DW | Amharic - News
News, Analysis and Service from Germany and Europe - in 30 Languages
Husk at besøge podcastens hjemmeside og støtte skaberen: www.dw.com
Hvor kan du lytte?
Podcasts i appen Replaio Radio Kommer snartPodcasts kommer snart til appen. Installer nu, og vær den første til at se en helt ny tilgang til podcasts
Episoder
በኢትዮጵያ መገናኛ ዘዴዎች ላይ የበረታው ጫና፥ ምሕዳሩ ወዴት እያመራ ነው? 15.11.2026
ኢትዮጵያ ውስጥ በመገናኛ አውታሮች ላይ የሚደርሰው ጫና ከጊዜ ወደ ጊዜ እጅግ እየበረታ ነው ። ከሰሞኑ እንኳን ሦስት ዐሥርተ ዓመታት ግድም ያስቆጠረው ሪፖርተር ጋዜጣ «ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ጥቅም ጋር የሚጻረሩ ይዘቶችን አሠራጭቷል» በሚል በኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን ላልተወሰነ ጊዜ ሙሉ ለሙሉ መታገዱ ተሰምቷል ። ወዴት እያመራ ነው?
ከሀሰት ዜናዎች ጋር የአፍሪካ ትግል 14.11.2026
አፍሪቃ ከሀሰት ዜናዎች ጋር ትግል ጀምራለች። ለመሆኑ እውነትን የሚወስነው ማን ነው? ከጋና እስከ ሞዛምቢክ አፍሪካውያን ከሀሰት ዜናዎች ጋር የሚያደርጉት ትግል ተስፋፍቷል።
በጀት ያጠረው የሱዳን ሰብአዊ ቀውስ 14.11.2026
የዓለም አቀፉ የስደተኞች ድርጅት (IOM) እና የተባበሩት መንግሥታት የስደተኞች ከፍተኛ ኮሚሽነር (UNHCR) የድረሱልን ጥሪ እያሰሙ ነው። ምክንያቱም ለሱዳን የተመደቡት የአስቸኳይ ጊዜ መጠለያዎች እና መሰረታዊ የምግብ አቅርቦት በገንዘብ እጥረት በጣም ቀንሷል።
ዶክተር ነገደ ጎብዜ በ83 አመታቸው ህዳር 3 ቀን 2019 ሀሙስ ሌሊት ለአርብ አጥቢያ ብራሰልስ ውስጥ ህይወታቸው ማለፉ ተሰምቷል 14.11.2026
በኢትዮጵያ የፖለቲካ ታሪክ ውስጥ ከቀደምቶች አንዱ የነበሩት ፖለቲከኛ ዶክተር ነገደ ጎበዜ አረፉ
ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ ለጦርነቱ ህወሓት እና የኤርትራ መንግስታትን ተጠያቂ ማድረጋቸው 14.11.2026
የኢትዮጵያ የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ በሰሜን ኢትዮጵያ በተለያዩ ምዕራፎች ለተከፈቱና አሁንም እየተካሄደ ላለው አውዳሚ ጦርነት ሕዝባዊ ወያኔ ሓርነት ግትራይ (ህወሓትን) ነቀፉ፡፡
