Zelalem Demissie

Drum of Changes

Society EN ↓ 36 episodes

From the heart of ancient kingdoms to the pulse of modern cities, a new rhythm echoes across the continent. Africa is rising — a formidable force shaping the world’s future. For generations, Africa has been the most spoken about, yet the least heard. But today, the call is unmistakable: Africa demands its rightful place at the table of global power. Welcome to 'Drum of Changes' — a program dedicated to the stories that matter to Africa. Here, we explore culture, history, art, politics, the economy, and more, all through the lens of Africa itself. 'Drum of Changes' brings you the voices of tran...

Author

Zelalem Demissie

Category

Society

Latest episode

Jul 8, 2026

Where to listen?

Podcasts in the app Replaio Radio Coming soon

Podcasts are coming to the app soon. Install now and be the first to see a whole new take on podcasts

Get it on Google Play Install for free Android 5M+ downloads · 4.8 rating iOS soon

Episodes

የላቭሮቭ ይፋዊ የስራ ጉብኝት፡ ኢትዮጵያ ፣ ብሪክስ እና ባለብዙ ዋልታው ዓለም 08.07.2026

"ሩሲያ ለኢትዮጵያም ሆነ ለአፍሪካ መልካም ወዳጅ ሆና ለዘመናት ቆይታለች። በተቃራኑው ደግሞ የምእራቡ አለም፣ አፍሪካን በማሳነስ በምእራቡ ላይ ጥገኛ ሆና እንድትቀር እየሰራ ይገኛል [...] ሩሲያ ግን የአፈሪካን ራስን የመቻል ፍላጎት በመሰረታዊነት የተረዳች ሀገር ነች" ሲሉ የሕግ ባለሞያ እና የዓለም ማቀፍ ፖለቲካ ተንታኝ ብሩክ መላኩ ለስፑትኒክ ካፍሪካ ተናግረዋል። በዛሬው የድረም ኦቭ ቼንጅስ ዝግጅታችን በቀዳሚነት የሩሲያው የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ሰርጌ ላቭሮቭን የኢትዮጵያ ጉብኝት አንስተን ሁለንተናዊ አንድምታዎቹን እንቃኛለን። ለዚህም የሕግ ባለሞያ እና የዓለም ማቀፍ ፖለቲካ ተንታኝ ብሩክ መላኩን አነጋግረናል። በሁለተኛው ጉዳ...

የተዘረፉ ቅርሶች፡ የአፍሪካን የታሪክ እውነት ለማስመለስ የሚደረገው ዓለም አቀፍ ትግል 15.06.2026

“[…] ከአፍሪካ በጉልበት የተወሰዱ የተለያዩ ቅርሶች ለአፍሪካውያን ባለቤቶቻቸው ሳይመለሱ በአውሮፓ ሙዚየሞች እንዲቆዩ የሚደረገው ደህንነታቸው በአስተማማኝ ሁኔታ እንዲጠበቅ ነው የሚለው መከራከሪያ እውነታነት የለውም። ምክንያቱም በሁለተኛው የዓለም ጦርነት ወቅት በአውሮፓ ውስጥ የሚገኙ ብዙ ሙዚየሞች በጦር መሳሪያውች ተደብድበዋልና። በቅርቡ በፈረንሳዩ ሉቭር ሙዚየም ጭምር በርካታ ስርቆቶች ተፈጽመዋል። ስለዚህ በምዕራቡ አገራት ያሉ ሙዚየሞች በሙሉ አስተማማኝ ናቸው ማለት አይቻልም” ሲሉ የማህበራዊ ጉዳዮች ተመራማሪው አሉላ ፓንከረስት (ዶ/ር) ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል። የዛሬው የድረም ኦቭ ቼንጅስ ዝግጅታችን በቀዳሚ ጉዳዩ፣ የ...

ሴንት ፒተርስበርግ ዓለምዓቀፍ የኢኮኖሚ ፎረም፣ ለአፍሪካ ምን አማራጮችን ይዞ መጥቷል? 04.06.2026

"አፍሪካ ከዚህ ጉባኤ [ከ ሴንት ፒተርስበርግ ኢንተርናሽናል ኢኮኖሚክ ፎረም] ትጠቀማለች [...] አሜሪካ በኢራን፣ በሩሲያ እና በሌሎች ሀገራት ላይ የጣለቻቸው ማዕቀቦ ምዕራባውያኑ በፋይናንስ አስተዳደር ረገድ እምነት የሚጣልባቸው አጋሮች ሊሆኑ እንደማይችሉ እያሳየ ጉዳይ ነው። በዚህም ምክንያት ሀገራት የዕዳ ቀውስን ለመፍታት ጨምሮ ለራሳቸው የሚበጀ የተሻለ ጎዳናነ መሻት ይኖርባቸዋል [...] ጉባኤው ከዚህ አንፃር ፋየዳው የጎላ ነው" ሲሉ የፖሊሲ አማካሪ እና የምጣኔ ሀብት ባለሙያው ቆስጠንጢኖስ በርኸተስፋ (ዶ/ር) ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል። የዛሬው የድረም ኦቭ ቼንጅስ ዝግጅታችን ቀዳሚው ጉዳይ እ.ኤ.አ. ከ ሰኔ 3 እስከ...

