ECFC in Finland

Ethiopian Christian Fellowship Church in Finland

This is a podcast from the Ethiopian Christian Fellowship in Finland, where you can listen to biblical teachings, messages, and sermons. May God bless all our listeners.

Určitě navštivte web podcastu a podpořte jeho tvůrce: ecfc-finland.org

Autor

ECFC in Finland

Kategorie

Religion

Web podcastu

ecfc-finland.org

Nejnovější epizoda

4. říj 2026

Kde poslouchat?

Podcasty v aplikaci Replaio Radio Už brzy

Podcasty míří do aplikace už brzy. Nainstaluj si ji teď a jako první uvidíš úplně nový pohled na podcasty

Stáhnout z Google Play Nainstaluj zdarma Android téměř 10 mil. stažení · hodnocení 4,8 iOS už brzy

Epizody

084_ጨምሩ! ክፍል 3 12.01.2020

"ጨምሩ!" በሚል ርዕስ በ2 ጴጥ. 1 ላይ ተመሥርቶ በወንድም ያቬሎ ናታዬ የቀረበ ተከታታይ የእግዚአብሔር ቃል መልዕክት 3ኛ ክፍል::

083_የሰው ስራ እና የእግዚአብሄር ስራ 05.01.2020

083_የሰው ስራ እና የእግዚአብሄር ስራ በፓስተር ሳምሶን ስምኦን አቤቱ ስራህን ሰርተህልናልና ሰላምን ትሰጠናለህ:: ኢሳ 26:12 ሰዎች የራሳቸውን ስራ የሚሰሩበት ጊዜ አለ እግዚአብሄር ደግሞ የራሱን ስራ የሚሰራበት ጊዜ አለ በዘፍ 15:1 ጀምሮ ባለው ላይ የተመሰረተ ከእግዚአብሄር ቃል መልእክት

082_እግዚአብሔርን ማወቅ ክፍል 2 01.01.2020

"እግዚአብሔርን ማወቅ" በሚል ርዕስ በወንጌላዊ ዘገዬ መኮንን የቀረበ የእግዚአብሔር ቃል መልዕክት ቀጣይና የመጨረሻ ክፍል:: የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች: /ለ) እግዚአብሔርን ማወቅ ራሱ ምንድን ነው? 1) የእግዚአብሔርን ህይወት መካፈል ነው መዝ. 46:10፣ ዮሐ. 4:10፣ ዮሐ. 14:27፣ 2) እግዚአብሔርን መታዘዝ ነው ኤር. 22:16 3) እውነተኛ አንድነት በቅዱሳን ኅብረት ማድረግ ነው ኤፌ. 4:13፣ 4) የህይወት ልምምድ ነው ኢዮ. 42:2-3፣ 2ጢሞ. 1:12 ሐ) እግዚአብሔርን አለመፈለግ የሚያመጣው ፍርድ ሮሜ 1:28፣ ዳን. 4:25 መ) ማጠቃለያ: ሆሴ. 6:3/

081_እግዚአብሔርን ማወቅ ክፍል 1 29.12.2019

"እግዚአብሔርን ማወቅ" በሚል ርዕስ በወንጌላዊ ዘገየ መኮንን የቀረበ የእግዚአብሔር ቃል መልዕክት የመጀመሪያው ክፍል:: የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች: መግቢያ/ኢሳ. 1:3፣ 1ሳሙ. 2:3፣ ፊል. 3:9-11፣ ኤፌ. 1:16-19/ ሀ) እግዚአብሔርን ማወቅ ለምን? የዘላለም ህይወት ነው: ዮሐ. 17:1-3፣ ለእግ/ር ህዝብ ዋና ነገር ስለሆነ: ዘዳ. 8:3፣ ሆሴዕ 6:6፣ እግዚአብሔርን ማወቅ ከስህተት ይጠብቃል: ማቴ. 22:29፣ እግዚአብሔርን ማወቅ የእግዚአብሔርን ቁጣ ያርቃል: ሆሴዕ 4:1፣ ከጥፋት ይከልላል. ሆሴዕ 4:6፣ ለ) እግዚአብሔርን ማወቅ ራሱ ምንድን ነው? ማስተዋልን ማግኘት ነው: ኢሳ. 6:1፣ ራዕ. 4:1፣ ማቴ 16:13-...

