DW
እንወያይ | Deutsche Welle
ኢትዮጵያን በሚመለከቱ ጉዳዮች ላይ ከተለያዩ እንግዶች እና በተለያዩት የዓለም ሀገሮች ከሚገኙት ወኪሎቻችን ጋ የምናካሂደውን እና በየሣምንቱ እሁድ ከምሽቱ አንድ ሰዓት ከአሥር ደቂቃ ላይ የሚተላለፈውን የውይይት ዝግጅት ያዳምጡ።
Podcast'in sitesini ziyaret etmeyi ve yapımcısını desteklemeyi unutma: www.dw.com?maca=amh-podcast_amh_diskussionsforum-8741-xml-mrss
Yazar
DW
Kategori
Podcast web sitesi
www.dw.com?maca=amh-podcast_amh_diskussionsforum-8741-xml-mrss
Son bölüm
27 Eyl 2026
Nereden dinlenir?
Uygulamada podcast'ler Replaio Radio Çok yakındaPodcast'ler çok yakında uygulamaya geliyor. Şimdi yükle ve podcast'lere yepyeni bir bakışı ilk gören sen ol
Bölümler
እንወያይ፤የኢትዮጵያ እና ኤርትራ ፍጥጫ ወደየት ያመራ ይሆን?መፍትሄውስ ምን ይሁን? 15.02.2026 47:35
በ2010 ዓ/ም እንደገና የጀመረው የኢትዮጵያ እና የኤርትራ ግንኙነት፤ በሀገር ውስጥም ሆነ በዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ዘንድ አድናቆት የተቸረው እና የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚንስትርን የሰላም ኖቬል እስከማሸለም የደረሰ ነበር።ይሁንና የሀገራቱ ሰላማዊ ግንኙነት የዘለቀው ለጥቂት ዓመታት ሲሆን፤ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ደግሞ አለመግባቱ እየተካረረ መጥቷል።
የትግራይ ግጭት እና ዘላቂው መፍትሔ 08.02.2026 41:32
የፌደራል ኃይሎች ከአወዛጋቢዎቹ ከአላማጣ እና ኮረም እንዲሁም ከሌሎች አጎራባች ከተሞች መውጣታቸው ከተሰማ በኋላ ነዋሪዎች ጦርነት ይቀሰቀሳል በሚል ከከተሞቹ መሸሽ መጀመራቸው ሌላው ስጋቱ እንዲጨምር ያደረገ ክስተት ነበር። በትግራይ የድሮን ጥቃቶች በሁለት አካባቢዎች ተፈጸሙ የመባሉ ዜና በሀገር ውስጥም በውጭም ጉዳዩን ይበልጥ አሳሳቢ አድርጎታል።
ውይይት፤ የትራምፕ ሽምግልና ለኢትዮጵያ ምን ይዞ ይመጣ ይሆን?እንዴትስ ጥቅሟን ታስከብር? 01.02.2026 44:16
የአሜሪካው ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ የአባይ ውሃ ባለድርሻነት ለዘለቄታው እልባት እንዲያገኝ በሚል፤iኢትዮጵያ እና ግብፅጽን ዳግም ወደ ድርድር ለማምጣት ሀገራቸው ቁርጠኛ መሆኗን ደጋግመው ገልፀዋል.።ያም ሆኖ ትራምፕ በተለያዩ ጊዜዎች የሚሰጧቸው ወደ ግብፅ ያዘነበሉ አስተያየቶች የገለልተኝነት እና የፍትሃዊነት ጥያቄ ማስነሳቱ አልቀረም።
ባለሙያዎች ከዓመታት በኋላ ወደ ነጠላ አሐዝ ስለወረደው የኢትዮጵያ የዋጋ ግሽበት ምን ይላሉ? 25.01.2026 40:17
የዋጋ ግሽበት ከዓመታት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ወደ ነጠላ አሐዝ ዝቅ እንዳለ የኢትዮጵያ ስታትስቲክስ አገልግሎት አስታውቋል። የዋጋ ግሽበት በታኅሳስ ወደ 9.7% ዝቅ እንዳለ የተገለጸው ሸማቾች በኑሮ ውድነት በሚፈተኑበት ወቅት ነው። ለመሆኑ የብሔራዊ ባንክ ገዥ “እጅግ የሚያስደምም” ያሉት ነጠላ አሐዝ የዋጋ ግሽበት በባለሙያዎች እንዴት ይታያል?
ባለሙያዎች ከዓመታት በኋላ ወደ ነጠላ አሐዝ ስለወረደው የኢትዮጵያ የዋጋ ግሽበት ምን ይላሉ? 25.01.2026 40:17
የዋጋ ግሽበት ከዓመታት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ወደ ነጠላ አሐዝ ዝቅ እንዳለ የኢትዮጵያ ስታትስቲክስ አገልግሎት አስታውቋል። የዋጋ ግሽበት የከዓመት ዓመት ዕድገት በህዳር ወር ከነበረበት 10.9 በመቶ በታኅሳስ ወደ 9.7 በመቶ ዝቅ ብሏል። የዋጋ ግሽበት በታኅሳስ ወደ 9.7% ዝቅ እንዳለ የተገለጸው ሸማቾች በኑሮ ውድነት በሚፈተኑበት ወቅት ነው። ለመሆኑ የብሔራዊ ባንክ ገዥ “እጅግ የሚያስደምም” ያሉት ነጠላ አሐዝ የዋጋ ግሽበት በባለሙያዎች እንዴት ይታያል?
