Leoul Zewelde

Sost kilo

Fiction AM ↓ 38 Folgen

Stories.https://linktr.ee/sostkilo

Autor

Leoul Zewelde

Kategorie

Fiction

Podcast-Website

t.me

Neueste Folge

20. Aug 2023

Wo hören?

Podcasts in der App Replaio Radio Bald verfügbar

Podcasts kommen bald in die App. Installiere sie jetzt und erlebe als Erster einen ganz neuen Blick auf Podcasts

Bei Google Play herunterladen Kostenlos installieren Android fast 10 Mio. Downloads · Bewertung 4,8 iOS bald

Folgen

የራህባን ጭስ 20.08.2023

#Spotify #Sostkilo #shortstory

ሮዛ ሮዚና 14.05.2023

ሮማናት – ናሽናል ካፌ . . . ሮዝ አገሯ ያለ ካፌ ስትቀጥረኝም ሆነ ቀጥራኝ ስትቆይ ለመጀመሪያ ግዜ ነው ። እንደደረስኩ ወፍራም የማሽን ቡና አዝዤ እሱን እየጠጣሁ ጥበቃዬን ጀመርኩ ። ካፌው ውስጥ ዝንቦች እንዳያስቸግሩ በሚል በየጠረጴዛው የሊም ቅጠል ተነጥፏል ። ውስጥ የሚተራመሰውን ሰው ...

የመንታ እናት ፖለቲካ ! 05.05.2023

የ መ ን ታ ፡ እ ና ት ፡ ፖ ለ ቲ ካ [ ል ዑ ል ፡ ዘ ወ ል ደ ] ለማበጠር ጀምራው ከነበር ፀጉሯ ውስጥ እጇን ወትፋ "ዋ………ይ"ብላ ጮኸች ። እሪታዋ ርዝመቱ በመሃል ቅላፄዋ እስኪለዋወጥ ነበር ። ጩኸቷን ተከትሎ ቤቱ ውስጥ ፀውታ (*ፀጥታ + ክውታ) ሰፈነ ። የድንገት ጩኸቷ ከሷ በፊት ሲርገበገቡ የነበሩ ሁለት የመንትዬ እንጥሎችን አርግቧል ። ሣራ ያለግዜ የመጣችባት ፅጌዋ(*ፔሬዷ) ምቾት ነስታት ድምፅ የሚባል ነገር መስማት አስጠልቷታል። አንዴ አግና በለቀቀችው ጩኸቷ ያሰፈነችውን ፀውታ ቶሎ ለመጠቀም አሰበች ። ከጆንያ ላይ ሃባ ክር መዛ ልጆቿ የተጣሉበትን ፊኛ የኮመዲኖው ጠርዝ ላይ ቋጠረችው። ድምር ለቅሷቸው ሲያስጨንቃት...

የአላውያን ሣልዮን | Good Friday 14.04.2023

Leoul Zewelde የሮም ወታደሮች እየተዟዟሩ ሶስቱ ዛይሎኖች ላይ ቅናዋት ሲወቅሩ ይታየናል በሩቅ … ከካህናት ዕሠይ ፤ ካይሁድ ጉርምርምታ አልፎ የሚረብሽ የአንዲት ሴት ስቅስቅታ ይሠማናል ከሩቅ … ለተጓዥ አላውያን መንፈቅ ትርዒት ፥ ከሩቅ ለምናየው …የአርብ መንገድ አድክሞን ከመስቀሉ ጀርባ ተጋርደን ለቆምነው … ክርስትና ርዕዮት ነው !

ያልተላኩ አምስት ቴክስቶች - Message 3  | Part II 18.02.2023

ያልተላኩ አምስት ቴክስቶች - Message 3  | Part II

ዛሬ ፥ ጨረቃዋን አይተሻታል ? ... ፩. አዲስ አበባ ፥ ካምፕ አስመራ 15.01.2023

ያልተላኩ አምስት ቴክስቶች ፤ Message 3

ኪ ሣ ኬ ሣ ፥ አ ዱ ሬ ን ፡ ቢ ኔ ሳ 17.11.2022

ራቢራ ሱራ ነኝ ። ቢራዬን እንደትኩስ ሻይ ...

