Zelalem Demissie

Drum of Changes

Society EN ↓ Epizody: 66

From the heart of ancient kingdoms to the pulse of modern cities, a new rhythm echoes across the continent. Africa is rising — a formidable force shaping the world’s future. For generations, Africa has been the most spoken about, yet the least heard. But today, the call is unmistakable: Africa demands its rightful place at the table of global power. Welcome to 'Drum of Changes' — a program dedicated to the stories that matter to Africa. Here, we explore culture, history, art, politics, the economy, and more, all through the lens of Africa itself. 'Drum of Changes' brings you the voices of tran...

Určitě navštivte web podcastu a podpořte jeho tvůrce: drum-of-changes.mave.digital

Autor

Zelalem Demissie

Kategorie

Society

Nejnovější epizoda

3. říj 2026

Kde poslouchat?

Podcasty v aplikaci Replaio Radio Už brzy

Podcasty míří do aplikace už brzy. Nainstaluj si ji teď a jako první uvidíš úplně nový pohled na podcasty

Stáhnout z Google Play Nainstaluj zdarma Android téměř 10 mil. stažení · hodnocení 4,8 iOS už brzy

Epizody

ስለአዲሱ የዓለም ሥርዓት ከቫልዳይ የተሰማው መልዕክት 03.10.2026

የዛሬው የድራም ኦቭ ቼንጅስ ዝግጅታችን፤ ፕሬዚዳንት ቭላዲሚር ፑቲን በቫልዳይ የውይይት ክለብ 2026 የመዝጊያ ስነ-ሰርዓት ላይ ተገኝተው ያደረጉትን ንግግር፣ ከባለብዙ ዋልታ የዓለም ሥርዓት እና ለአፍሪካ ከሚኖረው ፋይዳ አንፃር የምንቃኝበት ነው። ለዚህም በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የሰላም እና ደህንነት ተቋም መምህር እና ተመራማሪ ከሆኑት ሙሉጌታ አየለ (ዶ/ር) ጋር አውርተናል።

የአፍሪካ የሰላም ጎዳና፦ በባህላዊ ተቋማት የሚደረግ ግጭት መከላከል 03.10.2026

በዛሬው የድራም ኦቭ ቼንጅስ ዝግጅታችን፤ አፍሪካ በአገርበቀል ተቋሞቿ አማካኝነት ግጭትን ለመከላከልና ሰላምን ለማስፈን የምታደርገውን ጥረት ይዳስሳል። ለዚህም ከደኅንነት ጥናት ኢንስቲትዩት ተመራማሪ ከሆኑት ከሙሳ ሱማሆሮ ጋር ቆይታ አድርገናል::

አፍሪካ እና ጊዜ፣ በማን ሰዓት ላይ ነን? 30.09.2026

በአፍሪካ የእጅ ሰዓት ከመግባቱ ከብዙ ዘመናት በፊት፣ ጊዜ የሚለካው በሜካኒካል ሰዓት ቁጥሮች ሳይሆን የተፈጥሮ ዑደቶችን በጠበቁ ክስተቶች ነበር።  “የአፍሪካ የጊዜ አቆጣጠር ከምዕራባውያን የጊዜ ጽንሰ-ሐሳብ ፈጽሞ የተለየ ነው። ይኸውም ጊዜ በማህበራዊና ባህላዊ መነጽር የሚታይ፣ መኖርና ሊለማመዱት የሚገባ ክስተት በመሆኑ፣ ባለፈውና በአሁኑ ጊዜ ውስጥ ባሳለፍናቸው ነገሮች ላይ ትርጉም ሰጥተን እንድንገነዘበው ያስችለናል” ሲሉ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የአፍሪካና እስያ ጥናቶች ማዕከል መስራች አባል ጌታቸው ካሳ (ዶ/ር)  ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል። በዛሬው ድራም ኦቭ ቼንጅስ ዝግጅታችን የአፍሪካን የጊዜ ጽንሰ-ሐሳብ ከዘመናዊው...

