ECFC in Finland

Ethiopian Christian Fellowship Church in Finland

This is a podcast from the Ethiopian Christian Fellowship in Finland, where you can listen to biblical teachings, messages, and sermons. May God bless all our listeners.

Besuch unbedingt die Website des Podcasts und unterstütze die Macher: ecfc-finland.org

Autor

ECFC in Finland

Kategorie

Religion

Podcast-Website

ecfc-finland.org

Neueste Folge

4. Okt 2026

Wo hören?

Podcasts in der App Replaio Radio Bald verfügbar

Podcasts kommen bald in die App. Installiere sie jetzt und erlebe als Erster einen ganz neuen Blick auf Podcasts

Bei Google Play herunterladen Kostenlos installieren Android fast 10 Mio. Downloads · Bewertung 4,8 iOS bald

Folgen

134_እግዚአብሔር ምድራችንን ይፈውሳል! || ክፍል 2 || በወንጌላዊ ዘገየ መኮንን 29.11.2020

"እግዚአብሔር ምድራችንን ይፈውሳል!" በሚል ርዕስ በ2ኛ ዜና 7:11-14 ባለው ክፍል ላይ ተመሥርቶ በወንጌላዊ ዘገየ መኮንን የቀረበ የእግዚአብሔር ቃል መልዕክት ሁለተኛው ክፍል:: ተጨማሪ ጥቅሶች: ምሳ. 1:20-33/ኢሳ. 58:1-14/1 ዮሐ. 1:7-9

133 እግዚአብሔር ምድራችንን ይፈውሳል! || ክፍል 1 || በወንጌላዊ ዘገየ መኮንን 22.11.2020

"እግዚአብሔር ምድራችንን ይፈውሳል!" በሚል ርዕስ በ2ኛ ዜና 7:11-14 ባለው ክፍል ላይ ተመሥርቶ በወንጌላዊ ዘገየ መኮንን የቀረበ የእግዚአብሔር ቃል መልዕክት::

132 ጌታ ቅርብ ነው || ክፍል 2 || ወንድም ተከለ ማርቆስ (ዶ/ር) 15.11.2020

ርዕስ: ጌታ ቅርብ ነው || ክፍል 2 "ጌታ ቅርብ ነው" በሚል ርዕስ በወንድም ተከለ ማርቆስ (ዶ/ር) ፊል. 4:4-9 ባለው የእግዚአብሔር ቃል ላይ ተመሥርቶ የቀረበ የእግዚአብሔር ቃል መልዕክት::

131_ጌታ ቅርብ ነው || ክፍል 1 || በወንድም ተከለ ማርቆስ (ዶ/ር) 08.11.2020

ጌታ ቅርብ ነው  በተከለ ማርቆስ (ዶ/ር) በአባቶች ቀን ፕሮግራም ላይ  በፊሊ 4:6 ላይ የተመሰረተ ከ እ/ር ቃል መልእክት የቀረበ "ጌታ ቅርብ ነው። በነገር ሁሉ በጸሎትና በምልጃ ከምስጋና ጋር በእግዚአብሔር ዘንድ ልመናችሁን አስታውቁ እንጂ በአንዳች አትጨነቁ። አእምሮንም ሁሉ የሚያልፍ የእግዚአብሔር ሰላም ልባችሁንና አሳባችሁን በክርስቶስ ኢየሱስ ይጠብቃል።"ፊሊ 4:4-6 "እናንተም ትጠሩኛለችሁ፥ ሄዳችሁም ወደ እኔ ትጸልያላችሁ፥ እኔም እሰማችኋለሁ።  እናንተ ትሹኛላችሁ፥ በፍጹም ልባችሁም ከሻችሁኝ ታገኙኛላችሁ።"ኤር 29:12-13 "እግዚአብሔርም መልካሙን መዓዛ አሸተተ፤ እግዚአብሔርም በልቡ አለ፦ ምድ...