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ያቀረበችው ጥሪ 14.11.2026
የቤተክርስቲኗ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ከሰሞኑ አዲስ አበባ ውስጥ ከአሜሪካ አምባሳደር ኤርቪን ማሲንጋ ጋር ባደረጉት ውይይት “የአርሲ ችግር ዘላቂ መፍትሔ ባለማግኘቱ ዛሬም ሥጋቶች እንዳሉ ይሰማኛል” ሲሉ ተናግረዋል፡
የማይክሮሶፍት አገልግሎት መታወክ እያነጋገረ ነዉ 13.11.2026
የዩናይትድ ስቴትስሱ ግዙፍ የኮምፒዉተር ኩባንያ ማይክሮሶፍት የሚሰጣቸዉ የኢንተርኔት አገልግሎቶች ከሐሙስ ኅዳር 3 ቀን፤ ጀምሮ መታጎሎ የዓለምን የዓምደ መረብ እስትንፋስ ቀጥ አድርጎት ነዉ ያረፈደዉ። የዓምደ መረብ ሥራና እንቅስቃሴዉ በመዘበራረዙ፤ የመላዉ ዓለምን የዓምደ መረብ ሥራና እንቅስቃሴም ተዘበራርቋል።
በሞያለው ግጭት የተባባሰው ሰብዓዊ ቀውስ 13.11.2026
በደቡባዊ የኢትዮጵያ ድንበር ከተማ ሞያሌ የቀጠለውን ግጭት ሸሽተው ወደ ኬንያ የሚገቡ ፍልሰተኞች ቁትር እየጨመረ ነዉ። በአሁኑ ወቅት ለተፈናቃዮች በቂ ምግብ እና መጠለያ ለማቅረብ ፈታኝ እየሆነ መምጣቱን የኬንያ መርሳ ቤት ግዛትና ዓለም አቀፉ የፍልሰተኞች ድርጅት (IOM) አመልክተዋል። የአካባቢዉ ቀዉስ ”እጅግ አሳሳቢ” ተብሏል።
በራያ አላማጣ ከተማ ከ2013 ዓ.ም. በኋላ የተቀጠሩ ሰራተኞች ወደሥራ እንዳይመለሱ መከልከላቸውን ተሰማ 13.11.2026
በራያ ኡላማጣ ከተማ ከ2013 ዓ.ም በኋላ የተቀጠሩ ሰራተኞች ደሞዛቸው በአማራ ክልል እየተከፈለ ቢሆንም፣ አዲሱ የትግራይ ባላደራ አስተዳደር በቀድሞ የስራ ቦታቸው እንዳይሠሩ እንደከለከላቸው ተናገሩ። የራያ ላማጣና አካባቢው አሁን በትግራይ ክልል የባላደራ አስተዳደር ስር ቢሆንም ከ2013 ዓ.ም በኋላ ለተቀጠሩ የአማራ ክልል ደሞዝ እየከፈለ ነዉ።
ኢትዮጵያ እና ሱዳን ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት መሻከር 13.11.2026
የዲፕሎማሲያዊ ግንኙነታቸው እየሻከረ የመጣው ኢትዮጵያ እና ሱዳን አንዳቸው ሌላውን በውስጥ ጉዳያቸው ጣልቃ ገብነት ሲካሰሱ ቆይተዋል፡፡ ኢትየጵያ ሱዳን ከኢትየጵያ ታቂጣቂዎችን ከብሔራዊ ጦሩ ጋር በመወገን እንዲዋጉ ከማድረግ በተጨማሪ በምዕራብ በኩል ኢትዮጵያን እንዲወጉ የጦር መሳሪያና የፋይናንስ ድጋፍ እንደሚታደረግ ከዚህ ቀደም አሳውቃለች፡፡
አሳሳቢዉ የመቀሌ ከተማ ጸጥታ ስጋት 13.11.2026
