Zelalem Demissie

Drum of Changes

Society EN ↓ 66 episodes

From the heart of ancient kingdoms to the pulse of modern cities, a new rhythm echoes across the continent. Africa is rising — a formidable force shaping the world’s future. For generations, Africa has been the most spoken about, yet the least heard. But today, the call is unmistakable: Africa demands its rightful place at the table of global power. Welcome to 'Drum of Changes' — a program dedicated to the stories that matter to Africa. Here, we explore culture, history, art, politics, the economy, and more, all through the lens of Africa itself. 'Drum of Changes' brings you the voices of tran...

Be sure to visit the podcast's website and support the creator: drum-of-changes.mave.digital

Author

Zelalem Demissie

Category

Society

Latest episode

Oct 3, 2026

Where to listen?

Podcasts in the app Replaio Radio Coming soon

Podcasts are coming to the app soon. Install now and be the first to see a whole new take on podcasts

Get it on Google Play Install for free Android almost 10M downloads · 4.8 rating iOS soon

Episodes

በአውሮፓ እስረኛ የሆኑ ቅርሶች፡- ኢትዮጵያ ቅርሶቿን የማስመለስ ትግል 29.01.2026

የቅርብ ጊዜ ጥናቶች እንደሚያሳዩት ከ90-95 በመቶ የሚሆነው የአፍሪካ የባህል ቅርሶች ከአህጉሪቱ ውጭ ይገኛሉ። ዋና ዋናዎቹ የአውሮፓ ሙዚየሞች ብቻ ከ500,000 በላይ የአፍሪካ ቅርሶችን ይዘዋል።ከእነዚህም አብዝኃኛዎቹ በቅኝ ግዛት ዝርፊያ፣በአስገዳጅ ሁኔታዎች ወይም በሕገ-ወጥ ዝውውር የተገኙ ናቸው። "ከአገራችን ተዘርፈው ተወሰዱ ቅርሶቻችን በክፍያ መልሰን እንድንወስድ መጠየቃችን አሳዛኝ ነገር ነው። እነዚህን ቅርሶች የያዙ ሙዚየሞች ወይም የግል ቅርስ ሰባሳቢዎች ወደኢትዮጵያ እንዲመልሷቸው እናበረታታለን"ሲሉ የሺ ካሳ፣ የራስ ደስታ ዳምጠው የልጅ ልጅ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል። የኢትዮጵያ ቅርስ አስመላሽ ኮሚቴ ዋና ጸሐፊ አ...

የብሪክስ አዲስ ልማት ባንክ ከአፍሪካ ንግድና ምጣኔ ሐብት አኳያ ሲቃኝ 28.01.2026

''ብሪክስ እንደ አላማ አድርጎ ከተነሳው መካከል የፋይናንስ፣ ኢኮኖሚ፣ ንግድ፣ የመሠረተ ልማት ዝርጋታ፣ ንፁህ የአየር ከባቢ መፍጠርና የዲጂታል ሥራዎች ማስፋፋት ይገኙበታል። እኛ አፍሪካዊያን ነገሮችን በብስለት መምራትና መጠቀም ከቻልን ከብሪክስ የልማት ባንክ ብዙ መጠቀም እንችላለን። የልማት ባንኩ ከቀደመው የምዕራባዊያን የኢኮኖሚ ጫናም እንድወጣም የሚያስችል ነው '' ሲሉ አሉላ ተክለብርሃን አዲሱ፣ የምጣኔ ሀብትና ተያያዥ ጉዳዮች ባለሙያ እንዲሁም በሩሲያ፣ ቅዱስ ፒተርስበርግ ፖሊቴክኒክ ዩኒቨርሲቲ በኢኮኖሚክስ የትምህርት ክፍል እጩ ዶ/ር ለስፑትኒክ አፍሪካ አስረድተዋል። ሁለት አንኳር ጉዳዮችን በምንቃኝበት ፕሮግራማችን በክፍል...