የአፍሪካ ቀን እና የአንድነቱ መሐንዲሶች፡ የታሪክ አሻራ እና የዲፕሎማሲ ጉዞ 25.05.2026

“የአፍሪካውያን ማንነታችንን የምናከብርበት ብቸኛው ቀን ይህ [የአፍሪካ ነፃነት ቀን] በአህጉር ደረጃ ሊከበር የሚገባው ይመስለኛል። ትርጉሙን አባቴ [ከተማ የፍሩ] ያደረገውን፣ ኳሜ ንክሩማህ እና አፄ ኃይለ ሥላሴ ያከናወኑትን ማስታወስ ይኖርብናል” ሲሉ መኮንን ከተማ ይፍሩ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል። በየዓመቱ ግንቦት 17 ወይም እ.ኤ.አ ግንቦት 25 የጋራ ጉዟችንን እና ቅርሳችንን ለማክበር በመላው አፍሪካ የሚታሰበው ታሪካዊው የአፍሪካ ቀን ሆኖ ይከበራል። በዛሬው የድረም ኦቭ ቼንጅስ ዝግጅታችን ታዲያ በጥልቅ ተከፋፍላ የነበረችውን አፍሪካ በአንድ ሰንደቅ ዓላማ ስር ያሰባሰበውን ስትራቴጂካዊ ጥበብ ለመረዳት በአህጉሪቱ ታሪክ ው...

የአፍሪካ ቀን፦ በትውስታ፣ በትርጉሙ እና ባልተጠናቀቀው የአንድነት ጉዞ መካከል 21.05.2026

የአፍሪካ ቀን የአሁኑ የአፍሪካ ህብረት በፈረንጆቹ ሚያዝያ 25፤ 1963 የተመሰረተበትን ቀን የሚዘክር እለት ነው፤ በየዓመቱም ይከበራል። “የቀድሞው የአፍሪካ አንድነት ድርጅት፤ የአሁኑ የአፍሪካ ህብረት ምስረታ ወቅት የነበረው የአንድነት መንፈስ በዛሬዪቱ ተቀዛቅዟል [...] የአፍሪካ ነፃነት ቀንም የፍሪካን ነፃነት እያከበርን፣ ስለአፍሪካ እጣፈንታ ኮስተር ብለን የምንወያይበት እለትም ሆኖ ማለፍ ነው ያለበት”ሲሉ የአፍሪካ ዴይ ኢኒሼቲቭ ሶሳይቲ ኦርጋናይዜሽን መስራች እና ዋና ዳይሬከተር አሮን ስይፉ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል። በዛሬው የድረም ኦቭ ቼንጅስ ዝግጅታችን ታዲያ፣ የነፃዪቱ አፍሪካ ተላሚዎች፣ አባቶች ያለሟትን አፍሪካ...

85ኛው የአርበኞች ድል በዓል፡- የሊግ ኦፍ ኔሽንስ ክህደት እና የኢትዮጵያ ጽናት 05.05.2026

ኢትዮጵያ 85ኛውን የአርበኞች ድል በዓል ዛሬ ሚያዚያ 27 ቀን ፣ 2018 ዓ.ም አክብራለች፡፡ ''በወቅቱ የአውሮፓ ኃያላን ከአንደኛው የዓለም ጦርነት ያጡትን ካፒታልና ሀብት መልሶ ለማግኘት አፍሪካን እንደ ግብዓትና የጉልበት ምንጭ ተጠቅመዋል። ጣሊያን በ1889 በዓድዋ ጦርነት የደረሰባትን ሽንፈት ለመቀልበስና የኢንዱስትሪ አብዮቷን ለመደገፍ ኢትዮጵያን በሙሉ አቅሟ ለመቆጣጠር መጣች። [...] የሊግ ኦፍ ኔሽንስ በኢትዮጵያ ላይ የተደቀነውን ወረራ ማስቆም አልቻለም። እንዲያውም የድርጅቱ አባል የሆኑት እንደ ብሪታንያ እና ፈረንሳይ ያሉ ሀገራት በዲፕሎማሲው ረገድ ለጣሊያን መንገድ ከፍተዋል።" ሲሉ በአድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚየም የጥና...

