Great Commission Ministry Ethiopia

Melhik

መልህቅ ፖድካስት ክርስቲያን ወጣቶች በሁለንተናዊ ማለትም በመንፈሳዊ፣ በስሜታዊ፣ በአካላዊ እና በማህበረሰባዊ ህይወት እንዲያድጉ የሚያግዝ እና በወጣቶች ዘንድ አንገብጋቢ የሆኑ ጉዳዮችን በመዳሰስ መፅሐፍ ቅዱሳዊ የሆነ መሰረት እንዲኖረን የሚረዳን ፕሮግራም ነዉ። አብረን እንደግ!FIND US ON SOCIAL MEDIAFacebook: https://www.facebook.com/MelhikPodcastTelegram: https://t.me/melhikpodcastCONNECT WITH GREAT COMMISSION MINISTRY ETHIOPIAYouTube: https://www.youtube.com/watch?v=5ZudSfnekts&list=PLnLZmYeGTQhW5-byt7c97wUcS5RXSuOmZFacebook: https://www.facebook.com/GCMEthiopiaWebsite: https://www.gcmethiopia.org/#MelhikPodcast #Melhik #GCME #Melihik

Mindenképp látogasd meg a podcast oldalát, és támogasd a készítőjét: redcircle.com

Szerző

Great Commission Ministry Ethiopia

Kategória

Religion

A podcast weboldala

redcircle.com

Legutóbbi epizód

2026. aug. 8.

Hol hallgathatod?

Podcastok az alkalmazásban Replaio Radio Hamarosan

A podcastok hamarosan megérkeznek az alkalmazásba. Telepítsd most, és láss elsőként egy teljesen új megközelítést a podcastokhoz

Letöltés a Google Play-ről Telepítsd ingyen Android közel 10 M letöltés · 4,8-as értékelés iOS hamarosan

Epizódok

የእግዚአብሔርን ፈቃድ ማወቅ 17.03.2021

ዛሬ ስለእግዚአብሔር ፈቃድ በጥልቀት እናወራለን፤ ይህ ሀሳብ ብዙ ወጣቶች ጋር ትልቅ ጉይዳ ስለሆነና መረዳት ስለሚያስፈልገን በጥልቀት ለማውራት አስፈልጎናል። ከዶ/ር ማስረሻና ከባለቤታቸው ወ/ሮ መሰረት ጋር መፅሐፋቸውም ላይ ካሉት ሃሳቦች አንፃር እንጨዋወታለን። እንድታዳምጡን እንጋብዛችኋለን። FIND US ON SOCIAL MEDIA Facebook: https://www.facebook.com/MelhikPodcast Telegram: https://t.me/melhikpodcast CONNECT WITH GREAT COMMISSION MINISTRY ETHIOPIA YouTube: https://www.youtube.com/channel/UCMjGByWp01ahtj4...

የላጤነት ዉበት (The Beauty of Singleness) 10.03.2021

እስከዛሬ ስለዴቲንግና ስለትዳር ብዙ ብለናል ነገር ግን ከሁለቱም በፊት የሚቀድምን አንድ ነገር አላየንም፥ singleness ወይንም በአማርኛው የብቸኝነት ህይወት፥ ቃል በቃል ሲተረጎም የነጠላነት ህይወት ማለት ነው ። ይህ ወቅት ምን ማድረጊያ ነው? እግዚአብሔር እንደዚህ አይነቱን ጊዜ ለምን ሰጠን? ምን ማድረግ አለብን? በአጠቃላይ በዚህ ዙሪያ ከወንድም ክብሩ ታደሰ ጋር እንጨዋወታለን። በቆይታችን እንደምትጠቀሙ እምነታችን ነው።  መልካም ቆይታ። FIND US ON SOCIAL MEDIA Facebook: https://www.facebook.com/MelhikPodcast Telegram: https://t.me/melhikpodcast CONNECT...

የፍቅር ጓደኛ ምርጫ 03.03.2021

ትዳር ለመመስረት ስናስብ የትዳር ጓደኛችንን መምረጥ የመጀመሪያ ስራችን እንደሆነ ይታወቃል። ለምርጫችንም መስፈርት ማውጣታችን አይቀርም፣ ታዲያ አንዳንድ ጊዜ የምናያቸው ፊልሞች የምናነባቸው መጽሃፍት መስፈርቶቻችን ላይ በጎ ያልሆነ ተጽእኖን ያሳድሩብናል። በእርግጥ የትዳር ጓደኛችንን ለመምረጥ መስፈርት ማስቀመጥ ተገቢ ነው? የፍቅር ጓደኝነት ለመጀመር ትክክለኛ እድሜ ስንት ነው?  በዛሬው ክፍል ስለ ፍቅር ጓደኛ ምርጫ እንነጋገራለን ። FIND US ON SOCIAL MEDIA Facebook: https://www.facebook.com/MelhikPodcast Telegram: https://t.me/melhikpodcast CONNECT WITH GR...