የጋራ ሀብቶች እና የጋራ ዕጣ ፈንታዎች፦ ሉዓላዊነትን እና ትብብርን እንደገና ማጤን በአፍሪካ 27.01.2026

"አፍሪካውያን ሉዓላዊነትን የምንገልፅበት እና የምንረዳበት መንገድ ምዕራባውያን በ'ዌስታፋሊያ' ሰምምነት መሰረት ከሚነግሩን የሉዓላዊነት እሳቤ የተለየ ነው።[...] አፍሪካውያን የወረስነውን የምዕራቡን ዓለም ሉዓላዊነት መንገድ በመተዉ [...] ወደውስጥ መመልከት፣ የጋራ ሀብቶቻችንን በጋራ ስለመጠቀም ማሰብ አለብን።" ሲሉ በጆሃንስበርግ ዩኒቨርሲቲ የአስተዳደር እና የአፍሪካ ጥናት ማዕከል ዳይሬክተር ሰይፈ ታደለ ኪዳኔ (ዶ/ር) ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል። ዛሬ በድረም ኦቭ ቼንጅስ ቀዳሚ ጥንቅራችን 'አፍሪካ ሀብቶቿን በጋራ ለመጠቀም ትችል ዘንድ ሉዓላዊነትን በተመለከተ ያለውን ምዕራብ ተኮር እሳቤ መተው ስትችል ነው' የሚል መከ...

ሩሲያን የመነጠል ሙከራዎች መክሸፋና ከአፍሪካ ጋር የተጠናከረው ሁለንተናዊ ግንኙነት 22.01.2026

"በዩክሬን ውስጥ ምን እየሆነ እንዳለ [አሜሪካኖቹ] ሙሉ በሙሉ እንደሚረዱ እርግጠኛ ነኝ። ምዕራባውያን በተለይም አውሮፓውያን የሞራል ኪሳራ እንዲሁም በወታደራዊ አቅርቦት እና ቴክኖሎጂ አቅማቸው ላይ በዩክሬን ከፍተኛ ኪሳራ እንዳጋጠማቸው ተረድተዋል። የትራምፕ አስተዳደርም በዩክሬን ውስጥ ማን የበላይ እንደሆነ በትክክል ያውቃል። ስለዚህ ስለ ሰላማዊ መፍትሄ በቁም ነገር ማሰባቸው ተገቢ ነው።" ሲሉ በዲላ ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካ ሳይንስ እና ዓለም አቀፍ ግንኙነቶች መምህሩ ዳዊት መዝገበ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል። በድረም ኦቭ ቼንጅስ ዝግጅታችን በቀዳሚነት በጥር 20፣ 2026 (እ.ኤ.አ) የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌይ ላቭሮ...

ኢትዮጵያዊው ዲፕሎማት ከተማ ይፍሩ፦ ለፓን አፍሪካኒዝም እና ለአፍሪካ አንድነት ድርጅት መመስረት ምን ዋሉ ? 16.01.2026

"አባቴ፣ ለኢትዮጵያ ከአፍሪካውያን እህት ወንድሞቻችን የተሻለ አጋር የለም ብሎ ያምን ነበር … አባቴ በአሜሪካን ሀገር በትምህርት ላይ ሳለ ጥቁር በመሆኑ ብቻ የደረሰበትንም አልረሳም … እነዚህ ሁኔታዎች የፓንአፍሪካኒዝም እንቅስቃሴ ላይ እንዲበረታ አድርገዉታል"- ሲሉ መኮንን ከተማ ይፍሩ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል። በዛሬዉ ድረም ኦቭ ቼንጅስ ዝግጅታችን በቀዳሚነት ታላቁን ኢትዮጵያዊ ዲፕሎማት ከተማ ይፍሩን እንዘክራለን። ለዚህም በቅርቡ "ከተማ ይፍሩ፡ የሰላም፣ የእድገት እና የአፍሪካ አንድነት ሻምፒዮን" በሚል ርዕስ አባታቸዉን የሚዘክር መጽሐፍ ያሳተሙት ልጃቸው አቶ መኮንን ከተማ ይፍሩ እንግዳችን ናቸው። ሁለተኛው ጥንቅራችን...