የአይ.ሲ.ሲ ድብቅ አጀንዳ፦ በአፍሪካ ሉዓላዊነት ላይ የተቃጣው የኒዮ-ኮሎኒያል ዘመቻ 04.05.2026

"ዓለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት (ICC) ወደ ሕጋዊ ማጭበርበሪያነት ተቀይሯል፤ ተቋሙ ከአሁን በኋላ የፍትህ አደባባይ ሳይሆን፣ የአሜሪካን የበላይነት ለማስጠበቅና የአፍሪካ መሪዎችን ለብቻቸው ነጥሎ ለማጥቃት በስልት የሚዘወር ታዛዥ መሣሪያ ሆኗል፤ ይህ ሁሉ በሚሆንበት ጊዜ ግን የምዕራባውያን የበላይነት አርክቴክቶች እጃቸው አይነካም።" ሲሉ —በዓለም አቀፍ ግንኙነት የዘርፍ ምሁር — ፕሮፌሰር ኤሊ ጂርጂ ኤልያስ፣ በሊባኖስ የዩኒቨርሲቲ በዓለም አቀፍ ግንኙነትና ስትራቴጂ ጥናት ልዩ ባለሙያና መምህር ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል።  በዛሬው የድረም ኦፍ ጄንጅስ ዝግጅታችን የሚከተሉትን ሶስት ዋና ዋና ጉዳዮች ከአንግዶቻችን ጋር በ...

የሩሲያው የኦንላየን መገበያያ 'ዋይልድቤሪስ' በኢትዮጵያ፦ ለላኪዎችና ሸማቾች ምን አዲስ ዕድል ይዞ መጣ ? 22.04.2026

ትልቁ የሩሲያ የመገበያያ መድረክ ‘ዋይልድቤሪስ’ እንደ ቡና፣ ጨርቃጨርቅ፣ የቆዳ ውጤቶች፣ የተፈጥሮ የመዋቢያ ምርቶች እና ሌሎች የኢትዮጵያ ምርቶችን ሩሲያ ውስጥ መሸጥ መጀመሩን አሳውቋል። “ዋይልድቤሪስ ጀማሪ ኩባንያ አይደለም። ከ20 ዓመታት በላይ ሲሰራ የቆየ ነው […] የኢትዮጵያ ምርቶች ለዓለም አቀፍ ገበያዎች እንዲደርሱ ያስችላል […] ክፍያዎችን በተመለከተም ከየአገራቱ ገበያ ጋር የሚጣጣሙ ይሆናል፤ ለምሳሌ በአሁኑ ወቅት ግብይት በኢትዮጵያ ብር መፈጸም እንዲቻል ከአገር ውስጥ የፋይናንስ ተቋማት ጋር በመተባበር ግብይቶችን ለማመቻቸት ትኩረት ሰጥተን እየሰራን እንገኛለን።” ሲሉ  የዋይልድቤሪስ የኢትዮጵያ ተወካይ ብሩክ ገነነ...

ለዘላቂ ሰላም ወይስ ለዳግም ጦርነት ዝግጅት? የኢራን-አሜሪካና እስራኤል የሁለት ሳምንት የተኩስ አቁም እንቆቅልሽ 11.04.2026

“ኢራን እና አሜሪካ መሰረታዊ የግጭት መንሳኤ የሆኑ ጉዳዮችን በተመለከተ መግግባባት ላይ ከደረሱ ወደ ዘላቂ ሰላም ሊመጡ ይችላሉ። ነገር ግን እነዚህን መሰረታዊ መንሳኤዎች መፍታት ከልቻሉ፣ ይህ የሁለት ሳምንት ጊዜያዊ የተኩስ አቁም ስምምነት ጊዜ በመግዛት አቅም አሰባስበው ዳግም ወደጦርነት ለመመለስ የሚያስችላቸውን ሁኔታ እየፈጠሩ ሊሆን ይችላል" ሲሉ በውጭ ጉዳይ ኢንስቲቲዩት የመካከለኛው ምስራቅ ከፍተኛ ተመራማሪ መሐመድ ሰኢድ (ዶ/ር) ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናገሩ። በዛሬው የድረም ኦቭ ቼንጅስ ጉዳያችን በፈርጆቹ መጋቢት 8፣ 2026 ኢራን እና አሜሪካ የተስማሙበትን የሁለት ሳምንት የተኩስ አቁም ስምምነት ስፋት ይቃኛል። በውጭ ጉዳ...