130_ሰው ምንድን ነው? || ክፍል 5 || በወንድም ያቬሎ ናታዬ ያታሣ 01.11.2020

ይህ "ሰው ምንድን ነው?" በሚል ርዕስ በወንድም ያቬሎ ናታዬ እየቀረበ ያለው ተከታታይ ትምህርት አምስተኛውና የመጨረሻው ክፍል ነው:: ዘፍ. 1:26-28/ዘፍ. 2:7 በዚህ ክፍል የተዳሰሱ ዋና ዋና አሳቦች:- ርዕስ: ሰው ምንድን ነው? ክፍል 5: የሰው ዋጋ በዚህ ክፍል የተዳሰሱ አሳቦች: - -–ሌሎች ሥልጣኔዎችና ባህሎች ስለሰው ዋጋ ያላቸው ዕይታ –እስልምና ስለሰው ዋጋ ያላቸው ዕይታ –ምዕራባዊያን ስለሰው ዋጋ ያላቸው ዕይታ –መጽሐፍ ቅዱስ ስለሰው ዋጋ ምን ያስተምራል? –መጽሐፍ ቅዱሳዊውን ዕይታ መከተል ያሉት ክትለቶች (implications)

129_ሰው ምንድን ነው? || ክፍል 4 || በወንድም ያቬሎ ናታዬ ያታሣ 25.10.2020

ይህ "ሰው ምንድን ነው?" በሚል ርዕስ በወንድም ያቬሎ ናታዬ እየቀረበ ያለ ተከታታይ ትምህርት አራተኛው ክፍል ነው:: ዘፍ. 1:26-28/ዘፍ. 2:7 በዚህ ክፍል የተዳሰሱ ዋና ዋና አሳቦች:- ርዕስ: ሰው ምንድን ነው? ክፍል 4: "ሰው ሰው የሆነው ለምንድን ነው?/ሰው የተፈጠረበት ዓላማ ምንድን ነው?" ሰው በዋናነት የተፈጠረው ለኅብረት የሚለው አሳብ በስፋት ይተነተናል:: 1) ሰው ከእግዚአብሔር ጋር ያለው የወደ ላይ ኅብረት 2) ሰው ከሌሎች ሰዎችና ከተፈጥሮ ጋር ያለው ኅብረት 3) የክርስቶስ መስቀል ምሳሌነት ለሁለቱም የሰው የኅበረት አቅጣጫዎች 4) ፍቅር - ኅብረትን መተግበሪያ ዓይነተኛ መሣሪያ የሚሉ አሳቦች በስፋት ተዳስ...

128_የጌታ መንገድ || በወንድም አስቻለው ወልዴ 18.10.2020

የጌታ መንገድ በሚል ርዕስ በወንድም አስቻለው ወልዴ የቀረበ የእግዚአብሔር ቃል መልዕክት:: የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች: ዮሐ. 14:6/ ማቴ. 18:21-35 / ገላ. 5:19-21

127_የልብ መዝገብ ቢከፈት ምን ይወጣል? || በእህት ለምለም ጌታቸው 11.10.2020

"የልብ መዝገብ ቢከፈት ምን ይወጣል?" በሚል ርዕስ በ2ኛ ዜና 5 ላይ ተመሥርቶ በእህት ለምለም ጌታቸው የቀረበ የእግዚአብሔር ቃል መልዕክት:: የመልዕክቱ ጭብጥ: ቁጣንና ጦርነትን የሚያስቀር የልብ መዝገብ አለ/በተቃራኒው ደግሞ ቁጣና ጦርነትን የሚቀሰቅስ የልብ መዝገብ አለ/ለፈውስ የሚሆን የልብ መዝገብ አለ/ለደዌ የሚዳርግ የልብ መዝገብ አለ:: የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች: 2 ነገ. 5:1> /ምሳ. 20:21 /1 ነገ. 19:15-19 /ሉቃ. 6:43-45

126_እግዚአብሔር ያያል! || በተከለ ማርቆስ ፋሼ (ዶ/ር) 04.10.2020

"እግዚአብሔር ያያል" በሚል ርዕስ በወንድም ተከለ ማርቆስ ፋሼ (ዶ/ር) የቀረበ የእግዚአብሔር ቃል መልዕክት:: የመጽሐፍ ቅዱድስ ጥቅሶች: ዘፍ. 16:1-16/ኢዮብ 40:1-2/ኢዮብ 42:1-6/ሮሜ 5:3-4/