አፍሪካ የቆዳ ማንጫ ቅባቶን የመጠቀም ልማድ ማሻቀብ፣ መንስኤዎቹ እና ማህበራዊ መዘዞቹ 31.12.2025

“አፍሪካውያን የቆዳ ማንጫ ቅባቶችን እንዲጠቀሙ ከሚገፋፉ ምክያቶች መካከል የምዕራቡ ዓለም የውበት መስፈሪያ የራሱን አስተዋፅኦ አድርጓል[…]ምርቶች እንዲሸጡላቸውም በማህበራዊ ሚዲያ የውበት መስፈርትን የሚያወጡ ዓለም አቀፍ ተቋማትም አሉ” ሲሉ በአለርት ሆስፒታል የቆዳ እና አባላዘር ሕክምና ስፔሻሊስት እንዲሁም በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተባባሪ ፕሮፌሰር የሆኑት ዶክተር አኒሳ በፈቃዱ ለስፑትኒክ አፍሪካ  ተናግረዋል። በዛሬው የድረም ኦቭ ቼንጅስ ዝግጅታችን በመላው አፍሪካ፣ የቆዳ ማንጫ ቅባቶችን የሚጠቀሙ ዜጎች ቁጥር እየጨመረ መማጣቱን በማንሳት ጤና እና አጠቃላይ ማህበረሰቡ ላይ የሚያስከትለውን ቀውስ እንቃኛለን። በዚህ ወሳኝ ጉዳይ...

የእስራኤል እውቅና ለሶማሊላንድ ፦ የሶማሊያ ተቃዉሞ እና የቀጣናው እጣፈንታ 31.12.2025

ሶማሌላንድ ከእስራኤል ያገኘችው የሀገርነት እውቅና በተወሰነ ደረጃ ህጋዊነትን እንድታገኝ ቢያስችላትም፣ ከሶማሊያ፣ ከአፍሪካ ህብረት እና ከሌሎች ሀገራት እየተሰጠው ያሉ ምላሾች በመጭው ጊዜያት የግዛት አንድነት ጥያቄዎች ማዕከላዊ ሆነው እንደሚቆዩ ያሳያል። "እስራኤል ለሶማሊላንድ የሰጠችው እውቅና ከዓለም አቀፍ ሕግ ይልቅ፣ ፖለቲካዊ አንድምታው ጎልቶ ይታያል … በቀጣናው ሶማሊላንድ አዲስ ተዋናይ ሆና ብቅ ልትል ትችላለች፣ አዲስ ዓይነት የኃይል አሰላለፍም ሊፈጠር ይችላል" ሲሉ ጠበቃ፣ የዓለም አቀፍ ሕግ ባለሞያ አንዷለም በእውቀቱ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል። በዛሬው የድረም ኦቭ ቼንጅስ ዝግጅታችን ሦስት ጉዳዮችን እንመለከታለን።...

የአውሮፓ የከሸፈው ቁማር እና የሩሲያ ድል ፡- በፑቲን ወሳኙ ዓመታዊ ንግግር 24.12.2025

“ፕሬዝዳንት ፑቲን አሁን ኢኮኖሚውን በማረጋጋት እና ተጨባጭ እድገት ወደሚታይበት ደረጃ ማድረስ ችለዋል … ዛሬ በሩሲያ እያየን ያለነው የኢኮኖሚ ለውጥ ብቻ ሳይሆን፣ የፑቲንን አመራር ተጽእኖ ፈጣሪነት ነው” ሲሉ ዓለም አቀፍ የፖሊሲ አማካሪው ቆስጠንጢኖስ በርሁተስፋ (ዶ/ር) ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል። አዉሮፓዉያን ዛሬም በከሸፈ የቁማር መንገዳቸው ቢቀጥሉም የሩስያ ገናና ድል ግን ቀጥሏል።  ”አውሮፓውያን በውጭ አገራት የተቀመጡ የሩሲያን ንብረት እና ገንዘብ በመውሰድ ለዩክሬን ለመስጠት ማሰባቸው የደቡቡ ዓለም ከአውሮፓውያን ጋር የሚኖረውን አሰራር እንዲያጤን ቀጥተኛ መልዕክት የሚያስተላልፍ ነው” ያሉት ደግሞ በኢትዮጵያ ፐብሊክ...

