DW
እንወያይ | Deutsche Welle
ኢትዮጵያን በሚመለከቱ ጉዳዮች ላይ ከተለያዩ እንግዶች እና በተለያዩት የዓለም ሀገሮች ከሚገኙት ወኪሎቻችን ጋ የምናካሂደውን እና በየሣምንቱ እሁድ ከምሽቱ አንድ ሰዓት ከአሥር ደቂቃ ላይ የሚተላለፈውን የውይይት ዝግጅት ያዳምጡ።
Husk å besøke podkastens nettsted og støtte skaperen: www.dw.com?maca=amh-podcast_amh_diskussionsforum-8741-xml-mrss
Forfatter
DW
Kategori
Podkastens nettsted
www.dw.com?maca=amh-podcast_amh_diskussionsforum-8741-xml-mrss
Siste episode
11. okt 2026
Hvor kan du lytte?
Podkaster i appen Replaio Radio Kommer snartPodkaster kommer snart til appen. Installer nå, og bli den første som ser en helt ny tilnærming til podkaster
Episoder
ትግራይ፦ የኢትዮጵያ እና የኤርትራ መፋለሚያ? 11.10.2026 44:57
በትግራይ ክልል እየተደረገ የሚገኘው ውጊያ በኢትዮጵያ እና ኤርትራ ፍጥጫ ወደ ሌላ የግጭት ምዕራፍ ሊሸጋገር ዳር ዳር እያለ ነው። በመቶ ሺሕዎች የተገደሉባቸው ሁለት የጦርነት ታሪኮች ያላቸው አገራት ፍጥጫ ምን ያክል አስጊ ነው? ሦስት እንግዶች የተሳተፉበት ውይይት የውጊያውን አደጋ፤ ለሰላማዊ ሰዎች የሚያስከትከትለው መዘዝ ይፈትሻል።
ትግራይ፦ የኢትዮጵያ እና የኤርትራ መፋለሚያ? 11.10.2026 44:57
በትግራይ ክልል እየተደረገ የሚገኘው ውጊያ በኢትዮጵያ እና ኤርትራ ፍጥጫ ወደ ሌላ የግጭት ምዕራፍ ሊሸጋገር ዳር ዳር እያለ ነው። በመቶ ሺሕዎች የተገደሉባቸው ሁለት የጦርነት ታሪኮች ያላቸው አገራት ፍጥጫ ምን ያክል አስጊ ነው? ሦስት እንግዶች የተሳተፉበት ውይይት የውጊያውን አደጋ፤ ለሰላማዊ ሰዎች የሚያስከትከትለው መዘዝ ይፈትሻል።
አዲስ የሚመሰረተዉ የኢትዮጵያ መንግሥት ሀገሪቱ ከገባችበት ቀዉስ ሊያወጣ የሚችል መፍትሄን ያገኝ ይሆን? 04.10.2026 44:21
የጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ ብልፅግና ፓርቲ፤ አዲስ መንግሥት የሚመሰርተዉ፤ ሰሜን ኢትዮጵያ ዉስጥ በአዲስ ጦርነት ተቀሰቀሰ ከተባለ በኃላ ነዉ። ጦርነቱ የጀመረዉ በፌደራል መንግሥት እና በህወሓት፤ የአማራ ፋኖ፤ የኦሮሞ ነጻ አዉጭ ሰራዊትን ጨምሮ 7 አማፂ ኃይላት መንግሥትን ለመጣል የጋራ ጥምረት በመሰረቱ በሁለተኛዉ ቀን መሆኑ ነዉ።
ዉይይት፣ የኢትዮጵያ የአዲስ መንግሥት ምሥረታ ዝግጅትና የጦርነት እልቂት 27.09.2026 45:08
በኢትዮጵያ ፌደራላዊ መንግሥትና በህዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) መካከል የሚደረግ ያሉት ጦርነትን ሥለጀመረዉ ወገን ማንነት ተፋላሚ ኃይላት አንደሚጠበቀዉ አንዳቸዉ ሌላቸዉን እየወነጀሉ ነዉ።ዉጊያዉ ግን ቀጥሏል
ፅምዶ/ጥምረት ወዴት? 20.09.2026 46:08
ፅምዶ/ጥምረት ወዴት?
