DW

እንወያይ | Deutsche Welle

News AM ↓ 70 bölüm

ኢትዮጵያን በሚመለከቱ ጉዳዮች ላይ ከተለያዩ እንግዶች እና በተለያዩት የዓለም ሀገሮች ከሚገኙት ወኪሎቻችን ጋ የምናካሂደውን እና በየሣምንቱ እሁድ ከምሽቱ አንድ ሰዓት ከአሥር ደቂቃ ላይ የሚተላለፈውን የውይይት ዝግጅት ያዳምጡ።

Podcast'in sitesini ziyaret etmeyi ve yapımcısını desteklemeyi unutma: www.dw.com?maca=amh-podcast_amh_diskussionsforum-8741-xml-mrss

Yazar

DW

Kategori

News

Son bölüm

27 Eyl 2026

Nereden dinlenir?

Uygulamada podcast'ler Replaio Radio Çok yakında

Podcast'ler çok yakında uygulamaya geliyor. Şimdi yükle ve podcast'lere yepyeni bir bakışı ilk gören sen ol

Google Play'den indir Ücretsiz yükle Android 5 Mn+ indirme · 4,8 puan iOS yakında

Bölümler

ዉይይት፣ የኢትዮጵያ የአዲስ መንግሥት ምሥረታ ዝግጅትና የጦርነት እልቂት 27.09.2026

በኢትዮጵያ ፌደራላዊ መንግሥትና በህዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) መካከል የሚደረግ ያሉት ጦርነትን ሥለጀመረዉ ወገን ማንነት ተፋላሚ ኃይላት አንደሚጠበቀዉ አንዳቸዉ ሌላቸዉን እየወነጀሉ ነዉ።ዉጊያዉ ግን ቀጥሏል

ፅምዶ/ጥምረት ወዴት? 20.09.2026

ፅምዶ/ጥምረት ወዴት?

ፅምዶ/ጥምረት ወዴት? 20.09.2026

«ብልጽግና የህልውናችን አደጋ ስለሆነ መደምሰስ አለበት ብለው የሚያምኑ አንድ ላይ ተጣምረው አቅማቸውን አቀናጅተው በቦታና በጊዜ ጦርነት ሲገጥሙ የሚፈጠር አቅምና በብልጽግና ሥርአት ላይ የሚደርስ ምት የጠላትን ዕድሜ ለማሳጠር ይጠቅማል።»

ለ12ኛ ክፍል ተማሪዎች ውጤት መቅረት ማን ይጠየቅ? 13.09.2026
በኢትዮጵያ ሰላም ለምን እውን መሆን አልቻለም? 06.09.2026

የሰላም ጥሪው ምላሽ ሳያገኝ ይህ ሁሉ የስጋት ድምጽ እየተሰማባለበት ኢትዮጵያ ሌላ አዲስ ዓመት ልትቀበል ቀናት ቀርተዋል። ዛሬም ጥፋተኖች ለፍርድ ተጎጂዎችም ፍትህ ያግኙ የሚለው ጥሪ አላባራም። ለመሆኑ ኢትዮጵያ ውስጥ ሰላምን ማስፈን ለምን አቃተ? የሕዝቡ ሰቆቃስ ማብቂያው መቼ ነው? ዶቼ ቬለ በአዲስ ዓመት ዋዜማ ላይ እንግዶች ጋብዞ አወያይቷል።

የኦባሳንጆ የሰላም ጥረት በፌደራል መንግሥትና በትግራይ ክልል መካከል ያለውን ውጥረት ያረግባል? 30.08.2026
የኦባሳንጆ አዲስ የሰላም ጥረት በፌደራል መንግሥትና በትግራይ ክልል መካከል የተፈጠረውን ውጥረት ምን ያህል ሊያርግብ ይችላል ? 30.08.2026

ውጥረቱ በተባባሰበት በዚህ ሳምንት ሰኞ በአፍሪቃ ቀንድ የአፍሪቃ ኅብረት ልዩ መልዕክተኛ የቀድሞ የናይጀሪያ ፕሬዝዳንት ኦሊሴጉን ኦባሳንጆ መቀሌ መሄዳቸው መሰማቱ የሰላሙ ጥረት እንደገና የመንቀሳቀሱ ተስፋ ተደርጎ ተወስዷል። ከኢትዮጵያ መንግሥት በኩል እስካሁን ስለኦባሳንጆ ጉብኝት የተባለ ነገር የለም።

እንወያይ፤ የተጠናቀቀው ሀገራዊ ምክክር ጉባኤ ምክረ ሀሳቦች ምን ያህል ተፈፃሚ ናቸው? 23.08.2026

የኢትዮጵያ ሀገራዊ የምክክር ኮሚሽን የአዲስ አበባን ጉዳይ ጨምሮ በለያቸው ስምንት ዋና ዋና አጀንዳዎች ላይ ከአንድ ወር በላይ ሲመክር ቆይቶ ትናንት ቅዳሜ ተጠናቋል።ኮሚሽኑ የሀገሪቱን ችግሮች በምክክር ለመፍታት የሚደርገውን ጥረት በበጎ የሚያዩ እንዳሉ ሁሉ፤ ሂደቱን የሚተቹ እና የታለመለትን ብሔራዊ መግባባትና ሰላም ማምጣቱን የሚጠራጠሩም አሉ።