የናሬንድራ ሞዲ የኢትዮጵያ ጉብኝት አንድምታ እና የሩሲያ በዘመናት የተፈተነ ከጭቁኖች ጋር የመቆም ታሪክ 16.12.2025

“የብሪክስ መድረክ ለአባል ሀገራት የበለጠ ስትራቴጂካዊ፣ ዘላቂ እና የጋራ ጥቅምን መሰረት ያድረጉ ግንኙነቶችን ለመመስረት እድል ይሰጣል። ከዚህ አናፃር የኢትዮጵያ እና የህንድ ግንኙነት ከዚህ ማዕቀፍ በእጅጉ ይጠቀማል” ሲሉ በኢትዮጵያ ፐብሊክ ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ የፖሊሲ ጥናት መምህሩ ሙከረም ሚፍታህ (ዶ/ር) ሲሉ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል። የዛሬው የድረም ኦቭ ቼንጅስ ዝግጅታችን የሕንዱን ጠቅላይ ሚኒስቴር ናሬንድራ ሞዲ የኢትዮጵያ ጉብኝት ከብሪክስ አገራት ትብብር አንፃር ቀዳሚ ጉዳዩ አድርጎ ይቃኛል። ለዚህም በኢትዮጵያ ፐብሊክ ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ የፖሊሲ ጥናት መምህሩ ሙከረም ሚፍታህን (ዶ/ር) አነጋግረናል። በሁለተኛው ጥንቅ...

የጥቁር ህዝቦች የካሳና ፍትህ ጉዳይ ፦ አውሮፓዉያኑ እንዲነሳ የማይፈልጉት ጥያቄ ለምን ሆነ ? 10.12.2025

"ብዙዎቻችን ከየት እንደመጣን ምንም ባናውቅም፣ ስደተኞች ግን አይደለንም። በእገታ የተወሰድን አፍሪቃውያን ነን። አያት ቅድመ አያቶቻችን ማንነታቸዉን ሳያውቁ ወደ መቃብር ወርደዋል። የ'ባሪያ' ልጆች መሆናችንን ብቻ ነው የተማርነው። ይህም ለሕዝባችን ብዙ ግራ መጋባት ፈጥሯል፣ የማንነት እጦትን ፈጠሯል"- ሲሉ ጸሐፊ እና የፓንአፍሪካኒዝም አቀንቃኟ ጅኔል ሆይሌት ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል። በዛሬው የድረም ኦቭ ቼንጅስ ጥንቅራችን፣ የአፍሪካን የቅኝ ግዛት በደልና ፍትህ እንዲሁም የካሳ ጥያቄን እናነሳለን ፡፡ ይሄው ጥያቄ በአውሮፓውያን ዘንድ ከመውያያ አጀንዳነት ለምን እንደሚገፋና ሌሎችንም ጉዳዮችን መነሻ አድርገን ጸሐፊ እና የፓ...

ድርብ መስፈርት ፡- የዓለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት እና የአፍሪካ የፍትህ ጥያቄ 03.12.2025

