Zelalem Demissie
Drum of Changes
From the heart of ancient kingdoms to the pulse of modern cities, a new rhythm echoes across the continent. Africa is rising — a formidable force shaping the world’s future. For generations, Africa has been the most spoken about, yet the least heard. But today, the call is unmistakable: Africa demands its rightful place at the table of global power. Welcome to 'Drum of Changes' — a program dedicated to the stories that matter to Africa. Here, we explore culture, history, art, politics, the economy, and more, all through the lens of Africa itself. 'Drum of Changes' brings you the voices of tran...
Visita il sito del podcast e sostieni chi lo crea: drum-of-changes.mave.digital
Autore
Zelalem Demissie
Categoria
Sito del podcast
Ultimo episodio
8 ott 2026
Dove ascoltare?
I podcast nell'app Replaio Radio In arrivoI podcast stanno per arrivare nell'app. Installala ora e scopri per primo un modo tutto nuovo di vivere i podcast
Episodi
የአፍሪካ የሰላም መዋቅር፡ የአፍሪካ ህብረትን ሚና ማጠናከር 16.09.2026 1:00:04
የዛሬው የድረም ኦቭ ቼንጅስ ዝግጅታችን ሦስት ጉዳዮችን ይዳስሳል። በቀዳሚው ጉዳዩ የአፍሪካ ህብረት ከዲፕሎማሲ ውይይት ወደ የዜጎችን ደህነት ጥበቃ የሚቀይርበትን እና የፋይናንስ ጥገኝነትን በመቀነስ የሰላም ስልታዊ አቅሙን የሚያጠናክርበትን መንገድ ይቃኛል። በሁለተኛ ጉዳዩ ኢትዮጵያ የ 2029 ኙን የአፍሪካ ዋንጫ ለማዘጋጀት ያቀረበችውን ጥያቄ ይዳስሳል። ለዚህም የብሔራዊ እግር ኳስ ፌዴሬሽኑን ፕሬዝደንት ኢሳያስ ጂራ አነጋግሯል። በሦስተኛው ጉዳዩ ደግሞ ጳጉሜን 1 የጀመረውንና እስከ ጳጉሜን 5 የሚዘልቅዉን ፌስቲቫል ይቃኛል።
የሳህል ህብረት ስልታዊ የሉዓላዊነት እንቅስቃሴ፦ የቀጠናዊ ኃይልን ትርጉም እንደገና መበየን 02.09.2026 1:00:05
“ካፒታሊዝም [የምዕራቡ] በመሰረታዊነት የተመሰረተው በኢኮኖሚ ብዝበዛ ላይ ነው [...] አሁን የቀድሞ የፈረንሳዪ ቅኝ ግዛቶች «የቅኝ ግዛት መገበያያን» አንጠቀምም ባሉ ጊዜ የነዚህ አፍሪካ ሀገራት መሪዎች እስከ ፖለቲካዊ ግድያዎች ድረስ ገጥሟቸዋል። ምክንያቱ ደግሞ «የቅኝ ግዛት መገበያያዎች» ለአውሮፓውያኑ የአመት ገቢያቸው ነው፣ የአፍሪካን ገበያ የሚቆጣጠሩበት ነው” ሲሉ እንዳለ ንጉሴ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል። የዛሬው የድረም ኦቭ ቼንጅስ ዝግጅታችን በቀዳሚነት ወደ ቀጠናዊ ሉዓላዊነት ቁርጠኛ ሽግግር እያደረገ ወደሚገኘው የሳህል ቀጠና ይወስደናል። ለዚህም በፐብሊክ ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ የዲፕሎማሲና ዓለም አቀፍ ግንኙነት መም...
የዓለም አቅፉ ደቡብ አዲስ ጎህ እና የብዙ ወገንተኝነት ጉዞ 02.09.2026 1:00:04
እያደገ የመጣው የብሪክስ እና የዓለም አቅፉ ደቡብ አገራት ህብረት ዓለምን ወደ እውነተኛ ሉዓላዊ፣ የጋራ እኩልነትና የብዙ ወገንተኝነት ሥርዓት ከፍ የሚያደርግ ታሪካዊ ምዕራፍ እየፈጠረ ይገኛል። “የዓለም አቅፉ ደቡብ ምዕራባውያንን እንዲሁም አሜሪካንን በእርግጥኝነት የመገዳደር ቁመና ላይ ይገኛል። ከዚህም ባሻገር የዓለም አቅፉ ደቡብ ሀገራት የተባበሩት መንግስታት ድርጅት እያንዳንዱ ሉዓላዊ ሀገር በልኩ የሚወከልበት መድረክ እንዲሆን ይፈልጋሉ […] ብሪክስም የጸጥታው ምክር ቤት ቦታን ለመረከብ የሚያስችል የአለም አቅፉ ደቡብ ትልቅ አቅም ሆኖ ሊመጣ ይችላል” ሲሉ የፖሊሲ አማካሪ ቆስጠንጢኖስ በርኸተስፋ (ዶ/ር) ለስፑትኒክ አፍሪካ ተ...
