DW | Amharic - News
News, Analysis and Service from Germany and Europe - in 30 Languages
Určitě navštivte web podcastu a podpořte jeho tvůrce: www.dw.com
Kde poslouchat?
Podcasty v aplikaci Replaio Radio Už brzyPodcasty míří do aplikace už brzy. Nainstaluj si ji teď a jako první uvidíš úplně nový pohled na podcasty
Epizody
የአየር ንብረት ለውጥና የአውሮፕላን ጥቃት ያባባሰው ሰብአዊ ቀውስ በሱዳን 17.10.2026
የረድኤት ድርጅቶች ሱዳን ውስጥ ከቤት ንብረታቸው ለተፈናቀሉት አገልግሎት የሚሰጡ የጤና ተቋማት ሙሉ ለሙሉ ከሥራ ውጪ ሊሆኑ እንደሚችሉ እያስጠነቀቁ ነው። ሱዳን ውስጥ በሰሜን ኮርዶፋን እና በብሉ ናይል ግዛት አንዳንድ አካባቢዎች በሱዳን ጦር እና በፈጥኖ ደራሹ ኃይል መካከል የሚካሄደው ውጊያ ተጠናክሯል።
ኬንያ ራይላ ኦዲንጋ የታገሉለትን ዴሞክራሲያዊ ምህዳር ማስጠበቅ ትችል ይሆን? 17.10.2026
ኬንያውያን ባለፈው ዓመት በዚህ ወቅት ከዚህ ዓለም በሞት የተለዩት የቀድሞው የሀገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ራይላ ኦዲንጋ ለፖለቲካው ያበረከቷቸውን ጉዳዮች የሰሞኑ መነጋገሪያ አድርገዋቸዋል።
የኢትዮጵያ ፌድራል መንግሥት ባለአደራ አስተዳደር ሲመሰርት የትግራይ የሰላም እና ለውጥ ምክር ቤት ለምን ፈረሰ? 17.10.2026
ህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይን ከሥልጣን ለማስወገድ የተመሠረተው የትግራይ የሰላም እና ለውጥ ምክር ቤት ከአምስት ወራት ገደማ በኋላ መፍረሱን ትላንት አርብ ጥቅምት 06 ቀን 2019 አስታውቋል። የትግራይ የሰላም እና ለውጥ ምክር ቤት አባል የነበሩ ፓርቲዎች“የምርጫ ቦርድ ሕግ በሚፈቅደው መሠረት የጋራ ትግላቸውን” እንደሚቀጥሉ ተገልጿል።
የአሜሪካ አጋማሽ ዘመን ምርጫ 17.10.2026
የአሜሪካ ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ በሥልጣናቸው አጋማሽ የሚካሔደው ምርጫ ሲቃረብ ለሪፐብሊካን ዕጩዎች ድጋፍ ለማሰባሰብ ባደረጓቸው ንግግሮች የኢትዮጵያ፣ ታላቁ የህዳሴ ግድብ እና የሶማሊያን ጉዳይ አንስተዋል። ከሁለት ሣምንት ገደማ በኋላ የሚካሔደው ምርጫ የሕግ አውጪ ምክር ቤቶች፤ የግዛት አስተዳዳሪዎችና ከንቲባዎች የሚመረጡበት ነው።
የሚዲያ ነፃነትን የሚጋፉ "በርካታ" አሳሳቢ ጉዳዮች ተለይተዋል - የኢሰመኮ ዓመታዊ ሪፖርት 16.10.2026
በተጠናቀቀው በጀት ዓመት የሚዲያ ነፃነትን የሚጋፉ "በርካታ" ያላቸው አሳሳቢ ጉዳዮች መለየታቸውን የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን ባለፈው ሳምንት ይፋ ባደረገው ዓመታዊ የምርመራ ዘገባው አመለከተ። "የሚዲያ ምኅዳሩ ሕግን፣ ሀገራዊ እሴቶችን እና ፍላጎቶችን ባከበረ መልኩ እንዲንቀሳቀስ ይደርጋል" መባሉ ይታወሳል።
የጋምቤላ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን በደረሰው የጸጥታ ችግር የሰው ህይወት ማለፉን ገልጸው የሰዓት እላፊ ገደብ ጥለዋል፡፡ በዛው እለትም በከተማው የሰው እንቅስቃሳ እንደለለና ተቋማት ዝግ መሆናቸው ተገልጸዋል፡ 16.10.2026