ከድምፅ እስከ ታሪክ፡ የግሎባል ደቡብ ሕዝቦችን የሚያስተሳስረው የቋንቋ ገመድ 29.09.2026

ቤጂንግ የውጭ ጥናት ዩኒቨርሲቲ አማርኛን ማስተማር ከጀመረ 14 ዓመታት ማስቆጠሩ፣ በቻይና የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ውስጥ የኢትዮጵያን ባህልና ቋንቋ በቀጥታ ለማስተዋወቅ ትልቅ ድልድይ ፈጥሯል። “ይህማ [ቋንቋ] በጣም ትልቅና የላቀ ሚና አለው። ቋንቋ በሁለት ሕዝቦችና በሁለት አገሮች መካከል እንደ ድልድይ የሚያገለግል ቁልፍ ጉዳይ ነው። ቻይናውያን አማርኛን ሲማሩም በኢትዮጵያ የሚካሄዱ የንግድ፣ የልማትና የዲፕሎማሲ ሥራዎችን በቀጥታ ለመረዳት ያስችላቸዋል” ሲሉ በቻይና የቤጂንግ የውጭ ጥናት ዩኒቨርሲቲ የአማርኛ መምህርትና አስተባባሪ ስንቅነሽ አጣለ (ዶ/ር) ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል። የዛሬው የድራም ኦቭ ቼንጅስ ዝግጅት ቋን...

ከአፍሪካ ወሰን ባሻገር፡ የስደት ፖሊሲዎችን ማን፣ ለምን ይቀርጻል? 29.09.2026

የአውሮፓ ሀገራት የስደት እና የድንበር ፖሊሲ ድንበራቸውን በራሳቸው አካባቢ ብቻ የሚገድብ ሳይሆን፣ ስደትን ከመነሻው እና ከመሸጋገሪያ ሀገራት ጀምሮ ሄዶ መቆጣጠር ላይ ያተኮረ ነው። “አውሮፓ ሀገራት የውጪ ድንበራቸውን ለመጠበቅ በሚያደርጉት ጥረት የስደት ቁጥጥር ፖሊሲያቸው በአፍሪካ መነሻ እና መሸጋገሪያ ሀገራት ውስጥ ዘልቆ በመግባት ስደትን ከምንጩ ለመቆጣጠር ላይ ያተኮረ ነው [...] አውሮፓውያን በስደት ቁጥጥር ሰበብም የአፍሪካውያን ፖሊሲዎች [የፍልሰት] ቀረፃ ሂደት ላይ ጫና ያሳድራሉ” ሲሉ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የሰብአዊ መብቶች ማዕከል ተባባሪ ፕሮፌሰር ሜሮን ዘለቅ (ዶ/ር) ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል።  በዛሬው የ...

የብሪክስ ንግድ፦ አዳዲስ ዕድሎች፣ አዳዲስ ገበያዎች 29.09.2026

የብሪክስ አባል አገራት እርስ በርሳቸው የሚያደርጉት የንግድ ልውውጥ መጠን ከሃያ ዓመታት በፊት ከነበረበት 84.2 ቢሊዮን ዶላር በብዙ እጥፍ አድጎ 1.17 ትሪሊዮን የአሜሪካን ዶላር ደርሷል። “የብሪክስ ኒው ዴቨሎፕመንት ባንክ የዶላር ጥገኝነትን በመቀነስ ዓለምን ወደ ባለብዙ ዋልታ ኢኮኖሚ እያሸጋገረ ነው [...] ኢትዮጵያም አባል መሆኗ [የብሪክስ] የንግድ ማዕቀፎችን ለማብዛት፣ ኢንቨስትመንትን ለመሳብ እና ቴክኖሎጂ ለማግኘት ትልቅ ዕድል ይፈጥርላታል” ሲሉ በአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ የቢዝነስና ማኔጅመንት የምጣኔ ሀብት መምህርና ተመራማሪ ዱጋሳ ሙሉጌታ (ዶ/ር) ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል።  የዛሬው የድራም...