እንወያይ፤ የሀገራዊ ምክክር ጉባኤ ምክረ ሀሳቦች ምን ያህል ተፈፃሚ ናቸው? 23.08.2026
ኢትዮጵያ አሰቃቂ ግፎች ከሚፈጸምበት የግጭት አዙሪት መውጣት ለምን ተሳናት? 16.08.2026

በተደራራቢ ግጭቶች ውስጥ ለተፈጸሙ ግፎች ተጠያቂነት ሳይረጋገጥ ኢትዮጵያ ሌላ የጦርነት ሥጋት ተጋርጦባታል። ለበርካታ አስርት ዓመታት ስለ ዴሞክራሲ ቢሰበክም የፖለቲካ ልሒቃኑ አገሪቱን ከግጭት አዙሪት ማላቀቅ አልቻሉም። ለምን? የለየለት ጦርነት እንዳይቀሰቀስ ማቆም የሚችል ወገን አለ? ወይስ ረፍዷል? በአሜሪካው ኢንዲያና ዩኒቨርሲቲ ማወር የሕግ ትምህርት ቤት ተመራማሪ የሆኑት አለማየሁ ፈንታው፤ የአምነስቲ ኢንተርናሽናል የአፍሪካ ቀንድ ጉዳዮች ተመራማሪ ሐይማኖት አሸናፊ እና በግጭትና መፈናቀል ጉዳዮች ላይ ምርምር የሚያደርጉት ዶክተር ሳሙኤል ዘውዴ በውይይቱ ተሳትፈዋል።

የሰሜን ኢትዮጵያ ውጥረትና የተፈናቃዮች ብርቱ ሥጋት 09.08.2026

ባለፈው ሳምንት ቅዳሜ ካጋጠመው የሸረሪናው ውጊያ በተጨማሪ በአላማጣ የተፈጠረው ውጥረት የተፈናቃይ ጎርፍ አስከትሏል ። ከወራት በፊት ጀምሮም ለጦርነት የሚደረገውን ዝግጅት እና አስገዳጅ ወታደራዊ ምልመላ በመሸሽ ወደ ቆቦ ከተማ የሚገቡ ተፈናቃዮች ቁጥር ጨምሯል ። ሙሉውን ውይይት በድምፅና በጽሑፍ በማገናኛው ይከታተሉ ።

እንወያይ፤ ስደት፣ መንከራተት፣ ሞት ማቆሚያው የት? 02.08.2026

ዓለም አቀፍ የጠፉ ስደተኞችን አፈላላጊ ድርጅት እንዳስታወቀው ደግሞ ጎርጎሮሳውያኑ አቆጣጠር ከ2024 እስከ 2026 ባሉት ዓመታት በሜዲትራንያን ባሕርና በአትላንቲክ ውቅያኖስ የስደት መስመሮች ቢያንስ 15,000 ስደተኞች ሕይወታቸውን ማጣታቸውን ይፋ አድርጓል።

ስደት፣ መንከራተት፣ ሞት ማቆሚያው የት? 02.08.2026
የሐምሌ 19 ቀን 2018 ዓ/ም ሙሉ ስርጭት 26.07.2026
እንወያይ: ኢትዮጵያ ለዓመታት የጠበቀችው ሀገራዊ ምክክር ወዴት? 26.07.2026

የኢትዮጵያ ፖለቲካ ተዋናዮች እና ምሁራን ለበርዓታ ዓመታት እንዲደረግ ሲያሳስቡ የከረመው ሀገራዊ ብሔራዊ ምክክር ዘንድሮ እውን ሆኗል። ውይይት ምክክሩ ሁሉን አላካተተም በሚል ጥያቄዎች ይነሳሉ።

ዉይይት፣ የአዲስ አበባ፣ የመቀሌና የአስመራ መሪዎች ዉዝግብ ንሯል፤ቀጥሎስ? ጦርነት ወይስ ሰላም? 19.07.2026

የትግራይ ክልል በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤትም፣ በምርጫም፣ በምክክር ጉባኤ፣ በአገራዊ የፖሊሲ ዉሳኔዎችም አለመካፈሉ ክልሉን በሚመራዉ በሕዝባዊ ወያኔ ሐርነት ትግራይ (ህወሓት) ና በኢትዮጵያ ፌደራዊ መንግሥት መካከል የተፈጠረዉ ጠብ እየተካረረ መምጣቱን መስካሪ መስሏል