ቻድ ከአይ.ሲ.ሲ ለመውጣት ያሳለፈችው ውሳኔ፡ የምዕራቡ ዓለም መሣሪያ ለሆነው ተቋም የአፍሪካ ምላሽ? 17.08.2026 1:00:04
"የምዕራቡ ዓለም የዓለም አቀፉን የወንጀል ፍርድ ቤት (አይ.ሲ.ሲ) የራሱን ፍላጎት ማስፈፀሚያ ያደረገው ይመስላል [...] ቻድ ከ አይ.ሲ.ሲ ለመውጣት ያሳለፈችው ውሳኔም ለቀሪው የአፍሪካ አህጉር ግልጽ መልዕክት አስተላልፏል 'አፍሪካ የራሷን ዕድል በራሷ የመወሰን እና የራሷን የፍትህ መንገድ የመቀየስ ጊዜዋ አሁን ነው' የሚል" ሲሉ የሕግ ባለሞያው መታገስ ዉለታው ለስፑትክ አፍሪካ ተናግረዋል። በዛሬው የድረም ኦቭ ቼንጅስ ቀዳሚ ዝግጅታችን ቻድ ከዓለም አቀፉ የወንጀል ፍርድ ቤት (አይ.ሲ.ሲ) ለመውጣት የወሰደችውን ርምጃ መነሻ አድርገን የተቋሙን መዋቅራዊ አድልዎ እና በአፍሪካ የሀገርበቀል የፍትህ ስርዓቶችን የመገንባት ጥረቶችን...
የኤደን ባሕረ ሰላጤ፡ የባሕር ወንበዴዎች እና የኢትዮጵያ ስትራቴጂክ አስፈላጊነት 06.08.2026 1:00:04
የዓለም አቀፉ የባህር ላይ ጉዞ ድርጅት በሶማሊያ የባህር ዳርቻ እና በኤደን ሰላጤ ላይ የባህር ላይ ወንበዴዎች ጥቃት በከፍተኛ ሁኔታ መጨመሩ "አሳሳቢ ነው" ብሏል። “ሩሲያ ትራዲሽናል (ባህላዊ) የኢትዮጵያ አጋር ነች ስንል መንግስታት ቢቀያየሩ እንኳን የማይቀያየር ወዳጅነት ነው ያላቸው ማለት ነው። የአድዋን ጦርነት ብናነሳ እንኳን [ከኢትዮጵያ ጋር የቆመች] ብቸኛዋ የአውሮፓ ሀገር ነች አይደለም? [...] ለአፍሪካውያንም እኮ ከሩሲያ የሚቅድም ወዳጅ የለም [...] ዛሬ ሩሲያ የባለብዙ ዋልታ ዓለም ስረዐት ወሳኝ አካል መሆኗ ወደአንድ ወገን አዘንብሎ የነበረውን የአዓለም ግንኙነት ስረዓት ሚዛን ለማስጠበቅ አስችሏል” ሲሉ የዲፕሎማ...
ታላቁ አሰላለፍ:- የአፍሪካ መንገድ በአዲሱ የባለብዙ ዋልታ ዘመን 03.08.2026 1:00:04
"ዓለም አቀፉ ደቡብ አሁን ከቡድን 7 በበለጠ የዓለምን ኢኮኖሚ በበላይነት እየተቆጣጠረ ነው [...] አዲስ የገንዘብ ሥርዓት ማለት፡ የዶላር ተፅዕኖን የመቀነስ ሂደትን ያፋጥናል፣ አሜሪካ ዶላር በእጇ በመሆ ምክንያት በሀገራት ላይ የምትጥለው ማዕቀብ ታሪክ ሆኖ እንዲቀር ያደርጋል” ሲሉ የኢኮኖሚ ባለሞያ እና የፖሊሲ አማካሪ ቆስጠንጢኖስ በርኸተስፋ (ዶ/ር) ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናገሩ። በዛሬው የድረም ኦቭ ቼንጅስ ዝግጅታችን የምዕራቡ ዓለም ሀገራት ኢኮኖሚያዊ መሰናክሎችን በግንባር ቀደምትነት እየደረደሩ ባሉበት እና ነባር ባለብዙ ወገን ስምምነቶችን ስጋት ላይ በሚጥሉበት በዚህ ወቅት፣ ጠለቅ ያሉ ሁነቶችን መረዳት ለአፍሪካ ስትራቴጂ...