125_የመጥምቁ ዮሃንስ ምስክርነት || በዘገዬ መኮንን (ወ/ዊ) 27.09.2020

"የመጥምቁ ዮሃንስ ምስክርነት" በሚል ርዕስ በወንጌላዊ ዘገዬ መኮንን የቀረበ የእግዚአብሔር ቃል መልዕክት:: በዮሐ 1:20-30 እና በሉቃስ 1:76 ላይ ባለው የእግዚአብሄር ቃል ላይ የተመሰረተ መልእክት::

124_የሚያስፈልገው ጥቂት ነው! 20.09.2020

"የሚያስፈልገው ጥቂት ነው!" በሚል ርዕስ በሉቃ. 10:38-42 ባለው ክፍል ላይ ተምሥርቶ በወንጌላዊ ዘገየ መኮንን የቀረበ የእግዚአብሔር ቃል መልዕክት::  የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች: ሉቃ. 10:38-42/ኢየሱስ በነ ማርታና ማሪያም ቤት  || 1 ነገ. 17:7-14/ነቢዩ ኤልያስና የሰራፕታዋ ባልቴት || ማቴ. 15:32-38/ኢየሱስ 4000+ ሰዎችን በሰባት እንጀራና በጥቂት ዓሣ መመገቡ || መዝ. 37:16 ||    

123_ሰው ምንድን ነው? || ክፍል 3 || በወንድም ያቬሎ ናታዬ 13.09.2020

ይህ "ሰው ምንድን ነው?" በሚል ርዕስ በወንድም ያቬሎ ናታዬ እየቀረበ ያለ ተከታታይ ትምህርት ሦስተኛው ክፍል ነው:: ዘፍ. 1:26-28/ዘፍ. 2:7 በዚህ ክፍል የተዳሰሱ ዋና ዋና አሳቦች:- ርዕስ: ሰው ምንድን ነው? ክፍል 3: "ሰው መንፈስ ነው ፤ ነፍስ አለው ፤ በሥጋ ውስጥ ይኖራል!" ባዮች ስህተታቸው ምንድን ነው? 1) የቃል እምነት እንቅስቃሴ ስለሰው ምንነት ያላቸውን አመለካከት በጥልቀት እንመለከታለን 2) የሚጠቅሷቸውን የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎችና እንዴት እንደተሳሳቱ እንመለከታለን:: 3) ከስህተት ራሳችንን ለመጠበቅ ከእያንዳንዳችን ምን እንደሚጠበቅ እንመለከታለን:: የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች / ዘፍ. 1:26-27 / መዝ...

122_ሰው ምንድን ነው? || ክፍል 2 || በወንድም ያቬሎ ናታዬ 06.09.2020

ይህ "ሰው ምንድን ነው?" በሚል ርዕስ በወንድም ያቬሎ ናታዬ እየቀረበ ያለ ተከታታይ ትምህርት ሁለተኛው ክፍል ነው:: ዘፍ. 1:26-28/ዘፍ. 2:7 በዚህ ክፍል የተዳሰሱ ዋና ዋና አሳቦች:- ርዕስ: ሰው ምንድን ነው? ክፍል 2: ትክክለኛው መጽሐፍ ቅዱሳዊ የሰው ምንነት ዕይታ ሀ) ሰው በትክክል ምንድን ነው? ለ) የሰው ማንነት ክፍሎች የሰው መንፈስ የሰው ነፍስ የሰው ሥጋ/ቁሳዊ አካል የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች: 1 ተሰ. 5:23/ዕብ. 4:12/ኢዮብ 32:8/ሉቃ. 9:56/ማር. 14:34/ሉቃ. 23:46/ሐዋ. 7:59/መክ. 12:7/ፊል. 3:20-21