የእውነት እውነት ፥ እወድሻለሁ ! 17.10.2022

ውብትሽን ከሩቅ ለሚያይ 'ፍዝ' ነው ። ሎሚ እንዳቤዠው ሻይ ፥ ካልቀመሱት የአይን ስህተት ነው ። ይሄን ብዥታ እንደሀቅ ተቀብለው ፥ ይገፉሻል ። ለእኔ ግን ፥ ጣዕምሽን አውልዬ ለማውቀው ፥ ለሰው ብዬ አይደለም ! ከሰው መጥቶ አይደለም ! የእውነት ነው ። ከማታውቂው አገር ብትኮምሪ ፥ የቤትሽ የመጨረሻ ሰካራም ፥ እኔ ነው ምሆነው ። ትተሽ ብታዘምሪ ፥ ጭራ ልጌ አጅባለው ። ለእኔ ? ጣዕምሽን አውልዬ ለማውቀው ፥ ለሰው ብዬ አይደለም ! ከሰው መጥቶ አይደለም ! የእውነት ነው ። በፀጋ ሆነ ቅባት ፥ ብቻ ከአንዱ ሆነሽ ብትነፍቂ ፥ ጥላ ጥለትሽን ይዤ እከተልሻለው ። አንቺ በምታምኚው ፥ እኔ እታነመናለሁ ። ውርስ ሥጋዬ ለስደትሽ...

ሽ ፍ ደ ት ፡ በ አ ይ ን ፡ ይ ገ ባ ል ... 21.07.2022

የተንጣለለው አስፋልት በሚረግፈው የዳመና ቡትርፍ እየታጠበ ነው ። አቶ 'ሀ' ( ይቅርታ ፤ ስሙን ስለማላውቀው  ነው) ጭር ባለው ጎዳና እየተዘነበበት ወደቤቱ ያቀናል ። ተበታትኖ የሚወርደው የጨፈጨፍ ናዳ ሲያርፍ ይዘልና ሌላ  ቀድሞ የወረደ ጨፍ እየያዘ ወደዳር ይንቆረቆራል ። ተርታውን ያቀረቀሩት የመንገድ ዳር መብራቶች ገና ሳይመሽ በስህተት ብርሃናቸውን ወልተዋል ...

ኦቾሎኒ - አለንጋና ምስር | 1985 ሆላንድ 17.07.2022

ለአዳም ረታ - የልደት ማስታወሻ

አስኩቲን በትኩሱ:) 03.07.2022

የችኮላ ሥራ ሲገጥመኝ ትዝ የምትለኝ ነገር ነች። ቄራ ላይ የሆነ ነው ፥ ያው እንደጨዋታ ። አስኩቲ የሚባል እሳት ሞተረኛ ...

ከ ሀ - ፐ ስንት ኪሎሜትር ነው ? 24.06.2022

Excerpt : ድምቡሎ ጎዳና | Short story.

አንቺ የወደድሽው ፥ እኔ የማልሆነው ••• 20.06.2022

ጀግና የወደድሽ ሰሞን ፤ ጀግና አሳድዳለው ። ጎሽ ገድዬ ኮልባ ሎቲ እቀርፃለው ። ከነብር ገላ ላይ ለአንገት በርኖስ እላጫለሁ •••

ብዥ 01.06.2022

በመሃል እራት አለመብላቴ ትዝ ብሎኝ ደሞ በባዶ ሆዴ ተከዝኩ ። ችግሮቼ በጣም ስለሚወዱኝ ብቻዬን አይተውኝም ፥ አንዱ እንኳ ሲሄድ አንዱን ተክቶ ነው ....