080_ቅዱሱ የእግዚአብሔር ልጅ! 08.12.2019

"ቅዱሱ የእግዚአብሔር ልጅ" በሚል ርዕስ የጌታችንና የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ልደትን አስመልክቶ በወንጌላዊ ዘገዬ መኮንን የቀረበ የእግዚአብሔር መልዕክት:: የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል: /ሉቃ. 1:26-35/

079_ጨምሩ ክፍል 2 01.12.2019

ጨምሩ በሚል ርዕስ በ2 ጴጥ. 1 ላይ ተመሥርቶ በወንድም ያቬሎ ናታዬ የቀረበ የእግዚአብሔር ቃል መልዕክት ቀጣይ ክፍል::

078_ጨምሩ ክፍል 1 24.11.2019

078_ጨምሩ ክፍል 1 በወንድም ያቬሎ ናታዬ በመንፈሳዊ ህይወት ለመጨመር መለኮታዊ ባህርይን መላበስ 2 ጴጥ 1:1-11 ላይ የተመሰረተ 0.መግቢያ መጽሃፉና መልእክቱ 1.እ/ርና የሰው መለኮታዊ ማንነት 2.የተሰጠን የመለኮት ሃይልና ተስፋ ምንድናቸው:: 3.የመለኮቱ ሃይል እጅግ ታላቅና ክቡር የሆነው ተስፋ ለምን ተሰጠን:: 4.የመለኮታዊ ባህርይና የመንፈሳዊ ህይወት መሰረቶች (1ኛ.የሰው ድርሻ እና 2ኛ. የእ/ር ድርሻ)

077_ለምንድነው ዘወትር መጸለይ የሚያስፈልገን? 17.11.2019

077_ለምንድነው ዘወትር መጸለይ የሚያስፈልገን ወንድም ዶ/ር ተከለ ማርቆስ  በእለቱ የቀረበ የእግዚአብሄር ቃል መልእክት:  ሁልጊዜ ጸልዩ የሚለውን ቃል ላይ በመመስረት "ለምንድነው ዘወትር መጸለይ የሚያስፈልገን?" ለሚለው ምላሽ ይሆን ዘንድ በአስር ዋና ዋና ነጥቦች ከፋፍሎ  የሚያስረዳ በትምህርት መልክ የቀረበ መልእክት:: ጥቅሶች በጥቂቱ . ከእ/ር ጋር ህብረት ለማድረግ መዝ 42:1,ጥበብን ለማግኘት ያእ1:5, ከክፋት ለመጠበቅ መዝ20:1,ከፍርሃት እና ከጭንቀት ለመወጣት ፊሊ 4:4, እና... መዝ 32:1,ሉቃ 22:40 ,ሮሜ10:14,ኤፌ 1:15 ሌሎችም

076_ጸሎት 10.11.2019

"ጸሎት የአምልኮ ዋና ክፍል" በሚል አሳብ ላይ ተመሥርቶ በወንድም ተከለ ማርቆስ (ዶ/ር) የቀረበ የእግዚአብሔር ቃል መልዕክት:: መልዕክቱ ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለደቀ መዛሙርቱ ያስተማረውን ጸሎት መሠረት አድርጎ እኛም እንደ ክርስቶስ ተከታዮች ጸሎታችን ምላሽ ያለው እንዲሆን እንዴት መጸለይ እንደሚገባን ያስረዳል:: የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች: ማቴ. 21:22፣ 6:9-13/ሉቃ. 11:1-5/ዮሐ. 15:7/ያዕ. 4:3/ምሳ. 3:5

075_የወንድሙ ጠባቂ ማን ነው? 03.11.2019

"የወንድሙ ጠባቂ ማን ነው? ቁምና ልብህን ፈትሽ ቅጥርህንም ጠብቅ!" በሚል ርዕስ በእህት ለምለም ጌታቸው የቀረበ የእግዚአብሔር ቃል መልዕክት:: የመልዕክቱ ማዕከላዊ ሐሳብ ልክ እንደ ቃየን የወንድሞቻችንን ክፋት (ሞት) የምንጠብቅ ሳንሆን ልክ እንደ ሙሴ እህት ወንድሞቻችንን ከክፋት (ከሞት) የምንጠብቅ እንድንሆንና በክርስቶስ የተሰጠንን አንድነትና ኅብረት አስበን በዓለም ውስጥ እንዳሉት የጥፋት መሣሪያ ላለመሆን ልባችንን እንድንጠብቅ ማሳሰብ ነው:: የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች: ዘፍ. 4:1-10/1ቆሮ 1:9-10/ዘጸ. 2:1-10/ምሳ. 18:19-21