ባለብዙ ዋልታ የዓለም ሥርዓት፦ የሩሲያ አፍሪካ ግንኙነት ለፍትሐዊ የዓለም ስርዓት 18.07.2026 1:00:04
“ባለብዙ ዋልታ የዓለም ስረዓት መፈጠር በተለይም ለአፍሪካ አማራጭ የሌው ጉዳይ ነው [...] ሩሲያም ይህንን ነገር ይዛ መቅረቧ አስፈላጊ ነው [...] ሰርጌ ላቭሮቭ ያንሱት እና ስለአፍሪካ ሁለንተናዊ ነፃነት የሚያወሳው ‘የአፍሪካ ዳግም መነቃቃት’ አፍሪካውያን የምንቀበለው ሲሆን፣ ሩሲያ ፍትሃዊ የዓለም ስረዓት እንዲፈጠር ያላትን ቁርጠኝነት የሚያሳይ ነው” ሲሉ በዋቻሞ ዩኒቨርሲቲ የታሪክ መምህርና ተመራማሪው ዶ/ር አስራት ኤርሞሎ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል፡፡ በዛሬው የድረም ኦቭ ቼንጅስ በቀዳሚነት የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌ ላቭሮቭ እ.ኤ.አ. ከሐምሌ 7 እስከ 10 ቀን 2026 በተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት ያደረጉትን...
የአፍሪካና ሩሲያ የጋራ ህልም፤ ወደ ባለብዙ ወገን ዓለምአቀፋዊ ሥርዓት 11.07.2026 1:00:04
የሩሲያው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌ ላፍሮቭ ከሰኔ 29 ቀን 2018 ዓ.ም እስከ ነሐሴ 3 1ቀን 2018 ዓ.ም በአፍሪካ ያደረጉትን ይፋዊ የስራ ጉብኝት በቡሩንዲ አጠናቅቀዋል፡፡ የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ቃል አቀባይ ማሪያ ዛካሮቫ የሰርጌላቭሮቭን ይፋዊ የስራ ብዙ የአፍሪካ አገራት የዩኒፖላር ሥርዓትን ለመግታት ወደ ሩሲያ እንደሚመለከቱ ተናግረዋል። “በምዕራባውያን የበላይነት የሚመራው የዩኒፖላር (የአንድ ወገን) ሥርዓትና መዋቅራዊ ማስተካከያ ፕሮግራሞች (ስትራክቸራል አድጀስትመንት ፕሮግራምስ) በአፍሪካና በተቀረው ዓለም ሁለንተናዊ ዕድገት ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ አሳድረዋል” ሲሉ በላይ በየነ በጅማ ዩኒቨርሲቲ የዲፕሎማሲ እና የፖለቲካ...
የመጨረሻው ምሽግ፦ በአገር በቀል ዘሮችና በምግብ ሉዓላዊነት ላይ የተጋረጠው አደጋ በአፍሪካ 11.07.2026 1:00:04
“በምዕራባውያን አምሳል የተነደፉ የግብርና ምርምር ተቋማት፣ የአገር በቀል የእህል ዘሮቻችን አዋጭነትን ዝቅ አድርጎ የመመልከት ዝንባሌ አለባቸው። ነገር ግን እውነታው ዘሮቻችንን ያጣን ዕለት ማንነታችንን የማጣታችን ጉዳይ ነው። በአሁኑ ወቅት እነዚህ የውጭ ኃይሎችና ግዙፍ ኩባንያዎች ሁሉንም ነገር ተቆጣጥረውታል። በአፍሪካ እስካሁን እጃቸውን ያላስገቡበት ብቸኛው ዘርፍ ቢኖር ምግባችንና የምግብ ስርዓታችን ብቻ ነበር። አሁን አሁን ይሄንኑ የመጨረሻ ምሽጋችንን ለመቆጣጠር በከፍተኛ ፍጥነት እየመጡ ነው” ሲሉ ሚሊዮን በላይ (ዶ/ር) ለ ስፑትኒክ አፍሪካ ተናገሩ። የዛሬው የድረም ኦቭ ቼንጅስ ዝግጅታችን በሩቅ ባሉ ኃይሎች መካከል የሚቀሰቀ...