አፍሪካን የመበየን አባዜ፤ የምዕራባውያን የጥናት ተቋማት የኒዮ-ኮሎኒያሊዝም መሣሪያነት 07.04.2026

“የምዕራባውያን ስረዓቶች በአመፃ የታጀቡ ናቸው። ዛሬ በዓለም ዙሪያ ያሉትን ብዙ ግጭቶች ብንመለከት፣ በአንድ ወይም በሌላ መልኩ የምዕራባውያን እጅ አለበት። ይህንን ሁኔታ በተመሳሳይ ቀውስ ውስጥ ሁለት ሚና ይዞ መገኘት እለዋለሁ። ችግር ፈጣሪዎች ለችግሩ ስም ያወጡለታል፣ ለፈጠሩት ችግር ደግሞ መፍትሄ ፈጣሪዎች ሆነው ይመጣሉ። ይህ ምዕራባውያን መገለጫ ነው” ሲሉ በደቡብ አፍሪካው ዩኒቨርሲቲ የድህረ ምረቃ ምርምር ባልደረባ ቺዶካሼ ንዬሬ (ዶ/ር) ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግሩ። በዛሬው የድረም ኦቭ ቼንጅስ ቀዳሚው ጉዳያችን አፍሪካ የምትታይበትን እይታ የሚቀርፀው ማነው ስንል እንተይቃለን። ለዚህም በደቡብ አፍሪካ ዩኒቨርሲቲ የታቦ ምቤኪ...

የአውሮፓ አይሁዶችን በኢትዮጵያ ለማስፈር ተይዞ የነረው ውጥና የኢትዮጵያ ምላሽ 01.04.2026

“እርግጥ ነው፣ ሐሳቡ [የአውሮፓ አይሁዶችን በኢትዮጵያ ማስፈርን] በተመለከተ ለንጉሠ ነገሥት ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ የተላከው ደብዳቤ እንግሊዝ እና አሜሪካ መንግሥት ድጋፍ ነበረው። ይሁን እንጂ የኢትዮጵያ መንግሥት በአንድ አገር ውስጥ ሌላ አገር ለመፍጠር የሚያስችል ይሁንታ ለመስጠት ፈቃደኛ አልሆነም፤ ምክኛቱም ይህንን መፍቀድ የአገሪቱን ሉዓላዊነት አሳልፎ የሚሰጥ ነውና” ሲሉ ዓለም አቀፍ የፖሊሲ አማካሪው ቆስጠንጢኖስ በርኸተሰፋ (ዶ/ር) ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል። በዛሬው የድረም ኦቭ ቼንጅስ ቀዳሚው ጉዳያችን ወቅታዊውን የመካከልኛው ምስራቅ ሁኔታ መነሻ አድርገን በኢትዮጵያ የቀድሞው ሐረር ጠቅላይ ግዛት የአውሮጳ አይሁዶችን...

የፈውስ ክር:- በሚገባው ልክ ያልታወቀው በገና 30.03.2026

በገና በመንፈሳዊ ዝማሬዎች ውስጥ ካለው ቦታ ባለፈ፣ ለመንፈሳዊ ፈውስነት መዋል የሚችል ጥንታዊ እና ጥልቅ ሚስጥር ያለው ማሳሪያ ነው። “ዘመናዊ የኤሌክትሮኒክስ መሳሪያዎች ከጊዜ ወደ ጊዜ ከተፈጥሮ ውጪ የሆኑ ንዝረቶችን ያመነጫሉ ... ይህ ደግሞ የሰዎችን አዕምሮ ሎም አካል ሊጎዳ ይችላል። ይሁን እንጂ በገና በተቃራኒው ከዚህ በተለየ መልኩ ጥቅም ይሰጣል ... የውስጥ ሰላምን እና እርጋታን የሚያጎናፅፉ ንዝረቶችን ያመነጫል” ሲሉ ፕሮፌሰር ብረሃኑ ግዛው ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል። በዛሬው የድረም ኦቭ ቼንጅስ ዝግጅታችን በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ውስጥ ካሉ ጥንታዊ እና የጥልቅ መንፈሳዊ ዝማሬ ማጀቢያዎች መካከ...