ዝንየት ሦስት : ተፃብዖ (ሰማያዊና ቀይ ኮላዥ) 04.05.2022

ይሄኔ ነው ትርዒቱ የተለኮሰው ። መጀመሪያ የበረንዳው አምፖል ላምባ እንደጨረሰ ኩራዝ ጥር ጥር ሲል ቆይቶ ዚግዛጉ እስኪታይ ድረስ ከሰመ ። ተደፍቶ በስንፍናዬ ያልወለወልኩት ውሃን ወለሉ ሲመጠውና ጠቦ ጠቦ ሲጠፋ አየሁ ። በድንጋጤ እግሮቼን ወንበሬ ላይ ሰበሰብኩ ። የግቢያችን መታጠፊያ ሾላ ዛፍ ላይ የተከመሩ ወፎች ተበተኑ ። እነሱን ተከትለው የዛፉ ፍሬዎች ሿ ብለው ረገፉ .... ‎

ዝንየት ሁለት - ምርጫ ቀረበልኝ ፤ ከእውነት እና ፍቅር ? 27.03.2022

በሩ ሁለቴ ተንኳኳ ። ስከፍት የበሩን የውጭ ማዕዘን ተደግፋ ቆማለች ። ሰላምታ ሳትሰጠኝ አልፋኝ ገባችና ዘግቼው ወደሷ እስክዞር ጠብቃ " አርግዣለሁ " አለቺኝ ። ደንግጬ አየኌት ....

ዝንየት አንድ ፤ EP01 16.03.2022

የለበሰችው እጅጌ ሙሉ ፒትልስ ወልቆ ምኔ እርቃኗን እንደቀረች አታውቅም ። የተጨመታተረው አንሶላው ሀሩር ገላዋን እየነካ ሲቆጠቁጣት ገልፍፋ ጣለችው ....

ለምን ግን ትልቅ ሆነ ? 08.03.2022

ከትናንት ወዲያ ማታ ለት እናቴ እሪሪ ብላ እያለቀሰች ገረፈቺኝ ፤ እያነቡ እስክስታ ነገር ። ከደቂቃ በፊት ( ደብተሬ ላይ ጭረት እስካይና እስክጠይቃት) አገር ጎረቤት ሰላም ነው ብለን ስለ ሙሉ ቁጥሮች ተካፋይ ስታስረዳኝ ነበር ። ድንገት ተነስታ ጫማዋን አውልቃ አናት አናቴን እየጠፈጠች < ኧረ ሰዎች አቃተኝ ምናባቴ ላርገው ? > ብላ ለአገላጋዮቼ ታሳጣኛለች ፤ ሁለተኛ በደል ። ባህሪዋ ለማንም ግራ የሚገባ አይነት ነው ። እስኪ ልፈትናት ብዬ ሁለት ቀን የሚያስቅ ቀልድ ባወራት ራሱ ትንሽ ፈገግ ሳትል ወደ ጠብደል ምክር ትለውጠዋለች ። ምክሯ ከመብዛቱ የተነሳ አንዳንዴ እንዲሁ < ዛሬ አመክሪኝም ኣ ? > እላታለው ። በራሷ ስቃ...

#saynotowar 14.02.2022

... ረጅም የስደት ሰልፍ ፥ ሰሌን አናቷ ላይ ጠቅልላ የምትጓዝ እናት ፥ የታረዙ ብላቴኖች ፥ የተደፈሩ መበለት ፥ የተገፈፉ ክብሮች ፥ የከተማ ምሽጎች ፥ የተበሳሱ መስኮቶች ፥ የሚነዱ ቲያትር ቤቶች ፥ ከሰማይ የሚዘንቡ አረሮች ፥ በየቀጠናው የተማገዱ ጎረምሶች ፥ ባንጋ የቀላቸው አናቶች ፥ የሰቀቀን እሪታዎች ፥ ጆፌ የሚዞረው አንገት ፥ የልጁን ሬሳ የሚያናግር አባት ፥ ረጅም የእሾህ አጥር ፥ የስጋት ድንኳኖች ፥ ፈንጂ ዶሿቸው የሚደሁ ገላዎች ፥ እሳት አከፋፋይ ኦራሎች ፥ የነፍሴ አውጪኝ ትርምስ ፥ የሚያለቅሱ ቄሶች ፥ ሚናራቸው የወደቀ መስጂዶች ፥ የተጨነቁ ሩሆች ፥ የማይታይ ነጭ ባንዲራ ...