የነጻነት ዋጋ – የሃይቲ ያልታየው ገፅ 29.09.2026

የመጀመሪያዋ ነፃ የጥቁር ሪፐብሊክ የሆነችው ሃይቲ ዛሬ ላለችበት ውጥንቅጥ ምክንያት የጥቁር ህዝብ ድክመት ሳይሆን፣ የሁለት ክፍለ ዘመናት የምዕራባውያን የሀብት ዘረፋ እና የጣልቃ ገብነት ሴራ ውጤት ነው። “የሄይቲ ወቅታዊ ችግሮች በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ከሀገሪቱ የመጀመሪያ ስቴት ምስረታ ጀምሮ የጀመሩ ናቸው፤ አሜሪካውያንም ሄይቲን የጥቁር ነፃነት ፊት አውራሪ በመሆኗ እና ይህ አስተሳሰብ ወደ ሰሜን አሜሪካ ሊዛመት ይችላል በሚል ስጋት ይመለከቷታል” ሲሉ  በውጭ ጉዳይ ኢንስቲቱዩት የባለብዙ ወገን መንግስታዊ እና መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ጉዳዮች ተመራማሪ አዲስ አለማሁ  ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል። የዛሬው የድራም ኦቭ ቼን...

ሁለተኛው “የዓለም" ጦርነትና የተረሱት የአፍሪካ ተዋጊዎች 28.09.2026

በዛሬው የ ድራም ኦቭ ቼንጅስ ዝግጅት፤ መቶ ሺዎች የሚቆጠሩ አፍሪካውያን በቅኝ ግዛት ሠራዊት ተመልምለው የጦርነቱን ውጤት መቀየራቸውን እና ጦርነቱ ሲያበቃ ወደ አድሎአዊ ጡረታና ቀጣይ የቅኝ አገዛዝ መመለሳቸውን እንቃኛለን። እንግዳችንም በአሜሪካ ኮርኔልና በመቐለ ዩኒቨርሲቲዎች ታሪክ ያስተማሩትና አሁን በኢትዮጵያ ብሔራዊ መከላከያ ኮሌጅ መምህር የሆኑት  አየለ በከሪ (ዶ/ር) ናቸው።

የመስቀል በዓል መንፈሳዊ ፋይዳ፣ ታሪካዊ አመጣጥ እና የትውልድ ኃላፊነት 28.09.2026

የዛሬው የድረም ኦቭ ቼንጅስ ዝግጅታችን ትኩረት ያደረገው የመስቀል በዓል በመንፈሳዊና ታሪካዊ አመጣጡ፣ በዓለም አቀፋዊ ማህበራዊ ትስስሩ እንዲሁም አዲሱ ትውልድ ይህንን የዘመናት እሴት እንዴት ይዞ መዝለቅ እንዳበት ላይ ነው። ለዛሬው ውይይታችን እንግዳችን የሆኑት የቅድስት ሥላሴ ዩኒቨርሲቲ የቀኖና ቤተ ክርስቲያን መምህር ቀሲስ አንድነት አሸናፊ ናቸው።

ምስራቃዊው እጥፋት፡ ራሽያ፣ ቻይና እና አዲሱ መካከለኛው ምስራቅ 28.09.2026

በዛሬው የድራም ኦቭ ቼንጅስ ዝግጅት ሩሲያና ቻይና የምዕራባውያንን የበላይነት በመገዳደር ለአሜሪካ ጣልቃ ገብነት አማራጭ ማቅረባቸውን እና የአዲስ ምዕራፍ መሠረት መሆናቸውን እንቃኛለን። በጉዳዩ ላይ ከቀድሞው የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ከፍተኛ አማካሪ እና የአፍሪካ ሕብረት ፀረ-ሙስና ቦርድ ሊቀመንበር ቆስጠንጢኖስ በርሁተስፋ (ዶ/ር) ጋር አውርተናል።