የሕዝብ ቁጥር ፖሊሲ እንደ ጂኦፖለቲካ መሣሪያ፡- ‘የኪሲንጀር ሪፖርት’ እና የደቡቡ ዓለም እውነታ 26.03.2026

“የህዝብ ቁጥር መጨመርን በመግታት ላይ ብቻ አላተኮሩም [ምዕራባውያን]። በአዳጊ ሀገራት ውሰጥ የህዝብ ቁጥር መጨመርን በመግታት፣ የሀገራቱን ሀብት ለመበዝበዝ የሚያመች ስትራቴጂ እየከተሉ ነበር። ይህ ያፈጠጠ የብዝበዛ አካሄድ ነው። ምክንያቱም በእነዚህ ሀገራት አነስተኛ የህዝብ ቁጥር መኖር ማለት ለምዕራቡ ዓለም በፖለቲካ፣ በኢኮኖሚ፣ በማህበራዊ እና በቴክኖሎጂ ዘርፎች ላይ ቁጥጥር ወይም ተጽዕኖ እንዲያሳድሩ ቀላል ይሆንላቸዋል” ሲሉ በዲላ ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካ ሳይንስ እና ዓለም አቀፍ ግንኙነቶች መምህሩ ዳዊት መዝገበ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል። በዛሬው የድረም ኦቭ ቼንጅስ ዝግጅታችን እ.ኤ.አ. በ1974 በአሜሪካ ብሔራዊ ደህን...

ካሳ እና ፍትህ፡ በፓን አፍሪካዊ ማህደረ ትውስታ እና በዓለም አቀፍ የኃይል ፖለቲካ መካከል 24.03.2026

“አፍሪካ የራሷን ታሪክ፣ የራሷን እውነታ ለዓለም የምትነግርበት ድምፅ ይኖራት ዘንድ ፍፁም አስፈላጊ ነው። ምክኛቱ ደግሞ እስከዛሬ ድረስ አፍሪካን ብሎም የአፍሪካን ታሪክ በራሳቸው መንገድ ሲተርኩ ስለአፍሪካ ሲናገሩ የቆዩት አውሮፓውያን ናቸውና። ከአፍሪካ ውጭ [በአሜሪካ] እንዳደገች አንዲት ጥቁር ሰው እውነቱን ለመናገር ስለአፍሪካ መልካም ነገር ሰምቼ አላውቅም” ሲሉ ፓናፍሪካኒስቷ ጃኔል ሆይሌት ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል። በዛሬው የድረም ኦቭ ቼንጅስ ዝግጅታችን የባሪያ ንግድ፣ የቅኝ ግዛት እና መዋቅራዊ ብዝበዛ በጥቁር ሕዝቦች ላይ ጥሎ ስላለፈው አሻራ እንቃኛለን። ጨምረንም መላው የጥቁር ሕዝቦች ለፍትህ እና ካሳ የሚያደርጉትን...

በአፍሪካ የጤና ሉዓላዊነትን የመቀዳጀት ትርጉም እና አስፈላጊነት - መልከ ብዙው ትግል 18.03.2026

የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ያለጠው እውነታ ቢኖር አፍሪካ ዛሬም ድረስ የመድኃኒት አቅርቦት ፍላጎቷ በምዕራባውያን መድኃኒት አቅራቢ ኩባንያዎች በጎ ፈቃድ ላይ የተመሰረተ መሆኑን ነው። “የምዕራቡ ዓለም የአፍሪካን የሕዝብ ቁጥር ለመቀነስ ከሚፈልግባቸው ምክንያቶች መካከል ዘረኛ ፖሊሲው አንደኛው ነው [...] ሌላኛው ምክንያት ደግሞ ብዙ ወጣት ትውልድ ያላት አፍሪካ የዓለምን ሀብት ለመቆጣጠር ለያዙት ግብ እንቅፋት ትሆናለች የሚል ነው [...] ብሪክስ አፍሪካ ስለአፍሪካ የምታስብበት ብሎም አፍሪካ የራሷን ጥቅም ማስጠበቅ የምትችልበት ጠንካራ ህብረት ነው” ሲሉ የበርካታ ሽልማቶች አሸናፊ ደቡብ አፍሪካዊቷ የማህበረሰብ ጤና ባለሞያ ሻኪራ ቹና...