121_ሰው ምንድን ነው? || ክፍል 1 || በወንድም ያቬሎ ናታዬ 30.08.2020

ይህ "ሰው ምንድን ነው?" በሚል ርዕስ በወንድም ያቬሎ ናታዬ እየቀረበ ያለ ተከታታይ ትምህርት የመጀመሪያው ክፍል ነው:: ዘፍ. 1:26-28/ዘፍ. 2:7 በዚህ ክፍል የተዳሰሱ ዋና ዋና አሳቦች:- ርዕስ: ሰው ምንድን ነው? ክፍል 1: ዓለም ለሰው ያላት ዕይታ 1) የማቴሪያሊዝም ንጽረተ ዓለም አራማጆች  ስለሰው ምንነት ያላቸው ዕይታ 2) የአይዲያሊዝም ንጽረተ ዓለም አራማጆች ስለሰው ምንነት ያላቸው ዕይታ 3) ክርስቲያናዊ የሰው ምንነት ዕይታ

120_ጤናማ ቤተሰባዊ ግንኙነትን መገንባት || ክፍል 2 || ዶ/ር ሙላቱ በላይነህ 26.08.2020

ይህ ትምህርት ጤናማ ቤተሰባዊ ግንኙነትን መገንባት በሚል ርዕስ፣ የቤተሰብና ጋብቻ አማካሪ በሆነው በዶ/ር ሙላቱ በላይነህ በፊንላንድ ለሚኖሩ ኢትዮጵያዊያንና ኤርትራዊያን የቀረበ ትምህርት ሁለተኛው ክፍል ነው:: በዚህ ክፍል የሚከተሉት ዋና ዋና አሳቦች ተዳስሰዋል: - ርዕስ: ወላጆች ከልጆቻቸው ጋር ያላቸውን የግንኙነት ጤንነት መጠበቅ 1) መግቢያ 2) በልጆች ጉዳይ ወላጆች ላይ መሥራት የሚያስፈልግባቸው ምክንያቶች 3) በልጆችና ወላጆች መካከል ጤናማ ግንኙነት እንዳይኖር የሚያደርጉ ነገሮች 4) ወላጆች ከልጆቻቸው ጋር ያላቸውን ግንኙነት ጤንነት ለመጠበቅ የሚረዱ ነገሮች

119_ጤናማ ቤተሰባዊ ግንኙነትን መገንባት || ክፍል 1 || ዶ/ር ሙላቱ በላይነህ 25.08.2020

ይህ ትምህርት ጤናማ ቤተሰባዊ ግንኙነትን መገንባት በሚል ርዕስ፣ የቤተሰብና ጋብቻ አማካሪ በሆነው በዶ/ር ሙላቱ በላይነህ በፊንላንድ ለሚኖሩ ኢትዮጵያዊያንና ኤርትራዊያን የቀረበ ትምህርት የመጀመሪያው ክፍል ነው:: በዚህ ክፍል የሚከተሉት ዋና ዋና አሳቦች ተዳስሰዋል: - ርዕስ: ባልና ሚስት እርስ በርስ ያላቸውን የግንኙነት ጤንነት መጠበቅ 1) የትምህርቱ ዓላማዎች 2) ግንኙነቶቻችንን ሊረብሹ የሚችሉ ሁለንተናዊ አሉታዊ ተጽዕኖዎች 3) የጤናማ ግንኙነት ወይም ትዳር (መኖር/አለመኖር) መለኪያ መስፈርቶች 4) ግንኙነቶቻችንን ሊረብሹ የሚችሉ የታወቁ ምክንያቶች 5) የትዳርና የቤተሰብ ግንኙነትን ጤንነት መጠበቅ የሚቻልባቸው መንገዶች

118_ፅና ወይም ፅኑ ክፍል 3 / በወንጌላዊ ዘገዬ መኮንን 23.08.2020

118_ፅና ወይም ፅኑ ክፍል 3 / በወንጌላዊ ዘገዬ መኮንን  10. በጊዜውም ያለጊዜውም ቢመችም ባይመችም ተዘጋጅቶ መኖር 2 ጢሞ4:2 11. እስከ መጨረሻው መጽናት ማቲ 10:22 እንድንፀና የሚረዱን 4 ነገሮች 1 . የእግዚአብሄር ቃል በመታዘዝ ማቲ 7:26 እና 1 ዜና 28:5-7 2. ፀሎት  1ጴጥ  5:10 3. የእግዚአብሄር መንፈስ ቅዱስ  ሐዋ 1:8 4. ቅዱሳን ወንድሞች እና እህቶች  ሉቃ 22:32