በትግራይ ክልል በተለይም በክልሉ መዲና መቀሌ ይስተዋላሉ የሚባሉትን የጸጥታ ችግሮች ከመሰረቱ ለመቅረፍ የክልሉ ጊዜያዊ መስተዳድር የጦር መሳሪያ አሰሳን ጨምሮ የተለያዩ ስራዎችን እየሰራ መሆኑን ይገልጻል፡፡ ሆኖም የከተማው ነዋሪዎች የጸጥታ ተግዳሮቱ አሁንም በሚፈልጉት መጠን ተሻሽሎ አለማግኘታቸውን ያመለክታሉ፡፡
ዶይቼ ቬለ በኪረሙ ወረዳም ሆነ በአቤዶንጎሮ ወረዳ ሰላማዊ ዜጎቹ ላይ ደርሷል ስለተባለው የሲቪሎች ጥቃትና ጉዳት ከመንግስት አካላትም ሆነ ከሌላ ገለልተኛ አካላት ለማጣራት ያደረገው ጥረት አልሰመረም፡፡ 12.11.2026
በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ኦሮሚያ ዞን ኪረሙ ወረዳ ጉዲና ጅሬኛ ቀበሌ ባሳለፍነው ረቡዕ ጥቅምት 25 ቀን 2019 ዓ.ም. ታጣቂዎች በንጹሃን ማህበረሰብ ላይ ባደረሱት ጥቃት የበርካታ ሰዎች ሕይወት በማለፉ ከፍተኛ የንብረት ውድመትም በመድረሱ አከባቢው አሁንም የተረጋጋ አይመስልም፡፡
በጀጎል ቅርሶች ላይ ስጋት የደቀነዉ የኮሪደር ልማት 12.11.2026
በሐረር ከተማ በዓለም ቅርስ መዝገብ ላይ የሰፈረዉ፤ ጀጎል እየተከናወነ ባለዉ የኮሪደር ልማት ሰበብ በግንቡ ዉስጥ የሚገኙት ታሪካዊ ቤቶች መፍረሳቸዉ እየተነገረ ነዉ። የአካባቢዉ ነዋሪዎች እንደተናገሩት ከትዉልድ ትዉልድ፤ በቅብብሎሽ በታሪካዊ ቤቶች ዉስጥ ሲኖሩ የነበሩ ዜጎችም ተፈናቅለዋል። አሁን ቦታዉ ባለሃብት እንዲገዛዉ ጥሪ እየቀረበ ነዉ።
በጃናሞራና ጠለምት ደጃች ሜዳ ወረዳዎች ከተከሰተው ድርቅ ጋር ተያይዞ ምላሽ እንዲሰጡን ለሰሜን ጎንደር ዞን አደጋ ስጋትና ስራ አመራር ኮሚሽን ተጠሪ ጽህፈት ቤት ሃላፊ ስልክ ብንደውልም መልእክት ብንልክም ምላሽ ማግኘት አልቻልንም። 12.11.2026
በጠለምት ደጃች ሜዳ ወረዳ መረው ገብርኤል ቀበሌ ነዋሪ የሆኑት አቶ ጌጡ ጥሩሰውም ድርቁ የከፋ መሆኑን ገልጸው የሚሞት ሰውም እንዳለ ይናገራሉ። የረን ቀበሌ አስተዳዳሪ አቶ እሸቴ በረከተ አብም በቀበሌው ምንም እንኳ የሞተ ሰው ባይኖርም በረሃብ ምክንያት ግን የታመሙ ሰዎች አሉ ብለዋል።
ሁለቱ ሀገራት የኢትዮጵያ አማጺ ቡድኖችን ከመደገፍ ባለፈ በማን እንደሆነ በግልጽ ባይጠቅሱትም በኢትዮጵያ ግዛት ውስጥ "በተደጋጋሚ የድሮን ጥቃቶች መፈጸማቸውን" ለልዩ መልዕክተኛው ማብራሪያ መስጠታቸውንም አቶ ጌታቸው ተናግረዋል። 12.11.2026
ፕሬዝዳንት ኢሳያስ እና ጄኔራል አልቡርሃን "በኢትዮጵያ የሚንቀሳቀሱ አፍራሽ ኃይሎችን ለማስታጠቅ ለማደራጀትና ድጋፍ ለመስጠት እየሰሩ ነው ያሉትን እንዲሁም በኢትዮጵያ ግዛት ውስጥ በተደጋጋሚ የድሮን ጥቃቶችን መፈጸማቸውን አስመልክቶ" ዝርዝር ማብራሪያ መስጠታቸውን የገለፁት አቶ ጌታቸው፣ የድሮን ጥቃቶቹ መቼ፣ የትና በማን እንደተፈጸሙ አልገለጹም።