የህይወት አጋር ማግኘት 24.02.2021

የህይወት አጋር ያስፈልጋል ወይ? እግዚአብሔር ትዳርን ሲመሰርት አላማው ምን ነበር? ትዳር ለመመስረት መስፈርቱ ምንድነው?  ሰው በመጀመሪያ እግዚያብሔርን ሲያውቅና ከእርሱ ጋር ትክክለኛ ግንኙነት ሲኖረው ከሰው ጋር ያለው ግንኙነት ጤነኛ ይሆናል።  በዛሬው ክፍል የህይወትን አጋር ስለማግኘት ጠቃሚ ምክር ያገኛሉ። FIND US ON SOCIAL MEDIA Facebook: https://www.facebook.com/MelhikPodcast Telegram: https://t.me/melhikpodcast CONNECT WITH GREAT COMMISSION MINISTRY ETHIOPIA YouTube: https://www.youtube.com/channel/UCMj...

የተቃራኒ ፆታ ፍቅር 17.02.2021

እኛ ወጣቶች ብዙ ጊዜ የፍቅርን ትርጉም ከማወቃችን በፊት የፍቅር ግንኙነት ጀምረን ለፍቅር የራሳችንን ትርጉም እንሰጠዋለን። ይህም ለብዙ የልብ ስብራት አጋልጦናል። መጽሐፍ ቅዱስ በተቃራኒ ፆታ መሃል መኖር ስላለበት ፍቅር ምን ይላል? የእውነተኛ ፍቅር ግንኙነት መገለጫዎቹስ ምንድናቸው? በእርግጥ በፍቅር መውደቅ / መያዝ አለ? ዛሬ ከእነዚህ ጥያቄዎች ተነስተን ለፍቅር ግንኙነትዎ መልህቅ የሚሆን ትምህርት ይዘንላቹ ቀርበናል።  መልካም ጊዜ FIND US ON SOCIAL MEDIA Facebook: https://www.facebook.com/MelhikPodcast Telegram: https://t.me/melhikpodcast CONNECT WITH...

የአቻ ግፊት በፍቅር ግንኙነት /peer pressure/ 10.02.2021

በቅርቡ በወጣቶች ና በታዳጊዎች ላይ የተደረገ ጥናት የአቻ ግፊት በከፍተኛ ደረጃ የወጣቶች ተግዳሮት እንደሆነ ያሳያል ፤ ይህም ብቻ ሳይሆን ለሌሎቹም ተግዳሮቶች ዋና መንስኤ ነው። ታዲያ ይህ የአቻ ግፊት በወጣቶች ላይ ለምን በረታ? ጉዳቱስ ምን ያህል ነው? ከአቻ ግፊት እንዴት ነፃ መሆን ና ማሸነፍ ይቻላል? በዛሬው ክፍል ለእነዚህ ጥያቄዎች ከፍቅር ግንኙነት እና ከወሲብ አንፃር ምላሽ ያገኛሉ። FIND US ON SOCIAL MEDIA Facebook: https://www.facebook.com/MelhikPodcast Telegram: https://t.me/melhikpodcast CONNECT WITH GREAT COMMISSION MINISTRY E...

በDating የእግዚአብሔር ፈቃድ እና የሚደረጉ ጥንቃቄዎች 03.02.2021

በDating የእግዚአብሔር ፈቃድ እና የሚደረጉ ጥንቃቄዎች Dating ዉስጥ የእግዚአብሔርን ፈቃድ እንዴት እንወቅ? ብዙ ሰዎችን በአንድ ጊዜ Date ማድረግ ችግር አለዉ? ጥንቃቄዎቹና ስርአቶችሁ (Disciplines) ምንድናቸዉ? መልካም ጊዜ ከክፍል 6 ጋር FIND US ON SOCIAL MEDIA Facebook: https://www.facebook.com/MelhikPodcast Telegram: https://t.me/melhikpodcast CONNECT WITH GREAT COMMISSION MINISTRY ETHIOPIA YouTube: https://www.youtube.com/channel/UCMjGByWp01ahtj4yS7ohmag Facebook: htt...

የፍቅር ጓደኝነት (Dating) ምንድነዉ? 27.01.2021

እኛ ሰዎች ከፍጥረታችን ጀምሮ ከእኛ ውጭ ከሆኑ አካላት ጋር ግንኙነት እንዲኖረን ተደርገን የተፈጠርን ማህበራዊ ፍጥረታቶች ነን። ዛሬ የምንዳስሰው ባልተጋቡ ወንድና ሴት መካከል የሚፈጠርን የፍቅር ጓደኝነት ወይም dating ነው።  የፍቅር ጓደኝነት ወይም dating ማለት ምን ማለት ነው? አላማውስ? የፍቅር ግንኙነት ለመጀመር አስፈላጊ የሆኑ ነገሮች ምንድናቸው? እነዚህንና ሌሎች ጥያቄዎችን በዛሬው ክፍል እንዳስሳለን አብራችሁን ቆዩ። FIND US ON SOCIAL MEDIA Facebook: https://www.facebook.com/MelhikPodcast Telegram: https://t.me/melhikpodcast CONNECT WITH GR...