117_ፅና ወይም ፅኑ ክፍል 2 / በዘገዬ መኮንን /ወንጌላዊ 16.08.2020

117_ፅና ወይም ፅኑ ክፍል 2 / በዘገዬ መኮንን /ወንጌላዊ እንድንጸናባቸው ከታዘዝንባቸው 6 ነገሮች የመጀመሪያዎቹ 4ቱ በ 2ቆሮ 12: 9 እና ምዕ 8:1 ጀምሮ ላይ የተመሰረተ የእ/ር ቃል መልእክት በዘገዬ መኮንን /ወንጌላዊ 6.በጸጋ መጽናት 7.በፍቅር መጽናት 8.በአገልግሎት መጽናት 9.በወንጌል እውነት መጽናት

116_ፅና ወይም ፅኑ በዘገዬ መኮነን/ወንጌላዊ/ 09.08.2020

116_ፅና ወይም ፅኑ  በዘገዬ መኮነን/ወንጌላዊ/ ፅና ወይም ፅኑ  በኢያሱ 1:6 እና  በዘዳ 31:7 ላይ የተመሰረተ የእ/ር ቃል መልእክት      መፅናት በግል: በቤተሰብ: በሕብረት      መፅናት ለአማኞች የተሰጠ ትእዛዝ ነው:: ሀ.በመፅናት ምሳሌ የሆኑን :      ሐና: ዳዊት: አሳ ለ.እንድንፀናባቸው የታዘዝንባቸው ነገሮች      1.  በተስፋ መጽናት     2. በእምነት መጽናት   &...

115_ዘመኑ: በውጪ ያሉ ሰዎችና ንግግሮቻችን || ክፍል 2 || ያቬሎ ናታዬ 02.08.2020

115_ዘመኑ: በውጪ ያሉ ሰዎችና ንግግሮቻችን /ክፍል 2  / ያቬሎ ናታዬ የንግግሮቻችን 7 መመዘኛዎች 1- እያንዳንዱን ሰው ታሳቢ ማድረግ አለበት : 2-አውዳዊ ስልትን የተከተለ መሆን አለበት 3-እውቀትን መሰረት ያደረገ መሆን አለበት 4-ትክክለኛ መልእክት የያዘ መሆኑን መረጋገጥ አለበት 5-ሁልጊዜ ጥንቃቄ የተሞላበት መሆን አለበት 6-ንግግራችን የተቀመመ መሆን መረጋገጥ አለበት 7-ጸጋን የተሞላ መሆን አለበት በጠብ ሳይሆን በጥበብ ለመመላለስ ንግግራችን እነዚህን መስፈርቶች ማሟላት ይኖርበታል:: ቆላ 4:5-6 በተጻፈው በእግዚአብሔር ቃል መልእክት ላይ የተመሰረተ

114_ራዕይ ምዕ 5 ቁ 1-10 በወንጌላዊ ዘገዬ መኮንን 26.07.2020

114_ ራዕይ ምዕ 5 ቁ 1-10  ባለው ቃል ላይ የተመሰረተ መልእክት /በወንጌላዊ ዘገዬ መኮንን መጽሐፉን ትወስድ ዘንድ ማኅተሞቹንም ትፈታ ዘንድ ይገባሃል፥ ታርደሃልና፥ በደምህም ለእግዚአብሔር ከነገድ ሁሉ ከቋንቋም ሁሉ ከወገንም ሁሉ ከሕዝብም ሁሉ ሰዎችን ዋጅተህ ለአምላካችን መንግሥትና ካህናት ይሆኑ ዘንድ አደረግሃቸው፥ በምድርም ላይ ይነግሣሉ እያሉ አዲስን ቅኔ ይዘምራሉ።ራዕ 5:9-10 1. ጥቅልሉ መጽሐፍ ራዕ 5: 1-3 2. ከሽማግሌዎች አንዱ  ራዕ 5: 4-7 3. ለበጉ ክብር የምስጋና ዝማሬ ራዕ 5: 8-10