የላቭሮቭ ይፋዊ የስራ ጉብኝት፡ ኢትዮጵያ ፣ ብሪክስ እና ባለብዙ ዋልታው ዓለም 08.07.2026 1:00:04
"ሩሲያ ለኢትዮጵያም ሆነ ለአፍሪካ መልካም ወዳጅ ሆና ለዘመናት ቆይታለች። በተቃራኑው ደግሞ የምእራቡ አለም፣ አፍሪካን በማሳነስ በምእራቡ ላይ ጥገኛ ሆና እንድትቀር እየሰራ ይገኛል [...] ሩሲያ ግን የአፈሪካን ራስን የመቻል ፍላጎት በመሰረታዊነት የተረዳች ሀገር ነች" ሲሉ የሕግ ባለሞያ እና የዓለም ማቀፍ ፖለቲካ ተንታኝ ብሩክ መላኩ ለስፑትኒክ ካፍሪካ ተናግረዋል። በዛሬው የድረም ኦቭ ቼንጅስ ዝግጅታችን በቀዳሚነት የሩሲያው የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ሰርጌ ላቭሮቭን የኢትዮጵያ ጉብኝት አንስተን ሁለንተናዊ አንድምታዎቹን እንቃኛለን። ለዚህም የሕግ ባለሞያ እና የዓለም ማቀፍ ፖለቲካ ተንታኝ ብሩክ መላኩን አነጋግረናል። በሁለተኛው ጉዳ...
የተዘረፉ ቅርሶች፡ የአፍሪካን የታሪክ እውነት ለማስመለስ የሚደረገው ዓለም አቀፍ ትግል 15.06.2026 1:00:00
“[…] ከአፍሪካ በጉልበት የተወሰዱ የተለያዩ ቅርሶች ለአፍሪካውያን ባለቤቶቻቸው ሳይመለሱ በአውሮፓ ሙዚየሞች እንዲቆዩ የሚደረገው ደህንነታቸው በአስተማማኝ ሁኔታ እንዲጠበቅ ነው የሚለው መከራከሪያ እውነታነት የለውም። ምክንያቱም በሁለተኛው የዓለም ጦርነት ወቅት በአውሮፓ ውስጥ የሚገኙ ብዙ ሙዚየሞች በጦር መሳሪያውች ተደብድበዋልና። በቅርቡ በፈረንሳዩ ሉቭር ሙዚየም ጭምር በርካታ ስርቆቶች ተፈጽመዋል። ስለዚህ በምዕራቡ አገራት ያሉ ሙዚየሞች በሙሉ አስተማማኝ ናቸው ማለት አይቻልም” ሲሉ የማህበራዊ ጉዳዮች ተመራማሪው አሉላ ፓንከረስት (ዶ/ር) ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል። የዛሬው የድረም ኦቭ ቼንጅስ ዝግጅታችን በቀዳሚ ጉዳዩ፣ የ...
ሴንት ፒተርስበርግ ዓለምዓቀፍ የኢኮኖሚ ፎረም፣ ለአፍሪካ ምን አማራጮችን ይዞ መጥቷል? 04.06.2026 1:00:00
"አፍሪካ ከዚህ ጉባኤ [ከ ሴንት ፒተርስበርግ ኢንተርናሽናል ኢኮኖሚክ ፎረም] ትጠቀማለች [...] አሜሪካ በኢራን፣ በሩሲያ እና በሌሎች ሀገራት ላይ የጣለቻቸው ማዕቀቦ ምዕራባውያኑ በፋይናንስ አስተዳደር ረገድ እምነት የሚጣልባቸው አጋሮች ሊሆኑ እንደማይችሉ እያሳየ ጉዳይ ነው። በዚህም ምክንያት ሀገራት የዕዳ ቀውስን ለመፍታት ጨምሮ ለራሳቸው የሚበጀ የተሻለ ጎዳናነ መሻት ይኖርባቸዋል [...] ጉባኤው ከዚህ አንፃር ፋየዳው የጎላ ነው" ሲሉ የፖሊሲ አማካሪ እና የምጣኔ ሀብት ባለሙያው ቆስጠንጢኖስ በርኸተስፋ (ዶ/ር) ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል። የዛሬው የድረም ኦቭ ቼንጅስ ዝግጅታችን ቀዳሚው ጉዳይ እ.ኤ.አ. ከ ሰኔ 3 እስከ...