ፅምዶ/ጥምረት ወዴት? 20.09.2026 46:08
«ብልጽግና የህልውናችን አደጋ ስለሆነ መደምሰስ አለበት ብለው የሚያምኑ አንድ ላይ ተጣምረው አቅማቸውን አቀናጅተው በቦታና በጊዜ ጦርነት ሲገጥሙ የሚፈጠር አቅምና በብልጽግና ሥርአት ላይ የሚደርስ ምት የጠላትን ዕድሜ ለማሳጠር ይጠቅማል።»
በኢትዮጵያ ሰላም ለምን እውን መሆን አልቻለም? 06.09.2026 44:58
የሰላም ጥሪው ምላሽ ሳያገኝ ይህ ሁሉ የስጋት ድምጽ እየተሰማባለበት ኢትዮጵያ ሌላ አዲስ ዓመት ልትቀበል ቀናት ቀርተዋል። ዛሬም ጥፋተኖች ለፍርድ ተጎጂዎችም ፍትህ ያግኙ የሚለው ጥሪ አላባራም። ለመሆኑ ኢትዮጵያ ውስጥ ሰላምን ማስፈን ለምን አቃተ? የሕዝቡ ሰቆቃስ ማብቂያው መቼ ነው? ዶቼ ቬለ በአዲስ ዓመት ዋዜማ ላይ እንግዶች ጋብዞ አወያይቷል።
የኦባሳንጆ አዲስ የሰላም ጥረት በፌደራል መንግሥትና በትግራይ ክልል መካከል የተፈጠረውን ውጥረት ምን ያህል ሊያርግብ ይችላል ? 30.08.2026 41:55
ውጥረቱ በተባባሰበት በዚህ ሳምንት ሰኞ በአፍሪቃ ቀንድ የአፍሪቃ ኅብረት ልዩ መልዕክተኛ የቀድሞ የናይጀሪያ ፕሬዝዳንት ኦሊሴጉን ኦባሳንጆ መቀሌ መሄዳቸው መሰማቱ የሰላሙ ጥረት እንደገና የመንቀሳቀሱ ተስፋ ተደርጎ ተወስዷል። ከኢትዮጵያ መንግሥት በኩል እስካሁን ስለኦባሳንጆ ጉብኝት የተባለ ነገር የለም።
እንወያይ፤ የተጠናቀቀው ሀገራዊ ምክክር ጉባኤ ምክረ ሀሳቦች ምን ያህል ተፈፃሚ ናቸው? 23.08.2026 47:25
የኢትዮጵያ ሀገራዊ የምክክር ኮሚሽን የአዲስ አበባን ጉዳይ ጨምሮ በለያቸው ስምንት ዋና ዋና አጀንዳዎች ላይ ከአንድ ወር በላይ ሲመክር ቆይቶ ትናንት ቅዳሜ ተጠናቋል።ኮሚሽኑ የሀገሪቱን ችግሮች በምክክር ለመፍታት የሚደርገውን ጥረት በበጎ የሚያዩ እንዳሉ ሁሉ፤ ሂደቱን የሚተቹ እና የታለመለትን ብሔራዊ መግባባትና ሰላም ማምጣቱን የሚጠራጠሩም አሉ።
ኢትዮጵያ አሰቃቂ ግፎች ከሚፈጸምበት የግጭት አዙሪት መውጣት ለምን ተሳናት? 16.08.2026 45:47
በተደራራቢ ግጭቶች ውስጥ ለተፈጸሙ ግፎች ተጠያቂነት ሳይረጋገጥ ኢትዮጵያ ሌላ የጦርነት ሥጋት ተጋርጦባታል። ለበርካታ አስርት ዓመታት ስለ ዴሞክራሲ ቢሰበክም የፖለቲካ ልሒቃኑ አገሪቱን ከግጭት አዙሪት ማላቀቅ አልቻሉም። ለምን? የለየለት ጦርነት እንዳይቀሰቀስ ማቆም የሚችል ወገን አለ? ወይስ ረፍዷል? በአሜሪካው ኢንዲያና ዩኒቨርሲቲ ማወር የሕግ ትምህርት ቤት ተመራማሪ የሆኑት አለማየሁ ፈንታው፤ የአምነስቲ ኢንተርናሽናል የአፍሪካ ቀንድ ጉዳዮች ተመራማሪ ሐይማኖት አሸናፊ እና በግጭትና መፈናቀል ጉዳዮች ላይ ምርምር የሚያደርጉት ዶክተር ሳሙኤል ዘውዴ በውይይቱ ተሳትፈዋል።
የሰሜን ኢትዮጵያ ውጥረትና የተፈናቃዮች ብርቱ ሥጋት 09.08.2026 45:15
ባለፈው ሳምንት ቅዳሜ ካጋጠመው የሸረሪናው ውጊያ በተጨማሪ በአላማጣ የተፈጠረው ውጥረት የተፈናቃይ ጎርፍ አስከትሏል ። ከወራት በፊት ጀምሮም ለጦርነት የሚደረገውን ዝግጅት እና አስገዳጅ ወታደራዊ ምልመላ በመሸሽ ወደ ቆቦ ከተማ የሚገቡ ተፈናቃዮች ቁጥር ጨምሯል ። ሙሉውን ውይይት በድምፅና በጽሑፍ በማገናኛው ይከታተሉ ።
እንወያይ፤ ስደት፣ መንከራተት፣ ሞት ማቆሚያው የት? 02.08.2026 44:04
ዓለም አቀፍ የጠፉ ስደተኞችን አፈላላጊ ድርጅት እንዳስታወቀው ደግሞ ጎርጎሮሳውያኑ አቆጣጠር ከ2024 እስከ 2026 ባሉት ዓመታት በሜዲትራንያን ባሕርና በአትላንቲክ ውቅያኖስ የስደት መስመሮች ቢያንስ 15,000 ስደተኞች ሕይወታቸውን ማጣታቸውን ይፋ አድርጓል።