ሲመሽ ፤ ሲመሽ . . . ትዝ ይለኛል ! 09.02.2022

ሲመሽ – ፊት ላይ የሚለሰልስ ብርትኳናማ የፀሃይ ጨረር ሲፈናጠቅ – ከመስጂድ ሚናር የመግሪብ አዛን ሲሰማ – ህዝቤ ስራ ያንዠረገገው ሚስቶ ፊቱን ይዞ ወደቤቱ ሰከም ሰከም ሲል – የትራፊክና የፍሬቻ መብራቶች መድመቅ ሲጀምሩ – የእራት ወጥ ጢሶች ከየኩሽናው ወደሰማይ ሲወጡ . . . ሲመሽ ፤ ሲመሽ . . . ትዝ ይለኛል . . . !

ቻው ፡ ቻው | ጉራማይሌ መፅሐፍ 25.01.2022

እንደዛ ነው የሚያደርጉት ፤ ይሄዳሉ ። ምንም ሳይሉህ ይሄዳሉ ። እንደጨረቃ ሙላታቸው ይጎድላል - ይገምሳል - ይቀጥኑ ይቀጥኑና - በሆነ ቀን ቀና ስትል የሉም ። ለመከተያ እንኳ ዳና ሳይተውልህ - ልክ እንደ ወቅቶች ፤ እንዳምናዎች ፤ እንደትናንቶች ... ሄድን ሳይሉ ፥ ፍውው …! በዳ'ባድመ መሐል ጥለውህ ሄደውም እንዳልረሣሀቸው ማወቅ ይፈልጋሉ ። ይሄ መሻት እያደር ሲሞረሙራቸው ረፈዶ ከባቸ በኋላ 'ቻው' ይሉሃል ። ከሄዱ ከምናምን አመታት በኋላ አተኩሰው ይሰናበቱሃል ። ደሞ ቻው ሲሉህ . . . ቻው፡ቻው ! ያንተው ሃና ። …የደብዳቤው 31ኛ መስመር መቋጫ ላይ። ጠርዙን ቴምብር ካሽቆጠቆጠው ቅድ ፖስታ ውስጥ ለመጨረሻ ግዜ አው...

የተሸጠ ነብሥ ፥ አይመለስም••• 21.01.2022

ነብሴን በገዙኝ ማግስት የፀሓይን ሞት አረዱኝ ። በከባድ ምጥ ማለፏን እንደሰማሁ በዛለ ጀምበር ወደ ለቅሶው ሄድኩ። መቃብሯ የጀበል ቓፍ (*የምድር ጠርዝ) ኮረብቶች ላይ ነው ።ለቀሥተኛው እየተነዳዳ ወደ ቀብሩ ይግተለተላል። እንደህፃን እግር እየተከተልኩ መጓዝ ጀመርኩ። በገፍ ከሚጋዘዉ ለቀስተኛ እንባ የሚወጣኝ አንድ እኔ ነኝ ። ሌሎቹ የአይን መቅደሳቸው ተገልብጦ ከነጩ መቃድ የጠለሸ ደም ይፈሳል ። ዶቃ ብሌናቸው በቦታው የለም ። ወዮታቸውን ባልሰማም ከደረታቸው የሚነሳ ተደጋጋሚ ስቅታ ግን አለ። እየሄድን ነው ። ከፊቴ የቀደሙም ሆኑ ከጀርባ የተውኳቸው ለቀስተኞች አናታቸው የተመለጠ ሲሆን ከአናታቸው ዙርያ እንፋሎት ይጤሳል ። በተ...