በጋምቤላ ክልል ዋና ከተማ ባለፈው ማክሰኞ ምሽት ባልታወቁ ሰዎች ደርሰዋል በተባለው ጥቃት የአራት ሰዎች ህይወት ማለፉ ተከትሎ ትናንት እሰከ ማታ ድረሰ የተኩስ ድምጽ ሲሰማ ነበር ተብለዋል፡፡ በርካቶች ጥቃቱን በማውገዝ ወደ ክልሉ ምክር ቤት በመሄድ ድምጻቸውን ማስማታቸውን ያጋርናቸው የከተማወ ነዋሪዎች ተናግረዋል፡፡
በቆቦ ከተማ የሚገኙ ከስድስቱ የራያ አካባቢዎች የተፈናቀሉ ነዋሪዎች፣ በአካባቢያቸው የሚካሄደው ጊዜያዊ የሽግግር አስተዳደር የምርጫ ሂደት አካታችነትና ገለልተኛነት የጎደለው ነው በማለት እንዲቆም በሰላማዊ ሰልፍ ጠየቁ። 16.10.2026
ባለፈው አንድ ዓመት የማንነት ጥያቄ ካላቸው ስድስቱ የራያ አካባቢዎች ተፈናቅለው በቆቦ ከተማ የሚኖሩ የተሾመዉ ጊዜያዊ የሽግግር አስተዳደር ምርጫ እኛን ያገለለ ነዉ ሲሉ በሰላማዊ ሰልፍ ጠየቁ፡፡ በሰላማዊ ሰልፉ ተሳፊዎች የአላማጣ ዎፍላ ባላ ራያ አላማጣ ዛታና ኮረም ተፈናቃዮች እየተካሄደ ሁኔታ አካታችነትና ገለልተኛነት የጎደለው ነው ብለዋል፡፡
የኢትዮጵ መንግስት የትግራይ ክልልን የሚያጸና ያለውን የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር እንዲቋቋም የሚስችል ውሳኔ አስተላልፏል። አስተያየት ሰጪ የክልሉ ነዋሪዎች ከመስተዳድሩ መሰየም ጋር ተያይዞ ተስፋም ስጋትም እንዳላቸው ገልጸዋል፡፡ 16.10.2026
በትግራይ ክልል“በህወሓት ዕንቅፋትነት የተነሣ ሳይሳካ ቀርቷል” ያለው የኢትዮጵያ መንግስት የትግራይ ሕዝብ የራቀውን ሰላም እንዲጎናጸፍ፣ ራስን በራስ የማስተዳደር መብቱ እንዲረጋገጥ እንዲሁም ከሌሎች የኢትዮጵያ ሕዝቦች ጋር በኅብረ-ብሔራዊ አንድነት ጸንቶ እንዲኖር ለማስቻል የባለአደራ አስተዳደር መመስረቱን ዛሬ አስታውቋል፡፡
የፌዴራል መንግሥት በምን በምን ጊዜ ወደ ክልሎች ጣልቃ ይገባል? 16.10.2026
ከፌዴራል መንግሥት በሚሰጠው አቅጣጫና መመሪያ መሠረት ትግራይ ክልልን ለሚቀጥሉት 6 ወራት የሚያስተዳድር አሥር ተግባራት ያሉት ባለ አደራ አስተዳደር ተመሠረተ። ይህ ባለ አደራ አስተዳደር፣ ክልሉ ሰላሙን ማስከበር እንዲችል፣ ትኩረቱን በልማት ላይ እንዲያደርግ እና በአንድነት ጸንቶ መኖር እንዲችል ይሠራል ተብሏል።
በሰሜን ኢትዮጵያ አለመረጋጋት በሰፈነበት በአሁን ወቅት በኦሮሚያ ክልል አንዳንድ ቦታዎች ጸጥታ ችግሩ እንደቀጠለ መሆኑ ተናግረዋል። የክልሉ ነዋሪዎች እንዳመለከቱት የጸጥታው ስጋት አሁንም አልፎ አልፎ ስጋት መደቀኑን እንቀጠለ ነው፡፡ 16.10.2026
የኖኖ ወረዳ ነዋሪ “ባለፈው ሳምንት ውስጥ በድሬ እንጪኒ ወረዳ በመንግስት የጸጥታ ሃይሎች እና በኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት መካከል በነበረው ግጭት በርካታ ሰዎች ተገድለዋል። ከኖኖ ወረዳ እዛ ተመድበው የነበሩ ሦስት የጸጥታ አካላት መሞታቸዉንም አስታውቃለሁ” ብለዋል፡፡ ዶይቼ ቬለ ከባለስልጣናት መረጃዎችን ለማግኘት ያደረገው ጥረት አልተሳካም፡፡
ኢትዮጵያ ዉስጥ የጦርነቱ ዋነኛ ሰለባዎች ሴቶችና ህጻናት ናቸው-ግን ታዲያ i,ሴቶች ድምፅ በየመድረኩ ለምን ቀነሰ? 15.10.2026
በአገር ዉስጥ በሚቀሰቀስ ጦርነት፤ ሴቶችና ታዳጊ ህጻናት የመጀመርያ ተጎጅዎች ናቸዉ። በጦርነት ወቅት ሴቶች ላይ የሚደርሱ ዋና ዋና ጉዳቶች፤ ፆታዊ ጥቃትን እንደ መሳርያ መጠቀም፤ የሥነ ልቦና ጉዳት፤ መፈናቀል እና የኑሮ ዉድነት፤ የጤና አገልግሎት እጦትን መጥቀስ ይቻላል። ኢትዮጵያ ዉስጥ የሴቶች ድምፅ በየመድረኩ ለምን ቀነሰ መጣ? ጦርነት ይቁም!