‘‘ዓለም አቀፉ የጦር ወንጀለኞች ፍርድ ቤት በሶሪያ ፣ ኢራቅና አፍጋኒስታን ውስጥ የተፈጸሙ ወንጀሎች፣ በብሪታኒያ በተፈጸሙ ወንጀሎች ዙሪያ ተጀምረው የነበሩ ምርመራዎች በአሜሪካ ጣልቃ ገብነት በድንገት እንዲቋረጡ ሆነዋል፡፡ ለምን ብለህ ብትጠይቃቸው ግን አሳማኝ ምክንያት አይሰጡህም፡፡ ተመሳሳይ ነገሮችን በተለያየ መንገድ የሚዳኝበት መንገድ በጣም የገዘፈ ነው፡፡’’ ሲሉ ኢትዮጵያዊው የህግ ባለሙያና ጠበቃ አንዷለም በእውቀቱ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል፡፡ የዛሬው ድረም ኦፍ ቼንጅስ ዝግጅታችን በሁለት ጉዳዮች ላይ እንወያያለን፡፡ በቀዳሚነት አፍሪካን ማጥቂያ የሆነው በዓለምአቀፉ ወንጀለኞች ፍርድቤት የሚደርስባት አድሏዊ አሰራርና በ...

ከትናንት እስከ ዛሬ ፡ የዓለምአቀፍ ተቋማት አድሏዊነትና የፍትሐዊነት ጥያቄ ከሊግ ኦፍ ኔሽን እስከ ጸጥታው ም/ቤት 03.12.2025

"አፍሪካ እንደገና የተዋቀረ፣ ገለልተኛ፣ ተጠያቂነት የሰፈነበት ዓለም አቀፍ ስረዐት ያስፈልጋታል። የተባበሩት መንግስታት አሁን ባለው አቋም የአፍሪካን ጥቅም የሚያስከብር አይደለም። በእኔ እይታ የተባበሩት መንግስታት፣ በዩናይትድ ስቴትስ የሚጋለብ፣ምዕራባውያን የሚነዱት ፈረስ ነው።" - ሲሉ በዲላ ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካል ሳይንስ እና አለም አቀፍ ግንኙነት መምህርና ተመራማሪ የሆኑት አቶ ዳዊት መዝገበ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል። በዛሬው የድረም ኦቭ ቼንጅስ ጥንቅራችን ፣ በቀዳሚነት አፍሪካ በተባበሩት መንግስታት እና ሌሎች አለም አቀፍ ተቋመት ውስጥ ፍትሃዊ እና እኩል ውክልና ለማግኘት የምታደርገውን ቀጣይነት ያለው ጥረት እንፈትሻ...

የአፍሪካን ስነጽሁፍ ከቅኝ ግዛት እሳቤ ነጻ ማውጣት፦ በ ንጉግ ዋ ቲዮንጎ እይታ 24.11.2025

"እኛ ደግሞ አፍሪካውያኖች የራሳችን ታሪክ የምንነግርበት፣ ከትውልድ ወደ ትውልድ የምናስተላልፍበት ጥበብ፣ የራሳችን መንገድ አለን። ስለዚህ ይሄ የአውሮፓ ተኮር የሆነውን አመለካከት ከአፍሪካ ስነ ጽሁፍ ውስጥ አውጥተን በአፍሪካ ተኮር ወይም ደግሞ አፍሮ ሴንትሪክ በሆነው ስንተካ አንደኛ ዲኮሎናይዝ እያደረግን ነው ማለት ነው።" ሲሉ በጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ የእንግሊዘኛ ቋንቋና ስነጽሁፍ መምህርና በዩኒቨርሲቲው የማህበራዊ ሳይንስ እና ስነሰብ ኮሌጅ ዲን አስቻለው ለገሰ (ዶ/ር) ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል። በዛሬው የድረም ኦቭ ቼንጅስ ዝግጅታችን ፣ በጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ የእንግሊዘኛ ስነጽሁፍ አስተማሪ እና በዩኒቨርሲቲው የማህበራዊ ሳይ...

