DW | Amharic - News
News, Analysis and Service from Germany and Europe - in 30 Languages
Vizitează neapărat site-ul podcastului și susține-i creatorul: www.dw.com
Unde asculți?
Podcasturi în aplicație Replaio Radio În curândPodcasturile ajung în curând în aplicație. Instaleaz-o acum și fii primul care descoperă o abordare complet nouă a podcasturilor
Episoade
አርሲ ሽርካ ወረዳ ለደረሰዉ ጥቃት ኦነሠ ኃላፊነት ወሰደ 17.11.2026
የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት (ኦነሠ) በኦሮሚያ ክልል ሽርካ ዞን 48 ሰዎች በተገደሉበት የጥቅምት 14 ቀን 2019 ዓ.ም. ጥቃት ወቅት “እርምጃ” መውሰዱን በማረጋገጥ መግለጫ አውጥቷል። ይሁንና ታጣቂው ቡድኑ በተፈጸመው ጥቃት የተገደሉት ሲቪሎች ሳይሆኑ የትርፍ ጊዜ ተዋጊዎች” ናቸው ሲል ገልጿል።
ደብረ,ወርቅ ከተማ በተደረገ ዉጊያ 10 ሰዉ ተገደለ፣ ከተማይቱ ዛሬ ተረጋግታለች 17.11.2026
በመንግስትና በፋኖ ሀይሎች መካከል በአካባቢው ይህን መሰል ግጭት ከተካሄደ ከ11 ወራት በላይ ተቆጥሯል ያሉት አስተያየት ሰጭም ትናንት ግን በዞኑ የተለያዩ አካባቢዎች ተመሳሳይ ጦርነት እንደነበር ይናገራሉ፡፡
የተባበሩት መንግሥታት የልዑካን ቡድን ዛሬ በመቀሌ ይገኛል 17.11.2026
የአስተዳደሩ ዋና አስፈፃሚ አቶ አሰፋ አብርሃ ገለፃ የሰጡ ሲሆን ከ80 እስከ 90 በመቶ የሚሆነው የመቀለ ከተማ ሕዝብ አስቸኳይ ድጋፍ ፈላጊ መሆኑን በዚሁ ወቅት ስለመናገራቸው ተጠቅሷል።የልዑክ ቡድኑ ወደ ስፍራው መሄድ በበጎ የሚታይ መሆኑን የትንሳኤ ሰባ እንደርታ የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ አብርሃም ፅጌ ገልፀዋል።
ኢትዮጵያና ኤርትራ ድንበር ዉጊያ ነበር፤ ዉጥረትም አይሏል 17.11.2026
በትግራይ ክልል በባድሜ እና ሺራሮ አከባቢ የሚኖሩ አስተያየት ሰጪዎች ዛሬ ለዶይቼ ቬለ እንደነገሩት ባለፈው ሳምንት ማክሰኞ እና እሮብ እለት ለሁለት ተከታታይ ቀናት በከባባድ መሳሪያ የታገዘ ግጭትና የተኩስ ልውውጥ በሁለቱ አገራት (ኢትዮጵያ እና ኤርትራ) ድንበር አከባቢ መሰማቱን አመልክተዋል፡፡
ኢትዮጵያ እና የቡና የወጭ ንግድ የመሳካት ዕድል 16.11.2026
ኢትዮጵያ በተያዘው የ2019 በጀት 550 ሺህ ቶን ቡና ወደ ውጪ ገቢያው በመላክ አራት ቢሊየን የአሜሪካ ዶላር የወጪ ንግድ ገቢ ለማግኘት እንደምትሰራ በግብርና ሚኒስቴር እና በኢትዮጵያ ቡና እና ሻይ ባለስልጣን መስሪያ ቤት በኩል ውጥኗን አስቀድማ አሳውቃለች፡፡ የአየር ጠባይ ለውጥ የተፈለገውና የታቀደውን መጠን ምርት ለማግኘት አጠራጣሪ ሆንዋል፡፡
ማሕደረ ዜና፣ የሁቲዎች ድል፣ ያልተጠበቀዉ መራር ዕዉነት 16.11.2026
