Connect for Culture Africa
ሲኤፍሲኤ ኢትዮጵያ - Connect for Culture Africa - Ethiopia
የሲኤፍሲኤ ኢትዮጵያ ፖድካስት በባህል እንዲሁም በኢትዮጵያ በሚገኙ የባህላዊ እና የፈጠራ ኢንዱስትሪ (CCIs) ላይ ያተኮረ ተከታታይ ክፍሎች ያሉት ጥልቅ ውይይት የሚካሄድበት ፖድካስት ነው፡፡ ሃሳብን በሚኮረኩቱ የተለያዩ ክፍሎች ባለሞያዎችን እንዲሁም ባለድርሻ አካላት ከህዝብ/መንግስት ድጋፍ አንስቶ እስከ ስራ ፈጠራ፣ ሰላም ግንባታና እና ዲሞክራሲ ባህል በኅብረተሰብ ውስጥ ያለውን ሚና ይዳስሳል፡፡ በተሾመ ወንድሙ የሚዘጋጀው ይህ ፖድካስት ለቅስቀሳ እንዲሁም ወጣቶችን ለማብቃት መሳሪያ ሆኖ ያገለግላል፡፡ ሁሉም ክፍሎች በአማርኛ የሚቀርቡ ሲሆን የእንግሊዝኛ የግርጌ መግለጫ ይኖራቸዋል፡፡የበለጠ ለማወቅ የሚከተለውን ድረ-ገጽ ይጎብኙ https://cfcafrica.orgThe CfCA Ethiopia Podcast is a series of powerful conversations around culture and the cultural and creative industries (CCIs) in Ethiopia. Through thought-provoking episodes, we e...
Author
Connect for Culture Africa
Category
Podcast website
Latest episode
Jan 26, 2026
Where to listen?
Podcasts in the app Replaio Radio Coming soonPodcasts are coming to the app soon. Install now and be the first to see a whole new take on podcasts
Episodes
Institutionalizing the Arts: Policy, Heritage, and Ethiopia's Creative Economy - CfCA Ethiopia - Episode 14 26.01.2026 1:25:30
ኮኔክት ፎር ካልቸር አፍሪካ ኢትዮጵያ ፖድካስት | ክፍል 14 ሥርዓተ-ጥበብን መገንባት፦ ፖሊሲ፣ ቅርስና የኢትዮጵያ የፈጠራ ኢኮኖሚ እንግዳ፡ አቶ ሰርፀ ፍሬ ስብሐት | አዘጋጅ ተሾመ ወንድሙ በክፍል 14 ኮኔክት ፎር ካልቸር አፍሪካ ኢትዮጵያ ፖድካስት አዘጋጅ ተሾመ ወንድሙ የብሔራዊ ቤተ መዛግብትና ቤተ መጻሕፍት አገልግሎት (ወመዘክር) ዋና ዳይሬክተር ከሆኑት ከአቶ ሰርፀ ፍሬ ስብሐት ጋር ጥልቅ ውይይት ያደርጋል፡ ይህ ክፍል የኢትዮጵያን የኪነ-ጥበብ ዘርፍ ከባሕላዊና በበጎ ፈቃደኝነት ላይ ከተመሠረተ አሠራር ወጥቶ፣ ወደ ተደራጀና በፖሊሲ ወደተደገፈ ኢንዱስትሪ ለመቀየር የሚያስፈልጉ መሠረታዊ መዋቅራዊ ለውጦችን ይቃኛል፡፡ አቶ ሰርፀ...
Thread of Identity: Fashion as Culture and Industry | CfCA Ethiopia #13 02.01.2026 57:05
ኮኔክት ፎር ካልቸር አፍሪካ - ኢትዮጵያ ፖድካስት | ክፍል 13 የማንነት ክሮች - ፋሽን እንደ ባህል እና እንደ ኢንዱስትሪ እንግዳ፡ ማኅሌት ተክለ/ማርያም | አዘጋጅ ተሾመ ወንድሙ በክፍል 13 ኮኔክት ፎር ካልቸር አፍሪካ - ኢትዮጵያ ፖድካስት ፤ አዝጋጅ ተሾመ ወንድሙ የሀብ ኦፍ አፍሪካ ፋሽን ዊክ መስራች እና አዘጋጅ ከሆነችው ማኅሌት ተክለ/ማርያም ጋር ውይይት ያደርጋል፡፡ ይህ ክፍል የኢትዮጵያን ፋሽን እና የፈጠራ ኢንዱስትሪ እድገት፣ተግዳሮቶችን እና መፃኢ እጣ ፈንታን ይቃኛል፡፡ ማኅሌት ከውጭ አገራት እስከ አገር ውስጥ የዘለቀ ጉዞዋን፣ በአፍሪካ ውስጥ እስከ አሁን ድረስ የዘለቀ የፋሽን መድረክን ስለመገንባቷ በተጨማሪ...
