም የሆነው እንደዛ ነው ። ታሪካችን እንደተቋጠረ ቁልቁል ሰምጧል ። ትናንት ሲመሽ እንደሁሌው ጣቶቼን ይዛ አልፀለየችም ። ይልቁን አይኖቼ እስኪከደኑ ጠብቃ የቢጃማዋን መቀነት እየጎተተች ከቤት ወጣች ። አረማመዷ ከመሮጥ ለትንሽ ያዘገመ ነው ። ሻሿ ተፈቶ ከመሬት ሲወድቅ ፤ ፀጉሯ እርቃን ሲወጣ እስከማይሰማት...
ባለኮኮቡ ፓስቲኒ ! 02.01.2022 6:48
የዛሬ ሃያ ዓመት ገደማ ፤ በሆነ በማይታወሰኝ ቀን ከእንቅልፌ ተነስቼ ስንገላጀጅ የግንፍል ሾርባ ሽታ አፍንጫዬን ሰርስሮ ገባ ። ቅንድቦቼን በፍትጊያ አላቅቄ አነፈነፍኩ ' የፈጣሪ ያለህ ፓስቲኒ ነው ። ' ከስጋ ቀጥሎ የምር የምጠላውና - የሚጠላኝ መብል ፓስቲኒ ነው ። የዶሮ መረቅ ቢገባበትማ ራሴን ሲጥ አርጌ የማጠፋ ይመስለኛል ። ሰባት ዓመቴን ልደፍን የቀሩኝ ቀናት ቢሆንም ዛሬም እናቴ ያለሱ ቁርስ ያለ አይመስላትም ። አሰራሩ ቀላል ሆኖ ይሁን ቶሎ ስለሚደርስ እንጃ የቤታችን የጠዋት ጠዋት ሜኑ ሁለት ነው ። የተሰራልህን ፓስቲኒ ወደህ ፤ ወይ ደሞ የተሰራልህን በግድህ ትበላለህ ። ከአልጋዬ ወርጄ በባዶ እግሬ ወዳለችበት ስሄድ እ...
It's Christmas ••• 18.12.2021 2:11
ፅድ አናት ላይ - ሽልም የኮኮብ ዕድ ሳይ - በዝንፍንፍ ቅርንጫፍ የተጥመለመለ ሲባጎ ብልጭ - ድርግም ሲል - የአበርክቶ ሙዳይ ዙሪያው ሲከመር - ዜማ ሲናኝ ፥ በዓመቱ ኦሜጋ ሁሉም ወደልጅነቱ ሲሰበሰብ - በቀለም ያሸበረቁ ህፃናት ተሰብስበው ሲዘምሩ - ኩርሽም ከረሜላዎች አፋቸው ላይ እየሟሟ ሲወልል - ሞሳነት ፍፅምና መሆኑን አምነው ፥ አዛውንቶች በልጆች ሲመረቁ ፥ የበረዶ ጥጥ ብናኞችን አሳበው መላዕክት ሰብ'ን ሲስሙ - የከተማው ካቴድራሎች ስንጉሱ ብስራት ሲደውሉ - የተነጠፉ መንገዶች ሁሉ - ወደቤት አቅጣጫ ሲወስዱ - በብልቃጥ የነበረ መንፈስ ሲተን - ተኖ ቤት ሲሞላ ፥ ብርቅርቅ ኳሶች እየተብረቀረቁ ሲወዛወዙ - ቀያይ ሻማ...
Replaio n'est pas éditeur de podcasts ; les noms des émissions, les visuels et l'audio appartiennent à leurs auteurs et sont diffusés via des flux RSS publics