የደንጊ በሽታ በክልሉ ለመጀመሪያ ጊዜ መታየቱ የተገለጸው የአምስት ተጠርጠሪ ሰዎች ናሙና ወደ ኢትዮጵያ ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ተልኮ በምርመራ ከተረጋጋጠ በኃላ ህዳር 1/2019 ዓ.ም ነበር 12.11.2026
በመተከል ዞን ጉባ ወረዳ በ5 ሰዎች ላይ የደንጊ በሽታ ከተከሰተ በኋላ የደንጊ ተኅዋሲ በሽታን ለመከላከል ቅድመ ዝግጅት እያደረገ መሆኑን የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ጤና ቢሮ አስታውቋል።፡ የቢሮው የፕሮግራም ዘርፍ ምክትል ኃላፊ፣ ተመሳሳይ የበሽታው ምልክቶች በበርካታ ሰዎች ላይ መታየቱን ስርጭቱም በወረርሽኝ ደረጃ የሚገልጽ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡
የአፍሪካ ቀንድ ጉዳዮች ተንታኝ ዶ/ር እንጋላ ቾሜ እንደሚሉት፣ ግብፅና አጋሮቿ እንደዚህ አይነት አሰተያያቶችን መሰንዘርና መግለጫዎችን ማውጣት የጀመሩት በተለይ እንደ ጎርጎሮሳውያኑ የዘመን አቆጣጠር ከ2024 ዓ.ም. ጀመሮ ነው። 12.11.2026
ሊቢያ ከተዘጋጀው የሳህል- ሰሃራ ሀገራት ማኀበረሰብ የስራ አስፈጻሚ ምክር ቤት ሰብሰባ ጎን ለጎን በተካሄደው ውይይት፣ የቀይ ባሕር ደህንነትና አስተዳደር ጉዳይ የባሕሩ ቀጥተኛ አጎራባች ሀገራት ብቻ መኾኑን የግብፅ፣ የሶማሊያና የጂቡቲ ሚኒሰትሮች በድጋሚ አስታውቀዋል።ኢትዮጵያ በበኩሏየቀይ ባሕር ደህንነት ለጥቂት ሀገራት ብቻ የሚተው አይደለም ብላለች
የኢትዮጵያ የአገር ውስጥ ምርት ወደ 24 ትሪሊዮን ብር ሲከለስ የታክስ ነገር በዐይነ ቁራኛ የሚታይ ሆኗል 11.11.2026
በ2018 መንግሥት የሚሰበስበው ታክስ ከአገር ውስጥ ምርት (GDP) ያለው ምጣኔ ወደ 9.5 በመቶ ከፍ ይላል ተብሎ ይጠበቅ ነበር። የ2017 ኢኮኖሚ በወረቀት ላይ ተከልሶ 24 ትሪሊዮን ብር ሲተመን ምጣኔው ከ5% በታች ወርዷል። ይኸ በመንግሥት ዘንድ “ሕብረተሰቡ በቂ የሆነ ታክስ እየከፈለ አይደለም” የሚል ዕምነት እንዳያሳድር የሚያሰጋ ነው
የትግራይ ባለአደራ አስተዳደር ትናንት ስለሰጠው ሹመት የሕግ ባለሙያ አስተያየት 11.11.2026
የትግራይ ባለአደራ አስተዳደር ትግራይ እና አማራ ክልሎች በይገባኛል ጥያቄ ለሚወዛገቡበት እና «አከራካሪ» በሚል ለሚገለፅ አካባቢ አስተባባሪ ሾመ። የስድስት ወራት የሥራ ጊዜ ተሰጥቶት በፌዴራል መንግሥት የተቋቋመው የትግራይ ክልል ባለአደራ አስተዳደር ዋና አስፈጻሚ አሰፋ አብርሓ፣ አቶ ዳንኤል ነጋሽን የምዕራብ ትግራይ አስተባባሪ አድርገው ሾመዋል።