The Canvas Speaks: Visual and Fine Arts in Ethiopia | CfCA Ethiopia #12 12.12.2025 1:05:02
ኮኔክት ፎር ካልቸር አፍሪካ ኢትዮጵያ ፖድካስት፤ ክፍል 12 ''ሸራ ይናገራል፤ የእይታ ጥበባት እና ሥነ-ጥበብ በኢትዮጵያ'' እንግዳ፡ የእይታ ጥበባት አርቲስት፣ ገጣሚ እና በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ አለ የሥነ-ጥበብ እና ዲዛይን ትምህርት ቤት ፕሮፌሰር፤ፕሮፌሰር በቀለ መኮንን በዚህ አነቃቂና አይን ከፋች ክፍል፣ የኢትዮጵያን የእይታ ሥነ-ጥበባት እና የሥነ-ሥዕል ጥበብ ዘርፍ ጥልቀታቸውን፣ታሪካቸውን እና ተግዳሮታቸውን እንዳስሳለን፡፡ እንግዳችን ፕሮፌሰር በቀለ መኮንን በሥነ-ጥበብ እና በሙዚየም ስራ ውስጥ ለበርካታ አስርት ዓመታት እንደ የፈጠራ ሰራተኛ፣መምህር እና መሪ በመሆን ያገለገሉበትን ልምድ ይዘው የቀረቡ ሲሆን በጋራ በመ...
Stages of Change: The Transformative Power of Theatre | CfCA Ethiopia #11 21.11.2025 56:42
ክፍል 11፡ የለውጥ መድረኮች: የትያትር ኃይል ለዘላቂ ለውጥ እንግዳ፡ መዓዛ ወርቁ፤ ጸሐፊ ተውኔት አቅራቢ፡ ተሾመ ወንድሙ በዚህ የኮኔክት ፎር ካልቸር አፍሪካ ኢትዮጵያ ፖድካስት ከዝነኛዋ ጸሐፊ ተውኔት መዓዛ ወርቁ ጋር በመሆን በኢትዮጵያ የባህል ተረክ ውስጥ ትያትር የተጫወተውንና እየተጫወተ ያለውን ከፍተኛ ሚና እንዳስሳለን፡፡ በትምህርት ቤቶች እና ሆቴሎች ከጀመረበት ጊዜ አንስቶ፤ሀገርን ለአንድ ዓላማ እስከማስተባበር ድረስ፣መዓዛ የኢትዮጵያ ትያትር አስደማሚ ጉዞን ታስቃኘናለች፡፡ በተጨማሪም ትያትር ለፊልም፣ቴሌቪዥን፣ትምህርት፣የሀገር ግንባታ ያለውን አስተዋጽኦ እንዲሁም የጋራ ማንነትን በመቅረጽ ረገድ ያለውን አስተዋጽኦ ጸ...
Learning the Arts: The Role of Education in Cultural Development | CfCA Ethiopia #10 31.10.2025 1:18:25
ጥበብና ትምህርት፡ በባህል ልማት ውስጥ የትምህርት ሚና |ክፍል 10| ወደ ኮኔክት ፎር ካልቸር አፍሪካ ኢትዮጵያ ፖድካስት 10ኛ ክፍል እንኩዋን በደህና መጣችሁ! በዚህ ክፍል የሰላምና ሙዚቃዊ መስራች እና ዋና ዳይሬክተር ተሾመ ወንድሙ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የአለ የሥነ-ጥበብ እና ዲዛይን ትምህርት ቤት ምክትል ዲን/ኪዩሬተር፣ አርቲስት እንዲሁም ተመራማሪ ከሆኑት አገኘሁ አዳነ ጋር በመሆን የኢትዮጵያን ህዝብ በመቅረጽ ረገድ የሥነ-ጥበብ ትምህርት ያለውን ሚና ይዳስሳሉ፡፡ የሚዳሰሱ ርዕሶች · የሥነ-ጥበብ ትምህርት ከስር መሰረት የመሰጠቱ ጥቅም · ለኢትዮጵያ ሥነ-ጥበብ የነበሩ ታሪካዊ እና ዘመናዊ አስተ...