የኩባ ውለታና የአፍሪካ ምላሽ ? ጊዜ ያነሳው ጥያቄ 11.03.2026

ኩባ ለአፍሪካ የነፃነት እና የሉዓላዊነት ትግል የከፈለችው መስዕዋትነት የአህጉሪቱ የማይረሳ የታሪክ አንዱ ገጽ ነው። “ኩባ [...] የህልውና ፈተና በገጠመን ወቅት መስዋዕትነት በመክፈል ከጎናችን ቆማለች፤ አፍሪካውያን ግን በተዋለልን ልክ ለኩባ ደርሰንላታል ወይ?” ሲሉ የኢትዮ-ኩባ ወዳጅነት ማህበር አስተባባሪ አቶ አበበ አያሌው ይጠይቃሉ። ከየካቲት 29 እስከ መጋቢት 5/2018 ዓ.ም. “ህብረት ከግላኮማ ነፃ ለሆነች ዓለም” በሚል ጭብጥ የዓለም የግላኮማ ሳምንት ይከበራል።  “ግላኮማ ታማሚዎች ሳያውቁት የማይቀለበስ የዓይነ ስውርነት የሚያስከትል በሽታ ቢሆንም፣ የግንዛቤ እጥረት ሁኔታውን አክብዶታል” ሲሉ የግላኮማ ስፔሻሊስቷ ዶ...

የመካከለኛው ምስራቅ ቀውስ:- የአፍሪካ አገራትን እንዴት ሊጎዳ ይችላል ? 05.03.2026

የመካከለኛው ምስራቅ ውጥረት የነዳጅ ዋጋን ብሎም የዋጋ ግሽበትን እያባባሰ ባለብት ሁኔታ አፍሪካ ቆማ መመልከት አትችልም። አማራጭ የኃይል አቅርቦት ላይ ማተኮር፣ ቀጣናዊ ትስስርን ማፋጠን ግድ ይላታል። “ለአፍሪካ ይህ በጣም መጥፎ ዜና ነው። የነዳጅ ምርቶችን ወደ አገር ውስጥ የሚያስገቡ አብዛኞቹ አገራት እንዲህ ዓይነቱን ጫና ለቋቋም እጅጉን ይቸገራሉ። [...] ስለዚህ የአፍሪካ አገራት ስለ አማራጭ የኃይል ምንጮች የሚያስቡበት ጊዜ አሁን ነው።እንደሚታወቀው አፍሪካ ብዙ አማራጮች አሏት”ሲሉ ዓለም አቀፍ የፖሊሲ አማካሪው ቆስጠንጢኖስ በርኸተስፋ(ዶ/ር) ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል። በዛሬው የድረም ኦቭ ቼንጅስ ቀዳሚ ዝግጅታችን አ...

የሩሲያ ቀይ መስመር :- የፈረንሳይ እና ብሪታንያ ዩክሬንን የኒዩክሌር ጦር መሳሪያ የማሰታጠቅ ፍላጎት 25.02.2026

ፈረንሳይ እና ብሪታኒያ ለዩክሬን የኒዩክሌር ጦር መሳሪያ ለማስታጠቅ መንቀሳቀሳቸውን የሩሲያ የውጭ መረጃ ደህንነት ይፋ አድርጓል። "ምዕራባውያን ሩሲያን ወደ አቅም አልባ ትንንሽ ግዘቶች የመከፋፈል እቅዳቸው የቆየ ነው […] ከሰሞኑ ለዩክሬን የኒዩክሌር ጦር መሳሪያ ለማስታጠቅ ማሰባቸው ይህ እቅዳቸው በመክሸፉ ተስፋ የመቁረጣቸው ማሳያ ነው" ሲሉ የዓለም አቀፍ ግንኙነቶች መምህሩ ዳዊት መዝገበ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል። በዛሬው የድረም ኦቭ ቼንጅስ ልዩ ዝግጅታችን፣ የፈረንሳይ እና ብሪታንያ ለዩክሬን የኑክሌር ጦር መሳሪያ ለማስታጠቅ መዘጋጀታቸው ምን ዓለም አቀፍ ትርጓሜ አለው ስንል በዲላ ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካ ሳይንስ እና ዓለም...

የደቡቡ ዓለም መገናኛ ብዙኃን መንቃት፣ የራስ እውነታን ከራስ እይታ አንፃር የመንገር የትብብር ጉዞ 09.02.2026

የዓለም አቀፉ ደቡብ ጋዜጠኞችም ዓለም አቀፍ ክስተቶችን ከራሳቸው ታሪክ፣ ፍላጎት እና እውነታዎች አንፃር በመቃኘት የተዛነፉ ትርክቶችን ለማቅናት የጋራ ጥረቶችን ጀምረዋል። "ላለፉት አስርት ዓመታት ዓለም አቀፍ ዜናዎች ከአንድ አቅጣጫ የሚመጡ እና የአንድ ወገን ሐሳብን የሚያንቀባርቁ ነበሩ … በአንፃሩ ደግሞ አሁን ያለንበት ወቅት የደቡቡ ዓለም መገናኛ ብዙኃን ንቃት ጎልቶ ይስተዋላል … የዓለም ታሪክ ርዕሰ አንቀጽ እንጂ የማንኛውም ታሪክ ዳራ መሆንን እምቢኝ ያሉበት ወቅት ነው" ሲሉ በባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ የጋዜጠኝነት እና ስነ-ተግባቦት ት/ት ክፍል መምህርና እና የዓለም አቀፍ ጉዳዮች ተንታኝ አየለ አዲስ (ዶ/ር) ለስፑትኒክ አፍ...