የዓለምን ሠላም ያስከብራል የተባለዉ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅትም ከተፋላሚዎች አንዱን ምናልባትም የዓለም ገዢዎችን አገዛዝ የሚቃረነዉን ግን በኢራን የሚደገፈዉን አንሳር አላሕን ከመወንጀል-መቅጣት ባለፍ ጦርነት-ግጭቱን ለማስቆም እስካሁን የተከረዉ የለም
በአፍሪቃ ቀንድ የተመድ ልዩ ልዑክ ጉዋንግ ኮንግ ከአቶ ዘመነ ካሴ ጋር ተነጋገሩ 16.11.2026
የተባበሩት መንግስታት የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ ጉዋንግ ኮንግ ሰሞኑን ከአቶ ጌታቸው ረዳ ጋር ከተወያዩ ከጥቂት ቀናት በኋላ ትብብር ለሕልውና ከተባለው ጥምረት ሰብሳቢ ዘመነ ካሴ ጋር መገናኘታቸው ተዘግቧል። ዶቼ ቬለ በራሱ ባደረገው ማጣራት ግን እስካሁን የዚህን ዜና ተጨባጭነት ማረጋገጥ አልቻለም።
የሕዳር 07 ቀን 2019 የስፖርት መሰናዶ 16.11.2026
በአቡጃና በሆንግ ኮንግ በተደረጉ የማራቶን የሩጫ ውድድሮች፣ በዳካር የወጣቶች ኦሎምፒክ ኢትዮጵያውያን ድል ቀንቷቸዋል። ኢትዮጵያ በዓለም መድረክ ገናና በሆነችበት የአትሌቲክስ ውድድር የአበረታች ቅመሞች ጉዳይ አሳሳቢ ሆኗል። የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ችግሩን ለመቅረፍ ምን እየተሰራ እንደሆነ ፕሬዝደንቱ ስለሺ ስሕን ተጠይቀው መልስ ሰጥተዋል።
ለአላማጣ ከተማ ነዋሪዎች የሰብአዊ ድጋፍ በአስቸኳይ እንዲቀርብ ጥሪ ቀረበ 16.11.2026
ከተደጋጋሚ ግጭቶችና ጦርነቶች ገና ያላገገመዉ የራያ አላማጣ ከተማና አካባቢው፣ የክረምት ዝናብ ወቅቱን ጠብቆ አለመገኘትና የጦርነት አውዳሚነት ተደምረው ማህበረሰቡን ለከፋ የድርቅና የረሃብ አደጋ መዳረጋቸውን ነዋሪዎችና የስራ ሃላፊዎች ገለጹ። ይመረት የነበረ ማሽላና ጤፍ በዝናብ እጥረት ምክንያት አለመመረቱ ተነግሯል።
አቶ አደም ፋራህ የአየር ኃይል አዛዡን ተክተው የኢትዮጵያ አየር መንገድ የቦርድ ሰብሳቢ ሆኑ 16.11.2026
አቶ አደም ፋራህ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ የሥራ አመራር ቦርድ ሰብሳቢ ሆነው ተሾሙ። ሹመቱ የግዙፉ የመንግሥት የልማት ድርጅት ከፍተኛ አመራርን ከከፍተኛ የጦር መኮንን ወደ ከፍተኛ የፓርቲ ኃላፊ መሪነት ያዞረ ነው።
በኢትዮጵያ መገናኛ ዘዴዎች ላይ የበረታው ጫና፥ ምሕዳሩ ወዴት እያመራ ነው? 15.11.2026
ኢትዮጵያ ውስጥ በመገናኛ አውታሮች ላይ የሚደርሰው ጫና ከጊዜ ወደ ጊዜ እጅግ እየበረታ ነው ። ከሰሞኑ እንኳን ሦስት ዐሥርተ ዓመታት ግድም ያስቆጠረው ሪፖርተር ጋዜጣ «ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ጥቅም ጋር የሚጻረሩ ይዘቶችን አሠራጭቷል» በሚል በኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን ላልተወሰነ ጊዜ ሙሉ ለሙሉ መታገዱ ተሰምቷል ። ወዴት እያመራ ነው?