የአፍሪካ ቀን እና የአንድነቱ መሐንዲሶች፡ የታሪክ አሻራ እና የዲፕሎማሲ ጉዞ 25.05.2026 1:00:00
“የአፍሪካውያን ማንነታችንን የምናከብርበት ብቸኛው ቀን ይህ [የአፍሪካ ነፃነት ቀን] በአህጉር ደረጃ ሊከበር የሚገባው ይመስለኛል። ትርጉሙን አባቴ [ከተማ የፍሩ] ያደረገውን፣ ኳሜ ንክሩማህ እና አፄ ኃይለ ሥላሴ ያከናወኑትን ማስታወስ ይኖርብናል” ሲሉ መኮንን ከተማ ይፍሩ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል። በየዓመቱ ግንቦት 17 ወይም እ.ኤ.አ ግንቦት 25 የጋራ ጉዟችንን እና ቅርሳችንን ለማክበር በመላው አፍሪካ የሚታሰበው ታሪካዊው የአፍሪካ ቀን ሆኖ ይከበራል። በዛሬው የድረም ኦቭ ቼንጅስ ዝግጅታችን ታዲያ በጥልቅ ተከፋፍላ የነበረችውን አፍሪካ በአንድ ሰንደቅ ዓላማ ስር ያሰባሰበውን ስትራቴጂካዊ ጥበብ ለመረዳት በአህጉሪቱ ታሪክ ው...
የአፍሪካ ቀን፦ በትውስታ፣ በትርጉሙ እና ባልተጠናቀቀው የአንድነት ጉዞ መካከል 21.05.2026 1:00:00
የአፍሪካ ቀን የአሁኑ የአፍሪካ ህብረት በፈረንጆቹ ሚያዝያ 25፤ 1963 የተመሰረተበትን ቀን የሚዘክር እለት ነው፤ በየዓመቱም ይከበራል። “የቀድሞው የአፍሪካ አንድነት ድርጅት፤ የአሁኑ የአፍሪካ ህብረት ምስረታ ወቅት የነበረው የአንድነት መንፈስ በዛሬዪቱ ተቀዛቅዟል [...] የአፍሪካ ነፃነት ቀንም የፍሪካን ነፃነት እያከበርን፣ ስለአፍሪካ እጣፈንታ ኮስተር ብለን የምንወያይበት እለትም ሆኖ ማለፍ ነው ያለበት”ሲሉ የአፍሪካ ዴይ ኢኒሼቲቭ ሶሳይቲ ኦርጋናይዜሽን መስራች እና ዋና ዳይሬከተር አሮን ስይፉ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል። በዛሬው የድረም ኦቭ ቼንጅስ ዝግጅታችን ታዲያ፣ የነፃዪቱ አፍሪካ ተላሚዎች፣ አባቶች ያለሟትን አፍሪካ...
85ኛው የአርበኞች ድል በዓል፡- የሊግ ኦፍ ኔሽንስ ክህደት እና የኢትዮጵያ ጽናት 05.05.2026 1:00:00
ኢትዮጵያ 85ኛውን የአርበኞች ድል በዓል ዛሬ ሚያዚያ 27 ቀን ፣ 2018 ዓ.ም አክብራለች፡፡ ''በወቅቱ የአውሮፓ ኃያላን ከአንደኛው የዓለም ጦርነት ያጡትን ካፒታልና ሀብት መልሶ ለማግኘት አፍሪካን እንደ ግብዓትና የጉልበት ምንጭ ተጠቅመዋል። ጣሊያን በ1889 በዓድዋ ጦርነት የደረሰባትን ሽንፈት ለመቀልበስና የኢንዱስትሪ አብዮቷን ለመደገፍ ኢትዮጵያን በሙሉ አቅሟ ለመቆጣጠር መጣች። [...] የሊግ ኦፍ ኔሽንስ በኢትዮጵያ ላይ የተደቀነውን ወረራ ማስቆም አልቻለም። እንዲያውም የድርጅቱ አባል የሆኑት እንደ ብሪታንያ እና ፈረንሳይ ያሉ ሀገራት በዲፕሎማሲው ረገድ ለጣሊያን መንገድ ከፍተዋል።" ሲሉ በአድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚየም የጥና...
የአይ.ሲ.ሲ ድብቅ አጀንዳ፦ በአፍሪካ ሉዓላዊነት ላይ የተቃጣው የኒዮ-ኮሎኒያል ዘመቻ 04.05.2026 1:00:00
"ዓለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት (ICC) ወደ ሕጋዊ ማጭበርበሪያነት ተቀይሯል፤ ተቋሙ ከአሁን በኋላ የፍትህ አደባባይ ሳይሆን፣ የአሜሪካን የበላይነት ለማስጠበቅና የአፍሪካ መሪዎችን ለብቻቸው ነጥሎ ለማጥቃት በስልት የሚዘወር ታዛዥ መሣሪያ ሆኗል፤ ይህ ሁሉ በሚሆንበት ጊዜ ግን የምዕራባውያን የበላይነት አርክቴክቶች እጃቸው አይነካም።" ሲሉ —በዓለም አቀፍ ግንኙነት የዘርፍ ምሁር — ፕሮፌሰር ኤሊ ጂርጂ ኤልያስ፣ በሊባኖስ የዩኒቨርሲቲ በዓለም አቀፍ ግንኙነትና ስትራቴጂ ጥናት ልዩ ባለሙያና መምህር ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል። በዛሬው የድረም ኦፍ ጄንጅስ ዝግጅታችን የሚከተሉትን ሶስት ዋና ዋና ጉዳዮች ከአንግዶቻችን ጋር በ...