Owning Creativity: The State of Copyright and IPR in Ethiopia | CfCA - Ethiopia #9 10.10.2025 1:03:28
ክፍል 9፡ የፈጠራ ባለቤትነት፡ የቅጂ እና የአእምሯዊ ንብረት መብት በኢትዮጵያ| ኮኔክት ፎር ካልቸር አፍሪካ ኢትዮጵያ ፖድካስት ይህ የኮኔክት ፎር ካልቸር አፍሪካ ኢትዮጵያ ፖድካስት በኢትዮጵያ የፈጠራ ዘርፍ ውስጥ እጅግ አንገብጋቢ የሆኑትን የቅጂ መብት እና የአእምሯዊ ንብረት መብትን በጥልቀት ይዳስሳል፡፡ የሚዳሰሱ ጉዳዮች · አሁን በሚገኙ ህጎች እና ረቂቅ ፖሊሲዎች መካከል ያለው ክፍተት · የበርን ኮንቬንሽን እና ዓለም አቀፍ ፕሮቶኮሎች ጥቅም · የጋራ አስተዳደር ማኅበራት ሚና · ኢትዮጵያ ለምን አሁን ወደ ተግባር መግባት እንዳለባት · በዘርፉ የገንዘብ ድጋፍ፣...
Beyond the Spotlight: Circus as a Tool for Empowerment| Teklu Ashagir | CfCA - Ethiopia #8 19.09.2025 59:08
ከመድረክ ባሻገር፡ ሰርከስ እንደ አስቻይ የጥበብ ዘርፍ | ተክሉ አሻግር ከተሾመ ወንድሙ ጋር | ኮኔክት ፎር ካልቸር አፍሪካ ኢትዮጵያ ፖድካስት ሰላም ኢትዮጵያ ከኮኔክት ፎር ካልቸር አፍሪካ እንቅስቃሴ ጋር በጋራ ወደ ሚያቀርበው ኮኔክት ፎር ካልቸር አፍሪካ ኢትዮጵያ ፖድካስት እንኳን በደህና መጣችሁ፡፡ በዚህ ክፍል ተሾመ ወንድሙ ከኢትዮጵያ ሰርከስ ብሔራዊ ማኅበር ፕሬዝደንት ከተክሉ አሻግር ጋር በመሆን ሰርከስ ያለምንም ተቋማዊ ድጋፍ ወይም መሰረተ-ልማት እንዴት ህይወትን እንደለወጠ፣ወጣቶችን እንዳበቃ እንዲሁም ኢትዮጵያ በኪነ-ጥበቡ ዘርፍ ያላትን ዓለም አቀፍ ደረጃ ከፍ እያደረገ እንደሚገኝ አይን ገላጭ ውይይት ያካሂዳሉ፡፡ የሚዳሰ...
Writing Our Truths: The State of Literature in Ethiopia - CfCA - Ethiopia #7 29.08.2025 1:07:09
የሀገር ገፆች፡ የስነ-ጽሁፍ ሁኔታ በኢትዮጵያ ክፍል 7 - ሲኤፍሲኤ ኢትዮጵያ ፖድካስት ደራሲ የዝና ወርቁ እና ተሾመ ወንድሙ በጋራ በመሆን በአሁኑ ጊዜ በኢትዮጵያ ስነ-ጽሁፍ ውስጥ ያሉ ተግዳሮቶችንና እድሎችን ይዳስሳሉ፡፡ የንባብ ልምድ ከማዳበር እስከ ፖሊሲ አስተዋጽኦ፣የህትመት ችግሮች፣ የቋንቋ ብዝኃነት እና ኢትዮጵያዊ ታሪኮችን በመግለጽ ረገድ የዘርፉ መፃኢ እጣ ፈንታ በዚህ ውይይት ይነሳሉ፡፡ የሚካተቱ ርዕሶች ዝርዝር ጸሀፊዎች በኅብረተሰብ ውስጥ ያላቸው ሚና በተለያዩ የኢትዮጵያ ቋንቋዎች ውስጥ የኢትዮጵያ የስነ-ጽሁፍ ሁኔታ ለጸሀፊዎች የመሰረተ-ልማት እና ድጋፍ ያለበት ሁኔታ ንባብን እንዲሁም መጻፍን ለማበረታታት መደረግ ስላ...