113_ ዘመኑ: በውጪ ያሉ ሰዎችና ንግግራችን || ክፍል 1 || በወንድም ያቬሎ ናታዬ 19.07.2020

113_ ዘመኑ: በውጪ ያሉ ሰዎችና ንግግራችን    ተከታታይ ትምህርት :: በወንድም ያቬሎ ናታዬ ዘመኑን እየዋጃችሁ: በውጪ ባሉት ዘንድ በጥበብ ተመላለሱ :: "ለእያንዳንዱ እንዴት እንድትመላለሱ እንደሚገባ ታውቁ ዘንድ ንግግራችሁ ሁልጊዜ :በጨው እንደ ተቀመመ :በጸጋ ይሁን"::ቆላ 4:5 ክፍል 1 1:1 ዘመኑ ምን አይነት መልክ አለው? የሚዋጅ ዘመን  በኤፌ 5:15 እና 2ኛ ጢሞ3:1-5 ላይ የተመሰረተ ቃል:: 1)ዘመኑ የሚዋጅ ነው 2) ዘመኑ ክፉ ነው  3)ዘመኑን ዋጁ 1-2 ዘመኑን የምንዋጀው እንዴት ነው? በውጪ ባሉት ዘንድ በጥበብ ተመላለሱ::  ቆላ 4:5 1)ዘመኑን መልክ በመ...

112_እግዚአብሔር ተዋጊ ነው :: በዘገዬ መኮንን /ወንጌላዊ/ 12.07.2020

112_እግዚአብሔር ተዋጊ ነው :: በዘገዬ መኮንን /ወንጌላዊ/ 1/ እግዚአብሔር ተዋጊ ነው :: እግዚአብሔር ስሙን ከፍ ለማድረግ ይዋጋል::  ዘጸ 15:1-3 እግዚእብሔር  ያለማንም ጣልቃ ገብነት  ለህዝቡ ብቻውን ተዋግቶ : ድል ሲነሳ ስላዩ: ሙሴና የእስራኤል ህዝብ "እግዚአብሔር ተዋጊ ነው" አሉት:: 2/ እግዚእብሔር  የራሱን ህዝብ ከጠላቶቻቸው ጥቃት ለመታደግ 2ዜና 20: 14-15 3/ እግዚእብሔር ህዝቡን ወደ አሰበለት ስፍራ ለማስገባት:: ዘጸ 14: 14-23

111_እግዚአብሄር መሐሪ በወንጌላዊ ዘገዬ መኮነን 05.07.2020

111_እግዚአብሄር መሐሪ   በወንጌላዊ ዘገዬ መኮነን የእግዚአብሄር መሐሪነት የገባው እግዚአብሄር የሚምር የሚራራ መሆኑንን የተረዳው አብርሃም ስለሌሎች ያደረገውን ጸሎት እና ልመና ላይ የተመሰረተ ቃል ነው:: እኛም የእግዚአብሄር ምህረት እንደገበው ሰው እግዚአብሄር ለብዙዎች ምህረትን እንዲያደርግ  አጥብቀን እንጸልይ ዘንድ ያስፈልገናል::

110_የፈርሃ እግዚአብሔር በረከቶች 28.06.2020

"የፈርሃ እግዚአብሔር በረከቶች" በሚል ር ዕስ በወንድም ያቬሎ ናታዬ የቀረበ የእግዚአብሔር ቃል መል ዕክት:: የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች: መዝ. 25:12-14/ሚል. 3:16-18

Höre den Podcast Ethiopian Christian Fellowship Church in Finland in Replaio

Radio und Podcasts in einer App - kostenlos und ohne Anmeldung. Installiere sie noch heute und verpasse den Start nicht

Bei Google Play herunterladen

Replaio ist kein Herausgeber von Podcasts; die Namen der Sendungen, Cover und Audioinhalte gehören ihren Autoren und werden über öffentliche RSS-Feeds verbreitet