የሩሲያው የኦንላየን መገበያያ 'ዋይልድቤሪስ' በኢትዮጵያ፦ ለላኪዎችና ሸማቾች ምን አዲስ ዕድል ይዞ መጣ ? 22.04.2026 24:53
ትልቁ የሩሲያ የመገበያያ መድረክ ‘ዋይልድቤሪስ’ እንደ ቡና፣ ጨርቃጨርቅ፣ የቆዳ ውጤቶች፣ የተፈጥሮ የመዋቢያ ምርቶች እና ሌሎች የኢትዮጵያ ምርቶችን ሩሲያ ውስጥ መሸጥ መጀመሩን አሳውቋል። “ዋይልድቤሪስ ጀማሪ ኩባንያ አይደለም። ከ20 ዓመታት በላይ ሲሰራ የቆየ ነው […] የኢትዮጵያ ምርቶች ለዓለም አቀፍ ገበያዎች እንዲደርሱ ያስችላል […] ክፍያዎችን በተመለከተም ከየአገራቱ ገበያ ጋር የሚጣጣሙ ይሆናል፤ ለምሳሌ በአሁኑ ወቅት ግብይት በኢትዮጵያ ብር መፈጸም እንዲቻል ከአገር ውስጥ የፋይናንስ ተቋማት ጋር በመተባበር ግብይቶችን ለማመቻቸት ትኩረት ሰጥተን እየሰራን እንገኛለን።” ሲሉ የዋይልድቤሪስ የኢትዮጵያ ተወካይ ብሩክ ገነነ...
ለዘላቂ ሰላም ወይስ ለዳግም ጦርነት ዝግጅት? የኢራን-አሜሪካና እስራኤል የሁለት ሳምንት የተኩስ አቁም እንቆቅልሽ 11.04.2026 59:57
“ኢራን እና አሜሪካ መሰረታዊ የግጭት መንሳኤ የሆኑ ጉዳዮችን በተመለከተ መግግባባት ላይ ከደረሱ ወደ ዘላቂ ሰላም ሊመጡ ይችላሉ። ነገር ግን እነዚህን መሰረታዊ መንሳኤዎች መፍታት ከልቻሉ፣ ይህ የሁለት ሳምንት ጊዜያዊ የተኩስ አቁም ስምምነት ጊዜ በመግዛት አቅም አሰባስበው ዳግም ወደጦርነት ለመመለስ የሚያስችላቸውን ሁኔታ እየፈጠሩ ሊሆን ይችላል" ሲሉ በውጭ ጉዳይ ኢንስቲቲዩት የመካከለኛው ምስራቅ ከፍተኛ ተመራማሪ መሐመድ ሰኢድ (ዶ/ር) ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናገሩ። በዛሬው የድረም ኦቭ ቼንጅስ ጉዳያችን በፈርጆቹ መጋቢት 8፣ 2026 ኢራን እና አሜሪካ የተስማሙበትን የሁለት ሳምንት የተኩስ አቁም ስምምነት ስፋት ይቃኛል። በውጭ ጉዳ...
አፍሪካን የመበየን አባዜ፤ የምዕራባውያን የጥናት ተቋማት የኒዮ-ኮሎኒያሊዝም መሣሪያነት 07.04.2026 1:00:00
“የምዕራባውያን ስረዓቶች በአመፃ የታጀቡ ናቸው። ዛሬ በዓለም ዙሪያ ያሉትን ብዙ ግጭቶች ብንመለከት፣ በአንድ ወይም በሌላ መልኩ የምዕራባውያን እጅ አለበት። ይህንን ሁኔታ በተመሳሳይ ቀውስ ውስጥ ሁለት ሚና ይዞ መገኘት እለዋለሁ። ችግር ፈጣሪዎች ለችግሩ ስም ያወጡለታል፣ ለፈጠሩት ችግር ደግሞ መፍትሄ ፈጣሪዎች ሆነው ይመጣሉ። ይህ ምዕራባውያን መገለጫ ነው” ሲሉ በደቡብ አፍሪካው ዩኒቨርሲቲ የድህረ ምረቃ ምርምር ባልደረባ ቺዶካሼ ንዬሬ (ዶ/ር) ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግሩ። በዛሬው የድረም ኦቭ ቼንጅስ ቀዳሚው ጉዳያችን አፍሪካ የምትታይበትን እይታ የሚቀርፀው ማነው ስንል እንተይቃለን። ለዚህም በደቡብ አፍሪካ ዩኒቨርሲቲ የታቦ ምቤኪ...