ቋንቋዎች በአህጉራት መካከል እንደተዘረጋ ድልድይ 28.09.2026

የዛሬው የድራም ኦቭ ቼንጅስ ዝግጅት ቋንቋ የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነትን የሚያጠናክርበትን መንገድ ይዳስሳል። እንግዳችን በቻይና የቤጂንግ የውጭ ጥናት ዩኒቨርሲቲ የአማርኛ መምህርትና አስተባባሪ  ስንቅነሽ አጣለ (ዶ/ር) ናቸው።

ከኮሪያ እስከ ኮንጎ፡ የኢትዮጵያ የሰላም ማስከበር እና የአብሮነት ታሪክ 28.09.2026

በዛሬው የድራም ኦቭ ቼንጅስ ዝግጅታችን ኢትዮጵያ የረጅም ጊዜ የሰላም ማስከበር ታሪክ እያላት ለጀግኖቿ የተሰጠ ብሔራዊ ሙዚየም እስከዛሬ የሌላት ለምንድን ነው የሚለውን ጥያቄ ከታሪክ እና የሚዲያ ጥናት ባለሙያው ከተረፈ ወርቁ ጋር እንቃኛለን።

ጥበብ ወደመነሻ ለመድረስ፣ ጠበብ ሰላም ሰላምን ለማምጣት 28.09.2026

በዛሬው የድራም ኦቭ ቼንጅስ ዝግጅታችን መነሻችንን ማወቅ ማንነታችንን ለመገንባት የሚኖረውን ሚና እንቃኛለን። ጥበብ ይህንን ማንነት ለትውልድ ለማሻገር፣ ሰላምን ለማፅናት እና ሕዝቦችን ለማስተሳሰር ያላውን ድርሻ ከሰዓሊና የ«ኢትዮጲስ» ልጆች ፕሮግራም መስራች አርቲስት ሳምሶን መረሳ (ቲቶ) ጋር እንወያያለን።

ወደ ቀድሞው ዘመን፣ በዛሪው ዘመን ቴክኖሎጂ መመለስ 28.09.2026

በዛሬው የድራም ኦቭ ቼንጅስ ዝግጅታችን የኢትዮጵያን ጥንታዊ ጽሑፎች እና የታሪክ መጻሕፍት ወደ ዲጂታል የመቀየር ሂደት እንዲሁም የዘመናት ዕውቀት ከጥንታዊ ብራናዎች እና ከሩቅ መዛግብት ወደ ዲጂታል ዓለም ሲሸጋገር የሚያስከትለውን ውጤት እንቃኛለን። ለዚህም ማህበራዊ አንትሮፖሎጂስት አሉላ ፓንክኸርስትን (ዶ/ር) ጨምሮ ሌሎች ምሁራን ጋር ቆይታ አድርገናል።

በደቡብ-ደቡብ ትብብር ፓን-አፍሪካዊ እድገትን ማፋጠን 28.09.2026

የዛሬው ድራም ኦቭ ቼንጅስ ዝግጅታችን ትኩረት በደቡብ-ደቡብ ትብብር ላይ ነው። በማደግ ላይ ያሉ ሀገራት አጋርነት የአፍሪካን ኢንዱስትሪያላይዜሽን ማፋጠን የሚችልበትን እና ለምዕራባውያን ማዕቀፎች አማራጭ የሚሆንበትን መንገድ ከዲላ ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካ ሳይንስ እና ዓለም አቀፍ ግንኙነቶች መምህርና ተመራማሪ ዳዊት መዝገበ ጋር እንቃኛለን።

ከድንጋይ ወደ ሀብት፡ የአፍሪካ የእሴት አብዮት 24.09.2026

የዛሬው ድራም ኦቭ ቼንጅስ ዝግጅት የአፍሪካ ሀገራት ያልተቀነባበሩ ማዕድናትን ወደ ውጭ መላክ የመከልከል እንቅስቃሴዎችን ይቃኛል። በዚህም አፍሪካ ሀብቷን በሀገር ውስጥ በማስቀረት እሴት መፍጠር መጀመሯን እንመለከታለን። በጉዳዩ ላይ የአሶሳ ዩኒቨርሲቲ የማህበራዊ ኢኮኖሚ ጉዳዮች ተመራማሪ እና ዓለም አቀፍ ጉዳዮች ተንታኝ መሐመድ ኢብራሂም ማብራሪያ ሰጥተዋል።