የሰው ልጅ ታሪክ አዲስ መልክ፦ በኢትዮጵያ የተገኘው 2.6 ሚሊዮን ዓመት የሰው ልጅ ቅሪተ አካል ስለማንነታችን ምን ይነግረናል ? 29.01.2026

“ ከቆዳችን በታች ሁላችንም አንድ አይነት መሆናችንን እናያለን … ፖለቲከኞች ለራሳቸው ዓለማ ከዚህ የተለየ ኃቅ ሊያሳዩን የመቻል አቅማቸዉን አሳንሼ ግን ማየት አልፈልግም … ነገር ግን አሜሪካ፣ አፍሪካ፣ ሩሲያ ወይት ሌላ ቦታ ብንኖር ሰዎች ሁሉ አንድ ዘር ነን” ሲሉ ፕሮፌሰር ዘረሰናይ ዓለምሰገድ፣ የቀደምት ሰው ዘር መነሻ እና አመጣጥ ተመራማሪ (ፓሊዪአንትሮፖሎጂስት) ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል። በዛሬው ልዩ የድረም ኦቭ ቼንጅስ ዝግጅታችን እጅግ የተሟላ እና ጥንታዊ የሆነችውንና ከ3.3 ሚሊየን በላይ እድሜ ያላት የሰላምን (አውስትረሎፒቲከስ አፋረንሲስን) እና በቅርቡ የተገኘውን የ 2.6 ሚሊየን እድሜ ባለቤት ፓራንትሮፐስ ጨ...

በአውሮፓ እስረኛ የሆኑ ቅርሶች፡- ኢትዮጵያ ቅርሶቿን የማስመለስ ትግል 29.01.2026

የቅርብ ጊዜ ጥናቶች እንደሚያሳዩት ከ90-95 በመቶ የሚሆነው የአፍሪካ የባህል ቅርሶች ከአህጉሪቱ ውጭ ይገኛሉ። ዋና ዋናዎቹ የአውሮፓ ሙዚየሞች ብቻ ከ500,000 በላይ የአፍሪካ ቅርሶችን ይዘዋል።ከእነዚህም አብዝኃኛዎቹ በቅኝ ግዛት ዝርፊያ፣በአስገዳጅ ሁኔታዎች ወይም በሕገ-ወጥ ዝውውር የተገኙ ናቸው። "ከአገራችን ተዘርፈው ተወሰዱ ቅርሶቻችን በክፍያ መልሰን እንድንወስድ መጠየቃችን አሳዛኝ ነገር ነው። እነዚህን ቅርሶች የያዙ ሙዚየሞች ወይም የግል ቅርስ ሰባሳቢዎች ወደኢትዮጵያ እንዲመልሷቸው እናበረታታለን"ሲሉ የሺ ካሳ፣ የራስ ደስታ ዳምጠው የልጅ ልጅ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል። የኢትዮጵያ ቅርስ አስመላሽ ኮሚቴ ዋና ጸሐፊ አ...

የብሪክስ አዲስ ልማት ባንክ ከአፍሪካ ንግድና ምጣኔ ሐብት አኳያ ሲቃኝ 28.01.2026

''ብሪክስ እንደ አላማ አድርጎ ከተነሳው መካከል የፋይናንስ፣ ኢኮኖሚ፣ ንግድ፣ የመሠረተ ልማት ዝርጋታ፣ ንፁህ የአየር ከባቢ መፍጠርና የዲጂታል ሥራዎች ማስፋፋት ይገኙበታል። እኛ አፍሪካዊያን ነገሮችን በብስለት መምራትና መጠቀም ከቻልን ከብሪክስ የልማት ባንክ ብዙ መጠቀም እንችላለን። የልማት ባንኩ ከቀደመው የምዕራባዊያን የኢኮኖሚ ጫናም እንድወጣም የሚያስችል ነው '' ሲሉ አሉላ ተክለብርሃን አዲሱ፣ የምጣኔ ሀብትና ተያያዥ ጉዳዮች ባለሙያ እንዲሁም በሩሲያ፣ ቅዱስ ፒተርስበርግ ፖሊቴክኒክ ዩኒቨርሲቲ በኢኮኖሚክስ የትምህርት ክፍል እጩ ዶ/ር ለስፑትኒክ አፍሪካ አስረድተዋል። ሁለት አንኳር ጉዳዮችን በምንቃኝበት ፕሮግራማችን በክፍል...