ከሀሰት ዜናዎች ጋር የአፍሪካ ትግል 14.11.2026
አፍሪቃ ከሀሰት ዜናዎች ጋር ትግል ጀምራለች። ለመሆኑ እውነትን የሚወስነው ማን ነው? ከጋና እስከ ሞዛምቢክ አፍሪካውያን ከሀሰት ዜናዎች ጋር የሚያደርጉት ትግል ተስፋፍቷል።
በጀት ያጠረው የሱዳን ሰብአዊ ቀውስ 14.11.2026
የዓለም አቀፉ የስደተኞች ድርጅት (IOM) እና የተባበሩት መንግሥታት የስደተኞች ከፍተኛ ኮሚሽነር (UNHCR) የድረሱልን ጥሪ እያሰሙ ነው። ምክንያቱም ለሱዳን የተመደቡት የአስቸኳይ ጊዜ መጠለያዎች እና መሰረታዊ የምግብ አቅርቦት በገንዘብ እጥረት በጣም ቀንሷል።
ዶክተር ነገደ ጎብዜ በ83 አመታቸው ህዳር 3 ቀን 2019 ሀሙስ ሌሊት ለአርብ አጥቢያ ብራሰልስ ውስጥ ህይወታቸው ማለፉ ተሰምቷል 14.11.2026
በኢትዮጵያ የፖለቲካ ታሪክ ውስጥ ከቀደምቶች አንዱ የነበሩት ፖለቲከኛ ዶክተር ነገደ ጎበዜ አረፉ
ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ ለጦርነቱ ህወሓት እና የኤርትራ መንግስታትን ተጠያቂ ማድረጋቸው 14.11.2026
የኢትዮጵያ የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ በሰሜን ኢትዮጵያ በተለያዩ ምዕራፎች ለተከፈቱና አሁንም እየተካሄደ ላለው አውዳሚ ጦርነት ሕዝባዊ ወያኔ ሓርነት ግትራይ (ህወሓትን) ነቀፉ፡፡
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ያቀረበችው ጥሪ 14.11.2026
የቤተክርስቲኗ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ከሰሞኑ አዲስ አበባ ውስጥ ከአሜሪካ አምባሳደር ኤርቪን ማሲንጋ ጋር ባደረጉት ውይይት “የአርሲ ችግር ዘላቂ መፍትሔ ባለማግኘቱ ዛሬም ሥጋቶች እንዳሉ ይሰማኛል” ሲሉ ተናግረዋል፡
የማይክሮሶፍት አገልግሎት መታወክ እያነጋገረ ነዉ 13.11.2026
የዩናይትድ ስቴትስሱ ግዙፍ የኮምፒዉተር ኩባንያ ማይክሮሶፍት የሚሰጣቸዉ የኢንተርኔት አገልግሎቶች ከሐሙስ ኅዳር 3 ቀን፤ ጀምሮ መታጎሎ የዓለምን የዓምደ መረብ እስትንፋስ ቀጥ አድርጎት ነዉ ያረፈደዉ። የዓምደ መረብ ሥራና እንቅስቃሴዉ በመዘበራረዙ፤ የመላዉ ዓለምን የዓምደ መረብ ሥራና እንቅስቃሴም ተዘበራርቋል።
በሞያለው ግጭት የተባባሰው ሰብዓዊ ቀውስ 13.11.2026
በደቡባዊ የኢትዮጵያ ድንበር ከተማ ሞያሌ የቀጠለውን ግጭት ሸሽተው ወደ ኬንያ የሚገቡ ፍልሰተኞች ቁትር እየጨመረ ነዉ። በአሁኑ ወቅት ለተፈናቃዮች በቂ ምግብ እና መጠለያ ለማቅረብ ፈታኝ እየሆነ መምጣቱን የኬንያ መርሳ ቤት ግዛትና ዓለም አቀፉ የፍልሰተኞች ድርጅት (IOM) አመልክተዋል። የአካባቢዉ ቀዉስ ”እጅግ አሳሳቢ” ተብሏል።
በራያ አላማጣ ከተማ ከ2013 ዓ.ም. በኋላ የተቀጠሩ ሰራተኞች ወደሥራ እንዳይመለሱ መከልከላቸውን ተሰማ 13.11.2026
በራያ ኡላማጣ ከተማ ከ2013 ዓ.ም በኋላ የተቀጠሩ ሰራተኞች ደሞዛቸው በአማራ ክልል እየተከፈለ ቢሆንም፣ አዲሱ የትግራይ ባላደራ አስተዳደር በቀድሞ የስራ ቦታቸው እንዳይሠሩ እንደከለከላቸው ተናገሩ። የራያ ላማጣና አካባቢው አሁን በትግራይ ክልል የባላደራ አስተዳደር ስር ቢሆንም ከ2013 ዓ.ም በኋላ ለተቀጠሩ የአማራ ክልል ደሞዝ እየከፈለ ነዉ።
ኢትዮጵያ እና ሱዳን ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት መሻከር 13.11.2026