የአፍሪካ አረንጓዴ ጎህ፡ የማዕድን እሴትና የኢኮኖሚ ሉዓላዊነት 19.09.2026

የዛሬው ድራም ኦቭ ቼንጅስ ዝግጅታችን በሁለት አህጉራዊ ጉዳዮች ላይ ያተኩራል። የመጀመሪያው፣ አፍሪካ ከአዳዲስ ዓለም አቀፍ ጥምረቶች እና ከሻንጋይ የትብብር ድርጅት የምታገኛቸውን ትምህርቶች ከወራቤ ዩኒቨርሲቲው የምጣኔ ሀብት መምህር መሐመድ ኢሳ ጋር የምንዳስስበት ነው። ሁለተኛው ደግሞ፣ አፍሪካ ልማትና የድህነት ቅነሳን ሳታስተጓጉል ወደ ንጹሕ የኃይል አማራጭ የምታደርገውን ሽግግር ይመለከታል። በጉዳዩ ላይ ሪቻርድ ሚዩንጊ   (ዶ/ር) እና ከተባበሩት መንግሥታት የአፍሪካ ኢኮኖሚ ኮሚሽን ማሪት ቅጣው አስተያየታቸውን ሰጥተውበታል።

የመካከለኛው ምስራቅ ግጭት እና በአፍሪካ ሴቶች ላይ የሚያሳድረው ተፅዕኖ 17.09.2026

በዛሬው የድራም ኦቭ ቼንጅስ ዝግጅታችን በሩቅ የሚከሰቱ ግጭቶች ከዳካር እስከ ናይሮቢ የቤተሰብ ወጪንና የገበያ እንቅስቃሴን እንዴት እየቀየሩ እንደሆነ ከታዋቂ የመብት ተሟጋች ጋር ዳስሰናል። የዓለም አቀፍ አደጋዎችን አህጉራዊ ተፅዕኖና የሴቶችን የኢኮኖሚ ጫና በጥልቀት የምንመረምርበትን ዝግጅት እንድትከታተሉ እንጋብዛለን። ለዚህም ናይጄሪያዊቷን የመብት ተሟጋች ፋዴኬሚ አኬንፌዳሪንን አነጋግረናል።

ከኔቶ ባሻገር፡ ደህንነት፣ ሉዓላዊነት እና አፍሪካ እየተለወጠ ባለው ዓለም ውስጥ ያላት ቦታ 16.09.2026

አሜሪካን ማዕከል አድርጎ የሚንቀሳቀሰው የኢንዶ-ፓስፊክ ስትራቴጂ ኔቶን ወደ አዲስ የውድድር አውድ እንዲገባ እያደረገው ይገኛል። ይህ ደግሞ መረጋጋትን ሳይሆን አዲስ ቅራኔን ብቻ ነው የሚጋብዘው። “አሁን እኮ የኔቶ ዓላማ የጂኦ-ፖለቲካዊ ተጽዕኖ መፍጠሪያ እና ማሰፋፊያ ወደ መሆን አዘንብሏል [...] የአፍሪካ ሉዓላዊነት የሚረጋገጠው በኢኮኖሚ ነፃነት እና በራሷ የንግድ ማዕቀፎች እንጂ ከውጭ በሚመጡ ውሱን እርዳታዎች ብቻ አይደለም […] እኛ አፍሪካውያን የምንፈልገው አካታች የዓለም ሥርዓትን እንጂ አዲስ የቀዝቃዛ ጦርነት ውጥረት አይደለም” በማለት በኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርሲቲ የዓለም አቀፍ ግንኙነት እና ዲፕሎማሲ መምህር እንዳለ...