እንወያይ: ኢትዮጵያ ለዓመታት የጠበቀችው ሀገራዊ ምክክር ወዴት? 26.07.2026 44:10
የኢትዮጵያ ፖለቲካ ተዋናዮች እና ምሁራን ለበርዓታ ዓመታት እንዲደረግ ሲያሳስቡ የከረመው ሀገራዊ ብሔራዊ ምክክር ዘንድሮ እውን ሆኗል። ውይይት ምክክሩ ሁሉን አላካተተም በሚል ጥያቄዎች ይነሳሉ።
ዉይይት፣ የአዲስ አበባ፣ የመቀሌና የአስመራ መሪዎች ዉዝግብ ንሯል፤ቀጥሎስ? ጦርነት ወይስ ሰላም? 19.07.2026 45:15
የትግራይ ክልል በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤትም፣ በምርጫም፣ በምክክር ጉባኤ፣ በአገራዊ የፖሊሲ ዉሳኔዎችም አለመካፈሉ ክልሉን በሚመራዉ በሕዝባዊ ወያኔ ሐርነት ትግራይ (ህወሓት) ና በኢትዮጵያ ፌደራዊ መንግሥት መካከል የተፈጠረዉ ጠብ እየተካረረ መምጣቱን መስካሪ መስሏል
ዉይይት፣ የአዲስ አበባ፣ የመቀሌና የአስመራ መሪዎች ዉዝግብ ንሯል፤ቀጥሎስ? ጦርነት ወይስ ሰላም? 19.07.2026 45:15
የቃላቱ ጦርነት ደግሞ ከመቀሌና አዲስ አበባ አልፎ አስመራና ካርቱም እየደረሰ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚንስትር ዓብይ አሕመድ ባለፈዉ ሰኔ 30 ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ባደረጉት ንግግር ህወሓት፣ ከኤርትራ (ሻዕቢያ)፣ ከሱዳን (SAF)ና በስም ካልጠቀሷቸዉ ሌሎች ወገኖች ጋር ሆነዉ የኢትዮጵያን ሠላም ለማወክ እያሴሩ መሆናቸዉን አስታዉቀዋል
ሃገራዊ ምክክር የመጨረሻው ምዕራፍ ከተስፋ ባሻገር 12.07.2026 46:10
ኢትዮጵያ ሃገራዊ ምክክር ለማድረግ ጥቂት ቀናት ቀርተዋታል። ከተለያዩ የሀገሪቱ ክፍል በምክክሩ ላይ ይሳተፋሉ የተባሉ ከአራት ሺ በላይ ተወያዮች አዲስ አበባ ከተማ መግባታቸው ተገልጿል። የኢትዮጵያ ሃገራዊ የምክክር ኮሚሽን ከትግራይ ክልል ውጪ የምክክር አጀንዳ የማሰባሰብ ስራው ከሶስት ዓመታት በላይ እንደወሰደበት ታይቷል።
እንወያይ፤ የትግራይ ክልል ቀዉስ ወዴት እያመራ ነዉ? መፍትሔዉስ? 05.07.2026 43:25
በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ መንግሥትና በህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ መካከል የሚደረገዉ ዉዝግብና ቁርቁስ አሁንም እንደቀጠለ ነዉ። ህወሓት በፕሪቶርያ ስምምነት መሰረት የተሰየመዉን የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ከተቆጣጠረ ወዲህ ከመንግሥት ጋር የነበረዉ ቂም እየተካረረ መምጣቱ እየተነገረ ነዉ። ህወሓትም ወጣቶችን ለዉትድርና እያስገደደ ነዉ ተብሏል።
የሰባተኛው የኢትዮጵያ ጠቅላላ ምርጫ ውጤትና ፋይዳው እንዲሁም ተግዳሮቶቹና ተስፋው 28.06.2026 40:34
ምርጫው ከመካሄዱ አስቀድሞም በስፋት እንደተጠበቀው ገዥው ፓርቲ ብልጽግና ሲያሸንፍ ከቀደሙት ምርጫዎች በተለየ በአሁኑ ምርጫ ተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች ተጨማሪ የምክር ቤት መቀመጫዎችን ማግኘታቸው ትኩረት ስቧል።
Lignende podkaster
Replaio er ikke podkastutgiver; programnavn, omslag og lyd tilhører opphavspersonene og distribueres via offentlige RSS-feeder.