ዉይይት፣ የአዲስ አበባ፣ የመቀሌና የአስመራ መሪዎች ዉዝግብ ንሯል፤ቀጥሎስ? ጦርነት ወይስ ሰላም? 19.07.2026

የቃላቱ ጦርነት ደግሞ ከመቀሌና አዲስ አበባ አልፎ አስመራና ካርቱም እየደረሰ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚንስትር ዓብይ አሕመድ ባለፈዉ ሰኔ 30 ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ባደረጉት ንግግር ህወሓት፣ ከኤርትራ (ሻዕቢያ)፣ ከሱዳን (SAF)ና በስም ካልጠቀሷቸዉ ሌሎች ወገኖች ጋር ሆነዉ የኢትዮጵያን ሠላም ለማወክ እያሴሩ መሆናቸዉን አስታዉቀዋል

ምክክሩ በመጨረሻው ምዕራፍ ተስፋ እና ስጋት 12.07.2026
ሃገራዊ ምክክር የመጨረሻው ምዕራፍ ከተስፋ ባሻገር 12.07.2026

ኢትዮጵያ ሃገራዊ ምክክር ለማድረግ ጥቂት ቀናት ቀርተዋታል። ከተለያዩ የሀገሪቱ ክፍል በምክክሩ ላይ ይሳተፋሉ የተባሉ ከአራት ሺ በላይ ተወያዮች አዲስ አበባ ከተማ መግባታቸው ተገልጿል። የኢትዮጵያ ሃገራዊ የምክክር ኮሚሽን ከትግራይ ክልል ውጪ የምክክር አጀንዳ የማሰባሰብ ስራው ከሶስት ዓመታት በላይ እንደወሰደበት ታይቷል።

እንወያይ፤ የትግራይ ክልል ቀዉስ ወዴት እያመራ ነዉ? መፍትሔዉስ? 05.07.2026
እንወያይ፤ የትግራይ ክልል ቀዉስ ወዴት እያመራ ነዉ? መፍትሔዉስ? 05.07.2026

በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ መንግሥትና በህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ መካከል የሚደረገዉ ዉዝግብና ቁርቁስ አሁንም እንደቀጠለ ነዉ። ህወሓት በፕሪቶርያ ስምምነት መሰረት የተሰየመዉን የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ከተቆጣጠረ ወዲህ ከመንግሥት ጋር የነበረዉ ቂም እየተካረረ መምጣቱ እየተነገረ ነዉ። ህወሓትም ወጣቶችን ለዉትድርና እያስገደደ ነዉ ተብሏል።

የሰባተኛው የኢትዮጵያ ጠቅላላ ምርጫ ውጤትና ፋይዳው እንዲሁም ተግዳሮቶቹና ተስፋው 28.06.2026

ምርጫው ከመካሄዱ አስቀድሞም በስፋት እንደተጠበቀው ገዥው ፓርቲ ብልጽግና ሲያሸንፍ ከቀደሙት ምርጫዎች በተለየ በአሁኑ ምርጫ ተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች ተጨማሪ የምክር ቤት መቀመጫዎችን ማግኘታቸው ትኩረት ስቧል።

በአርሲ ዞን ጥቃት ግድያው ለምን ተደጋገመ? 22.06.2026
በአርሲ ዞን ጥቃት ግድያው ለምን ተደጋገመ፥ እንዴትስ ይቆማል? 21.06.2026

ኢትዮጵያ ውስጥ ከቅርብ ዓመታት ወዲህ ሰላማዊ ሰዎች ላይ ተደጋጋሚ ጥቃቶች ይሰነዘራሉ ። በተለይ በኦሮሚያ ክልል አርሲ ዞን የኦርቶዶክስ ክርስትና እምነት ተከታዮች በተለያዩ ጊዜያት በተደጋጋሚ የመገደል የመፈናቀላቸው፣ የቤት ንብረታቸው መዘረፍና መውደም ሰበቡ ምን ይኾን፥ እንዴትስ ይቁም? ሙሉ ውይይቱን በማገኛው በኩል ማድመጥ ይቻላል ።

ውይይት፤በምርጫው ከሚያሸንፈው መንግስት በመጭው አምስት የስልጣን ዓመታት ምን ይጠበቃል? 14.06.2026

በኢትዮጵያ ከ54 ሚሊዮን በላይ መራጮች የተመዘገቡበት ጠቅላላ ምርጫ ተካሂዷል።ያም ሆኖ 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ የተካሄደው የኑሮ ውድነት፣ ስራ አጥነት እና የኢኮኖሚ ችግር ባየለበት እና በተለያዩ አካባቢዎች ግጭት፣መፈናቀል እና ሞት በሚሰማበት ነው። ለመሆኑ ከመንግስት በመጭዎቹ 5 ዓመታት ምን ይጠበቃል?ቅድሚያ የሚሰጠው አንገብጋቢ ጉዳይስ የቱነው?

እንወያይ | Deutsche Welle podcast'ini Replaio'da dinle

Radyo ve podcast'ler tek uygulamada - ücretsiz, kayıt gerektirmez. Bugün yükle ve lansmanı kaçırma

Google Play'den indir

Replaio bir podcast yayıncısı değildir; program adları, kapak görselleri ve ses içerikleri yazarlarına aittir ve herkese açık RSS beslemeleri aracılığıyla dağıtılır