የጋራ ሀብቶች እና የጋራ ዕጣ ፈንታዎች፦ ሉዓላዊነትን እና ትብብርን እንደገና ማጤን በአፍሪካ 27.01.2026

"አፍሪካውያን ሉዓላዊነትን የምንገልፅበት እና የምንረዳበት መንገድ ምዕራባውያን በ'ዌስታፋሊያ' ሰምምነት መሰረት ከሚነግሩን የሉዓላዊነት እሳቤ የተለየ ነው።[...] አፍሪካውያን የወረስነውን የምዕራቡን ዓለም ሉዓላዊነት መንገድ በመተዉ [...] ወደውስጥ መመልከት፣ የጋራ ሀብቶቻችንን በጋራ ስለመጠቀም ማሰብ አለብን።" ሲሉ በጆሃንስበርግ ዩኒቨርሲቲ የአስተዳደር እና የአፍሪካ ጥናት ማዕከል ዳይሬክተር ሰይፈ ታደለ ኪዳኔ (ዶ/ር) ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል። ዛሬ በድረም ኦቭ ቼንጅስ ቀዳሚ ጥንቅራችን 'አፍሪካ ሀብቶቿን በጋራ ለመጠቀም ትችል ዘንድ ሉዓላዊነትን በተመለከተ ያለውን ምዕራብ ተኮር እሳቤ መተው ስትችል ነው' የሚል መከ...

ሩሲያን የመነጠል ሙከራዎች መክሸፋና ከአፍሪካ ጋር የተጠናከረው ሁለንተናዊ ግንኙነት 22.01.2026

"በዩክሬን ውስጥ ምን እየሆነ እንዳለ [አሜሪካኖቹ] ሙሉ በሙሉ እንደሚረዱ እርግጠኛ ነኝ። ምዕራባውያን በተለይም አውሮፓውያን የሞራል ኪሳራ እንዲሁም በወታደራዊ አቅርቦት እና ቴክኖሎጂ አቅማቸው ላይ በዩክሬን ከፍተኛ ኪሳራ እንዳጋጠማቸው ተረድተዋል። የትራምፕ አስተዳደርም በዩክሬን ውስጥ ማን የበላይ እንደሆነ በትክክል ያውቃል። ስለዚህ ስለ ሰላማዊ መፍትሄ በቁም ነገር ማሰባቸው ተገቢ ነው።" ሲሉ በዲላ ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካ ሳይንስ እና ዓለም አቀፍ ግንኙነቶች መምህሩ ዳዊት መዝገበ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል። በድረም ኦቭ ቼንጅስ ዝግጅታችን በቀዳሚነት በጥር 20፣ 2026 (እ.ኤ.አ) የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌይ ላቭሮ...

ኢትዮጵያዊው ዲፕሎማት ከተማ ይፍሩ፦ ለፓን አፍሪካኒዝም እና ለአፍሪካ አንድነት ድርጅት መመስረት ምን ዋሉ ? 16.01.2026

"አባቴ፣ ለኢትዮጵያ ከአፍሪካውያን እህት ወንድሞቻችን የተሻለ አጋር የለም ብሎ ያምን ነበር … አባቴ በአሜሪካን ሀገር በትምህርት ላይ ሳለ ጥቁር በመሆኑ ብቻ የደረሰበትንም አልረሳም … እነዚህ ሁኔታዎች የፓንአፍሪካኒዝም እንቅስቃሴ ላይ እንዲበረታ አድርገዉታል"- ሲሉ መኮንን ከተማ ይፍሩ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል። በዛሬዉ ድረም ኦቭ ቼንጅስ ዝግጅታችን በቀዳሚነት ታላቁን ኢትዮጵያዊ ዲፕሎማት ከተማ ይፍሩን እንዘክራለን። ለዚህም በቅርቡ "ከተማ ይፍሩ፡ የሰላም፣ የእድገት እና የአፍሪካ አንድነት ሻምፒዮን" በሚል ርዕስ አባታቸዉን የሚዘክር መጽሐፍ ያሳተሙት ልጃቸው አቶ መኮንን ከተማ ይፍሩ እንግዳችን ናቸው። ሁለተኛው ጥንቅራችን...

Listen to the Drum of Changes podcast in Replaio

Radio and podcasts in one app - free, with no sign-up. Install today and do not miss the launch

Get it on Google Play

Replaio is not a podcast publisher; show names, artwork and audio belong to their authors and are distributed through public RSS feeds.