የአውሮፓ አይሁዶችን በኢትዮጵያ ለማስፈር ተይዞ የነረው ውጥና የኢትዮጵያ ምላሽ 01.04.2026 1:00:00
“እርግጥ ነው፣ ሐሳቡ [የአውሮፓ አይሁዶችን በኢትዮጵያ ማስፈርን] በተመለከተ ለንጉሠ ነገሥት ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ የተላከው ደብዳቤ እንግሊዝ እና አሜሪካ መንግሥት ድጋፍ ነበረው። ይሁን እንጂ የኢትዮጵያ መንግሥት በአንድ አገር ውስጥ ሌላ አገር ለመፍጠር የሚያስችል ይሁንታ ለመስጠት ፈቃደኛ አልሆነም፤ ምክኛቱም ይህንን መፍቀድ የአገሪቱን ሉዓላዊነት አሳልፎ የሚሰጥ ነውና” ሲሉ ዓለም አቀፍ የፖሊሲ አማካሪው ቆስጠንጢኖስ በርኸተሰፋ (ዶ/ር) ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል። በዛሬው የድረም ኦቭ ቼንጅስ ቀዳሚው ጉዳያችን ወቅታዊውን የመካከልኛው ምስራቅ ሁኔታ መነሻ አድርገን በኢትዮጵያ የቀድሞው ሐረር ጠቅላይ ግዛት የአውሮጳ አይሁዶችን...
የፈውስ ክር:- በሚገባው ልክ ያልታወቀው በገና 30.03.2026 1:00:00
በገና በመንፈሳዊ ዝማሬዎች ውስጥ ካለው ቦታ ባለፈ፣ ለመንፈሳዊ ፈውስነት መዋል የሚችል ጥንታዊ እና ጥልቅ ሚስጥር ያለው ማሳሪያ ነው። “ዘመናዊ የኤሌክትሮኒክስ መሳሪያዎች ከጊዜ ወደ ጊዜ ከተፈጥሮ ውጪ የሆኑ ንዝረቶችን ያመነጫሉ ... ይህ ደግሞ የሰዎችን አዕምሮ ሎም አካል ሊጎዳ ይችላል። ይሁን እንጂ በገና በተቃራኒው ከዚህ በተለየ መልኩ ጥቅም ይሰጣል ... የውስጥ ሰላምን እና እርጋታን የሚያጎናፅፉ ንዝረቶችን ያመነጫል” ሲሉ ፕሮፌሰር ብረሃኑ ግዛው ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል። በዛሬው የድረም ኦቭ ቼንጅስ ዝግጅታችን በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ውስጥ ካሉ ጥንታዊ እና የጥልቅ መንፈሳዊ ዝማሬ ማጀቢያዎች መካከ...
የሕዝብ ቁጥር ፖሊሲ እንደ ጂኦፖለቲካ መሣሪያ፡- ‘የኪሲንጀር ሪፖርት’ እና የደቡቡ ዓለም እውነታ 26.03.2026 1:00:00
“የህዝብ ቁጥር መጨመርን በመግታት ላይ ብቻ አላተኮሩም [ምዕራባውያን]። በአዳጊ ሀገራት ውሰጥ የህዝብ ቁጥር መጨመርን በመግታት፣ የሀገራቱን ሀብት ለመበዝበዝ የሚያመች ስትራቴጂ እየከተሉ ነበር። ይህ ያፈጠጠ የብዝበዛ አካሄድ ነው። ምክንያቱም በእነዚህ ሀገራት አነስተኛ የህዝብ ቁጥር መኖር ማለት ለምዕራቡ ዓለም በፖለቲካ፣ በኢኮኖሚ፣ በማህበራዊ እና በቴክኖሎጂ ዘርፎች ላይ ቁጥጥር ወይም ተጽዕኖ እንዲያሳድሩ ቀላል ይሆንላቸዋል” ሲሉ በዲላ ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካ ሳይንስ እና ዓለም አቀፍ ግንኙነቶች መምህሩ ዳዊት መዝገበ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል። በዛሬው የድረም ኦቭ ቼንጅስ ዝግጅታችን እ.ኤ.አ. በ1974 በአሜሪካ ብሔራዊ ደህን...