በብራና የተጻፈ፡ የኢትዮጵያ ሕያው የሥልጣኔ መዝገብ 16.09.2026

የዛሬው የ ድራም ኦቭ ቼንጅስ ዝግጅታችን ትኩረት ከነሓሴ 28፣ 2018 ዓ.ም. እስከ መስከረም 3፣ 2019 ዓ.ም. በአዲስ አበባ በመካሄድ ላይ ባለው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የብራና መጻሕፍት ዓለም አቀፍ ኤግዚቢሽን ላይ ነው። በዚሁ ጉዳይ ላይ የሐመር ብርሃን የብራና መጻሕፍት ሥራ ድርጅት የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ ትንሳኤ ተስፋሚካኤልን እና የፕሮጀክት ማናጀሯን ቃልኪዳን ብርሃኑን አነጋግረናል።

ከቃል ኪዳን ወደ ትግበራ ኃይል፡ የአፍሪካ የአየር ንብረት አጀንዳ 16.09.2026

በዛሬው የድረም ኦቭ ቼንጅስ ዝግጅታችን ከባድ ድርቅና ጎርፍ የዜጎችን የዕለት ተዕለት ኑሮ ከመፈተኑ ጀምሮ፣ እስከ ታላላቅ የድርድር መድረኮች ቃላት ከድርጊት የሚበልጡበትን አዝማሚያ ጨምሮ፣ አፍሪካ የአየር ንብረት ሉአላዊነቷን ለማስከበር የምታደርገውን የረጅም ጊዜ ትግል ታላቅ ታሪክ አካል አድርገን እናቀርበዋለን። ዝግጅቱን ከ 14ኛው የአፍሪካ የአየር ንብረት ለውጥና ልማት ጉባኤ አንጻር የምናቀርበው ሲሆን፣ በጉባኤ ላይ ተገኝተን ዮሴፍ አመሓን (ዶ/ር)፣ በተባበሩት መንግስታት የአፍሪካ ኢኮኖሚ ኮሚሽን የአየር ንብረት ተማራማሪ ጨምሮ የተለያዩ ተሳታፊዎችን አውርተናል።

የአፍሪካ የሰላም መዋቅር፡ የአፍሪካ ህብረትን ሚና ማጠናከር 16.09.2026

የዛሬው የድረም ኦቭ ቼንጅስ ዝግጅታችን ሦስት ጉዳዮችን ይዳስሳል። በቀዳሚው ጉዳዩ የአፍሪካ ህብረት ከዲፕሎማሲ ውይይት ወደ የዜጎችን ደህነት ጥበቃ የሚቀይርበትን እና የፋይናንስ ጥገኝነትን በመቀነስ የሰላም ስልታዊ አቅሙን የሚያጠናክርበትን መንገድ ይቃኛል። በሁለተኛ ጉዳዩ ኢትዮጵያ የ 2029 ኙን የአፍሪካ ዋንጫ ለማዘጋጀት ያቀረበችውን ጥያቄ ይዳስሳል። ለዚህም የብሔራዊ እግር ኳስ ፌዴሬሽኑን ፕሬዝደንት ኢሳያስ ጂራ አነጋግሯል። በሦስተኛው ጉዳዩ ደግሞ ጳጉሜን 1 የጀመረውንና እስከ ጳጉሜን 5 የሚዘልቅዉን ፌስቲቫል ይቃኛል።