የኤአይ የዳታ ማዕከሎች ግንባታ በአሜሪካ እና በአውሮፓ ለምን ተቃውሞ ገጠማቸው? 11.11.2026
የሰው ሠራሽ አስተውሎት (AI) ቴክኖሎጂ በፍጥነት እያደገ በመምጣቱ በአሜሪካና በአውሮፓ ግዙፍ የዳታ ማዕከላት ግንባታ እየተስፋፋ ነው። እነዚህ ማዕከላት የAI ሥርዓቶችን ለማሠልጠን የሚያስፈልጉ ከፍተኛ የኮምፒውተር አቅምና የመረጃ ማከማቻ ቋት ሆነው ያገለግላሉ።ሆኖም የእነዚህ ማዕከላት መስፋፋት በአካባቢው ነዋሪዎች ዘንድ ተቃውሞ እያስከተለ ነው።
የሩሲያ፤ ዩክሬንና አሜሪካ የሦስትዮሽ የሰላም ውይይት በአቡዳቢ 11.11.2026
በአሜሪካ አደራዳሪነት በተባበሩት አረብ ኤሚሪትስ አቡዳቢ ከተማ ከትናንት ጀምሮ ለሁለት ቀናት ሲካሄድ የቆየው የሩሲያና ዩክሬን የሰላም ድርድር ተጠናቀቀ።
በአርሲ ጥቃቶች የተፈናቀሉ ዜጎች የእርዳታ ጥያቄ 11.11.2026
በኦሮሚያ ክልል ደቡብ ምሥራቅ ዞን በተለያዩ ወረዳዎች በተለያዩ ጊዜያት የተፈናቀሉ ዜጎች በእርዳታ እጦት መቸገራቸውን አመለከቱ።
ሰሀላ ወረዳ፤ ድርቅ፤ ረሀብና ወባ ወረርሽኝ ያስከተሉት የከፋ ሰብአዊ ቀውስ 11.11.2026
በአማራ ክልል የዋግምራ ብሔረሰብ አስተዳደር ዞን ሰሀላ ወረዳ የደረሰው ከባድ ድርቅና የወባ በሽታ መዛመት ከረሀብ ጋር ተዳምሮ ነዋሪዎችን ለከፋ ሰብአዊ ቀውስና ለሞት እየዳረጋቸው መሆኑ ተገለጸ።
በጅማ በተፈጠረው ግጭት የሰው ሕይወት ማለፉ 11.11.2026
በኦሮሚያ ክልል ደቡብ ምዕራብ ዞን ጅማ ከተማ ቦሬ ተብሎ በሚታወቅ ቀበሌ አካባቢ ባለፉት ሁለት ቀናት በአካባቢው ማኅበረሰብ እና የአካባቢው የጸጥታ አካላት መካከል በተፈጠረው አለመግባብት የሰው ሕይወት ማለፉ ተነገረ።
በ2013 ዓ.ም. ወደትውልድ አካባቢያቸው ፖለቲካ የተመለሱት አይግነር በግዛቲቱ ጠ/ሚ ኽርስት ዜሆፈር የስልጣን ዘመን በባቫርያ የኤኮኖሚ ሚኒስትር ነበሩ። በወቅቱም ዜሆፈር አይግነር እርሳቸውን እንዲተኩ ሙከራ አድርገው ነበር። 10.11.2026
የጀርመን መራኄ መንግሥት ፍሪድሪሽ ሜርስ የክርስቲያን ሶሻል ኅብረት ፓርቲ ፖለቲከኛ ኢልዘ አይግነርን ትናንት በይፋ ለሀገሪቱ ፕሬዝዳንትነት በእጩነት አቅርበዋቸዋል። የሶሻል ዴሞክራቶቹ ፓርቲም በአይግነር እጩነት ሲስማማ ከአረንጓዴዎቹ ፓርቲም ይሁንታ አግኝተዋል። አማራጭ ለጀርመን ግን የአይግነርን ለፕሬዝዳትነት መታጨት ተቃውሟል።
Replaio er ikke podcastudgiver; programmernes navne, coverbilleder og lyd tilhører deres ophavsmænd og distribueres via offentlige RSS-feeds.