የመጨረሻዋ እራት 10.01.2022

የተለያየነው የተገናኘን 'ለት ነው ። እንዲህ እልህ ፍቅራችንን ሳይወርስ በፊት አንዳችን የአንዳችን ደቅ ነበርን ። አሁን በነብስም በስጋም ተለያይተናል ። ሰው ስለይ ጎበዝ እንደሆንኩ እነግራት ነበር ። የትናንት እንጥፍጣፊ ውስጤ አላስቀርም ። ክፉንም ደግ ጠጠር እንደሞላው አቁፋዳ እንዲረሳ አድርጌ ከባህር እሰደዋለው ። አሁንም የሆነው እንደዛ ነው ። ታሪካችን እንደተቋጠረ ቁልቁል ሰምጧል ። ትናንት ሲመሽ እንደሁሌው ጣቶቼን ይዛ አልፀለየችም ። ይልቁን አይኖቼ እስኪከደኑ ጠብቃ የቢጃማዋን መቀነት እየጎተተች ከቤት ወጣች ። አረማመዷ ከመሮጥ ለትንሽ ያዘገመ ነው ። ሻሿ ተፈቶ ከመሬት ሲወድቅ ፤ ፀጉሯ እርቃን ሲወጣ እስከማይሰማት...

ባለኮኮቡ ፓስቲኒ ! 02.01.2022

የዛሬ ሃያ ዓመት ገደማ ፤ በሆነ በማይታወሰኝ ቀን ከእንቅልፌ ተነስቼ ስንገላጀጅ የግንፍል ሾርባ ሽታ አፍንጫዬን ሰርስሮ ገባ ። ቅንድቦቼን በፍትጊያ አላቅቄ አነፈነፍኩ ' የፈጣሪ ያለህ ፓስቲኒ ነው ። ' ከስጋ ቀጥሎ የምር የምጠላውና - የሚጠላኝ መብል ፓስቲኒ ነው ። የዶሮ መረቅ ቢገባበትማ ራሴን ሲጥ አርጌ የማጠፋ ይመስለኛል ። ሰባት ዓመቴን ልደፍን የቀሩኝ ቀናት ቢሆንም ዛሬም እናቴ ያለሱ ቁርስ ያለ አይመስላትም ። አሰራሩ ቀላል ሆኖ ይሁን ቶሎ ስለሚደርስ እንጃ የቤታችን የጠዋት ጠዋት ሜኑ ሁለት ነው ። የተሰራልህን ፓስቲኒ ወደህ ፤ ወይ ደሞ የተሰራልህን በግድህ ትበላለህ ። ከአልጋዬ ወርጄ በባዶ እግሬ ወዳለችበት ስሄድ እ...

It's Christmas ••• 18.12.2021

ፅድ አናት ላይ - ሽልም የኮኮብ ዕድ ሳይ - በዝንፍንፍ ቅርንጫፍ የተጥመለመለ ሲባጎ ብልጭ - ድርግም ሲል - የአበርክቶ ሙዳይ ዙሪያው ሲከመር - ዜማ ሲናኝ ፥ በዓመቱ ኦሜጋ ሁሉም ወደልጅነቱ ሲሰበሰብ - በቀለም ያሸበረቁ ህፃናት ተሰብስበው ሲዘምሩ - ኩርሽም ከረሜላዎች አፋቸው ላይ እየሟሟ ሲወልል - ሞሳነት ፍፅምና መሆኑን አምነው ፥ አዛውንቶች በልጆች ሲመረቁ ፥ የበረዶ ጥጥ ብናኞችን አሳበው መላዕክት ሰብ'ን ሲስሙ - የከተማው ካቴድራሎች ስንጉሱ ብስራት ሲደውሉ - የተነጠፉ መንገዶች ሁሉ - ወደቤት አቅጣጫ ሲወስዱ - በብልቃጥ የነበረ መንፈስ ሲተን - ተኖ ቤት ሲሞላ ፥ ብርቅርቅ ኳሶች እየተብረቀረቁ ሲወዛወዙ - ቀያይ ሻማ...

Höre den Podcast Sost kilo in Replaio

Radio und Podcasts in einer App - kostenlos und ohne Anmeldung. Installiere sie noch heute und verpasse den Start nicht

Bei Google Play herunterladen

Replaio ist kein Herausgeber von Podcasts; die Namen der Sendungen, Cover und Audioinhalte gehören ihren Autoren und werden über öffentliche RSS-Feeds verbreitet