የሳህል ህብረት ስልታዊ የሉዓላዊነት እንቅስቃሴ፦ የቀጠናዊ ኃይልን ትርጉም እንደገና መበየን 02.09.2026

“ካፒታሊዝም [የምዕራቡ] በመሰረታዊነት የተመሰረተው በኢኮኖሚ ብዝበዛ ላይ ነው [...] አሁን የቀድሞ የፈረንሳዪ ቅኝ ግዛቶች «የቅኝ ግዛት መገበያያን» አንጠቀምም ባሉ ጊዜ የነዚህ አፍሪካ ሀገራት መሪዎች እስከ ፖለቲካዊ ግድያዎች ድረስ ገጥሟቸዋል። ምክንያቱ ደግሞ «የቅኝ ግዛት መገበያያዎች» ለአውሮፓውያኑ የአመት ገቢያቸው ነው፣ የአፍሪካን ገበያ የሚቆጣጠሩበት ነው” ሲሉ እንዳለ ንጉሴ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል። የዛሬው የድረም ኦቭ ቼንጅስ ዝግጅታችን በቀዳሚነት ወደ ቀጠናዊ ሉዓላዊነት ቁርጠኛ ሽግግር እያደረገ ወደሚገኘው የሳህል ቀጠና ይወስደናል። ለዚህም በፐብሊክ ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ የዲፕሎማሲና ዓለም አቀፍ ግንኙነት መም...

የዓለም አቅፉ ደቡብ አዲስ ጎህ እና የብዙ ወገንተኝነት ጉዞ 02.09.2026

እያደገ የመጣው የብሪክስ እና የዓለም አቅፉ ደቡብ አገራት ህብረት ዓለምን ወደ እውነተኛ ሉዓላዊ፣ የጋራ እኩልነትና የብዙ ወገንተኝነት ሥርዓት ከፍ የሚያደርግ ታሪካዊ ምዕራፍ እየፈጠረ ይገኛል። “የዓለም አቅፉ ደቡብ ምዕራባውያንን እንዲሁም አሜሪካንን በእርግጥኝነት የመገዳደር ቁመና ላይ ይገኛል። ከዚህም ባሻገር የዓለም አቅፉ ደቡብ ሀገራት የተባበሩት መንግስታት ድርጅት እያንዳንዱ ሉዓላዊ ሀገር በልኩ የሚወከልበት መድረክ እንዲሆን ይፈልጋሉ […] ብሪክስም የጸጥታው ምክር ቤት ቦታን ለመረከብ የሚያስችል የአለም አቅፉ ደቡብ ትልቅ አቅም ሆኖ ሊመጣ ይችላል” ሲሉ የፖሊሲ አማካሪ ቆስጠንጢኖስ በርኸተስፋ (ዶ/ር) ለስፑትኒክ አፍሪካ ተ...

ቻድ ከአይ.ሲ.ሲ ለመውጣት ያሳለፈችው ውሳኔ፡ የምዕራቡ ዓለም መሣሪያ ለሆነው ተቋም የአፍሪካ ምላሽ? 17.08.2026

"የምዕራቡ ዓለም የዓለም አቀፉን የወንጀል ፍርድ ቤት (አይ.ሲ.ሲ) የራሱን ፍላጎት ማስፈፀሚያ ያደረገው ይመስላል [...] ቻድ ከ አይ.ሲ.ሲ ለመውጣት ያሳለፈችው ውሳኔም ለቀሪው የአፍሪካ አህጉር ግልጽ መልዕክት አስተላልፏል 'አፍሪካ የራሷን ዕድል በራሷ የመወሰን እና የራሷን የፍትህ መንገድ የመቀየስ ጊዜዋ አሁን ነው' የሚል" ሲሉ የሕግ ባለሞያው መታገስ ዉለታው ለስፑትክ አፍሪካ ተናግረዋል። በዛሬው የድረም ኦቭ ቼንጅስ ቀዳሚ ዝግጅታችን ቻድ ከዓለም አቀፉ የወንጀል ፍርድ ቤት (አይ.ሲ.ሲ) ለመውጣት የወሰደችውን ርምጃ መነሻ አድርገን የተቋሙን መዋቅራዊ አድልዎ እና በአፍሪካ የሀገርበቀል የፍትህ ስርዓቶችን የመገንባት ጥረቶችን...

Poslouchej podcast Drum of Changes v Replaio

Rádio a podcasty v jedné aplikaci - zdarma a bez registrace. Nainstaluj si ji ještě dnes a nepropásni premiéru

Stáhnout z Google Play

Replaio není vydavatelem podcastů; názvy pořadů, obálky a audio patří jejich autorům a šíří se přes veřejné RSS kanály