ፍቅር ምንድነው? 20.01.2021

ሁሉም ሰው ፍቅርን በራሱ መንገድ ትርጉም ይሰጠዋል … ከመጽሐፍ ቅዱስ አንፃር እውነተኛው የፍቅር ትርጓሜ ምንድነው? ለጤናማ እና ትክክለኛ የፍቅር ግንኙነት መሠረቱ ምን መሆን አለበት? እንዴትስ እንዋደድ?… በዚህ ክፍል ይህን ይዘንላቹ እንቀርባለን። FIND US ON SOCIAL MEDIA Facebook: https://www.facebook.com/MelhikPodcast Telegram: https://t.me/melhikpodcast CONNECT WITH GREAT COMMISSION MINISTRY ETHIOPIA YouTube: https://www.youtube.com/channel/UCMjGByWp01ahtj4yS7ohmag Facebook: https://w...

የጾታ ትርጓሜና ዓላማዉ 13.01.2021

በዚህ ዘመን የፆታ ጉዳይ ብዙ የተሳሳተ ትርጓሜ ይሰጠዋል። ብዙ አዳዲስ አስተሳሰቦች ትውልዱን ግራ እያጋቡት ይገኛሉ። እኛም እነዚህን የተሳሳቱ ትርጓሜዎች በትክክለኛው ትርጓሜ ማሸነፍ እንድንችል የሚያግዘንን እውነተኛውን ትርጓሜ ከመፅሐፍ ቅዱስ አንፃር አብረን እናያለን። FIND US ON SOCIAL MEDIA Facebook: https://www.facebook.com/MelhikPodcast Telegram: https://t.me/melhikpodcast CONNECT WITH GREAT COMMISSION MINISTRY ETHIOPIA YouTube: https://www.youtube.com/channel/UCMjGByWp01ahtj4yS7ohmag Facebo...

በተፈጥሮ እድገት ሂደት የሚመጡ ለውጦች እና የምንሰጠው ምላሽ 06.01.2021

የሰው ልጆች ከውልደት እስከ አዋቂነት ባለው ጊዜ ውስጥ ብዙ የሚያልፉባቸው ሂደቶች አሉ፣ በእነዚህ ሂደቶች ውስጥ ስነልቦናዊ ፥ ስነአይምሮአዊ ፥ ባዮሎጂያዊ ፥ ሆርሞናል ፥ የሞራልና ማህበራዊ ለውጦች አሉ ። ታዲያ በተፈጥሮ ለምን በእንደነዚህ አይነት ለውጦች እንድናልፍ ሆነ? እነዚህንስ ለውጦች እንዴት ማስተናገድ ያስፈልጋል? እነዚህን እና ሌሎች ጥያቄዎችን በዛሬዉ ክፍላችን እንዳስሳለን። FIND US ON SOCIAL MEDIA Facebook: https://www.facebook.com/MelhikPodcast Telegram: https://t.me/melhikpodcast CONNECT WITH GREAT COMMISSION MINISTRY ETHIOP...

መልህቅ እና አላማዉ 30.12.2020

በዛሬዉ ክፍለ ጊዜ እነዚህ ጥያቄዎች ይዳሰሳሉ - መልህቅ ምንድነዉ? አላማዉስ? አዘጋጆቹስ እነማን ናቸዉ? እናንተም አድማጮቻችን የዚህን ፖድካስት አላማዉን ተረድታችሁ ከእኛ ጋራ እንድትሆኑ ጥሪያችን ነዉ፣ ለሌሎቹም ማጋራት አይርሱ፣ ተባረኩ። FIND US ON SOCIAL MEDIA Facebook: https://www.facebook.com/MelhikPodcast Telegram: https://t.me/melhikpodcast CONNECT WITH GREAT COMMISSION MINISTRY ETHIOPIA YouTube: https://www.youtube.com/channel/UCMjGByWp01ahtj4yS7ohmag Facebook: https://www.fa...

Intro 25.12.2020

መልህቅ ፖድካስት ክርስቲያን ወጣቶች በሁለንተናዊ ማለትም በመንፈሳዊ፣ በስሜታዊ፣ በአካላዊ እና በማህበረሳዊ ህይወት እንዲያድጉ የሚያግዝ እና በወጣቶች ዘንድ አንገብጋቢ የሆኑ ጉዳዮችን በመዳሰስ መፅሐፍ ቅዱሳዊ የሆነ መሰረት እንዲኖረን የሚረዳን ፕሮግራም ነዉ። አብረን እንደግ!

Hallgasd a(z) Melhik podcastot a Replaióban

Rádió és podcastok egy alkalmazásban - ingyen és regisztráció nélkül. Telepítsd még ma, és ne maradj le a premierről

Letöltés a Google Play-ről

A Replaio nem podcastkiadó; a műsorok nevei, borítóképei és hanganyagai a szerzőiket illetik, és nyilvános RSS-csatornákon keresztül terjednek.