074_[ለታላቁ ተልዕኮ] ንቁ! 27.10.2019

"ንቁ" በሚል ርዕስ በፓስተር ሰሎሞን አምደ የቀረበ የእግዚአብሔር ቃል መልዕክት:: የመልዕክቱ ማዕከላዊ ሀሳብ ሰዎችን ከዘላለም ጥፋት ለማዳን ወንጌልን መመስከር የእያንዳንዱ አማኝ ደቀ መዝሙር ኃላፊነት መሆኑንና ለወንጌላዊያን ብቻ የሚተው ሥራ አለመሆኑን አጽንዖት ሰጥቶ መግለጽ ነው:: የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች: ማቴ. 28:18-20/ሐዋ. 1:8/ማቴ. 13:24-30

073_በውስጥህ/ሽ ወንዝ አለ! 25.10.2019

ማክሰኞ ምሽት (22.10.2019) "በውስጥህ/ሽ ወንዝ አለ!" በሚል ርዕስ በፓስተር ሰሎሞን አምዴ የቀረበ የእግዚአብሔር ቃል መልዕክት:: የመልዕክቱ ዋና ትኩረት ለኢየሱስ ክርስቶስ ህይወቱን የሰጠና መንፈስ ቅዱስን የተቀበለ ማንኛውም ሰው የሌሎችን ህይወት መለወጥ የሚችል እምቅ መንፈሳዊ አቅም (ወንዝ) በውስጡ እንዳለ በእግዚአብሔር ቃል መሠረት መተንተንና ማስገንዘብ ነው:: የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች: ሕዝ. 47:1-12/ራዕ. 22:1-2/ዮሐ. 7:38

072_ጌታ ኢየሱስ ተመልሶ ይመጣል! 20.10.2019

"ጌታ ኢየሱስ ተመልሶ ይመጣል!" በሚል ርዕስ በወንጌላዊ ዘገዬ መኮነን የቀረበ የእግዚአብሔር ቃል መልዕክት:: የመልዕክቱም ዋና ጭብጥ "ስለ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ዳግም መምጣት ማውቅ ለምን  ያስፈልጋል?"  የሚል ሲሆን 1) ተዘጋጅቶ ለመኖር  2) ከጌታ የተሰጠንን አደራ በትጋት ለመፈጸም እንዲረዳን  እና 3) በህይወት ጎዳና መጽናኛችን ስለመሆኑ በመልዕክቱ በስፋት ተብራርቷል::  የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች: ሐዋ 1:9-11/ ራዕይ 1:5-7፣ ራዕይ 22:12/ማቴ. 24:37-44, 45-51/ሉቃ. 12:35-40, 41-48/1 ተሰ. 4:13-18 

071_አምልኮ 13.10.2019

"አምልኮ" በሚል ርዕስ በወንድም ተከለ ማርቆስ (ዶ/ር) የቀረበ የእግዚአብሔር ቃል መልዕክት::

070_ጌታ እንዳስተማረን እንጸልይ! 06.10.2019

"ጌታ እንዳስተማረን እንጸልይ!" በሚል ርዕስ በማቴ. 6:9-13 ባለው ክፍል ላይ ተመሥርቶ በወንድም ያቬሎ ናታዬ ያታሣ የቀረበ የእግዚአብሔር ቃል መል ዕክት::

069_የስኬታማ ጸሎት ቁልፎች 29.09.2019

"የስኬታማ ጸሎት ቁልፎች" በሚል ርዕስ በወንድም ያቬሎ ናታዬ የቀረበ የእግዚአብሔር ቃል መልዕክት:: የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች ዮሐ. 15:7/ መዝ. 37:4/ ማቴ. 6:33

068_በበጎ ስራና በቃል መጽናት 22.09.2019

068_በበጎ ስራና በቃል መጽናት ዶ/ር ተከለ ማርቆስ እንግዲያስ፥ ወንድሞች ሆይ፥ ጸንታችሁ ቁሙ፥ በቃላችንም ቢሆን ወይም በመልእክታችን የተማራችሁትን ወግ ያዙ። ራሱ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስና የወደደን በጸጋም የዘላለምን መጽናናት በጎንም ተስፋ የሰጠን እግዚአብሔር አባታችን ልባችሁን ያጽናኑት በበጎም ሥራና በቃል ሁሉ ያጽኑአችሁ።2ኛ ተሰ 2:15-15 ላይ የተመሰረተ መልእክት::