የዲፕሎማሲያዊ ግንኙነታቸው እየሻከረ የመጣው ኢትዮጵያ እና ሱዳን አንዳቸው ሌላውን በውስጥ ጉዳያቸው ጣልቃ ገብነት ሲካሰሱ ቆይተዋል፡፡ ኢትየጵያ ሱዳን ከኢትየጵያ ታቂጣቂዎችን ከብሔራዊ ጦሩ ጋር በመወገን እንዲዋጉ ከማድረግ በተጨማሪ በምዕራብ በኩል ኢትዮጵያን እንዲወጉ የጦር መሳሪያና የፋይናንስ ድጋፍ እንደሚታደረግ ከዚህ ቀደም አሳውቃለች፡፡
አሳሳቢዉ የመቀሌ ከተማ ጸጥታ ስጋት 13.11.2026
በትግራይ ክልል በተለይም በክልሉ መዲና መቀሌ ይስተዋላሉ የሚባሉትን የጸጥታ ችግሮች ከመሰረቱ ለመቅረፍ የክልሉ ጊዜያዊ መስተዳድር የጦር መሳሪያ አሰሳን ጨምሮ የተለያዩ ስራዎችን እየሰራ መሆኑን ይገልጻል፡፡ ሆኖም የከተማው ነዋሪዎች የጸጥታ ተግዳሮቱ አሁንም በሚፈልጉት መጠን ተሻሽሎ አለማግኘታቸውን ያመለክታሉ፡፡
ዶይቼ ቬለ በኪረሙ ወረዳም ሆነ በአቤዶንጎሮ ወረዳ ሰላማዊ ዜጎቹ ላይ ደርሷል ስለተባለው የሲቪሎች ጥቃትና ጉዳት ከመንግስት አካላትም ሆነ ከሌላ ገለልተኛ አካላት ለማጣራት ያደረገው ጥረት አልሰመረም፡፡ 12.11.2026
በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ኦሮሚያ ዞን ኪረሙ ወረዳ ጉዲና ጅሬኛ ቀበሌ ባሳለፍነው ረቡዕ ጥቅምት 25 ቀን 2019 ዓ.ም. ታጣቂዎች በንጹሃን ማህበረሰብ ላይ ባደረሱት ጥቃት የበርካታ ሰዎች ሕይወት በማለፉ ከፍተኛ የንብረት ውድመትም በመድረሱ አከባቢው አሁንም የተረጋጋ አይመስልም፡፡
በጀጎል ቅርሶች ላይ ስጋት የደቀነዉ የኮሪደር ልማት 12.11.2026
በሐረር ከተማ በዓለም ቅርስ መዝገብ ላይ የሰፈረዉ፤ ጀጎል እየተከናወነ ባለዉ የኮሪደር ልማት ሰበብ በግንቡ ዉስጥ የሚገኙት ታሪካዊ ቤቶች መፍረሳቸዉ እየተነገረ ነዉ። የአካባቢዉ ነዋሪዎች እንደተናገሩት ከትዉልድ ትዉልድ፤ በቅብብሎሽ በታሪካዊ ቤቶች ዉስጥ ሲኖሩ የነበሩ ዜጎችም ተፈናቅለዋል። አሁን ቦታዉ ባለሃብት እንዲገዛዉ ጥሪ እየቀረበ ነዉ።
በጃናሞራና ጠለምት ደጃች ሜዳ ወረዳዎች ከተከሰተው ድርቅ ጋር ተያይዞ ምላሽ እንዲሰጡን ለሰሜን ጎንደር ዞን አደጋ ስጋትና ስራ አመራር ኮሚሽን ተጠሪ ጽህፈት ቤት ሃላፊ ስልክ ብንደውልም መልእክት ብንልክም ምላሽ ማግኘት አልቻልንም። 12.11.2026
በጠለምት ደጃች ሜዳ ወረዳ መረው ገብርኤል ቀበሌ ነዋሪ የሆኑት አቶ ጌጡ ጥሩሰውም ድርቁ የከፋ መሆኑን ገልጸው የሚሞት ሰውም እንዳለ ይናገራሉ። የረን ቀበሌ አስተዳዳሪ አቶ እሸቴ በረከተ አብም በቀበሌው ምንም እንኳ የሞተ ሰው ባይኖርም በረሃብ ምክንያት ግን የታመሙ ሰዎች አሉ ብለዋል።
ሁለቱ ሀገራት የኢትዮጵያ አማጺ ቡድኖችን ከመደገፍ ባለፈ በማን እንደሆነ በግልጽ ባይጠቅሱትም በኢትዮጵያ ግዛት ውስጥ "በተደጋጋሚ የድሮን ጥቃቶች መፈጸማቸውን" ለልዩ መልዕክተኛው ማብራሪያ መስጠታቸውንም አቶ ጌታቸው ተናግረዋል። 12.11.2026
ፕሬዝዳንት ኢሳያስ እና ጄኔራል አልቡርሃን "በኢትዮጵያ የሚንቀሳቀሱ አፍራሽ ኃይሎችን ለማስታጠቅ ለማደራጀትና ድጋፍ ለመስጠት እየሰሩ ነው ያሉትን እንዲሁም በኢትዮጵያ ግዛት ውስጥ በተደጋጋሚ የድሮን ጥቃቶችን መፈጸማቸውን አስመልክቶ" ዝርዝር ማብራሪያ መስጠታቸውን የገለፁት አቶ ጌታቸው፣ የድሮን ጥቃቶቹ መቼ፣ የትና በማን እንደተፈጸሙ አልገለጹም።
Replaio nu este editorul podcasturilor; numele emisiunilor, coperțile și materialul audio aparțin autorilor lor și sunt distribuite prin fluxuri RSS publice