Sounds of a Nation: The Ethiopian Music Scene - CfCA - Ethiopia #6 08.08.2025 1:27:28
ኮኔክት ፎር ካልቸር አፍሪካ - ኢትዮጵያ ፖድካስት | ክፍል 6 ርዕስ፡ የሀገር ድምፅ-የኢትዮጵያ ሙዚቃ ወግ እንግዳ፡ ጆርጋ መስፍን - ሳክስፎኒስት፣ሙዚቃ አቀናባሪ አዘጋጅ፡ ተሾመ ወንድሙ - የሰላም እና ሙዚቃዊ መስራች እና ዋና ስራ አስኪያጅ በዚህ የኮኔክት ፎር ካልቸር አፍሪካ - ኢትዮጵያ ፖድካስት ክፍል የኢትዮጵያን ሙዚቃ ትሩፋት፣የአሁን ተግዳሮቶቹን እንዲሁም ለወደፊት ያለውን ከፍተኛ አቅም እንዳስሳለን፡፡ እንግዳችን ጆርጋ መስፍን የኢትዮጵያ የሙዚቃ ትሩፋት ላይ በማተኮር ከቅዱስ ያሬድ እስከ ዛሬ ዘመን የሚገኘው ወጣት መር ፈጠራን ይዳስሳል፡፡ ጆርጋ መስፍንና ተሾመ ወንድሙ በጋራ በመሆን እንደ የኦሪጅናል ካሴቶች አለመኖር፣ተገ...
The Reel Story: A Conversation on Ethiopia's Film - CfCA Ethiopia #5 18.07.2025 1:15:12
በኢትዮጵያ ፊልም ዙሪያ ያተኮረ ውይይት| ሲኤፍሲኤ ኢትዮጵያ ፖድካስት - ምእራፍ 2 ወደ ኮኔክት ፎር ካልቸር አፍሪካ (ሲኤፍሲኤ) ኢትዮጵያ ፖድካስት እንኳን በደህና መጡ፤ በዚህ ክፍል በባህል እና በዘላቂ ልማት መካከል ያለውን ቁልፍ ግንኙነት እንዳስሳለን፡፡ በዚህ በኢትዮጵያ ፊልም ዙሪያ ያተኮረ ውይይት ላይ ከዝነኛው ፊልም አዘጋጅ ሄኖክ አየለ እንዲሁም ተሾመ ወንድሙ ጋር የኢትዮጵያ ፊልም ዘርፍ ላይ ወቅታዊ እና ግልጽ ውይይት እናደርጋለን፡፡ በዚህ ክፍል የሚከተሉትን ቁልፍ ጥያቄዎችን እናነሳለን፡ የኢትዮጵያ ፊልም ኢንዱስትሪ እንደ ኔትፍሊክስ ላሉ ዓለም አቀፍ መተግበሪያዎች ዝግጁ ነው? የፊልም ትምህርትን፣የገንዘብ ድጋፍን እና የ...
Culture as a Catalyst for Peace, Rights, and Democracy - CfCA Ethiopia #4 27.06.2025 55:29
ክፍል 3፡ የባህል ሚና ለሰላም, ሰብዓዊ መብት እና ዲሞክራሲ ግንባታ በዚህ ክፍል የባህል ተመራማሪ ከሆኑ ዶ/ር ጥላሁን በጅቷል ጋር ኪነ-ጥበብ፣ባህል እና ፈጠራ በሰላም ግንባታ፣ሕብረተሰብ ላይ ተሃድሶ በመፍጠር እንዲሁም በብሔራዊ ኢትዮጵያዊ ማንነት ላይ ምን አይነት ሚና እንደሚጫወቱ እንዳስሳለን፡፡ ከባህላዊ ትሩፋቶች እስከ ዘመናዊ ኪነ-ጥበብ ድረስ ያሉትን ሁኔታዎች እንዲሁም በባህል፣በግጭት መፍታት እና በሰብዓዊ መብት መካከል ያሉትን ጥልቅ ትስስሮች ዶ/ር ጥላሁን ይተነትናሉ፡፡ በተጨማሪም የበርካታ አመታት ጥናት ላይ ተመርኩዘው ዶ/ር ጥላሁን የሚከተሉት ላይ ምልከታቸውን ያጋራሉ፡፡ · ከበፊት የተወረሱ፣ጎልተው የሚታዩ...