ዉይይት፣ የትራምፕ አስተዳደር ርምጃ፣ የዓለም ሕግና ሥርዓት እንዴትነት 18.01.2026 45:30
የትራምፕ መስተዳድር የቬኑሱዌላን መሪ ማገት ብቻ ሳይሆን የነዳጅ ሐብቷንም ተቆጣጥሯል።የአሜሪካ ባለሥልጣናት ማዱሮን ከማሳገታቸዉ በፊት የየመን ሁቲዎችን፣ የሶማሊያ፣ የኢራቅ፣ የሶሪያና የናጄሪያ ሸማቂዎችን አጠፋለሁ በሚል ሐገራቱን በተደጋጋሚ ደብድበዋል።እስራኤልን አግዘዉ ኢራንን ደብድበዋልም።
እንወያይ፦ ዓለም በጎርጎሪዮሱ 2025 ዓ.ም 04.01.2026 44:41
የጎርጎሪዮሱ 2025 ዓ.ም ተጠናቅቆ አዲስ ዓመት ከባተ እነሆ ዛሬ አራተኛ ቀኑ ተቆጥሯል ። የዛሬው እንወያይ የጎርጎሪዮሱ 2025 ዐበይት ክስተቶችን ወደ ኋላ መለስ ብሎ ይቃኛል ። በዛሬው እንወያይ መሰናዶ ሦስት ተሳታፊዎች ትንታኔ ሰጥተዋል ።
ኢትዮጵያውያንን ጨምሮ ስደተኞች በአሜሪካና በአውሮፓ የገጠማቸው ፈተና 28.12.2025 42:56
ከ5ሺህ በላይ ይሆናሉ የተባሉ ኢትዮጵያውያን ድንገት ወደሀገራቸው እንዲሚመለሱ ተነግሯቸዋል። ኢትዮጵያውንንም ተጠቃሚ ያደርግ የነበረው ቋሚ የመኖሪያና የስራ ፈቃድ የሚያስገኘው የDV መርሃ-ግብር መቋረጡ ተነግሯል። እነዚህ ስደተኞችን የሚያዋክቡ አሰራሮች ወደ አውሮጳ ኅብረት አባል ሀገራትና ብሪታንያም ጭምር የመዛመታቸው አዝማሚያ ያሰጋል።
የመገናኛ ብዙኀን ሁኔታና መጪው ምርጫ በኢትዮጵያ 21.12.2025 45:16
ከጥቂት ዓመታት በፊት የዓለም የፕረስ ነጻነትን ቀን የማስተናገድ እጋጣሚ ሰምሮላት በነበረው ኢትዮጵያ የመገናኛ ብዙኀን የነጻነት ሁኔታ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየከፋ መምጣቱ መነገር ከጀመረ ውሎ አደረ።
እንወያይ፤ ጦርነት ያባባሰው ወሲባዊ ጥቃት በአማራ ክልል 07.12.2025 47:54
ጾታን መሰረት ያደረገ ጥቃት በኢትዮጵያ ስር የሰደደ ችግር ቢሆንም፣ በአገሪቱ እየተከሰቱ ባሉ የትጥቅ ግጭቶች ሳቢያ ጥቃቱ እየተባባሰ መምጣቱ ይነገራል። በአማራ ክልል ላለፉት ሁለት አመታት በፌደራል መንግስትና በፋኖ ሃይሎች መካከል እየተካሄደ ያለው ግጭትም በሴቶች ላይ የሚደርሰውን ወሲባዊ ጥቃት ማባባሱን የቅርብ ጊዜ ዘገባዎች ያመለክታሉ።
ዉይይት፣ የኢትዮጵያ የምርጫ ዝግጅት፣ የተቃዋሚዎች ሥጋትና የሰላም ጥያቄ 30.11.2025 45:30
የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ አሕመድ ባንፃሩ በቅርቡ ከሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ለቀረቡላቸዉ ጥያቄዎች በሰጡት መልስና ማብራሪያ «ምርጫ ለማድረግ መንግሥት በቂ አቅም አለዉ፤ምርጫ እንኳን ዘንድሮ ባለፈዉም ምርጫ አድርገናል እየተዋጋን።» ብለዋል።በግጭት፣ ዉጥረት፣ ተቃርኖና ዉዝግ መሐል ነፃና ፍትሐዊ ምርጫ ሊደረግ ይችላል? ምርጫ ማድረግ ወይም አለማድረጉስ የኢትዮጵያን ዉስብስብ ችግሮች ለማቃለል ይጠቅማል? እንዴት? በዉይይታችን የሚነሱ ጥያቄዎች ናቸዉ።
ውይይት፦ ምን ያስተሳስረው ይሆን? ግጭት ኢትዮጵያ እና ጎረቤት አገራት 23.11.2025 43:01
ውይይት፦ ኢትዮጵያ ውስጥ የሚከሰተው ግጭት ሱዳን ውስጥ፥ የሱዳኑ ኢትዮጵያ ውስጥ ነጸብራቁ በጉልኅ ይታያል ። ከፍ ሲል ግብጽ ከወደታች ደግሞ ሶማሊያም በግጭት ውጥረቱ ስማቸው በተደጋጋሚ ይነሳል ። የኢትዮጵያ መንግሥትን ደግፎ በትግራይ ክልል ጦር ያዘመተው የኤርትራ መንግሥት ያኔ ከደገፈው ጋር አሁን ዐይን እና ናጫ ከመሆንም አልፈው ተፋጥጠዋል ።
Benzer podcast'ler
Replaio bir podcast yayıncısı değildir; program adları, kapak görselleri ve ses içerikleri yazarlarına aittir ve herkese açık RSS beslemeleri aracılığıyla dağıtılır