አሜሪካን ጨምሮ ብዙዎች እንዲናገሩ እያደረገ ያለው የኢትዮጵያና የኤርትራ ውጥረት 15.10.2026
የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማርኮ ሩቢዮ በአፍሪካ ቀንድ አካባቢ የሚገኙ ሁሉም ሃገራት የጎረቤቶቻቸውን «ሉዓላዊነትና የግዛት አንድነት ማክበር» እንዳለባቸው ተናገሩ።
በሰሜን ኢትዮጵያ የሰብዓዊ ድጋፍ አቅርቦት 15.10.2026
የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰብዓዊ እርዳታ ማስተባበሪያ ድርጅት (UN-OCHA) በሰሜን ኢትዮጵያ የሰብዓዊ አቅርቦት መሻሻል ማሳየቱን አስታወቀ። የተባበሩት መንግሥታት ደግሞ ከአስቸኳይ እርዳታ ምላሽ ማዕከሉ (CERF) በሰሜን ኢትዮጵያ ለሕይወት አድን እርዳታ 8.5 ሚሊየን ዶላር መመደቡን ነው አመልክቷል።
በጦርነት በምትታመሰው የመን የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ተማጽኖ 15.10.2026
በየመን የሚገኙ የኢትዮጵያ ስደተኞች አሳሳቢ ሰብአዊ ሁኔታ ላይ ስለምንገኝ ድምፃችን እንዲሰማ ሲሉ ጥሪ አቀረቡ። እነዚህ ወገኖች ለዶቼ ቬለ በጻፉት የተማጽኖ ደብዳቤ፤ «በየመን ውስጥ የምንኖር የኢትዮጵያ ስደተኞች በእጅጉ አስከፊ የሰብአዊ፣ የጤና እና የደኅንነት ችግር ውስጥ እንገኛለን» ብለዋል።
በሰሃላ ሰየምት ወረዳ የተከሰተው አስከፊ ድርቅ 15.10.2026
በዋግህምራ ብሔረሰብ አስተዳደር ዞን ሰሃላ ሰየምት ወረዳ በ13 ቀበሌዎች ከ66 ሺህ በላይ ሰዎች ሲኖሩ ከእነዚህም ውስጥ ከ58 ሺህ በላይ ሰዎች የረሃብ ተጠቂ መሆናቸውን የወረዳው ግብርና ጽሕፈት ቤት መረጃ ያመለክታል።
በትግራይ የሚካሄደው ውጊያ እንዲቆም መጠየቁ 15.10.2026
በትግራይ ክልል የሚካሄደው ግጭት ቆሞ ወደ ሰላም የሚያመራ እውነተኛ መንገድ እንዲጀመር የትግራይ ማኀበረሰብ ዳያስፖራ ድርጅቶች ጥሪ አቀረቡ።
ቃለ መጠይቅ፣ «ያልተጠናቀቀ ፍቺ፣ ያልተሳካ ጉርብትና-የኤርትራና የኢትዮጵያ ጉዳይ» አቶ የሱፍ ያሲን 1991 15.10.2026
ታዛቢዎች ኋላ እንዳሉት የጠቅላይ ሚንስትር ዓብይ አሕመድና የፕሬዝደንት ኢሳያስ አፈወርቂ ወዳጅነት አንደኛ፣- በግልፅ፣ በሕግና በሕዝብ ይሁንታ የተደገፈ አልነበረም።ሁለተኛ፣- የጋራ «ጠላት» የሚሉትን ህዝባዊ ወያኔ ሓርነትን ትግራይ (ህወሓት)ን ለመዉጋት ሥለነበር የሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት በሰላም ሥምምነት ሲያበቃ ወዳጅነቱም ወደጠላትነት ተቀይሯል
የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ድርቅ የተደመረበትን የጦርነት ጫና መሸከም ይችላል? 14.10.2026