067_ለአገልጋይ የተሰጠ ማበረታቻ :መመሪያ እንዲሁም ምክር 08.09.2019

067_ለአገልጋይ የተሰጠ ማበረታቻ :መመሪያ እንዲሁም ምክር በወንጌላዊ ዘገዬ መኮነን በ1ኛ ጢሞቲዎስ ከምእራፍ 1 እስከ ምእራፍ 6 ድረስ በአለው መልእክቱ ላይ ስለ አገልጋይ እውነተኛ ማንነት:እውነትን ስለማሳወቅ ባጠቃላይ እውነት ላይ አትኩሮት ሰጥቶ ሃዋርያው ጳውሎስ ለጢሞቲዎስ በጻፈው መልእክት ላይ የተመሰረተ ነው::

066_እድል እና ምህረትን መስጠት የእግዚአብሄር ስጦታ ነው:: 02.09.2019

066_እድል እና ምህረትን መስጠት የእ/ር ስጦታ ነው:: በእህት ለምለም ጌታቸው "አስቀድሞ ተሳዳቢና አሳዳጅ አንገላችም ምንም ብሆን ይህንን አደረገልኝ ::ነገር ግን ሳላውቅ ባለማመን ስላደረግሁት ምህረት አገኘሁ" ሐዋ 1:13 ወደ ፊሊሞና 1:1-25  አናሲሞስ እና ሐዋ 9:1-21 ሳኦል(ጳውሎስ)

065_ማስተስረያውስ ምንድን ነው? 27.08.2019

065_ዳዊትም የገባዖንን ሰዎች፦ የእግዚአብሔርን ርስት ትባርኩ ዘንድ ምን ላድርግላችሁ? ማስተስረያውስ ምንድር ነው? አላቸው።  መጽሐፈ ሳሙኤል ካልዕ 21:3

064_እግዚአብሄር እንደተናገረ ያደርጋል! 18.08.2019

 "እግዚአብሔር እንደተናገረ ያደርጋል" በሚል ርዕስ በወንጌላዊ ዘገዬ መኮንን የቀረበ የእግዚአብሔር ቃል መልዕክት:: ዘፍ. 21:1

063_የሚመካ በእግዚአብሔር ይመካ! 11.08.2019

በሉኪ በተደረገው የቤተ ክርስቲያን የሽርሽር ጊዜ ላይ "የሚመካ በእግዚአብሔር ይመካ" በሚል ርዕስ በ 1ቆሮ. 1:22-31 ላይ ተመሥርቶ በወንጌላዊ ዘገዬ መኮንን የቀረበ የእግዚአብሔር ቃል መልዕክት:: 

062_የልብን ክፋት ልብ እንበል! 04.08.2019

"የልብን ክፋት ልብ እንበል!" በሚል ርዕስ በኤር. 17:9 ላይ ተመሥርቶ በወንድም ያቬሎ ናታዬ የቀረበ የእግዚአብሔር ቃል::

061_ለእግዚአብሔር መሰጠት 21.07.2019

የተፈጠርንበትን መልካም ሥራ ለማድረግ "ለእግዚአብሔር መሰጠት" በሚል ርዕስ በወንድም ተከለ ማርቆስ (ዶ/ር) መዝ. 37:1-6 ላይ ተመሥርቶ የቀረበ የእግዚአብሔር ቃል መልዕክት:: 

060_ቃል/የቃል ጉልበት 14.07.2019

 በመዝ. 34:12 ላይ ተመሥርቶ በእህት ለምለም ጌታቸው የቀረበ የእግዚአብሔር ቃል መልዕክት:: 

Poslouchej podcast Ethiopian Christian Fellowship Church in Finland v Replaio

Rádio a podcasty v jedné aplikaci - zdarma a bez registrace. Nainstaluj si ji ještě dnes a nepropásni premiéru

Stáhnout z Google Play

Replaio není vydavatelem podcastů; názvy pořadů, obálky a audio patří jejich autorům a šíří se přes veřejné RSS kanály