ካሳ ወይስ የቀድሞውን መመለስ ፡ የአፍሪካ ጥሪ ለእውነተኛ ፍትህ 19.11.2025

 "ይህ የአፍሪካ ዕዳ ተብሎ የሚጠራው ነገር በቀላሉ መወገድ አለበት። ሌባ ከቤትህ ሰርቆ ሲያበቃ እንዴት እንካ ቤትህን ስራበት ብሎ ገንዘብ ሊያበድርህ ይችላል? እንዴትስ ከራስህ ሰርቆ ያበደረህ ገንዘብ ላይ ወለድ ሊጥል ይችላል? ይህ ግራአጋቢ ነገር ነው።" ሲሉ የኢትዮጵያ ዓለም አቀፍ ፌዴሬሽን በአዲስ አበባ ተወካይ ከሆኑት አምብሮስ ኪንግ (ራስ ወልደ ስላሴ) ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል፡፡ "ፍትህ ለአፍሪካውያን እና አፍሪካዊ ዝርያ ላላቸው ሁሉ በካሳ መልክ" የሚለው ሐሳብ የአፍሪካ ኅብረት እ.ኤ.አ 2025 መሰባሰብያ ጭብጥ ነው። የአፍሪካ ፍትህና ካሳ በምን መልኩ ሊለካ ይችላል ፣ መልሱ ከባድ አከራካሪም ነውና ለዚሁ ጉዳይ የ...

የአፍሪካ ቀጣናዊ ጥምረቶች ፣ የአህጉር አቀፍ ትስስር ካስማዎች ወይስ ወጥመዶች? 18.11.2025

"አፍሪካ የገንዘብ ሀብት እጥረት እንደሌለባት ልብ ማለት ያስፈልጋል - አፍሪካውያን የጎደለን የአስተሳሰብ ለውጥ ለማምጣት የሚሆን ፍላጎት ነው። በእውነት የሚያስፈልገን ተቋማዊ አቅምን ለማጎልበት የሚያስችል ቁርጠኝነት ነው። የዚህ ዓይነቱ ቁርጠኝነት ስለጎደለንም ልብ በሚሰብር መልኩ ከውጭ በሚገኝ የገንዘብ ድጋፍ ላይ ጥገኛ ሆነን ቀርተናል" ሲሉ በጆሃንስበርግ ዩኒቨርስቲ መምህርና የፓን አፍሪካ አስተሳሰብ እና ውይይት ተቋም ከፍተኛ የምርምር ባልደረባ እና የአስተዳደር እና የአፍሪካ ውስጥ የንግድ ጥናቶች ማዕከል ዳይሬክተር ሰይፈ ታደለ ኪዳኔ (ዶ/ር) ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል፡፡ ድራም ኦፍ ቼንጅስ በዛሬው ዝግጅቱ ሁለት የተለያ...

ከምዕራቡ ዓለም ባሻገር :- ኢትዮጵያ ለቱሪዝሟ እድገት ወደ ደቡባዊው ዓለም ታማትራለች 12.11.2025

"ኢትዮጵያ በአፍሪካ ውስጥ ያለውን ሁሉ አቅፋ ይዛለች ። ስለዚህ አንድ ሰው አፍሪካን በእውነት መጎብኘት ከፈለገ፣ ወደ ኢትዮጵያ መጥቶ ሁሉንም ማየት ይችላል።[…] ስለዚህ፣ በብሪክስ ውስጥ፣ ዓለም አቀፍ ተጽዕኖ ፈጣሪ የሆኑ አገሮችን፣ ጥሩ የህዝብ ብዛትን እና ጥሩ ኢኮኖሚን በተመሳሳይ ጊዜ እናገኛለን፤ ይህም እነርሱን የቱሪስት እንግዶቻችን ልናደርጋቸው ያስችለናል።[...] ስፑትኒክ አፍሪካ የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ እየተከናወኑ ያሉ ሥራዎችን ብዙዎች ጋር ለማድረስ ይረዳናል። ሚዲያው ቢሮውን በኢትዮጵያ መክፈቱም ከራዕያችን ጋር በእጅጉ የተጣጣመ ነው" - ሲሉ የቱሪዝም ሚኒስቴር ዴኤታ አቶ ስለሺ ግርማ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል...

Listen to the Drum of Changes podcast in Replaio

Radio and podcasts in one app - free, with no sign-up. Install today and do not miss the launch

Get it on Google Play

Replaio is not a podcast publisher; show names, artwork and audio belong to their authors and are distributed through public RSS feeds.