Culture as a Driver for Job Creation - CfCA Ethiopia #3 06.06.2025 58:30
ባህል እና የባህል እና ፈጠራ ኢንዱስትሪው ላይ ለካበተ እና ጥልቅ ውይይት መድረክ በሆነው የሲኤፍሲኤ ኢትዮጵያ ፖድካስት 3ኛ ክፍል ባህል ለስራ እድል ፈጠራ ያለው ሚና የሚል ውይይት ይዘንላችሁ ቀርበናል፡፡ በተሾመ ወንድሙ ተዘጋጅቶ የሚቀርበው እና የእንግሊዝኛ የግርጌ መግለጫ ያለው ይህ ክፍል በባህል እና በስራ ቅጥር መካከል ያለውን ወሳኝ ሚና ይዳስሳል፡፡የባህል ትሩፋት የዘላቂ ስራ እና የኢኮኖሚ እድገት ምንጭ ሊሆን ይችላል? በውይይቱ የሚዳሰስ ጉዳይ ነው፡፡ ውይይቱ የኢትዮጵያን ባህል፣አፈ-ታሪክ እንዲሁም ሕብረተሰብ በማጥናት የአራት አስርት አመታት ልምድ ያላቸው ዶ/ር ባይለየኝ ጣሰው እንግዳ በመሆን የቀረቡበት ሲሆን ከተሾመ ወ...
Public Funding for the Culture and Creative Sector in Ethiopia - CfCA Ethiopia #2 16.05.2025 55:55
የሲኤፍሲኤ ኢትዮጵያ ፖድካስት ሁለተኛው ክፍል 'የመንግስት ድጋፍ ለባህል' የሚል ሲሆን- በባህል እና የባህል እና ፈጠራ ኢንዱስትሪ ላይ የካበቱ እና ጥልቀት ያላቸው ውይይቶች የሚካሄዱበት መድረክ ነው፡፡ በተሾመ ወንድሙ ተዘጋጅቶ ከእንግሊዝኛ የግርጌ መግለጫ ጋር የሚቀርበው ይህ ክፍል በኢትዮጵያ እንዲሁም ከዛም ባሻገር ኪነ-ጥበብን ለመደገፍ የመንግስት ድጋፍ እንዴት እንደሚመደብ ይዳስሳል፡፡በባህል ላይ የመንግስት ኢንቨስትመንት ምን ይመስላል? ተስፋ ሰጪ የሆኑ አዳዲስ ክንውንኖች ምንድን ናቸው፤ክፍተቶችስ ያሉት እምን ጋ ነው? የሚሉትን ጥያቄዎች ይመለከታል፡፡ ይህንን ውይይት የሚቀላቀሉት ዶ/ር ይስማ ጽጌ ሲሆኑ ጥናታዊ ምርምር ስራ...
Defining Culture and Its Importance - Firehiwot Bayu (PhD) - CfCA Ethiopia #1 25.04.2025 54:43
የባህል ምንነት እና ፋይዳው የሚለው የመጀመሪያ ክፍል የፖድካስት ዝግጅት የሲኤፍሲኤ ፖድካስት ተከታታይ ክፍሎችን መክፈቻ ዝግጅት ሲሆን ይህ ፖድካስት በባህል እና በባህላዊ እና ፈጠራ ኢንዱስትሪው ላይ ላተኮሩ የካበቱ እንዲሁም ጥልቅ ምልከታን የያዙ ውይይቶች የሚንጸባረቁበት መድረክ ነው፡፡ በዚህ በተሾመ ወንድሙ አቅራቢነት በሚቀርበው እና የእንግሊዝኛ የግርጌ መግለጫ ባለው የመክፈቻ ክፍል 'ባህል ምንድነው? ፋይዳውስ?ኅብረሰተብን በመቅረጽ ረገድ ምን ሚና ይጫወታል? እና በባህል ጥላ ስር የሚገኙት ዘርፎች ምንድናቸው?' የሚሉ መሰረታዊ ጥያቄዎችን በማንሳት መድረኩን እንከፍታለን፡፡ ዶ/ር ፍሬሕይወት ባዩ በምልከታቸው ባህል በ...
Similar podcasts
Replaio is not a podcast publisher; show names, artwork and audio belong to their authors and are distributed through public RSS feeds.