ከ2019 የኢትዮጵያ 2.4 ትሪሊዮን ብር በጀት ውስጥ 96.3 ቢሊዮን ብር የሚሆነው ለመከላከያ ተመደበ ነው። ይሁንና ጦርነት የሚያስፈልገው ከፍተኛ ገንዘብ በመንግሥት ወጪ እና የበጀት ጉድለት ላይ ጫና ሊያሳድር ይችላል። በምንዛሪ ሥርዓት ለውጥ እየተዳከመ የሔደው ብር ጭምር እና የዋጋ ግሽበት ድርቅ በተደመረበት የጦርነት ዳፋ መፈተናቸው አይቀርም።
የኢትዮጵያ ኃይሎች የኤርትራ ድንበር አቅራቢያ የምትገኝ ከተማ መድረሳቸው ተገለፀ 14.10.2026
የኢትዮጵያ ፌደራል መንግሥት ኃይሎች እና ተባባሪዎቹ ከኤርትራ ድንበር አቅራቢያ ከምትገኘው ዛላንበሳ ከተማ መድረሳቸውን እማኞች ገልፀዋል።አንድ የአካባቢው ነዋሪ ለዶቼ ቬለ እንደገለፁት የኤርትራ ሠራዊት ዛላአምበሳ ከተማ ላይ የሚገኝ ቢሆንም በዙሪያው በሚገኙ የገጠር ቀበሌዎች ግን የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት መግባቱን ገልፀዋል።
በትግራይ ክልል ከሚንቀሳቀሱ የፖለቲካ ፓርቲዎች አንዱ ሳልሳይ ወያነ ያወጣው መግለጫ ምን ይላል? 14.10.2026
በትግራይ ክልል የተከሰተው ረሃብ እና የተፈናቃዮች ሁኔታ ቅድሚያ እንዲሰጥ ተጠየቀ
የትግራይ ክልል ህዝብ አስተዳዳሪዎቹን መምረጡ መረጋጋቱን ያረጋግጥለት ይሆን? 14.10.2026
በትግራይ ክልል የአካባቢ መስተዳድሮች መዋቀር እና ወቅታዊ ሁኔታ
የቀጠለው የደቡብ ወሎና የሰሜን ሸዋ ውጊያ 14.10.2026
በአማራ ክልል ደቡብ ወሎ እንዲሁም ሰሜን ሸዋ በመንግሥት ኃይሎች እና በፋኖ ታጣቂዎች መካከል ውጊያ ተጠናክሮ መቀጠሉን የአካባቢው ነዋሪዎች ለዶቼ ቬለ ገለጹ።
የሶማሌ ላንድ ለዶናልድ ትራምፕ ንግግር የሰጠችው መልስ እና አንድምታው 14.10.2026
የሶማሌ ላንድ ለረዥም ጊዜ ስትጠብቅ የነበረው ዓለማቀፍ ዕውቅና ቀርቦ ይኾን?
በአማራ ክልል በሶስት ዞኖች የሚደረገዉ ዉጊያ ቀጥሏል 13.10.2026
ሌላው የወገልጤና ከተማ ነዋሪም ጦርነቱ በወገልጤና ከተማ ውስጥ መሆኑን ገልጸው ተዋጊዎቹ ማህበረሰቡን ከተማ ለቆ እንዲወጣ ጥሪ ማቀረባቸውን ይናገራሉ። ትናንት በመጀመርያው ጦርነትም በተባራሪ ጥይት የተመቱ ሰዎች መኖራቸውና ጉዳቱ ግን የከፋ አለመሆኑን ተናግረዋል።
የዩናይትድ ስቴትስና ብሪታንያ ወደ ኢትዮጵያ ለሚጓዙ ዜጎቻቸዉ አዲስ ማሳሰቢያ አወጡ 13.10.2026
ትናንት ባወጣው የጉዞ ማሳሰቢያ የተለያዩ ምንጮችን የጠቀሰው በኢትዮጵያ የአሜሪካ ኤምባሲ፣ የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት እና የትግራይ የሰላም ኃይሎች ትግራይ ክልል ውስጥ አዲግራት፣ አድዋ እና ሽሬን ጨምሮ አቢ አዲ ከተሞችን መቆጣጠራቸውን፣ ከሰሜን አፋር አካባቢ የታጠቁ የተቃዋሚ ኃይሎችን ማስወገዳቸውንም አመልክቷል።
Replaio není vydavatelem podcastů; názvy pořadů, obálky a audio patří jejich autorům a šíří se přes veřejné RSS kanály