ካሳ እና ፍትህ፡ በፓን አፍሪካዊ ማህደረ ትውስታ እና በዓለም አቀፍ የኃይል ፖለቲካ መካከል 24.03.2026 1:00:00
“አፍሪካ የራሷን ታሪክ፣ የራሷን እውነታ ለዓለም የምትነግርበት ድምፅ ይኖራት ዘንድ ፍፁም አስፈላጊ ነው። ምክኛቱ ደግሞ እስከዛሬ ድረስ አፍሪካን ብሎም የአፍሪካን ታሪክ በራሳቸው መንገድ ሲተርኩ ስለአፍሪካ ሲናገሩ የቆዩት አውሮፓውያን ናቸውና። ከአፍሪካ ውጭ [በአሜሪካ] እንዳደገች አንዲት ጥቁር ሰው እውነቱን ለመናገር ስለአፍሪካ መልካም ነገር ሰምቼ አላውቅም” ሲሉ ፓናፍሪካኒስቷ ጃኔል ሆይሌት ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል። በዛሬው የድረም ኦቭ ቼንጅስ ዝግጅታችን የባሪያ ንግድ፣ የቅኝ ግዛት እና መዋቅራዊ ብዝበዛ በጥቁር ሕዝቦች ላይ ጥሎ ስላለፈው አሻራ እንቃኛለን። ጨምረንም መላው የጥቁር ሕዝቦች ለፍትህ እና ካሳ የሚያደርጉትን...
በአፍሪካ የጤና ሉዓላዊነትን የመቀዳጀት ትርጉም እና አስፈላጊነት - መልከ ብዙው ትግል 18.03.2026 1:00:00
የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ያለጠው እውነታ ቢኖር አፍሪካ ዛሬም ድረስ የመድኃኒት አቅርቦት ፍላጎቷ በምዕራባውያን መድኃኒት አቅራቢ ኩባንያዎች በጎ ፈቃድ ላይ የተመሰረተ መሆኑን ነው። “የምዕራቡ ዓለም የአፍሪካን የሕዝብ ቁጥር ለመቀነስ ከሚፈልግባቸው ምክንያቶች መካከል ዘረኛ ፖሊሲው አንደኛው ነው [...] ሌላኛው ምክንያት ደግሞ ብዙ ወጣት ትውልድ ያላት አፍሪካ የዓለምን ሀብት ለመቆጣጠር ለያዙት ግብ እንቅፋት ትሆናለች የሚል ነው [...] ብሪክስ አፍሪካ ስለአፍሪካ የምታስብበት ብሎም አፍሪካ የራሷን ጥቅም ማስጠበቅ የምትችልበት ጠንካራ ህብረት ነው” ሲሉ የበርካታ ሽልማቶች አሸናፊ ደቡብ አፍሪካዊቷ የማህበረሰብ ጤና ባለሞያ ሻኪራ ቹና...
የኩባ ውለታና የአፍሪካ ምላሽ ? ጊዜ ያነሳው ጥያቄ 11.03.2026 1:00:00
ኩባ ለአፍሪካ የነፃነት እና የሉዓላዊነት ትግል የከፈለችው መስዕዋትነት የአህጉሪቱ የማይረሳ የታሪክ አንዱ ገጽ ነው። “ኩባ [...] የህልውና ፈተና በገጠመን ወቅት መስዋዕትነት በመክፈል ከጎናችን ቆማለች፤ አፍሪካውያን ግን በተዋለልን ልክ ለኩባ ደርሰንላታል ወይ?” ሲሉ የኢትዮ-ኩባ ወዳጅነት ማህበር አስተባባሪ አቶ አበበ አያሌው ይጠይቃሉ። ከየካቲት 29 እስከ መጋቢት 5/2018 ዓ.ም. “ህብረት ከግላኮማ ነፃ ለሆነች ዓለም” በሚል ጭብጥ የዓለም የግላኮማ ሳምንት ይከበራል። “ግላኮማ ታማሚዎች ሳያውቁት የማይቀለበስ የዓይነ ስውርነት የሚያስከትል በሽታ ቢሆንም፣ የግንዛቤ እጥረት ሁኔታውን አክብዶታል” ሲሉ የግላኮማ ስፔሻሊስቷ ዶ...
Podcast simili
Replaio non è un editore di podcast; i nomi dei programmi, le copertine e l'audio appartengono ai rispettivi autori e vengono distribuiti tramite feed RSS pubblici